Tuesday, August 18, 2020

የአውደ ጥናት ዘግእዝ ልዩ አባል ይሁኑ

 

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው


 መጻሕፍት ለመግዛት ይህንን ይጫኑ 

ወይም በ +1 703 254 6601 ይደውሉ

ምን አልባት “አውደ ጥናትን እና አውደ ጥናት ዘግእዝን ” የማታውቁ ካላችሁ ትንሽ ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ። ከስያሜው ለመነሳት ያህል “አውደ ጥናት” ማለት የጥናት፣ የትምህርት ወይም ባጭሩ የምርምር ማዕከል ማለት ነው።

  “አውደ ጥናት ዘግእዝ ማለት” ደግሞ የግእዝ ቋንቋ ትምህርትና ጠቅላላ ይዘት የሚጠናበት ማለት ሲሆን አውደ ጥናትም ሆነ አውደ ጥናት ዘግእዝ  በመላው ዓለም ለሚኖሩ ሁሉ  ቦታና ጊዜ የማይወስናቸው በመላው ዓለም የሚገኙ፤ በመላው ዓለም የሚገኙትን ማስተናገድ የሚችሉ “የዩቱብ ቻናሎች ወይም ድረገጾች” ሲሆኑ የትምህርትና የጥናት ማዕከላት ናቸው።

በአውደ ጥናትና በአውደ ጥናት ዘግእዝ

·        የአማርኛ

·        የግእዝ

·        የእንግሊዘኛ እንዲሁም ወደፊት

·        የግሪከኛ ቋንቋ ትምህርት በሰፊው ይሰጣል።

ባጠቃላይ በአውደ ጥናት እና በአውደ ጥናት ዘግእዝ በመንፈሳዊና በማሕበራዊም ሕይወት ዙሪያ ልዩ ልዩ መረጃዎችን እና የጥናት ጽሁፎችን ያገኛሉ።

 

 በተለይ ለኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ተከታዮች ወሳኝ የሆኑ ድረ-ገጾች ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ የዘወትር ጸሎት፤ የውዳሴ ማርያም፤ የመልክአ ማርያም እና መልክአ ኢየሱስ፤ የዶግማና የቀኖና የዘመናት አቆጣጠር ሌሎችም ልዩ ልዩ ትምህርቶችን ቀላል፣ ግልጽና ዘመናዊ በሆነ የማስተማር ዘዴ ከቤታችሁ ሳትወጡ፤ ከቤተሰባችሁ ሳትለዩ በያላችሁበት ቦታ፤ በምትኖሩበት ዓለም ሁሉ በስልካችሁም ሆነ በኮምፕዩተራቸሁ ማለትም በማነኛውም ድጅታል መሣሪያ ጊዜና ቦታ ሳይወስናችሁ ጊዜያችሁን መርጣችሁ ልትማሩባቸው፤ ልጆቻችሁንም ልታስተምሩባቸው የምትችሉባቸው ድረገጾች ናቸው።

 

በአውደ ጥናት እና በአውደ ጥናት ዘግእዝ በሚተላለፉት ሁለ ገብ የእምነትና የሥነ ምግባር ትምህርቶች ራሳችሁን እና ልጆቻችሁን ማስተማርና ማነጽ ትችላላችሁ። በመሆኑም ዛሬውኑ ሰብስክራይብ በማድረግ የአውደ ጥናትና የአውደ ጥናት ዘግእዝ ተጠቃሚዎች መሆን ትችላላችሁ።

 

በተጨማሪም በአውደ ጥናት ዘግእዝና በአውደ ጥናት የሚሰጠው አገልግሎት ከማረካችሁና በተሻለ መልኩ አገልግሎቱን እንድያሳድግ የምትፈልጉ ከሆነም በበጎ ፈቃድ ልዩ አባል በመሆን መርዳት የምትፈልጉ ከሆነ መርዳት የምትችሉበት ዕድል በሚከተለው ዓይነት የሚገኝ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።

በአውደ ጥናት ዘግእዝ የሚከተሉት 4 የልዩ አባልነት ደረጃዎች ይገኛሉ፤ ክፍያቸውና ያላቸው ልዩ አገልግሎትም አብሮ ተጠቅሶ ይገኛል፤ የምትችሉትንና የምትፈልጉትን ደረጃ መምረጥ ትችላላችሁ።

 

1ኛ ደረጃ አባልነት በየወሩ $1፡99

2ኛ ደረጃ አባልነት በየወሩ $4፡99

3ኛ ደረጃ አባልነት በየወሩ $9፡99 እና

4ኛ ደረጃ አባልነት $19፡99 ይከፈላል ወይም ያስከፍላሉ።

 

በልዩ አባልነት የሚያገኙት ጥቅም ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል።

 

1.  አንደኛ ደረጃ አባላት በወር አንድ ጊዜ በመረጡት ርእስ የቀጥታ ስርጭት ትምህርት ወይም ውይይት ይደረግላቸዋል፤

2.  ሁለተኛ ደረጃ አባላት በወር አንድ ጊዜ በመረጡ ርእስ የቀጥታ ስርጭት ትምህርት ወይም ውይይት ይደረግላቸዋል። በተጨማሪም ከአውደ ጥናት ከሚገዧቸው ነገሮች (ብዙ ጊዜ መጻሕፍት) 25% ቅናሽ ያገኛሉ።

3.  ሦስተኛ ደረጃ አባላት በወር ሁለት ጊዜ የግእዝ ቋንቋ ተከታታይ ትምህርት በቀጥታ ስርጭት ይሰጣቸዋል። 25% ቅናሽም ያገኛሉ።

4.  አራተኛ ደረጃ አባላት በክፍያ በተከታታይ በዋትስአፕ ከሚሰጠው ተከታታይ የአንድ ዓመት የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ገብተው መማር ይችላሉ። እንዲሁም 25% ቅናሺም ያገኛሉ።

 

ከዚህ ሌላ ሁሉም አባላት የተለየ መታወቂያ ይኖራቸዋል። ማለትም አስተያየት በሚሰጡ ጊዜ የተለየ እና ከሌላው አባል ካልሆነው ሰው ይልቅ በዩቱብ ቻናል ተሳትፏቸው ጎልተው እንዲታዩ የሚያደርግ ድጅታል አርማ ወይም መታወቂያ ይኖራቸዋል። ልዩነታቸው የሚታወቀው ማለትም አርማቸው የሚታየው አስተያየት ሲሰጡ ወይም ጥያቄ ሲያቅርቡ ነው።

 

በመሆኑም የአውደ ጥናት ዘግእዝ ልዩ አባል ለመሆን ሲወስኑ ቀጥታ ወደ አውደ ጥናት ዘግእዝ ቻናል ሲገቡ “Join” የሚል ምልክት ያገኛሉ እሱ ይጫኑ፤ ከገቡ በኋላ ማብራርያውን ወይም መመሪያውን ይከታተሉ። አመሰግናለሁ።

 ቪድዮውን ለመስማት ይህንን ይጫኑ

https://youtu.be/u3LKldvGvCc




ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

No comments:

Post a Comment