Friday, June 3, 2016

ክፍል 34 ተናባቢ ፊደላት


ተናባቢ ሆሄያት


ተናባቢ ማለት ተያያዥ ማለት ሲሆን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላት በአንድ ላይ ተያይዘው ሲጻፉና ሲነበቡ ተናባቢወይም ኃረግም ይባላሉ። ባለቤትነትን ከምናመለክትባቸው መንገዶች መካከልም ተናባቢ ቃላት ናቸው። 

ቃላት የሚናበቡበት ምክንያት ለሦስት አበይት ሥራዎች ነው
1.      ባለቤትነትን ወይም ባለንብረትነትን ለመጠቆም ወይም ለማመልከት
2.     ምንነትን ማንነትን ወዘተ ለመግለጽ
3.     ንግግርን ለማራዘምና ሥርዓተ ዜማን  ወይም ንባብን ለማስተካከል የሚሉት ሲሆኑ ከነዚህም ውጭ  ሌሎች ተመሳሳይ  አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላትን ለማናበብ የምንፈልገውን ቃል ወይም ንብረቱን መጀመሪያ ላይባለንብረቱን ቀጥለን እናስቀምጣለን ፤ሆሄያትን ለማናበብ  የቃሉን የመጨረሻ ሆሄ መሠረት ያደረገ ሕግን መከተል አለብን። ይህም

·       ሳልስን ወደ ሐምስ (በሣልስ የሚጨርስ ቃል ሲሆን ማለት ነው)
·       ሳድስን ወደ ግእዝ መቀየር አለብን (በሳድስ የሚጨርስ ቃል ሲሆን ማለት ነው)
·       ግእዝ(በግእዝ ሆሄ የሚጨርስ ቃል)
·       ራብዕ(በራብዕ ሆሄ የሚጨርስ ቃል)
·       ሐምስ (በሐምስ ሆሄ የሚጨርስ ቃል) እና
·       ሳብዕ (በሣብዕ ሆሄ የሚጨርስ ቃል)  ሳይቀየሩ መናበብ ይችላሉ::

ምሳሌ፦ በግእዝ “መጽሐፍ” ማለት በአማርኛም በቁሙ መጽሐፍ ነው፤ ይህ የያዝሺው ወይም የያዝከው  የምታነቡት ማለቴ ነው መጽሐፍ የማን መሆኑን ከምንገልጽባቸው መንገዶች አንዱ  በማናበብ ነው ብለናል ስለዚህ “መጽሐፍ” የነበረውን ቃል  ከባለ መጽሐፉ ጋር ለማናበብ ማለት መጽሐፉ የማን እንደሆነ ለመናገር ቃሉ በሳድስ ከጨረሰ ወደ ግእዝ ይቀየራል ብለናል ስለዚህ መጽሐ የሚጨርሰው በሳድስ ስለሆነ የመጨረሻዋን ሳድስ ፊደል ወደ ግእዝ በመቀየር “መጽሐ መላኩ” ብትሉ ወደ አማርኛ ሲቀየር “የመላኩ መጽሐፍ” ይሆናል። ስለዚህ መጽሐፉ የማን ንብረት ነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ የመላኩ ይሆናል። 

ተናባቢ ቃላትን ስንተረጉም ብዙ ጊዜ “የ” የሚል አመልካች ሆሄ ከሁለቱ ቃላት መካከል ይወጣል። የሚከተሉትን ምሳሌዎች ይመልከቱ
·        መጽሐፈ ነገሥት = የነገሥታት መጽሐፍ

https://amzn.to/2IhIfvs
·       

የክርስትና ስም ሁሉ ተናባቢ ነው
መድኃኔ ዓለም= የዓለም መድኃኒት
·        ጽጌ ገነት = የገነት (የጓሮ) አበባ
·        ደመና ሰማይ =  የሰማይ ደመና
·        ተወክፎ ነግድ = እንግዳን መቀበል
















No comments:

Post a Comment