Saturday, November 28, 2015

ግእዝ ፈተና 2 ክፍል 31

Ge'ez part 31 exam 2



የግእዝ ትምህርት ክፍል ሁለት ጠቅላላ የመመዘኛ ፈተና   



ዛሬ በዚህ በክፍል 31 ትምህርታችን ክፍል ሁለት አጠቃላይ የመመዘኛ ፈተናን እንሠራለን። ይህ ፈተና ከክፍል 13 ጀምሮ እስከ ክፍል 30 ያሉትን ሁሉ ያጠቃለለ ነው። በዚህ የመመዘኛ ፈተና ውስጥ 31 ጥያቄዎች ሲኖሩ ክነዚህ ውስጥ 21ዱ አንድ አንድ ጥያቄዎችን የያዙ ሲሆን ቀሪዎቹ 10 ጥያቄዎች ደግሞ ከአንድ በላይ የሚሆኑ ጥያቄዎችን ይዘዋል። ለማስታዎስ ያህል 1ኛው 4 ጥያቄዎች፤ 3ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 4ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 6ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 12ኛው 5 ጥያቄዎች፤ 19ኛው 3 ጥያቄዎች 25ኛው 5 ጥያቄዎች፤ 26ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 27ኛው 2 ጥያቄዎች፤ እና 29ኛው 2 ጥያቄዎች አሏቸው። በጠቅላላ 50 ይሆናሉ ስለዚህ እያንዳንዱ ጥያቄ ሁለት ነጥብ ይኖረዋል ማለት ነው። 20 ጥያቄዎችን ለማቅረብ ነበር የተነጋገርነው የበለጠ ለማጥናት ይጠቅማችኋል ብየ ስላሰብኩ 50 አደረግሁላችሁ። ስለዚህ ሰፊ ጌዜ እሰጣችኋለሁ በርትታችሁ አጥኑ። መልካም ፈተና።

ለሚከተሉት 15 ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ።

1.  “ዛቲ ጦማረ መልእክት ትብጻህ ኀበ አርድእተ ልሣነ ግእዝ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ
·       የዐ/ነገሩን ባለቤት-----
·       የዐ/ነገሩን ማሠሪያ አንቀጽ------------
·       የ”ጦማርን” ቅጽል ይናገሩ------------------(4)

2. አበይት አናቅጽ የሚባሉትን አራት ግሦች “ሰብሐ” በሚለው ግሥ ምሳሌ ያሳዩ

3. አእማድ” የሚባሉት  ስንት ናቸው? ስማቸውንም ይጥቀሱ(2)እርማት ተደርጎበታል (በቪድዮው ላይ ሳነብ ሆሄያት ብያለሁ "አዕማድ" ግን ሆሄያት ሳይሆኑ በሆሄያት አማካኝነት ትርጉማቸውን የሚቀይሩ ግሦች ናቸው። ስለዚህ "ሆሄያት" የሚለው ቃል ይቀራል)

4. “አሥራው” የሚባሉት ሆሄያት ስንት ናቸው? ስማቸውንም ይጥቀሱ(2)

5. “ኢታንሥእ ዘኢያንበርከ” ማለት ምን ማለት ነው?

6. በ5ኛ ተራ ቁጥር ላለው ዐ/ነገር ትእዛዝ ሰጭውንና ትእዛዝ ተቀባዩን በተውላጠ ስሞች ይናገሩ፤(2)

7. “አስማት” ማለት ምን ማለት ነው?

የሚከተሉትን ወደ ግእዝ ቋንቋ ይቀይሩ

8. እንደ ምን አደርክ ወንድሜ?

9. ልጂሽ የት ነው እኅቴ?

10. እንደ ምን አደሩ እናቴ?

11. ለምን መጣችሁ ወንድሞቼ?

12. ቅድመ ሠለስቱ ዓመታት ፈለስኩ እምነ ብሔርየ ከመ እሁር ኀበ ሐገረ ባእድ፤ ወድኅረ ክልኤቱ አውራኅ እትመየጥ መንገለ አዝማድየ። ባሕቱ አቡየ ይቤለኒ ኢትትመየጥ ኀበ ዝንቱ ሐገር።

ከዚህ በላይ ባለው ምንባብ ውስጥ ተጠቅሰው የሚገኙትን 5 ግሦች ወይም አናቅጽ ለይተው በማውጣት የያንዳንዱን ግሥ ዓይነት ይናገሩ (የሚገልጸውን ጊዜ) ።(5)

13. ከ4ቱ አበይት አናቅጽ ውስጥ በቀጥታ ራሱን ችሉ የዐረፍተ ነገር ማሠሪያ መሆን የማይችለው ግሥ የትኛው ነው? ስሙን ይጥቀሱ።

14. ወለተ ማርያም ለብሰት ጸሊመ ልብሰ። በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ “ጸሊም” የሚለው ቃል የሚቀጸለው ለማነው? ወይም የሚገልጠው ማንን ነው?

15. “ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን” የዚህ ዐ/ነገር ማሠሪያ አንቀጽ “ቀዳማይ፤ ካልአይ፤ ሳልሳይ፤ ወይስ ራብአይ አንቀጽ የትኛው ነው?

16. “እግዚአብሔር ይባርኪ ወያብርህ ገጾ ላእሌኪ” ምን ማለት ነው?

17. “ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ “ድንግል” የሚለው ቃል ስንተኛ መደብ ነው?

18. እፎ ሐደርከ (ኪ፤ክሙ፤ክን) ለዚህ ቃል መልሳችን ሊሆን የሚችለውን በግእዝ ይጻፉ

19. “አርዌ ምድር አስፈጠተኒ ወበላእኩ”(3)
·       በዚህ ዐ/ነገር(በ19ኛው ጥያቄ) “አስፈጠተኒ” የሚለው ቃል መሠረታዊ ግሡ ማነው?
·       ትርጉሙስ ምን ማለት ነው?
·       “አስፈጠተኒ” የሚለው ቃል ራሱን ችሎ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ምን ማለት ነው?

20. “ገንጰለ” ማለት ምን ማለት ነው?
21. መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ ወ ቅኔ ተምሂሮ እምነ አውደ ጥናት ዘግእዝ። ምን ማለት ነው?

22. “ንግሩኒ ስማ ለብእሲት” ምን ማለት ነው?

23. ማነኛውም ርባ ግሥ መነሻው ምን ዓይነት የግዜ ትርጉም ነው?

24. “ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ማለት ምን ማለት ነው?

25. በአውደ ጥናት የትምህርት ማእከል ተገኝተው ስለ ግእዝና ቅኔ ሰፊ ማብራርያ የሰጡት የቤተ ክርስቲያናችን ምሁር ማን ይባላሉ? ከቻሉ ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ የሰጡትን መልስ ጠቅለል አድርገው በ5 ወይም ከዚያ በታች በሆኑ ዐ/ነገሮች ይግለጹት። (5)

ለሚከተሉት 5 ጥያቄዎች እውነት ሐሰት በማለት ይመልሱ

26. “ዛቲ ጦማረ መልእክት ትብጻህ ኀበ አርድእተ ልሣነ ግእዝ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ እንደ ሚከተለው ነው።(2)
·       ዛቲ = የጦማር ቅጽል
·       ጦማር = የዐ/ነገሩ ባለቤት
·       መልእክት = የጦማር ዘርፍ
·       ትብጻህ = ማሠሪያ አንቀጽ
·       ኀበ = ንዑስ አገባብ
·       አርድእት(ተ) =  አገባብ የወደቀበት
·       ልሳን =  የአርድእት ዘርፍ
·       ግእዝ = የልሳን ዘርፍ

27. “አምጣነ አቅረብኩ ለከ እሳተ ወ ማየ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ” የዚህ ዐ/ነገር የአማርኛ ትርጉምና የያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ የሚከተለውን ይመስላል።(2)

= እሳትና ውሀን አቅርቤልሃለሁና እጅህን ወደ ወደድከው(ወደ መረጥከው) አስገባ (ጨምር)
·       አቅረብኩ = የአገባብ ባለቤት
·       ለከ = ለአንተ ማለት ሲሆን ዝርዝር ይባላል (አንተ ለሚለው ይዘረዘራል)
·       እሳት =  የአቅረብኩ ተሳቢ
·       ወ =   አጫፋሪ(እሳትንና ውሀን)
·       ውሀ =  በ ወ ተጫፍሮ የአቅረብኩ ተሳቢ
·       ደይ = ማሠሪያ አንቀጸ
·       እዴከ =  የ “ደይ” ተሳቢ
·       ኀበ =  ንዑስ አገባብ
·       ዘ =  አቢይ አገባብ ሲሆን ፈቀድከ የሚለው ግሥ እንዳያሥር ይጠብቀዋል
·       ፈቀደ =  አገባብ(ዘ) የወደቀበት (ባለቤት)

28. 99 ሴቶችና 1 ወንድ በድምሩ 100 ሰዎች በአንድ አዳራሽ ተሰብስበዋል፤ እርሰዎ በዚህ ጉባኤ ላይ ከጥዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ (በአገራችን አቆጣጠር) በግእዝ ቋንቋ ንግግር እንዲያደርጉ ስለተጋበዙ በታዳሚዎቹ ፊት ለፊት ቆመው “ እፎ ሐደርክን አኃትየ ወእኁየ”? በማለት መጀመር ይጠበቅበዎታል።

29. “ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ይእቲ” በሚለው ዐ/ነገር ውስጥ የሚከተሉት ትክክል ናቸው።(2)
·       ቤት(ቤተ) = የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት
·       ክርስቲያን = የቤት ዘርፍ
·       ቅድስት = የ ቤት ቅጽል
·       ይእቲ = ማሠሪያ አንቀጽ

30. “እለ ትነብሩ ተንሥኡ” በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ
ትእዛዝ የሚሰጠው በተውላጠ ስም ሲቀመጥ “አነ” ወይም “ንሕነ” ትእዛዝ የሚቀበሉት ደግሞ “አንትሙ” የሚባሉት ናቸው፡፡(ማለትም 1ኛ መደብ እና 2ኛ መደብ)

31. ከአውደ ጥናት ለእናንተ (ለግእዝ ተማሪዎች) ደብዳቤ መላክ ቢያስፈልግ ከፖስታው ጀርባ ላይ የሚከተሉት ይጻፋሉ።

እምነ/ ከ/ From
አውደ ጥናት Awde Tinat
1111 Gojam Ave.
Damot, GM 666
            
ለ/ ለ /To
አርድእተ ግእዝ/Ardete Ge’ez
2222 Piasa St. 444