Personal pronouns part 8
Personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውን/
ሰብአዊ ወይም አካላዊ የስም ተለዋጮች
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው፤ በዛሬው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ስለ personal
pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ ነው የምንማረው። ባለፈው እንደመግቢያ እንዳየነው pronounse/ፕሮናውንስ ብዙ ዓይነት እንደሆኑ፤
ከብዙዎቹ መካከልም አንድዱ “ፐርሰናል ፕሮናውን/personal pronoun” የሚባለው እንደሆነና “ፐርሰናል ፕሮናውንስ” ራሳቸው
በ3 እንደሚከፈሉ። ተነጋግረን ነበር።
ስለዚህ ዛሬ ስለ ሦስቱ የስም ተለዋጭ/personal
pronouns ዓይነቶች በምሳሌ እናያለን እንከታተል። ሰብስክራይብ እና ሽር ማድረግን አትርሱ።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ
መጻሕፍት ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ በአድራሻዎ ይላክለዎታል።
ባለፈው ባጭሩ እንደጠቀስኩት Personal Pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ በ3 ዐበይት
ክፍሎች ይከፈላሉ፤ እነሱም
1. Subjective/ስብጀክቲብ (ባለቤት የሚሆኑ)
2. Objective/ኦብጀክቲቭ(ተሳቢ የሚሆኑ) እና
3.
Possessive
pronouns/ፖሰሲብ (ባለቤትነትን አመልካች) ፕሮናውንስ የሚባሉት
ሲሆኑ Subjective/ሰብጀክቲቭ የዐ/ነገር ባለቤት፣ Objective/ኦብጀክቲቭ ተሳቢ፣ Possessive/ፖሰሲብ ደግሞ ባለቤትነትን
የሚጠቁም ወይም የሚያመለክቱ ተውላጠ ስሞች ናቸው።
ከዚህ በታች ባሉት 4 የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ዐረፍተ ነገራት ሦስቱን የስም ተለዋጮችና እንዴት ዓይነት አገልግሎትን
እንደሚሰቱ እንመለከታለን ተከታተሉ። በተጓዳኝም ስለ ዐረፍተ ነገራቱ መዋቅር እና ስለ እያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ
ባጭሩ እንዳስሳለን።
በመጀመሪያ በአማርኛችን ግልጽ እንዲሆንልን የአማርኛውን
ዐ/ነገራት አንድ በአንድ አስረዳና ወደ እንግሊዘኛው አልፋለሁ። በቀይ በተጻፉት ወይም ቀስቱ የተመለከተባቸውን ቃላት ላይ የበለጠ
አትኩሮት ስጡ።
ምሳሌዎቹ የሚናገሩት ስላለፈ ጊዜ ነው፤ ትምህርታችን
ግን የሚያተኩረው ስለ ጊዜው ሳይሆን ስለ ዐረፍተ ነገር ባለቤቶች እና ተሳቢዎች ነው።
ማለትም “ፐርሰናል ፕሮናውንስ” ስለሚባሉት አርእስት ነው።
በተሰጡት 4 ዐ/ነገራት ውስጥ ሰብጀክቲብ/Subjective፤ኦብጀክቲብ/
Objective እና ፖሰሲቭ/Possessive ፕሮናውንስ/Pronouns የሚባሉት አገባቦች ይገኛሉ። ይህ ማለት ሦስቱም የስም ተለዋጭ
ዓይነቶች ወይም ፕሮናውንስ ይገኙበታል ማለት ነው።
በመጀመሪያው ዐ/ነገር “እኔ” እና “አቤል” የሚባሉት ሁለት ቃላት ናቸው የሚፈለጉት። “እኔ” የሚለው የስም ተለዋጭ ሲሆን በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም
ሥራውን የሠራው አካል ነው። በእንግሊዘኛው “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን/Subjective
Pronoun” ይባላል። ባለቤታዊ የስም ተለዋጭ ማለት ነው። ወይም በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ በባለቤትነት የተጠቀሰውን ሰው
ወይም አካል ተክቶ የሚሠራ የስም ተለዋጭ ነው።
“አቤል” የሚለው ቃል ግን የስም ተለዋጭ ሳይሆን ራሱ የሰው ስም ነው። የሥራ ድርሻውም ተሳቢ “ኦብጀክት” መሆን ነው። ስለዚህ በስም ተለዋጭ ሲተካ “እሱን” ማለት ይሆናል፤ በሁለተኛው ዐ/ነገር ላይ ተጠቅሷል። “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን” “who/ማን”? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ የስም ተለዋጭ ነው።
በሁለተኛው ዐ/ነገር “እኔ” እና “እሱን” የሚባሉት ሁለት ቃላት ናቸው የሚፈለጉት። “እኔ” የሚለው የስም ተለዋጭ ሲሆን በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም
ሥራውን የሠራው አካል ነው። በእንግሊዘኛው “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን/Subjective
pronoun” ይባላል ባለቤታዊ የስም ተለዋጭ ማለት ነው።
“እሱ” የሚለው ቃል ከላይ “አቤል” ብለን የጠቀስነው “ኦብጀክቲቭ
ናውን/Objective” “እሱን” በሚለው የስም ተለዋጭ ተተክቷል።
ይህም “ኦብጀክቲቭ ፕሮናውን/Objective” የሚባለው ነው። ኦብጀክቲብ ፕሮናውንስ
“ምንን whom”? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው።
በሦስተኛው ዐ/ነገር “የእኔ” የሚለው ቃል ብቻ ነው በዚህ
ትምህርታችን የሚፈለገው። ይህ ባለቤትነትን የሚያመለክት የስም ተለዋጭ ወይም ፖሰሲብ ፕሮናውን ይባላል። ምክንያቱም መጽሐፉ የእኔ
መሆኑን የሚገልጽ ወይም የሚናገር ስለሆነ ነው። ይህም “የማን/whose” ? የሚለውን
ጥያቄ የሚመልስ አመልካች ነው።
በአራተኛው ዐ/ነገር “የእኔ” የሚለው ቃል ብቻ ነው በዚህ
ትምህርታችን የሚፈለገው። ይህ የስም ተለዋጭ እንደ ሦስተኛው የስም ተለዋጭ ባለቤትነትን የሚያመለክት ሲሆን ሁለቱ የሚለዩት
የሚመለከተውን ወይም በዚህ ዐረፍተ ነገር “መጽሐፍ” የሚለውን ንብረት ከፊት ለፊታቸው
ወይም ከኋላቸው በማስቀመጥ ነው።
ስለዚህ 3ኛው የስም ተለዋጭ “ፖሰሲብ አድጀክቲቭ/Possessive
Adjective” ይባላል (ቅጽላዊ አመልካች ማለት ነው)
በ4ኛው ዐ/ነገር የሚገኘው የስም ተለዋጭ ደግሞ
“ፖሰሲብ ፕሮናውን/Possessive
Pronoun”(ባለቤታዊ አመልካች) ይባላል። ወደፊት የሁለቱን ልዩነት በሰፊው እንማራለን።
ዐረፍተ ነገራቱን እናንብ ።
1.
እኔ ትላንት አቤልን ዐየሁት
2.
እኔ ትላንት እሱን ዐየሁት
3.
ይህ የእኔ መጽሐፍ ነው
4.
ይህ መጽሐፍ የእኔ ነው
·
I saw Abel yesterday
አይ ሳው(ሳ) አቤል የስተርደይ
እኔ አቤልን ትናንት አየሁት
·
I saw him yesterday
አይ ሳው ሒም የስተርደይ
እኔ እሱን ትላንት አየሁት
·
This is my book
ዚስ ኢዝ ምይ ቡክ
ይህ የእኔ መጽሐፍ ነው
·
This book is mine
ዚስ ቡክ ኢዝ ማይን
ይህ መጽሐፍ የእኔ ነው
Read on you phone this English E book
መጽሐፉ አካላዊ ሳይሆን በስልክ ወይም
በሌላ ኤሌክትሮኒስ መሳሪያ የሚነበብ (ኪንድል ቡክ ነው) በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንደኝነት አልፈው ሽልማትን ያስገኙ የእንግሊዘኛ
ግጥሞቼ ናቸው
ቃላት/wors
Subject/Subjective = ርዕስ፣ ርዕሰ ጉዳይ (በዚህ ትምህርታችን የዐረፍተ ነገር ባለቤት)
Object/Objective = ነገር፣ አካል፣ (በዚህ ትምህርታችን ተሳቢ)
Possessive = የባለቤት አመልካች (ንብረትን እና ባለ ንብረትን የሚያመለክት)
To see – saw = ማየት፣ ሃላፊ ጊዜ(አየሁ)
1ኛ መደብ/አካል = First person(s)
2ኛ መደብ/አካል = second person(s)
3ኛ መደቦች/አካል = Third Person(s)
ለዛሬው
ከዚህ ላይ ይበቃናል
ልዑል
አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ
No comments:
Post a Comment