Noun and Parts of nouns/ ስሞች እና የስሞች አከፋፈል
Nouns/
ስም-ስሞች
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ ነው፤ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ይቀጥላል።
መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት ይህንን ሊንክ ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ
ባለፈው በክፍል 5 የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ስለ ስምንቱ(8) የንግግርክፍሎች ባጭሩ የያንዳንዱን የስም ዓይነት ምንንነት አይተን ነበር። በመቀጠል የምናየው እያንዳንዱን በተናጠል ሲሆን ዛሬ በክፍል 6 ትምህርታችን ከ8ቱ አንዱ ስለ ሆነው ስለ ስም ሰፋ አድርገን በምሳሌ ጭምር እንማራለን ተከታተሉ።
ስለ ስም የሚከተሉትን ሦስት ነጥቦች እንማራለን
1ኛ ለመሆኑ ስም ምንድነው?
(ስለ ስም ምንነት)
2ኛ የስም አከፋፈል
(ስንት ዓይነት ክፍል አለው)
3ኛ ስም ከስምንቱ(8ቱ)
የንግግር ክፍሎች መሠረታዊ ሥራው ምን መሆን ነው?
ማነኛውም ነገር መጀመሪያ በራሳችን ቋንቋ ግልጽ እንዲሆንልን ማድረግ አለብን፡ በራሳችን ቋንቋ ስያሜውን ማንነቱን፣ ሥራውን ወዘተ ያለምንም ጥርጥር ከተረዳን በእንግሊዘኛው አንድ ነገር ብቻ ነው ለማወቅ የሚጠበቅብን ይኸውም ምንድነው? ትርጉም።
1ኛ ለመሆኑ ስም ምንድነው? (ስም ምንነት)
What is a noun?
A Noun is a
name of person, place, thing, feeling, and idea. =
ስም የሰው፣ የቦታ፣
የነገር፣ የስሜትና የሐሳብ መጠሪያ ነው። ስለዚህ ስም አንዱን ከሌላው ለመለየት የሚሰጥ ልዩ ስያሜ ነው፤ ስም ባይኖር አንዱን ከሌላው
ለይቶ ማወቅ ስለማይቻል ነገሮች የተደበላለቁ ወይም የተሳከሩ ይሆኑ ነበር ማለት ነው።
2ኛ የስም አከፋፈል/parts of Noun (ስንት ዓይነት ክፍል አለው)
ስም በጣም ብዙ ዓይነት
ክፍሎች ቢኖሩትም በሚከተሉት አበይት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን፤
እነዚህም በአማርኛ
·
Concrete and Abstract Nouns/ ቁሳዊና መንፈሳዊ ስሞች
·
Common and Proper Nouns/ የወል እና የግል ስሞች
·
Countable and Uncontable Nouns /የሚቆጠሩና የማይቆጠሩ ስሞች
1. Concrete Nouns: (ካንክሪት ናውንስ)
ካንክሪት ናውንስ
የሚባሉት ለሚዳሰሱ ነገሮች የሚሰጡ ስያሜዎች ሲሆኑ
በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቶቻችን የሚገለጹ ናቸው ማለትም
በማየት፣ መንካት፣ ማሽተት፣ መቅመስ፣ መስማት የምንችላቸው ነገሮች ናቸው
Seen, touched, smell, taste, hear,
2. abstract = አብስትራክት ናውን የሚባሉት
ግን
የሐሣብ እና የስሜት ስሞች ሲሆኑ
የማይዳሰሱ፣ የማይታዩ፣ የማይቀመሱ፣ የማይሸተቱ፣ እና የማሰሙ ናቸው። በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት የማይገለጹ ማለትም
የማይታዩ፣ የማይዳሰሱ፣ የማይቀመሱ፣የማይሸተቱ፣ እና የማይሰሙ ናቸው።
ምሳሌዎቹን እንመልከት
Example: 1 ለሚዳሰሱ ነገሮች
Ephrem likes to go to the park and see the birds.
ይህ ዐረፍተ ነገር ወደ አማርኛ ሲመለስ
ኤፍሬም ወደ መናፈሻ መሄድና ወፎችንም ማየትን ይወዳል። ማለት ሲሆን በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ
ሦስት ካንክሪት ወይም ቁሳውያን ስሞች አሉ፤ እነሱም “ኤፍሬም” የሰው ስም፤ “ፓርክ” የቦታ ስም፤ እና “በርድ” የእንስሳት
ስም”
Example: 2 ለማይዳሰሱ ነገሮ
Love is
one of the ten commandments (ከማንድመንትስ). Or “Honesty is the best Policy”
ፍቅር ከዐሥሩ ትእዛዛት አንዱ ነው። ወይም “ሐቀኝነት እጅግ መልካሙ ሥርዓት ነው” ማለት ሲሆን በነዚህ ዐረፍተ ነገራት ዐራት የአብስትራክት ስሞች አሉ፤ እነሱም “ፍቅር” እና “ትእዛዛት” “ሐቀኝነት እና ሥርዓት”
የሚባሉት ናቸው። ምክንያቱም ፍቅር እና ትእዛዝ የሚታይ፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፤ የሚሰማ፣ የሚቀመስ፣ ወይም የሚሸተት አይደለም።
3. Common (ካመን ናውን)
Common nouns (ካመን
ናውንስ) የሚባሉት የጋራ መጠሪያዎች ናቸው፤ እነዚህም ለምሳሌ
Human, man, woman, animals, plants, city, country, month, day/ሰው፣ ወንድ፣ ሴት፣ እንስሳት፣ እፀዋት፣ ከተማ፣ አገር፤ወር፣ ቀን፤ ወዘተ የሚባሉት ናቸው።
4. Proper፡ ፕሮፐር ናውን፡ የግል መጠሪያ ወይም መጠሪያ ስም ማለት ነው
Proper nouns:(ፕሮፐር ናውንስ)
የሚባሉት ደግሞ የግል
መጠሪያዎች ወይም ስያሜዎች ናቸው ለምሳሌ
Abera, Alemitu, Ethiopia, Addis ababa, January, and Friday/ አበራ፣ አለሚቱ፣ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ ጥር፣ አርብ፣ የመሳሰሉት ናቸው።
5. Collective and Group (ከለክቲብ ኤንድ ግሩፕ ናውንስ)
Collective noun:(ከለክቲብ ናውን)
ከለክቲብ ናውንስ እና ግሩፕ ተቀራራቢዎች
ናቸው በተወሰነ ደረጃ ነው የሚለዩት
ብዙ ተጫዋቾች በአንድ ላይ Players/ፕለየርስ ይባላሉ፤(ግሩፕ) የፕለየሮቹ ስብስብ ደግሞ Team/“ቲም” ይባላል(ከለክቲብ)
Group noun: (ግሩፕ ናውን)
Employee/ኢምፕሎይ ማለት ሠራተኛ ማለት ሲሆን Employees/ “ኢምፕሎይስ” ለብዙ ሠራተኞች ማለት ነው፤ ስለዚህ Employees/“ኢምፕሎይስ” (ግሩፕ) ሲሆን “የኢምፕሎይስ” ስብስብ ደግሞ Staff/ “ስታፍ” ይባላል፤ ስለዚህ Staff/“ስታፍ” Collective noun/ “ኮለክቲብ ናውን” ይባላል።
6. Countable (count- able)
– Uncountable (un-count-able) (የሚቆጠር እና የማይቆጠር) “ካውንት” መቁጠር ሲሆን “አን” የሚለው
ቃል “ኢ” ወይም አፍራሽ ነው።
Countable: የሚቆጠሩ ነገሮች ለምሳሌ
Book, pen, spoon, መጽሐፍ፣ ስክብሪቶ፣ ሹካ፣
Un-countable: የማይቆጠሩ ነገሮች ደግሞ ለምሳሌ፡
Water, air, sugar, milk /ውሀ፣ አየር፣ ሱካር፣ ወተት፣ ወዘተርፈ የሚባሉት ናቸው።
· ስሞች በዐረፍተ ነገር ውስጥ መሠረታዊ ሥራቸው የዐረፍተ ነገር ባለቤት(subject) መሆን ነው። በተጨማሪ ደግሞ ተሳቢ(object) እና ዘርፍም ይሆናሉ።
ከዚህ በታች ያሉትን ቃላት አጥኑ፡ ከዚህ በላይ ካለው ትምህርት ጋር የተያያዙ ናቸው።
·
Noun = ስም
·
Concrete =የሚዳሰስ(ቁስ ነገር)
·
Human = ሰው(ሰብአዊ ፍጡር)
·
Man = ወንድ (ሰው)
·
Woman = ሴት
·
Place = ቦታ
·
Thing = ነገር
·
Abstract = የማይዳሰስ)
·
Idea = ሐሣብ/ አመለካከት
·
Thought = ሐሣብ
·
To see = ማየት
·
To hear = መስማት
·
To smell = ማሽተት
·
To touch መንካት
·
Common = የጋራ(የወል)
·
Proper = ትክክለኛ፣ ተገቢ
·
Proper noun = የግል መጠሪያ
·
Collective = ስብስብ
·
Group = ግሩፕ/አንድነት
·
Team = ግሩፕ
·
Employee = ሠራተኛ(ተቀጥሮ የሚሠራ)
·
To count = መቍጠር
·
Able = መቻል
·
Un = ኢ
·
Suffix = ድኅር (ከቃል መጨረሻ ላይ የሚገባ)
·
Prefix = ቅድም/መቅድም
(ከቃል መጀመሪያ ላይ የሚገባ ቀዳሜ ቃል)
Pronoun/ፕሮ ናውን ማለት ምን ማለት ነው? |
መጻሕፍት ለመግዛት ይህንን ይጫኑ ወይም በ +1 703 254 6601 ደውሉ
Pronouns
ሰላም ጤና ይስጥልኝ
ከአውደ ጥናት ነው፤
በዛሬው በክፍል
7 የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን የምንማረው ከ8ቱ የንግግር ክፍሎች በሁለተኛ ደረጃ የጠቀስነውን Pronoun/ፕሮናውን የተባለውን ርእስ ነው። Pronouns/ፕሮናውንስ የሚባሉት በጣም ብዙ ዓይነት ናቸው እኛ ግና ለጊዜው
የተወሰኑትን ብቻ ነው የምንማረው። በመጀመሪያ
·
Pronoun/ፕሮ
ናውን ማለት ምን ማለት ነው?
·
የፕሮናውን ሥራ
ምንድ ነው?
·
ፕሮ ናውን ስንት
ዓይነት ነው?
የሚሉትን ሦስት
መሠረታውያን ጥያቄዎች ከመለስን በኋላ Pronouns/ፕሮ ናውንስ በተግባር በዐረፍተ ነገር ሲገቡ ምን እንደሚመስሉ አንድ በአንድ
እንማራለን። መልካም ትምህርት።
Pronoun/ፕሮናውን ምን ማለት ነው፡ (ስያሜን የሚመለከት ማብራርያ)
Pronoun: A word that replaces a noun in a sentences or takes the
place of noun in a sentence. = ፕሮ ናውን የሚባለው በዐረፍተ ነገር ውስጥ ስምን ተክቶ የሚገባ ወይም የስምን
ቦታ የሚይዝ ነው
ባለፈው በክፍል
6 ትምህርታችን Noun/“ናውን” ማለት “ስም” ማለት እንደሆነና የተለያዩ የስም ዓይነቶችን በመጥቀስ ተምረን ነበር።
ስለዚህ የዛሬው
ደግሞ Pro/“ፕሮ” የሚለውን Prefix/ “ፕሪፊሽ” ከማስቀድሙ በስተቀር Noun/“ናውን” የሚለው ስያሜ አይቀየርም፤ Pro/ፕሮ
የሚለው ተቀጽላ ስላለ ግን ለየት ያለ ማብራርያን እሰጣለሁ ።
·
Pro/ፕሮ
= ምትክ/ፈንታ
·
Noun/ናውን
= ስም
·
ስለዚህ በአንድ ላይ Pronoun/“ፕሮ ናውን” ወይም በብዙ Pronouns/“ፕሮናውንስ” = በስም ፈንታ ወይም
ምትክ ማለት ይሆናል። በግእዝ “ተውላጠ ስም” በአማርኛ “የስም ተለዋጮች” የሚባሉት
ሲሆኑ ስምን ወይም ስሞችን ተክተው የሚገቡ ናቸው። በእንግሊዘኛው
“in place of noun” ማለት ነው። ይህም ማለት በስም ምትክ ማለት ነው።(በስም ምትክ የሚገቡ ለማለት ነው)
የፕሮ ናውንስ ሥራ ምንድነው? (የሚሠጡትን አገልግሎት
የሚመለከት)
ፕሮናውንስ ሥራቸው በስም ምትክ መግባትና ስም የሚሠራውን መሥራት
ነው። (The word that replaces noun in sentence is called “pronoun”) በዐረፍተ ነገር ውስጥ
ስምን የሚተካ ቃል ፕሮናውን ይባላል። ስለዚህ ፕሮናውንን ወይም ተውላጠ ስሞችን መቸና እንዴት እንደ ምንጠቀም
በሚከተሉት ምሳሌዎች እንመልከት።
ምሳሌ፡ በመጀመሪያ በአማርኛ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው
በትክክል ሊገባን ይገባል፤ ስለዚህ በመጀመሪያ በእንግሊዘኛ ዐረፍተ ነገር ከመሥራታችን በፊት በአማርኛ እናያለን።
·
አበራ ከአልማዝ ጋር ይሠራል
·
አበራ ከአልማዝ ጋር መሥራት
ይወዳል
·
አበራ እና አልማዝ አብረው መሥራት
ይወዳሉ። በነዚህ ሦስት ዐረፍተ ነገራት ሁለት ስሞች አሉ ስሞቹ 6 ጊዜ ተደጋግመው ተጠቅሰዋል። ስለዚህ የስሞች መደጋገም ደግሞ
ንግግርን የማይማርክ ወይም አሰልች ያደርጋል። በመሆኑም ድግግሞሺን
ለማስቀረት “ተውላጠ ስሞችን” መጠቀም አለብን።
አበራ ከአልማዝ
ጋር ይሠራል፤
እሱ ከእርሷ
ጋር መሥራትን ይወዳል፤
እነሱ አብረው መሥራት ይወዳሉ።
አሁን የፕሮናውንን
ወይም የስም ተለዋጮችን ሥራ አስተውሉ፤ አበራ ከአልማዝ ጋር ይሠራል ካልን በኋላ እንደ ገና ተመሳሳይ ስሞችን ከመደጋገም ማለትም
“አበራ” በማለት ፈንታ “እሱ” “አልማዝ” በማለት ፈንታ “እርሷ”፣ አበራና አልማዝ በማለት ፈንታ “እነሱ” የሚባሉትን ተውላጠ
አስማት ወይም የስም ተለዋጮች በመጠቀም 1ኛ ስማቸውን ከመደጋገምና አስልች ድግግሞሽ ከማድረግ ተቆጠብን፤ ሁለተኛ 4 ቃላትን (አበራና አልማዝን ሁለት ጊዜ) ከመጻፍ “እሱ” “እሷ” “እነሱ” በሚሉት ቃላት በማጠቃለል ወረቀትና ጊዜን መቆጠብ ቻልን
ማለት ነው።
እነዚህ ሦስት ከላይ የሠራናቸው ዐረፍተ ነገራት በእንግሊዘኛ ደግሞ
እንደሚከተለው ይቀመጣሉ።
·
Abera
works with Almaz (አበራ ወርክስ ዊዝ አልማዝ)
·
Abera
likes working with Almaz(አበራ ላይክስ ወርኪንግ ዊዝ አልማዝ)
·
Abera
and Almaz like working together (አበራ ኤንድ አልማዝ ላይክ ወርኪንግ ትጌዘር)
አሁንም ከላይ በአማርኛው እንዳየነው በሦስቱም የእንግሊዘኛ ዐረፍተ
ነገራት የተደጋገሙ ስሞች አሉ። ስለዚህ ዐረፍተ ነገሩ የማይስብና የሚያሰለች ድግግሞሽ እንዳይሆን “ተውላጠ ስሞችን/ፕሮናውንን እንጠቀማለን”
ስለዚህ.
·
Abera works with
Almaz.
·
He likes working with her.
·
They like working together.
በመሆኑም ተውላጠ ስሞችን የምንጠቀመው አንደኛ የስሞች ድግግሞሽን
ለመቀነስና ዐረፍተ ነገሩን ማራኪ የማይሰለች ለማድረግ፤ ሁለተኛ ደግሞ ስም መጥራት የማንፈልግ ከሆነ ተውላጠ ስሞችን እንጠቀማለን።
ተውላጠ ስሞችን በመጠቀም ወረቀትና ጊዜን መቆጠብ እንደምንችልም አትዘንጉ
ፕሮናውንስ ስንት ዓይነት ነው/ናቸው?(አከፋፈላቸውን የሚመለከት)
ከላይ ስጀምር እንደነገርኳችሁ pronouns/ፕሮናውንስ
የሚባሉት ብዙ ዓይነት ናቸው ለምሳሌ
1. Personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ
2. Relative pronous/ረለቲብ ፕሮናውንስ
3. Reflexive pronouns/ረፍለክሲብ ፕሮናውንስ
4. Interrogative pronouns/ኢንተሮጌቲብ ፕሮናውንስ
ወዘተርፈ ይገኙበታል።
ለዛሬው የመጀመሪያውን “ፐርሰናል ፕሮናውን”
የሚባለውን እንማራለን ማለት ነው።
Personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውን/
ሰብአዊ ወይም አካላዊ የስም ተለዋጮች
ፐርሰናል ፕሮናውን “ፐርሰን” ማለት ሰው
ወይም አካል ማለት ሲሆን “ፐርሰናል ፕሮናውን” የሚለው = ሰብአዊ ወይም አካላዊ ተውላጠስም ማለት ነው። ፐርሰናል ፕሮናውኖች ለሰዎች
እና ለቤት እንሥሳት የምንጠቀምባቸው ናቸው። በሦስት አበይት ክፍሎች ይከፈላሉ። እነሱም የዐረፍተ ነገር ባለቤቶች፣ ተሳቢዎች፣ እና
ባለቤትነትን የሚያመለክቱ ተውላጠ ስሞች ይባላሉ በእንግሊዘኛው እንደሚከተለው ይገለጻሉ።
·
Subjective pronouns/ባለቤት የሚሆኑ ተውላጠ ስሞች
·
Objective pronouns and /ተሳቢ የሚሆኑ ተውላጠ ስሞች እና
·
Possessive pronouns/ ባለቤትነትን የሚያመለክቱ ተውላጠ ስሞች
የሚባሉት ሲሆኑ በሚቀጥለው በክፍል 8 ትምህርታችን
እያንዳንዳቸውን በተናጠል በምሳሌ እንመለከታለን።
Words in this video to be learned/ በዚህ ቪድዮ ውስጥ የሚገኙ መጠናት ያለባቸው
ቃላት
·
Pronoun = የስም ተለዋጭ
·
Subject = ባለበት/የዐረፍተ ነገር ባለቤት
·
Object = ተሳቢ ወይም ተደራጊ
·
Possessive = አመልካች(ባለቤትነትን፤ባለንብረትነትን የሚያመለክት)
·
Person = ሰው/አካላዊ ሰው
·
Relative = ተዛማጅ/ዘመድ
·
Reflexive = መልሶ የሚያንጸባርቅ/ወደራሱ የሚያመለክት
·
Interrogative = መጠየቂያ/መመርመሪያ
·
To like = መውደድ
·
To work = መሥራት(ግስ)
·
Working =መሥራት(ስም ከ አር፣ ወይም ኢዝ ከሚባሉት ግሶች
ጋር ግስ የሚሆንበትም ጊዜ አለ)
·
With = ጋር ወይም ጋራ/አብሮ..
·
He = እሱ
·
She = እሷ
·
Her = እሷን/የሷ..
·
They = እነሱ
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ
If you are interested in learning Geez Language from Awde Tinat Zegeez, leave you phone # and I will contact you for more information's.
ReplyDeleteሰላም ለክሙ!
ReplyDeleteየግእዝን ቋንቋ ከአውደ ጥናት መማር የሚፈልጉ ከሆነ ስልክ ቁጥረዎን ያስቀምጡ ወይም Learngeez@outlook.com ኢሜይል ይላኩልኝ። ሠናይ ለክሙ!
I need to learn Geez Language how can ..
ReplyDeletebetmatik
ReplyDeletekralbet
betpark
tipobet
slot siteleri
kibris bahis siteleri
poker siteleri
bonus veren siteler
mobil ödeme bahis
647Q
ardahan
ReplyDeleteartvin
aydın
bağcılar
balıkesir
BTBC
ataşehir
ReplyDeleteistanbul
çeşme
uşak
samsun
BCK2
شركة تنظيف افران wrixlutIoY
ReplyDelete