Sunday, December 23, 2018

የግእዝ ቋንቋ፡ የመጀመሪያው የሰብአዊ ፍጡር ቋንቋ/Ge'ez Language: The First Language of Hu...



“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” ስለግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ታሪክ ነው።
የግእዝ ቋንቋ የመጀመሪያው የሰብአዊ ፍጡር ቋንቋ ነው ወይስ አይደለም?
“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የተሰኘውን የግእዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፌን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ

https://amzn.to/2WUPz3x 

አንድን ነገር ነው ወይም አይደለም ለማለት፤ የአንድን ታሪክ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የምንጠቅሰው አንዱ የጽሁፍ
ማስረጃ ቢሆንም የጽሁፍ ማስረጃ ብቻ ግን አይደለም፤ ነገር ግን ቡዙ ሌሎች መንገዶችም አሉ።
ከነዚህም መካከል፡
·       
ስለ ወቅቱ በቃል የሚነገሩና
እየተያያዙ የመጡ፤
·       
ተጓዳኝ የሆኑ ሌሎች ታሪኮችን
በማመሳሰል፤
·       
በወቅቱ ሰዎች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ
ቁሳቁሶች፤ አባባሎች ወዘተ ይገኙበታል። ስለዚህ እኛም ስለግእዝ
ቋንቋ ስንነጋገር ስያሜውን፤ ትርጉሙን፤ የሰጠውን አገልግሎትና በሰዎች
ዘንድ ያለውን ሲያያዝ የመጣ ተጨባጭ ታሪክ
(በቃልም ቢሆን) ወዘተ አብረን እናያለን።

ለማነኛውም በመጀመሪያ “ግእዝ” ስለሚለው ቃል ወይም ስለ ስያሜው፤
እንነጋገራለን
ስያሜና ትርጉም

“አግአዘ” ነፃ አወጣ ከሚለው ግእዛዊ ግሥ “ግእዝ”
የሚል ቃል ይወጣል ትርጉሙ “ነፃነት” ማለት ነው።
ግእዝ ይዘቱን መሠረት በማድረግ “መጽሔተ አእምሮ”
ተብሎ ይጠራል። የእውቀት መስተዋት
(እውቀትን ወይም ጥበብን የሚያሳይ) ማለት ነው። የግእዝ
ቋንቋ መዝገበ ቃላት መጽሐፍ “መጽሐፈ ሰዋስው መጽሔተ አእምሮ” የሚል ርእስ አለው።

1. 
ለመሆኑ የሰው ልጅ የሚግባባው
በአንድ ቋንቋ ብቻ ነበር ወይስ ብዙ ቋንቋዎች ነበሩት? ስለዚህ ጉዳይ
መጽሐፍ ቅዱስ
ምን ይላል?፤ ዓለማውያን ጠበብትስ (የቋንቋ ምሁራን) ምን ይላሉ? “ ወአሐዱ ነገሩ ለኵሉ ዓለም ወአሐዱ ቃሉ።

የዓለም ቋንቋዎች ቤተሰብ
Ethnology
ባለፈው እንደተነጋገርነው የቋንቋ ቤተሰቦች (ላንጉች ፋሚሊ) የሚባሉት በጣም ብዙ ዓይነት ናቸው ለምሳሌያህል።
·       
የሚባሉት ብዙዎች ናቸው
·       
ለምሳሌ
·       
ኢንዶ ኤብሮፒያን
·       
አውስትሮንኢዥያን
·       
አፍሮ አስያቲክ
·       
ኒሎ ሳሃራን
ወዘተ የሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
 የቋንቅው ቤተሰብ ወይም ላንጉች
ፋሊሊ ትልቁ አከፋፈል ሲሆን በውስጡ ደግሞ ብራንች ወይም ቅርንጫፍ በመባል ይከፋፈላሉ።
(የኛ የሰመቲክ ቋንቋ ቤተሰብ የሚባሉት በዚህ
ውስጥ ይመደባሉ ማለትም የአፍሮ አስያቲክ ወይም የኒሎ ሳሓራን ቋንቋ ቤተሰብ የሚባሉት
ቅርንጫፎች ናቸው)

 የመጀመሪያው
የሰው ልጅ ቋንቋ ከዛሬ ሁለት መቶ ሺህ እና አምስት መቶ ሺህ ዓመታት መካከል በነበሩት ዓመታ
200,000 years ago and 50,000 years ago በምስራቅ አፍሪካ ይነገር እንደነበር ፕሮቶ ላንጉች (proto-language) በማለት
የቋንቋ ምሁራን ይናገራሉ።

2. 
ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የግእዝ
ቋንቋ እግዚአብሔር ፍጥረቱን የፈጠረበት የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ለማለት ከሚሰጧቸው ምክንያቶች መካከል አንዱና ዋናው ምንድን ነው?

3. 
ግእዝ የመጀመሪያው የሰብአዊ
ፍጡር ቋንቋ ባይሆን ኖሮ ለምን የውጭ ዜጎች ይፈልጉታል፤ ለምንስ እንደ ቅዱስና በጣም ተፈላጊ ቋንቋ አድርገው ለምን ይቆጥሩታል?

4. 
የግእዝ ቋንቋ ከሌሎቹ የአገራችን
ቋንቋዎችና ከዓለምም ቋንቋዎች ተለይቶ በተለየ ብሔር ያለመጠራቱና ኢትዮጵያዊኛ እየተባለ በጠራቱ ምንን የሚያመለክት ይመስለዎታል?

የዓለማዊ ሳይንቲስቶች
ምስክርነት
Ethnology
ባለፈው እንደተነጋገርነው የቋንቋ ቤተሰቦች (ላንጉች ፋሚሊ) የሚባሉት
በጣም ብዙ ዓይነት ናቸው ለምሳሌያህል።
·       
የሚባሉት ብዙዎች ናቸው
·       
ለምሳሌ
·       
ኢንዶ ኤብሮፒያን
·       
አውስትሮንኢዥያን
·       
አፍሮ አስያቲክ
·       
ኒሎ ሳሃራን
ወዘተ የሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
 የቋንቅው ቤተሰብ ወይም ላንጉች
ፋሊሊ ትልቁ አከፋፈል ሲሆን በውስጡ ደግሞ ብራንች ወይም ቅርንጫፍ በመባል ይከፋፈላሉ። (የኛ የሰመቲክ ቋንቋ ቤተሰብ የሚባሉት
በዚህ ውስጥ ይመደባሉ ማለትም የአፍሮ አስያቲክ ወይም የኒሎ ሳሓራን ቋንቋ ቤተሰብ
የሚባሉት ቅርንጫፎች ናቸው)

 የመጀመሪያው
የሰው ልጅ ቋንቋ ከዛሬ ሁለት መቶ ሺህ እና አምስት መቶ ሺህ ዓመታት መካከል በነበሩት ዓመታ
200,000 years ago and 50,000 years ago በምስራቅ አፍሪካ ይነገር እንደነበር ፕሮቶ ላንጉች (proto-language) በማለት
የቋንቋ ምሁራን ይናገራሉ።

ታላቁ ሊቅ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት
ሕዲስ” በተሰኘው የቋንቋዎች መድበል ግእዝና እና አማርኛን ትግርኛን ሌሎቹንም የአገራችን ቋንቋዎች ሳይቀር ከእብራይስጥ፤ ከአረብኛ
ከግሪክኛ ቋንቋዎች ጋር በማመሳጠር ከምንጩ ከመነሻው የሚያስረዳ የቋንቋ መድበል ነው። እና ይህ መጽሐፍ በመግቢያው በገጽ 10 ላይ

“ የዓለም
ቋንቋ ሁሉ በየነገዱ ስም ሲጠራ ግእዝ ብቻ በራሱ ስም ብቻ ይጠራል” ግእዝ 1ኛ መጀመሪያ ማለት ነው፤
“የብሉይ መምህራን ይልቁንም የጀርመን ሊቃውንት እነ ሲዲ ጳውሎስ፤ መአልም ዮሐንስ የተባሉት “ ወኮነ ኵሉ ምድር አሐተ ከንፈረ ወአሐደ ነገር.. ያለውን ይዘው ግእዝ የአዳም
ቋንቋ ነው
ይላሉ”

“ወአሐዱ ነገሩ ለኵሉ ዓለም ወአሐዱ ቃሉ።” “ወይቤ እግዚአብሔር
ናሁ አሐዱ ዘመድ ውእቱ ኵሉ ወአሐዱ ነገሩ ወከመዝ አሐዙ ይግበሩ ወኢየኀድጉ ይእዜኒ ገቢረ ዘሐለዩ በልቦሙ።

“ንዑ ንረድ ወንዝርዎ ለነገሮሙ ከመ ኢይሳምዑ ነገሮሙ አሐዱ ምስለ
ካልኡ። ወዘረወ እግዚአብሔር ነገሮሙ ወዘረዎሙ ውስተ ኵሉ ገጸ ምድር ወኀደጉ እንከ ነዲቆታ ለይእቲ ሀገር ወለውእቱ ማኅፈድ”

= የዓለም ሁሉ ቋንቋ አንድ ንግግሩም አንድ ነበረ፤ ---- እግዚአብሔርም
አለ እንሆ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፤ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ መሥራትን
አይተውም፤ ኑ እንውረድ አንዱ የሌላውን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው። እግዚአብሔርም ቋንቋቸውን ለያየ፤ ከዚያም
በምድር ፊት ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከዚያም በኋላ ከተማይቱንና ግንቡን መሥራትን ተዉ።
ስለዚህም ስሟ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ
ሁሉ ደባልቋልና፤ … ዘፍ. 11፡1

 “ዳግመኛም
የሐዲስ መምህራን፦ “ወአሐዙ ይንብቡ በልሳናት ካልኣት” ያለውን እና “ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር” ካለው አያይዘው “ልሳናት ካልኣት” ከተባሉት አንደኛው ግእዝ ነው፤ ከኢትዮጵያ ለፋሲካ በአል
የሄዱት ፈላሾችና አይሁድ የጰራቅሊጦስ ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስን ስብከት በግእዝ ቋንቋቸው ስለሰሙ አምነው ተጠምቀው ከ3ቱሺህ አርድእት/ተከታዮች
ተቆጥረዋል” ይላሉ።
የሐዋርያት ሥራ 2፤ መዝሙር 67፡31
እምነ አውደ ጥናት ዘግእዝ
“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን”
በሰላም ያስተራክበነ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጸሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት፤

Wednesday, December 12, 2018

Wednesday, September 19, 2018

የዜማ ተማሪ ወደ አዲስ ትምህርት ቤት በመሄድ መረጃ በመጠየቅ ላይ /Traditional Student Looking F...



ሰላም ለክሙ አርድእት 
በዚህ ቪድዮ ላይ የምታዩዋቸው እና የሙትሰሟቸው ቅኔ ወይም ግእዝ የሚያውቁ የዘማ ተማሪዎች ናቸው፤ ሆኖም ግን በንግግራቸው ውስጥ ብዙ የቃላትና የአገባብ ስህተቶችን እንሰማለን፤ እኔ ግን እያስተካከልኩ በመጻፍ በቪዲዮው ውስጥ እንድታዩት አድርጊያለሁ። ነገር ግን እናንተ ተማሪዎቹ የሚናገሩትን ለመስማትና ለመጻፍ ሞክሩ፤ ከቻላችሁም እኔ ካስተካከልኩት ጋር በማነጻጸር ጉድለታቸውን ለመግለጽ ሞክሩ። መልካም ምርምር።
ተማሪ አንድ(፩)፦ እፎ ወአልከ እሁየ?

ተማሪ ሁለት(፪)፦ እግዚአብሔር ይሰባሕ

ተማሪ አንድ(፩)፦ ሐዳፉ ሀሎኑ እምዝ ኪያሁ ሐሲስየ ነበርኩ?

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ለምንት ሀሰስኮ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ ከመ እትሜሀር በዝ እምኔሁ ምስሌክሙ ሐሲስየ ነበርኩ

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ሐሰስኮኑ ለመምህር ናሁ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ እዎ ሐሰስክዎ

ተማሪ ሁለት(፪)፦ እምኀበ አይቴ መጻእከ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ አንሰ ዘመጻእኩ ቦቱ “ጎንደር” ይትበሃል፤

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ጎንደር! መኑ ውእቱ መምህሩ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ መምህሩ፤ የንታ ይትባረክ ይትበሃል፤

ተማሪ ሁለት(፪)፦ የንታ ይትባረክ? ሀሎኑ ናሁ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ እዎ ሀሎ፤

ተማሪ  ሁለት(፪)፦ ብዙኅ ተመሀሪ(መርድእ) ወይም (ብዙኃን አርድእት) ሀለዉኑ ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ እዎ አርድእት ሀለዉ

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ምንተ ከዊነከ መጻእከ(ለምንት መጻእከ)?

ተማሪ አንድ(፩)፦ አርሚምየ ውእቱ፤ አላ፡ ሰማእኩ ከመሀሎ በዝ ንስቲት ግብር ወመጻእኩ በዝ ይኄይሰኒ ብሂልየ።

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ኢይኄይስኑ ጎንደር እምዝንቱ መካን (ቤተ ትምህርት)?

ተማሪ አንድ(፩)፦ አንተ ለእመ ተጋሕከ በዘሆርከ ቦቱ ኵሉ ዘይኄይስ በከመ ዚአከ ውእቱ።

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ሀሎኑ መምህር  ውስተ ጎንደር?

ተማሪ አንድ(፩)፦ እዎ ሀሎ ----(?)

ተማሪ ሁለት(፪)፦ እስፍንት ተመሀሪ ሀሎ? (እስፍንት አርድእት ሀለዉ)?

ተማሪ አንድ(፩)፦ ተመሀሪ? ዘድጓ ወዘቅኔ?

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ዘቅኔ፡

ተማሪ አንድ(፩)፦ ዘቅኔ፤ ላዕለ ሠለስቱ ምዕት( አርድእተ ቅኔ ይትረከቡ ላዕለ ሠለስቱ ምዕት)

ትማሪ ሁለት(፪)፦ ዘድጓ?

ተማሪ አንድ (፩)፦ ዘድጓ፤ አርብዐ ወሐምስቱ

ተማሪ ሁለት(፪)፦ መኑ ዘተሐሥሶ መምህር?

ተማሪ አንድ(፩)፦ ዘዚአክሙ፡ እምዝ ዘሀሎ( መምህረ ዚአክሙ ዘሀሎ እምዝ)

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ምንተ ዘይሜህር ውእቱ ዘተሐሥስ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ ዜማ፤ ጾመ ድጓ

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ዜማ ምንተ ትትሜሀር? እምነ አይቴ በጻሕከ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ አንሰ?

ተማሪ ሁለት(፪)፡- እወ

ተማሪ አንድ(፩)፦አዲ ውእቱ፤ “ከመ ያፈቅር” ወጠንኩ ናሁ።

ተማሪ ሁለት(፪)፦ በጻሕከኑ ላዕለ “ከመ ያፈቅር”?

ተማሪ አንድ(፩)፦እዎ ላዕለ ላዕለ “ጎስዐ ልብየ”( እዎ በጻሕኩ ላዕለ ጎስዐ ልብየ)

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ተአምሮኑ ስሞ ለመምህሩ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ ዘዝ?

ተማሪ ሁለት(፪)፦ እዎ!

ተማሪ አንድ(፩)፦ ኢየአምሮ፤ መኑ ይትበሐል?

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ኢተአምሮኑ በስም?

ተማሪ አንድ(፩)፦ ኢየአምሮ!

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ኢተአምሮኑ ለመምህረ ድጓ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ ኢየአምሮ አዲ አንሰ እንግዳ ውእቱ

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ኢያእመርኮኑ በዜና? ለእመ ኢያእመርከ(ኮ) መኑ ብሂለከ መጻእከ?

ተማሪ አንድ(፩)፦ በዝ ሀሎ ዘይሜህር ዜማ ዘጾመ ድጓ ወዝማሬ ተብሂልየ ውእቱ ዘመጻእኩ

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ሰማዕከኑ አው ኢሰማእከ ከመ ይትበሃል ስሙ ገብረ ጻድቅ?



ተማሪ አንድ(፩) ፦ በዜና አጽምኢየ ሀሎኩ ከመ ዘይትበሃል “የኔታ ገብረ ጻድቅ፤


ተማሪ ሁለት(፪)፦ የኔታ ገብረ ጻድቅ መምህረ ድጓ ናሁ ኢሀሎ እምዝ፡


ተማሪ አንድ(፩)፦ እክህልኑ ከመ እጸንሆ እምዝ ነቢርየ?

ተማሪ ሁለት(፪)፦ እንዘ ይመጽእ እጼውአከ፤

ተማሪ አንድ(፩)፦ በዝ ነቢርየ እጸንሆ፤

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ሠናይ! አልቦ ተጽናስ፤

ተማሪ አንድ(፩)፦ ኦሆ፤

ተማሪ ሁለት(፪)፦ ጽንሆ ነቢረከ ንስቲተ፤

ተማሪ አንድ(፩)፦ ኦሆ፤ እጸንሆ(እጸንህ)








Saturday, August 18, 2018

የግማሽ ክፍያ ቅናሽ 12 ቀናት ይቀሩታል! ይህ ታላቅ ዕድል አያምልጠዎ!!


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው


ዛሬ ባጭሩ በአውደ ጥናት ዘግእዝ ስለሚሰጠው የ2019 ዓ/ም ትምህርት ለሦስተኛና ጊዜ እነግራችኋለሁ። ምክንያቱም የተሰጠው የጊዜ ገደብ እያለቀ ነው፡ እና ሁሉም የጊዜ ጥበት እንዳለበት አውቃለሁ ስለዚህ ስለሚረሳ ላስታውሳችሁ ብየ ነው።





ስለ ግእዝ ቋንቋ ትምህርት እጅግ ተፈላጊነት ሁላችንም እያወቅን ነው ብየ አምናለሁ ማለትም
·        የግእዝ ቋንቋ የታሪካችን ምንጭ ነው
·        የማንነታችን መለያ ማኅተም ነው
·        ባጭሩ የግእዝ ቋንቋ ሥጋዊውም ሆነ መንፈሳዊው ታሪካችን የተመዘገበበት ወይም የተጻፈበት ቋንቋ ነው

ስለዚህ፡ ራሳችንን እና ስለራሳችን ጥርት አድርገን ማወቅ ከፈለግን፤ ታሪካችን የተመሠረተበትን ቋንቋ መማር አለብን፤ ስለ እምነታችን በሚገባ ማወቅ የምንሻ ከሆነም የእምነታችን መሠረቶችና መመሪያዎች የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት ከመጀመሪያው የተጻፉበትን ቋንቋ ግእዝን መማር አማራጭ የለውም።

እንኳን እኛ ግእዝ ቋንቋችን የሆነ ይቅርና ቋንቋቸው ያልሆነ ፈረንጆች የግእዝን ቋንቋ ለመማር ደፋ ቀና እያሉ ይታያሉ፤ ከዚያም አልፎ የግእዝ ምሁራን መሆን የቻሉ ብዙ ፈረንጆች አሉ። ለምን ቢባል ምክንያቱም ግእዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ ነው፤ ከአምላክ ጋር በቃሉ አማካኝነት ለመገናኘት ግእዝን ማወቅ ወሳኝ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው።

በቀደምት ታሪክ የተጻፈውን እና በሌሎች የምንሰማውን ትተን አሁን ባለፈው ሳምንት በአውደ ጥናት በኩል በላክሁላችሁ ቪዲዮ በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ጥናት በማካሄድ ላይ የሚገኙት አሜሪካዊው አቶ ዳንኤል ዲከዝን የተባሉት ሰው የሚናገሩትን በእንግሊዘኛም በአማርኛም ሰምታችሁታል።

አቶ ዳንኤል መጽሐፈ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ዘንድ በተላከው በመልአኩ ቅዱስ ኡራኤል አማካኝነት ለነቢዩ ሄኖክ ተገልጾለት በግእዝ ቋንቋ እንደተጻፈ፤ ከዚያም ለታላቁ ለእግዚአብሔር ወዳጅ ለኖኅ እንደተላለፈና ይህንን መጽሐፍ ከጥፋት ውኃ በኋላ ሁሉ ጠብቆ እንዳቆየው፤ ከዚያም አባታችን አብርሃም ከሚስቱ ከሣራ ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ መጽሐፈ ሄኖክን በግእዝ ቋንቋ በማስተማሩ በግብጻውያን ዘንድ ሞገሥን እንዳገኘ እንደሚያምኑ እና ባደረጉት ጥናት መሠረትም እንደተገነዘቡ ይናገራሉ።

ስለግእዝ ቋንቋ ዘርፈ ብዙ የሆነ ሥጋዊና መንፈሳዊ ጥቅም በአውደ ጥናትም ሆነ በልዩ ልዩ የሕዝብ መገናኛ ድረ ገጾቼ በተደጋጋሚ ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር አስረድቻለሁ፤

እንዲሁም አሉ የተባሉ ታላላቅ የቤተክርስቲያናችንን እና የሐገራችንን ሊቃውንት በአውደ ጥናት እየጋበዝኩ ስለ ቋንቋው ጥልቅ ምሥጢር እና የማይመጠን ጥቅም በሰፊው እንዲያስተምሩ አድርጊያለሁ፤
ካለኝ የቋንቋው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ በዘመናዊ አቀራረብ የተዘጋጀ በቀላል ዘዴ የምትማሩበትን የመማርያ መጽሐፍ በአውደ ጥናት ስም አሳትሜ በአማዞን፤ በጉግል ፕሌይና በግልም በኩል እየተሠራጨ በዓለም ዙሪያ በመዳረስ ላይ ይገኛል።

ከሁሉም በላይ፡ ወደ የትም ቦታ ሳትሄዱ ሳትወጡ፤ ሳትወርዱ፤ በቦታና በጊዜ ሳይወሰን በያላችሁበት በቤታችሁም ሆነ በሥራ ቦታችሁ፤ ተኝታችሁም ሆነ ተቀምጣችሁ በየትም ቦታ፤በማነኛውም ጊዜ፤ በሥልካችሁ፤ በኮምፒዩተራችሁ፤ በታብሌት፤በአይፓድ ወዘተርፈ እየመጣላችሁ፤ እንድትማሩ ማድረግ ችያለሁ፤ ይህ ማለት እንደተገለጠ መጽሐፍ በእጃችሁ መዳፍ ቀርቦላችኋል ማለት ነው።

የሚገርመው ነገር፤ ለዚህ ብዙዎች ለመሰከሩለት (በሚከተለው የመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ስለ መጽሐፉና የትምህርት አሰጣጡ የተሰጠውን ምስክርነት ይመልከቱ)








ቀላል፤ ግልጽና ለመከታተል አመች ለሆነ የትምህርት አቀራረብ የምትከፍሉት ክፍያው ከጓደኞቻችሁ ጋር ለግብዣ ወደ አንድ ሆቴል ብትሄዱ ለአንድ ምሽት የእራት ዋጋን እንኳን የማይሸፍን ገንዘብ ነው። ከዚያም አልፎ አሁን ደግሞ ቋንቋውን ለሁላችሁም ለማዳረስና ሁላችሁንም ተጠቃሚ ለማድረግ ባለኝ ጽኑ  ፍላጎት ምክንያት ከዚያው ከነበረው አንስተኛ ክፍያ ግማሹን ቀንሸ ሁላችሁም የመማር ዕድሉ እንዲኖራችሁ አድርጊያለሁ።

ስለዚህ አሁን በተሰጠው ዕድል የመጠቀሙ ፈንታ የናንተ ድርሻ ይሆናል። በአሁኑ ጊዜ የተሰጠው ቅናሽ የጊዜ ገደቡን ሊጨርስ 12 ቀናት ይቀሩታል። ስለዚህ ይህ ዕድል ሳያመልጣችሁ ተጠቀሙበት እላለሁ።

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ።

Thursday, August 9, 2018

Mr Daniel de Caussin About the Book of Enoch and Geez language Amharic t...


አቶ ዳንኤል ዲ ካሲን የተባለው ስው በእንግሊዘኛ 
በአውደ ጥናት ካስተላለፈው ቪዲዮ የተተረጎመ 


Hello, my name is Daniel de Caussin, I live here in Dunedin, Florida USA with my wife Martha, and [I have been interfacing with [Melaku Besetegn, I hope I pronounced that correctly, who is a deacon and preacher in the Ethiopian Orthodox Tewahido Church]  and he asked me to make this video which I am doing now, and he asked me three questions the first question was

1.  How did I become interested in Ge'ez, the second question 
2.  Why do I want to learn keys in the third question is 
3.  What do I know and believe about the Ge'ez language the history of the Ge'ez language.

So I will address those in this short video, the first question is why did I become interested in Ge'ez: it is because my wife and I started reading the book of Henoch and in its various translations we discovered that some translators would add words, subtract words, change the order of the chapters around and verses, just at whatever whim they had at the time.

Many of the people who did these books didn't even believe that the book of Henoch was inspired words of our heavenly father, they believe that "a man" wrote them down at various times throughout history, but we know that this book was specific for us, you and I, for these end times and this, was the desire of Henoch's heart, is that we all would read this and read the words properly,



so what we were inspired to do was to look for the original versions of the book of Henoch which happened to be in Ge'ez, and that's why we became interested in the Ge'ez language,

and we actually have four different versions or four different digital copies of handwritten manuscripts, which we are comparing word by word and letter by letter to see where people had opportunity to add whatever they want it over the years, and some of these manuscripts are from the 1300s and so we are talking many many many years of opportunity to add subtract or wrest the words that were given to Henoch by the angel Uriel.



We also know that Henoch gave his grandson, Noah, the book that he had, and after the flood Noah carried this book through the flood and he later on his grandchildren, Abraham especially came to live with Noah, and Abraham learned this book of Henoch, and learned Ge'ez and was able to read it and actually speak to people in his area in Ge'ez



and the time that from the Dead Sea Scrolls we have it written that Abraham when he went down into Egypt, read the book of Henoch to the people of Egypt, and gained favor because of this reading of the book of Henoch, and I believe that was in Ge'ez, and the Ethiopians have influenced people throughout the Scriptures. Moses married an Ethiopian woman and probably spoke Ge'ez at that time as well, so Ge'ez has an old and very rich history, the book of Henoch was written especially for us, this is why it is important for us to find the original information and present it properly.



 ግእዝ የመጀመሪያው የሰብአዊ ፍጡር ቋንቋ ነው!!

እርሰዎስ ምን ይላሉ? ሼር አድርጉት!!!

የግእዝን ቋንቋ በመማር መጽሐፈ ሄኖክን ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎምና ስለ መጽሐፉና ስለ ግእዝ ቋንቋም ልዩ ጥናትን በማካሄድ ላይ የሚገኘው አሜሪካዊው አቶ ዳንኤል ዲ ካሲን የተባለው ስው በእንግሊዘኛ በአውደ ጥናት ካስተላለፈው ቪዲዮ የተተረጎመ ነው። እንግሊዘኛውም አብሮ አለ።





“ ሰላም ስሜ ዳንኤል ዲ ካሲን ይባላል የምኖረው ከባለቤቴ ከማርታ ጋር በአሜሪካ ፍሎሪዳ ውስጥ ዱኔዲን በምትባል ቦታ ነው።



እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዲያቆንና ሰባኬ ወንጌል ከሆነው ከመምህር መላኩ አስማማው ጋር (በትክክል ተናግሬው ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ) ታሪካዊ የመረጃ ልውውጥ ስናደርግ ይህንን አሁን የማደርገውን ቪዲዮ እንዳዘጋጅ ጠየቀኝ እንዲሁም ስለ ግእዝ ቋንቋ ሦስት ጥያቄዎችን ጠየቀኝ



ጥያቄዎቹም ፦

የመጀመሪያው ጥያቄ “ስለ ግእዝ ቋንቋ እንዴ ፍላጎቱ ሊያድርብኝ ቻለ”? የሚል ነበር

2ኛው ጥያቄ ደግሞ “ለምን የግእዝን ቋንቋ መማር እንደምፈልግ”

3ኛው ጥያቄ፡“ስለ ግእዝ ቋንቋ ቅድመ ታሪክና ምንነት የማውቀውና የማምነው ነገር ምንድነው? የሚሉ ናቸው።



ስለዚህ የተጠቀሱትን ሁሉ በዚህ አጭር ቪዲዮ አቀርባቸዋለሁ።

ስለ ግእዝ ቋንቋ እንዴት ፍላጎት ሊያድርብህ ቻለ ለሚለው ለመጀመሪያው ጥያቄ ምክንያቱ እኔና ባለቤቴ መጽሐፈ ሄኖክን ማንበብ ጀመርን፤ እና ብዙ በተለያዩ ሰዎች የተተረጎሙ  ልዩ ልዩ ቅጅዎችን ስንመለከት አንዳንዶቹ ትርጉሞች የቃላት መቀነስ፤ መጨመር፤ የምዕራፍና የቁጥር መዘዋወር ይታይባቸዋል፤ በአጠቃላይ የተዘበራረቁ ናቸው።



እነዚህን ቅጅዎች የተረጎሙ አብዛኛዎቹ ሰዎች መጽሐፉ ከብዙ ዘመናት በፊት በታሪክ ሂደት አንድ የሆነ ሰው የጻፈው እንጂ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ የሰማያዊው አባታችን የእግዚአብሔር ቃል መሆኑንም የሚያምኑ አልነበሩም።



ነገር ግን ይህ መጽሐፍ በተለይ ለዚህ ለፍጻሜ ዘመን ለዚህ ጊዜ በቀጥታ ለእኔና ለእናንተ የተሰጠ እንደ ሆነ እናውቃለን፤ ይህም የሆነው እኛ ሁላችን ይንን መጽሐፍ በትክክል እንድናነበው የነቢዩ ሄኖክ የልብ መሻት ስለሆነ ነው፤ 



ስለዚህ እኛ የዚህን መጽሐፍ ትክክለኛ ትርጉም ከምንጩ ለማወቅ በመንፈስ አነሣሽነት ተነሣሳን፤ ምንጩ የመጀመሪያ ኦርጅናሉ ደግሞ የተጻፈው በግእዝ ቋንቋ ስለሆነ የግእዝን ቋንቋ ለማወቅ ፍላጎቱ ያደረብኝ ምክንያት ይህ ነው።



በነገራችን ላይ አራት የተለያዩ ትርጉሞች ወይም አራት የተለያዩ በዕጅ የተጻፉ የእጅ ጽሁፍ ቅጅዎች አሉን፤ ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ የተነሳሳንበት ምክንያት በነዚህ ቅጅዎች ውስጥ ፊደልን ከፊደል፤ ቃልን ከቃል፤ ጋር በማነጻጸር ሰዎች በዘመናት ሂደት (ብዛት) የሚፈልጉትን ቃል ሁሉ ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ እንዴት ዕድል እንዳገኙ ለማየት ወይም ለመመርመር በመሻት ነው፡፡



አንዳንዶቹ ጽሁፎች በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን (ቅድመ ክርስቶስ ማለት ነው) የነበሩ ናቸው፤ ይህ ማለት በጣም በጣም ብዙ ብዙ ስለሆኑ ዘመናት ነው እያወራን ያለነው። ይህ ማለት ደግሞ እግዚአብሔር በመልአኩ በቅዱስ ኡራኤል አማካኝነት ለነቢዩ ሄኖክ በሰጠው ቃል ላይ ሰዎች የፈለጉትን ቃል ለመጨመር፤ለመቀነስ፤ ብሎም ለመደምሰስ የረጅም ጊዜ ዕድል ነበራቸው ማለት ነው፡፡



እኛ ደግሞ ነቢዩ ሄኖክ ለልጅ ልጁ ለኖህ ይህንን መጽሐፉን እንደሰጠው እናውቃለን፤ ኖህም ይህንን መጽሐፍ ከጥፋት ውኃ በፊትና በኋላም ይዞት ቆይቷል፤ ቆይቶም የልጅ ልጆቹ በተለይም አብርሃም ወደሱ መጥቶ ከኖኅ ጋር አብሮ እየኖረ ይህንን መጽሐፍ መጽሐፈ ሄኖክን አጠና፤ የግእዝን ቋንቋም ተማረ፤  መጽሐፉን በግእዝ ማንበብ ቻለ፤



ብሎም በአካባቢው ካሉት ሰዎች ጋር በግእዝ ቋንቋ መነጋገር ወይም መግባባት ቻለ፤ በሙት ባሕር ከተገኙት ጥቅልሎች ወይም ቅጅዎች በኋላ አብርሃም ወደ ግብፅ በወረደ ጊዜ መጽሐፈ ሄኖክን ለግብጻውያን በግእዝ ቋንቋ ያነብላቸው ነበር፤ በዚህም ምክንያት ሞገስን አግኝቶበታል፤ መጽሐፈ ሄኖክን ያነበበላቸው በግእዝ ቋንቋ እንደነበርም አምናለሁ።



ኢትዮጵያውያንም በዚህ መጽሐፍ ወይም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሰዎችን በማሳመን ማርከውበታል፤አሳምነዋል።

ነቢዩ ሙሴም እንደዚሁ ኢትዮጵያዊቷን አግብቶ ስለ ነበር በዚያን ጊዜ ምናልባትም የግእዝን ቋንቋ ይናገር ነበር ማለት ይቻላል።



ስለዚህ ግእዝ ጥንታዊና የታሪክ ባለጸጋ የሆነ ቋንቋ ነው፤

መጽሐፈ ሄኖክ ይልቁንም ለኛ የተጻፈ ነው፤ ለዚህም ነው ኦርጅናሉን ወይም ምንጩን በግእዝ ቋንቋ የተጻፈውን መረጃ ወይም ጽሁፍ አግኝተን ትክክለኛውን ቃል በተገቢው መንገድ ማቅረባችን ተፍላጊ የሆነበት ምክንያት።”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አሜን

ትርጉም በመ/ር መላኩ አስማማው ዘአውደ ጥናት

ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

Saturday, June 30, 2018

ለ2019/2011 ዓ/ም የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ምዝገባ ዛሬ ተጀመረ/Registration for Ge'ez Langua...


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ የአውደ ጥናት ዘግእዝን የቀጣይ የትምህርት ዘመን የምዝገባና የአከፋፈል እንዲሁም የትምህርት ሁኔታ አንድ በአንድ አስረዳችኋለሁ ቪዲዮውን በትኩረት በመስማት በተሰጠው መመሪያ መሠረት ምዝገባችሁን ከወዲሁ ታጠናቅቃልችሁ ማለት ነው።  መልካም የምዝገባ ጊዜ።
በ2019 ወይም 2011 በአውደ ጥናት ዘግእዝ ለሚስጠው የልሣነ ግእዝ ትምህርት የወጣ ማስታዎቂያ
አውደ ጥናት ዘግእዝ በመጭው ዓመት 500 አምስት መቶ ተማሪዎችን ለማስተማር በዝግጅት ላይ እንገኛለን።
ለጀማሪዎችና ለመካከለኞች የሚሰጡ ሁለት ዓይነት የትምህርት ደረጃዎች ብቻ ይኖራሉ. በያንዳንዳቸው 250 ተማሪዎችን ብቻ እንቀበላለን።
በዚሁ ዓመት በአውደ ጥናት ዘግእዝ የብዙኃኑን የመማር ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ቅናሽ አድርገናል።
ከአሁን በፊት ከነበረው የአከፋፈል መንገድ የተደረገ ለውጥም አለ ይህም ለውጥ የሚከተለዉን ይመስላል።
1.  ባለፈው ዓመት እንደምታውቁት የአከፋፈል አማራጭ ከሙሉ ክፍያ ጀምሮ እስከ ወርሃዊ ክፍያ ድረስ የመክፈል አማራጭ ነበረ፤ ሁኖም ግን እስካሁን ከልምድ እንዳየነው ተማሪዎች በወቅቱ ባለመክፈል፤ከከፈሉ በኋላም የተሟላ መረጃ ባለመላክ አሠራሩን አመች እንዳይሆን አድርገውታል።
 ማለትም በተለያየ መንገድ የሚላከውን ክፍያ ለመቀበል ከአንድ ጊዜ በላይ በመመላለስ፤ በመደዋወል ጊዜን የሚያባክን በመሆኑ ይህንን ሁኔታ የተሻለ ለማድረግ ሲባል በ2019 ሁለት  የአከፋፈል አማራጮች  ብቻ ይኖራሉ፤ እነዚህም በየ ዓመቱና በየ 6 ወር  የሚፈጸሙ ናቸው።
2.  የክፍያ መጠንን በተመለከተ አዲስ የወጣ የክፍያ ቅናሽ አለ ይህንን ቅናሽ ማግኘት የሚችሉት ግን የዓመቱን በአንድ ጊዜ የሚከፍሉ ተማሪዎች ብቻ ናቸው፤ በየ6 ወራት የሚከፍሉ ቅናሽ አያገኙም ማለት ነው። አንድ ጊዜ የሚከፍሉ ብቻ ናቸው የቅናሹ ተጠቃሚዎች ማለት ነው።
የተማሪዎች ብዛትና የወጣው ልዩ ቅናሽ፡ እንዲሁም ቅናሹን ለማግኘት ወይም ሙሉውን ለመክፈል የሚቻልባቸው ቀናት
በሁለቱም ደረጃዎች(ለጀማሪና ለመካከለኛ) 500 ተማሪዎች ብቻ ይመዘገባሉ።እነዚህም በጀማሪ 250 በመካከለኛ 250 ድምር 500 ተማሪዎች ማለት ነው።
ይህ ማስታዎቂያ ከወጣበት ከዛሬ ከ ከሰኔ 28/ 2018/ ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 1 ቀን 2018/ መስከረም 2 ቀን 2011 ዓ/ም ድረስ ክፍያቸውን አጠናቀው የተመዘገቡ የመጀመሪያ 300 ተማሪዎች እንደየ አገሩ ከተመደበው ዓመታዊ ክፍያ ላይ ጀማሪዎች የግማሽ ዋጋ ቅናሽ፤ መካከለኞች ደግሞ የ 50 ብር ወይም ዶላር ቅናሽ ያገኛሉ።
ማለትም እንደየ አገሩ
·        በአፍሪካ የሚኖሩ በጀማሪዎች የመጀመሪያ 150 ተማሪዎች 1000 (አንድ ሺህ ብር)፤
·        በዐረብ አገራት የሚኖሩ $63 (63 ዶላር)፤
·         በአሜሪካና በአውሮፓ በሌሎችም አገራት (ከአፍሪካና ከዐረብ አገሮች ውጭ)ያሉ $100 (አንድ መቶ ዶላር) ይሆንላቸዋል።
በመካከለኞች ክፍል፡ የመጀመሪያ 150 ተማሪዎች 50 ብር ወይም ዶላር ተቀንሶላቸው ማለትም
በአሜሪካና በአውሮፓ በሌሎችም አገራት (ከአፍሪካና ከዐረብ አገሮች ውጭ)ያሉ
·        $125 ዶላር፤
በዐረብ አገራት የሚኖሩ
·        $75 ዶላር
በአፍሪካ የሚኖሩ
·        1950 ብር በመክፈል ለአንድ ዓመት መማር ይችላሉ
ከዚህ ላይ ግልጽ ለማድረግ ከተወሰነው ቀን ወይም ከ 300 ተማሪዎች በኋላ የሚገቡ ተማሪዎች ግን በተመደበው ክፍያ መሠረት ሙሉውን ክፍያ በመክፈል መማር ይችላሉ ማለትም ቅናሹ ለ300 ተማሪዎች(150 ከጀማሪ፤ 150 ከመካከለኛ) ብቻ ነው የሚሰጠው፤ ስለዚህ ቀኑን መጠበቅ የለባችሁም፤ ምክንያቱም ቀኑ ከመድረሱ በፊት 150 ሰው ከያንዳንዱ ደረጃ ከተመዘገበ ቅናሹ ይቆማል ማለት ነው።
·        ነባር ተማሪዎች ማለትም በአሁኑ ጊዜ በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ መካከለኛ ስለሚሸጋገሩ በግማሽ ዋጋ መቀጠል ይችላሉ። ነገር ግን  ነባር ተማሪዎችም ቢሆኑ ቅናሹን ለማግኘት በተመደበው ጊዜ ቀድመው መመዝገብና መክፈል ይኖርባቸዋል።
·        ትምህርቱ የሚጀመረው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር አንድ ቀን ሲሆን በአገራችን አቆጣጠር ታሕሳስ 23 ቀን ነው የሚሆነው ከዚያ በፊት ቢያንስ ጥር ከመግባቱ በፊት ማለትም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከታህሳስ 23 በፊት ምዝገባውን መጨረስ ግድ ነው ።
በ2019 የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ባጭሩ የሚከተሉት ናቸው የተጠቀሱት መሠረታውያኑ ናቸው እንጂ በውስጣቸው ስፋ ብለው የሚሰጡ ናቸው።
ለጀማሪዎች ከሚሰቱት ዋና ዋናዎቹ
ስለ ፊደላት ታሪክ፤ ስያሜ፤ብዛት፤ አይነት፤ ስምጽና አከፋፈል
ስለ ሆሄያት ተናባቢና አናባቢ
ስለ መኩሸ ሆሄያትና አጠቃቀማቸው
ስለ ቍጥሮች መሠረታዊ ትምህርት የሚሉት ሲሆኑ በምእራፍ አንድ የሚጠቃለሉ ናቸው።
በምዕራፍ ሁለት የሚሰጠው ስምንቱን የንግግር ክፍሎች የሚያጠቃልል ሲሆን ስምንቱ የንግግር ክፍሎች ደግሞ በተለያዩ ምዕራፎች ይከፈላሉ።
ማለትም
3.  ስም
4.  ተውላጠ ስም
5.  ግሥ
6.  ረዳት ግሥ
7.  ቅጽል
8.  መስተዋድድ
9.  መስተጻምር
10.         ቃለ አጋኖ የሚባሉት ሲሆኑ ለጀማሪዎች በሚመጥን መልኩ ይሰጣሉ።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና አርእስትና ሌሎችንም ከነዚሁ ጋር የሚያያዙትን ስንማር በሦስት ዓይነት መልኩ በጥልቀት እንማራለን፤ መጀመሪያ ትምህርቱ በድምጽና በጽሁፍ ይተላለፋል፤ ቀጥሎ ከ3 ቀናት በኋላ ከትምህርቱ የተውጣጡ አሥር ጥያቄዎች ይሰጣሉ፤ ተማሪዎች በተማሩት መሠረት በጥያቄዎቹ አማካኝነት ራሳቸውን ወይም ችሎታቸውን ይፈትሻሉ፤ በመጨረሻም ለተሰጡ አሥር የመመዘኛ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስና ሙሉ ማብራርያ ጭሙር በድምጽና በጽሁፍ ይለቀቃል ተማሪዎችሁ መልሳቸውን በማስተያየት ስህተታቸውን ያርማሉ።
ለመካከለኞች የሚሰጠው ትምህርት በመሠረታዊነት በስምንቱ የንግግር ክፍሎች ዙሪያ ሲሆን ልዩነቱ ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ይሄዳል፤ ለምሳሌ ግሥነ ብንወስድ በጀማሪዎች የሚሰጡት አበይት ግሦች ብቻ ሲሆኑ በመካከለኞች ሙሉ ትንታኔውን ጭምር እንማራለን ማለትም ከግሥ የሚወጡ ዘሮችን ጭምር በሰፊው እናረባለን፤ ውስብስብ የሆኑ ዐረፍተ ነገራትን እንሠራለን፤
የትምህርት አሠጣጡን በተመለከት በሁለቱም ክፍሎች አንድ አይነት ነው ትምህርት፤ጥያቄ፤መልስ በየሳምንቱ ይሰጣል ማለት ነው።
በተጨማሪም ተማሪዎች እርስ በርሳቸው በግእዝ ቋንቅው የሚወያዩበት የተለየ ግሩፕ ይኖራቸዋል።
በጭሩ ይህንን ይመስላል፡ የመማር ፍላጎቱ ያላችሁ ቀደም ብላችሁ በመመዝገብ መጀመር ትችላላችሁ።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

Wednesday, March 21, 2018

Learn Geez Through WhatsApp Group

በአውደ ጥናት ዘግእዝ የሚሰጡ የግእዝ ቋንቋ የትምህርት ደረጃዎችና ይዘታቸው


















በአውደ ጥናት ዘግእዝ የሚሰጡ የግእዝ ቋንቋ የትምህርት ደረጃዎችና ይዘታቸው
አውደ ጥናት ዘግእዝ ክፍል ፩ዱ ለወጣንያን(ለጀማሪ)
1.   ፊደልና ስለ ፊደላት አከፋፈል - ድምጽ- ከግእዝ እስከ ሣብዕ በደንብ ግንዛቤን መስጠት
2.   አጫጭር ዐ/ነገራትን በሚከተሉት አርእስት መሠረት የሰላምታ ቃላትና  አጠቃቀማቸው
3.   ደቂቅ አገባቦችን ትርጉማቸውና እና በዐ/ነገር እያስገቡ ማሳየት
4.   የመጠየቂያ ቃላትንና አጠቃቀማቸውን በአጫጭር ዐ/ነገር
5.   የሁለት ቃላትን አነባበብ ለምሳሌ (ሙያንና ባለ ሙያን በማያያዝ የአንድን ሰው ችሎታ ወይም ሙያ መናገር መምህር (ባለ ሙያ) ግእዝ (ሙያ)
6.   አሥሩ መራሕያን እና አጠቃቀማቸው
7.   የግሥ ርባታ ከአቢይ አንቀጽ እስከ ንዑስ አንቀጽ
8.   ቁጥር ከ1 እስከ 19 ያሉ የግእዝን ቁጥሮች
9.   የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል

አውደ ጥናት ዘግእዝ  ማዕከላውያን(ለመካከለኛ)፡
1.   ስምንቱ የንግግር ክፍሎች
2.   ግሥና የግሥ አወራረድ ከንኡስ አንቀጽ እስከ መጨረሻው
3.   ግልጽ የሆኑ(ግልጠ ዘ) ቅጽሎች
4.   ተውላጠ ግሥ
5.   ከግሥ የሚወጡ ዘሮች
6.   ባለቤት፤ ማሠሪያ አንቀ፤ ቅጽል፤ እና ተውሳከ ግሥ ያላቸው ዐ/ነገራትን መፍጠር
7.   የዐ/ነገራትን አካላትና ሙያ ማወቅ
8.   ደቂቅ አገባቦችን ማወቅ
9.   የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል

አውደ ጥናት ዘግእዝ  ፍፁማን(ለከፍተኛ)፡
1.   አገባቦችና አጠቃቀማችው
2.   8ቱ  መራኁት
3.   8ቱ  አርእስት
4.   50ው ሠራዊት
5.   4ቱ  አዕማድ
6.   4ቱ  አሥራው
7.   4ቱ  ፀዋትው
8.   ጽሁፎችን ከግእዝ ወደ አማርኛ መተርጎም እና የሥነ ጽሁፍ ልምምድ
9.   የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መ/ር መላኩ ነኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

ስለ ትምህርት አሰጣጡና አጠቃላይ ማብራርያ የሚከተለውን ቪድዮ ያዳምጡ

ተጨማሪ ማብራርያ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

ልዑል እግዚአብሔር ለዚች ቅጽበት በሰላም ጠብቆ ስላደረሰን የተመሰገነ ይሁን።

የግእዝ ቋንቋ ተከታታይ ትምህርታችን ታህሣስ አንድ ቀን (ታህሣስ 10 በፈረንጆች) ይጀመራል። ስለዚህ ከዚያ በፊት ምዝገባና ክፍያችሁን ማጠናቀቅ አለባችሁ። ክፍያውን እስከ ህዳር 30 (ታህሣስ 9 በፈረንጆች) ትከፍሉና ክፍያው የሚያዝላችሁ ግን ከጥር 1 ቀን በፈረንጆች ጀምሮ ለአንድ ዓመት ነው፤ ስለዚህ ከጥር በፊት ያለው አንድ ወር ነጻ ነው ማለት ነው።

በትምህርቱ የተመዘገባችሁት አብዛኛዎቻችሁ ሁላችሁም ማለት ይቻላል “በጀማሪ” ደረጃ ነው። ስለዚህ ሁለት ሰዎች ቢሆኑ ነው በመካከለኛ ደረጃ ያሉት፤ በከፍተኛ ያለ ግን የለም።

የራሴን አስተያየት ለመስጠት ያህል ከመጀመሪያው መጀመሩ በጣም የተሻለ ነው። ምክንያቱም መሠረቱን ማጥበቁ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ከመጀመሪያው እንጀምራለን፤ መጀመሪያው ደግሞ ፊደል ስለሆነ ከፊደል ነው የምንጀምረው፤ ምን አልባት ፊደል ሁሉም የሚያውቀውና ስለፊደል መማር መደጋገም መስሎ ሊታየን ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን ብዙ የማናውቀውና የጎደለብን ነገር ያለ የማይመስለን ብዙ ሊናውቀው የሚገባ ትምህርት በፊደሎች ውስጥ አለ። በተለይ ለግእዝ ትምህርት ስለፊደላት ሁለንተና በቃል ጭምር ማወቅና መያዝ በጣም ወሳኝ ነው። ስለዚህ የምናውቀው ነው ብላችሁ ሳትዘናጉ መከታተል ይኖርባችሁዋል።

ግሩፑን አንድ ግሩፕ ለጀማሪዎች አድርገን እንጀምረውና እንቀጥላለን ማለትም ክፍል አንድ የሚቀላችሁ ካላችሁ ለመካከለኞች ግሩፕ መክፈት ይቻላል፤ ክፍተኛም ካለ እንደዚሁ በሂደት ይሆናል። ትምህርቱ ለየት ባለና ጠለቅ ባለመልኩ በያንዳንዱ ንዑስ ርእስ ጭምር የልምምድ ጥያቄዎችን በመሥራት የሚሰጥና ቀላል፤ግልጽና በቂ ዕውቀትን የሚያስጨብጥ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ።

 ከናንተ የሚጠበቀው የሚሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ መተግበር ነው። ይህ ትምህርት በተለይ የትምህርቱ የማስተማር ስልት በየትም ቦታ ሊታገኙት እንደማትችሉ ምንም አያጠራጥርም። ይህ ማላት ባለሙያዎች የሉም ማለት ሳይሆን 1ኛ ያለውን ትንሺም ሆነ ብዙ ለሌሎች የማስተላለፉ ዘዴና ችሎታ የያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር የየግል ልዩ ስጦታ ነው። 2ኛው ደግሞ የቦታ፤የጊዜ፤ እና የዘመናዊ መሣሪያዎች አመች ሆነው መገኘታቸውም ሌላው ምክንያት ነው። ስለዚህ እነዚህን ሁሉ እግዚአብሔር ስላመቻቸልን እድሉን መጠቀም የያንዳንዳችን ድርሻ ነው።

የሚሰጠው የትምህርት ንድፍ የሚከተለውን ይመስላል

ለአንድ ዓመት ሰፋ ባለመልኩ የሚሰጡት አበይት የትምህርት ዓይነቶች በዘጠኝ ንዑሳን ክፍሎች የተከፈሉ ሲሆኑ የሚከተሉት ናቸው። (በጣም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ቃላትና ትምህርቶች/ዐ/ነገራት የበለጠ ግልጽ እንዲሆንላችሁና ተጨማሪ ዕውቀትንም ታገኙ ዘንድ ዓለም አቀፍ በሆነው በእንግሊዘኛም እንዴት እንደሚተረጎሙ እንነጋገራለን እንማራለን ይህም እንግሊዘኛን ለሚማሩ ተጨማሪ ጥቅም ነው)

1.   ፊደልና ስለፊደል በሚለው ንዑስ ርእስ
·         ደል ማለት ምን ማለት እንደሆነ እስከ መነሻው፤ ታሪክን ጨምሮ፤ ፊደል የሚጠራባቸው ልዩ ልዩ ስሞች፤ የግል፤የወል፤የደረጃ፤ ወዘተ ስያሜዎች፤ ዓይነት፤ ድምጽ፤ መኩሸ ፊደላትና የሚለያዩባቸው፤ የሚዋሃዱባቸው፤
·         ከፊደላት ውስጥ ከፊደልነት ሥራቸው ሌላ አገልግሎትን የሚሰጡ ፊደላትን አዲስ እና ልዩ በሆነ የአውደ ጥናት ብቻ የማስተማር ዘዴ ለይተን እንማራለን፤(ለበወ) እንዲሁም ሌሎች ከፊደላት ጋር የተያያዙ ዕውቀቶች በጥልቀት ይተነተናሉ።
·         በያንዳንዱ ንዑስ ርእስ የግንዛቤ ጥያቄ ዎች ይሰጣሉ

2.   አጫጭር ዐ/ነገራትን በሚከተሉት አርእስት መሠረት የሰላምታ ቃላትና  አጠቃቀማቸው
·         የሰላምታ ቃላትን መሠረት በማድረግ ልዩ ልዩ ትርጉሞ ያላቸውን ዐ/ነገራት መሥራት
·         ስለራሳችን ማንነት እና ታሪክ ባጭሩ መናገር እና መጻፍ
·         በምንማራቸው ዐ/ነገራት የምንጠቀምባቸውን ቃላት ትርጉም ማወቅ
·         በዐ/ነገራቱ ውስጥ የሚገኙትን ቃላትና የሥራ ድርሻቸውን ማወቅ
3.   ደቂቅ አገባቦችን ትርጉማቸውና እና በዐ/ነገር እያስገቡ ማሳየት
·         ደቂቅ አገባብ ምን ማለት እንደ ሆነ፤ አገልግሎትና ትርጉም
·         መቸና እንዴት ደቂቅ አገባቦችን እንደምንጠቀም ልዩ ልዩ ዐ/ነገራትን በመሥራት ልምምድ ማድረግ
4.   የመጠየቂያ ቃላትንና አጠቃቀማቸውን በአጫጭር ዐ/ነገር
·         የመጠየቂያ ቃላትን ትርጉም እና አጠቃቀም በዐ/ነገራት በማስገባት
·         ቦታን የሚመለከት
·         ጊዜን የሚመለከት
·         ርቀትን የሚመለከት
·         ቁጥርን የሚመለከት ወዘተ በመከፋፈል በሰፊው ልምምድ ማድረግ

5.   የሁለት ቃላትን አነባበብ ለምሳሌ (ሙያንና ባለ ሙያን በማያያዝ የአንድን ሰው ችሎታ ወይም ሙያ መናገር መምህር (ባለ ሙያ) ግእዝ (ሙያ)
·         በግእዝ ቁዋንቋ ህግ ሁለት ቃላት እንዴት ይያያዛሉ(ይናበባሉ)፤ ለምን ይናበባሉ፤
·         ሁለት ቃላትን ለማያያዝ የሚጠቅሙን ፊደላት፤
·         ሁለት ቃላትን በማያያዝ የሚገኙ ጥቅሞች
·         ሙያን፤ ባለሙያን፤ ወይም ሐብትን፤ እና ባለሐብትን ወዘተ እንዴት ማወቅ እንደሚቻል
·         ለምሣሌ፤ የክርስትና ስሞችን፤ የትምህርት ዓይነቶችን፤ ወዘተ ምሣሌ በማድረግ በሰፊው መነጋገር
6.   አሥሩ መራሕያን እና አጠቃቀማቸው
·         መራሕያን ስምና ትርጉም፤ ብዛትና ከሌሎች ቁዋንቁዋዎች ጋር ንፅጽር
·         አሥሩ መራህያን የሥነ ጽሁፍ ሁሉ መሠረቶች ስለሆኑ ሙሉ በሙሉ በቃል ጭምር መያዝ አለባቸው። ስለዚህ በግእዝ፤ በአማርኛ፤ እንዲሁም በእንግሊዘኛ ይብራራሉ።
·         ለምን ስሞችን ትተን ተውላጠ ስሞችን እንደምንጠቀም፤ መቸ እንደምንጠቀም፤ በተግባር በዐ/ነገር በሰፊው እናያለን፤
·         በአሥሩም ተውላጠ ስሞች ልዩ ልዩ ምሳሌዎችን መሥራት
7.   የግሥ ርባታ ከአቢይ አንቀጽ እስከ ንዑስ አንቀጽ
·         ግሥ/አንቀጽ ስያሜ፤ ምድብና ሥራ
·         ሐላፊ ግሥ/አንቀጽ
·         ትንቢት ግሥ/አንቀጽ
·         ዘንድ ግሥ/አንቀጽ
·         ንዑስ ግሥ/አንቀጽ
·         ከሃላፊ እስከ ንዑስ ያሉትን አናቅጽ በዐ/ነገራት እያስገባን በምሣሌ ማስረዳት
8. ቁጥር ከ1 እስከ 19 ያሉ የግእዝን ቁጥሮች
·         ቁጥር ትርጉምና ምድብ
·         ከ1 እስከ 10 ያሉ ቁጥሮች
·         ከ11 እስከ 19 ያሉ ቁጥሮች
·         ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መሠረታውያን ቁጥሮች በልምምድ ማስረዳት
·         ከቁጥር ጋር የተያያዙ አርእስትን ለምሣሌ የሣምንቱ ቀናትን፤ ከግእዝ እስከ ሳብእ ያሉ ሆሄያትን መዳሰስ

9. የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል
·         ትምህርቱ ከተጀመረ ከ2 ወራት በሁዋላ ተማሪዎች በውይይት ግሩፕ እርስ በርሳቸው ይወያያሉ፤ ጥያቄ ይጠያየቃሉ፤ መልስ ይሰጣጣሉ፤ መጨረሻ ላይ እኔ አየውና ማስተካከያ እሰጣለሁ።

የትምህርቱ መተላለፊያ መንገዶች

ትምህርቱ በድምጽ፤በጽሁፍና በቪዲዮም ይሰጣል እስካሁን በአውደ ጥናት ይሰጡ የነበሩት የግእዝ ትምህርቶች በአውደ ጥናት ዘግእዝ ቻናል ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህ ቪዲዮዎች ለሁሉም ሰው ነጻ ናቸው። ከአሁን በኁዋላ የሚለቀቁ ቪዲዮዎችም ግሩፑ እንዳይጨናነቅ የሚለቀቁት ወደአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው። ነገር ግን እየከፈሉ የሚማሩ ተማሪዎች ብቻ ሊንክ እየተላከላቸው የሚገኙ እንጂ ለሁሉም የሚታዩ አይደሉም (ፕራይቤት ይሆናሉ)፡ (አልፎ አልፎ ነጻ ትምህርቶችም ስለሚኖሩ) ስለዚህ ሁላችሁም እስካሁን የተለቀቁትን በነጻ ለመከታተል አዲስ የሚለቀቁትንም ለማየት በአውደ ጥናት ዘግእዝ  ሰብስክራይብ አድርጉ
ትምህርት የሚለቀቅባቸው ቀናትና የሚለቀቀው ትምህርት፡
ትምህርቱ የሚለቀቅባቸው ቀናት (አርብና ለቅዳሜና ሰኞ ለማክሰኞ ነው ግን ሰዓቱ እንደየ አገራቱ ይለያያል)
አንድን ትምህርት በሚገባ ለመማርና እውቀቱን ይዞ ለመውጣት ጊዜ ወሳኝ ነው ማለትም ትምህርቱን ደጋግመን ለማጥናት ጊዜ ማግኘት ግድ ነው። ስለዚህ አንዱ ትምህርት በሌላው ላይ መደራረብ ሳይኖር አንዱን አሸንፈን ወደ ቀጣዩ መራመድ አለብን በመሆኑም በሳምንት 2 ጊዜ ትምህርት ይለቀቃል አንዱ ትምህርቱ ነው፣ ሁለተኛው የጥያቄዎች ማብራርያና መልስ ነው። ስለዚህ
·          አንዱ ትምህርቱ ተዘጋጅቶ በድምጽ ይለቀቃል (ተማሪዎች ግን ባላቸው ጊዜያት ሁሉ እየመላለሱ መስማትና ማጥናት አለባቸው)
·         ሁለተኛ የሚለቀቀው ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራርያና መልስ ነው
·         በግል ማብራርያ የሚፈልግና የበለጠ ርዳታ የሚፈልግ ማነኛውም ተማሪ በውስጥ መስመር ሊያነጋግረኝ ይችላል፤ ከቻልሁ ወዲያውኑ እመልሳለሁ ካልቻልኩ ግን መልእክታችሁን ወይም ጥያቂያችሁን ብታስቀምጡ መልሱን ይዠ አነጋግራችሁዋለሁ። ማንም ተማሪ ትምህርቱ ከብዶት፤አልገባው ብሎ የሚቀር አይኖርም።

ክፍያና የክፍያ ሁኔታ
ክፍያው ከዚህ በፊትም ደጋግሜ ገልጨዋለሁ።
·         በኢትዮጵያ ለሚኖሩ 2000(ሁለት ሺህ) በዓመት
·         በአረብ አገራት ለሚኖሩ 3000(ሦስት ሺህ ብር ወይም 125 ዶላር) ባመት
·         በአሜሪካና በሌሎች የአውሮፓና እስያ አገሮች 200(ሁለት መቶ ዶላር) ባመት

አከፋፈል
·         በባንክ የቁጠባ ሂሣብ ቀጥታ የሚያስገቡ ሰዎች ወደ ባንክ ያስገቡበትን ደረሰኝ በስልካቸው ፎቶ አንስተው ለእኔ (በዋትስ አፕ ይልኩልኛል)ደረሰኙ ሲደርሰኝ መክፈላቸውን እመዘገባለሁ ለነሱም ደረሰኙን መቀበሌን መልሸ እጽፍላቸዋለሁ
·         በዌስተርን ዩኒየን(በኃዋላ) መላክ የሚፈልጉ ቀጥታ በስሜ ስለሚልኩት ከደረሰኝ በሁዋላ ከፍለዋል ብየ እመዘግባለሁ ለነሱም ገንዘቡን መቀበሌ ወደ ስልካቸው መልእክት እልክላቸዋለሁ።
·         በአካል የሚከፍሉም ከተቀበልኩ በሁዋላ እንዳይረሻ ወደ ስልካቸው ለመክፈላቸው ማረጋገጫ መልእክት እልክላቸዋለሁ።
የግሩፑ ሕግ
አንድ አስተማሪ የሚያውቀውን ሁሉ ለተማሪዎች የሚያስተምር ወይም የሚናገር ከሆነ አስተማሪ አይባልም አስተማሪ ማለት መጥኖ፤ ለክቶ፤ በሚያስተምራቸው ተማሪዎች ደረጃና መጠን እያዘጋጀ ነው ማስተማር ያለበት፤ የሚያውቀውን ሁሉ ከተናገረ፤ ለአንደኛ ክፍል ተማሪዎች የስድስተኛ ክፍል ትምህርትን ቀላቅሎ የሚናገር ከሆነ ተማሪዎችን ግራ በማጋባት መስመር ያስታቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም።

ስለዚህ በተማሪዎች መጠን የተዘጋጀውን ትምህርት ብቻ ለማስተማር በአስተማሪው ብቻ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ ትምህርቶች ብቻ በአስተማሪው በኩል ይለቀቃሉ:
·         በግሩፑ ውስጥ ከአስተማሪ በስተቀር ማንም ሰው፤ ምንም ነገር፤ መንፈሳዊም፤ ሥጋዊም፤ ስለ ግእዝ ትምህርትም ቢሆን ወደ ግሩፑ መልቀቅ አይችልም።

በተረፈግን የግእዝን ትምህርት በሚገባ ማንበብ መጻፍና መናገርም እንድትችሉ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መ/ር መላኩ ነኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው