ዛሬ ባጭሩ በአውደ ጥናት ዘግእዝ ስለሚሰጠው የ2019 ዓ/ም ትምህርት ለሦስተኛና ጊዜ እነግራችኋለሁ።
ምክንያቱም የተሰጠው የጊዜ ገደብ እያለቀ ነው፡ እና ሁሉም የጊዜ ጥበት እንዳለበት አውቃለሁ ስለዚህ ስለሚረሳ ላስታውሳችሁ ብየ
ነው።
ስለ ግእዝ ቋንቋ ትምህርት እጅግ ተፈላጊነት ሁላችንም እያወቅን ነው ብየ አምናለሁ ማለትም
·
የግእዝ ቋንቋ የታሪካችን ምንጭ ነው
·
የማንነታችን መለያ ማኅተም ነው
·
ባጭሩ የግእዝ ቋንቋ ሥጋዊውም ሆነ መንፈሳዊው ታሪካችን የተመዘገበበት ወይም የተጻፈበት
ቋንቋ ነው
ስለዚህ፡ ራሳችንን እና ስለራሳችን ጥርት አድርገን ማወቅ ከፈለግን፤ ታሪካችን የተመሠረተበትን ቋንቋ መማር
አለብን፤ ስለ እምነታችን በሚገባ ማወቅ የምንሻ ከሆነም የእምነታችን መሠረቶችና መመሪያዎች የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት ከመጀመሪያው
የተጻፉበትን ቋንቋ ግእዝን መማር አማራጭ የለውም።
እንኳን እኛ ግእዝ ቋንቋችን የሆነ ይቅርና ቋንቋቸው ያልሆነ ፈረንጆች የግእዝን ቋንቋ ለመማር ደፋ
ቀና እያሉ ይታያሉ፤ ከዚያም አልፎ የግእዝ ምሁራን መሆን የቻሉ ብዙ ፈረንጆች አሉ። ለምን ቢባል ምክንያቱም ግእዝ የመጽሐፍ ቅዱስ
ቋንቋ ነው፤ ከአምላክ ጋር በቃሉ አማካኝነት ለመገናኘት ግእዝን ማወቅ ወሳኝ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው።
በቀደምት ታሪክ የተጻፈውን እና በሌሎች የምንሰማውን ትተን አሁን ባለፈው ሳምንት በአውደ ጥናት በኩል
በላክሁላችሁ ቪዲዮ በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ጥናት በማካሄድ ላይ የሚገኙት አሜሪካዊው አቶ ዳንኤል ዲከዝን የተባሉት ሰው የሚናገሩትን
በእንግሊዘኛም በአማርኛም ሰምታችሁታል።
አቶ ዳንኤል መጽሐፈ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ዘንድ በተላከው በመልአኩ ቅዱስ ኡራኤል አማካኝነት ለነቢዩ
ሄኖክ ተገልጾለት በግእዝ ቋንቋ እንደተጻፈ፤ ከዚያም ለታላቁ ለእግዚአብሔር ወዳጅ ለኖኅ እንደተላለፈና ይህንን መጽሐፍ ከጥፋት ውኃ
በኋላ ሁሉ ጠብቆ እንዳቆየው፤ ከዚያም አባታችን አብርሃም ከሚስቱ ከሣራ ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ መጽሐፈ ሄኖክን በግእዝ ቋንቋ በማስተማሩ
በግብጻውያን ዘንድ ሞገሥን እንዳገኘ እንደሚያምኑ እና ባደረጉት ጥናት መሠረትም እንደተገነዘቡ ይናገራሉ።
ስለግእዝ ቋንቋ ዘርፈ ብዙ የሆነ ሥጋዊና መንፈሳዊ ጥቅም በአውደ ጥናትም ሆነ በልዩ ልዩ የሕዝብ መገናኛ
ድረ ገጾቼ በተደጋጋሚ ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር አስረድቻለሁ፤
እንዲሁም አሉ የተባሉ ታላላቅ የቤተክርስቲያናችንን እና የሐገራችንን ሊቃውንት በአውደ ጥናት እየጋበዝኩ
ስለ ቋንቋው ጥልቅ ምሥጢር እና የማይመጠን ጥቅም በሰፊው እንዲያስተምሩ አድርጊያለሁ፤
ካለኝ የቋንቋው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ በዘመናዊ አቀራረብ የተዘጋጀ በቀላል ዘዴ የምትማሩበትን የመማርያ
መጽሐፍ በአውደ ጥናት ስም አሳትሜ በአማዞን፤ በጉግል ፕሌይና በግልም በኩል እየተሠራጨ በዓለም ዙሪያ በመዳረስ ላይ ይገኛል።
ከሁሉም በላይ፡ ወደ የትም ቦታ ሳትሄዱ ሳትወጡ፤ ሳትወርዱ፤ በቦታና በጊዜ ሳይወሰን በያላችሁበት በቤታችሁም
ሆነ በሥራ ቦታችሁ፤ ተኝታችሁም ሆነ ተቀምጣችሁ በየትም ቦታ፤በማነኛውም ጊዜ፤ በሥልካችሁ፤ በኮምፒዩተራችሁ፤ በታብሌት፤በአይፓድ
ወዘተርፈ እየመጣላችሁ፤ እንድትማሩ ማድረግ ችያለሁ፤ ይህ ማለት እንደተገለጠ መጽሐፍ በእጃችሁ መዳፍ ቀርቦላችኋል ማለት ነው።
የሚገርመው ነገር፤ ለዚህ ብዙዎች ለመሰከሩለት (በሚከተለው የመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ስለ መጽሐፉና የትምህርት
አሰጣጡ የተሰጠውን ምስክርነት ይመልከቱ)
ቀላል፤ ግልጽና ለመከታተል አመች ለሆነ የትምህርት አቀራረብ የምትከፍሉት ክፍያው ከጓደኞቻችሁ ጋር
ለግብዣ ወደ አንድ ሆቴል ብትሄዱ ለአንድ ምሽት የእራት ዋጋን እንኳን የማይሸፍን ገንዘብ ነው። ከዚያም አልፎ አሁን ደግሞ ቋንቋውን
ለሁላችሁም ለማዳረስና ሁላችሁንም ተጠቃሚ ለማድረግ ባለኝ ጽኑ ፍላጎት
ምክንያት ከዚያው ከነበረው አንስተኛ ክፍያ ግማሹን ቀንሸ ሁላችሁም የመማር ዕድሉ እንዲኖራችሁ አድርጊያለሁ።
ስለዚህ አሁን በተሰጠው ዕድል የመጠቀሙ ፈንታ የናንተ ድርሻ ይሆናል። በአሁኑ ጊዜ የተሰጠው ቅናሽ
የጊዜ ገደቡን ሊጨርስ 12 ቀናት ይቀሩታል። ስለዚህ ይህ ዕድል ሳያመልጣችሁ ተጠቀሙበት እላለሁ።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን
ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ።
No comments:
Post a Comment