Wednesday, July 29, 2020

ወዘተ/ወዘተርፈ ወይም ወዘተረፈ ማለት የመሳሰሉትን፣ የቀሩትንም፣ የተረፉትንም ጨምሮ ማለት ነው



በዚህ ቪድዮ ስለ ወዘተ፣ ወዘተርፈ ወይም ወዘተረፈ ስለሚባሉት የቃላት ማሳጠሪያዎች ሙሉ ማብራርያን
ያገኛሉ፤ መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ ወይም በ + 1 703 254 6601 ይደውሉ።

Sunday, July 26, 2020

መጽሐፈ ዕዝራ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት/The book of Ezra: Bible study part 15





 

መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት ራሳቸው መጻሕፍቶቹን ይጫኑ ወይም በ +1 703 254 6601 በመደወል ያነጋግሩኝ በኣድራሻዎ ይላክለዎታል፤

#PartsOfSpeech~The Eight Parts of Speech part 5/ ፰ቱ(ስምንቱ) የንግግር ክፍሎች የእን...



The Eight parts of speech
ሰላም ጠና ይስትልኝ ከአውደ ጥናት ነው፤ ዛሬ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል አምስትን ነው የምንማረው።

ስለ ቋንቋና ስለ ሆሄያት ቅድመ ታሪክ ከተማርናቸው አራት የመግቢያ ክፍሎች ሌላ ከክፍል አንድ ጀምረን ስለ ፊደላት ስለ አናባቢና ተናባቢ ፊደላት እንዲሁም አናባቢ ፊደላት እና ተናባቢ ፊደላት ተቀናጅተው እንዴት ቃልን ወይም ቃላትን እንደሚፈጥሩ ተምረናል።

በዛሬው በክፍል አምስት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ደግሞ ስለ ቃላት አከፋፈል እንማራለን ማለት ነው። ለመሆኑ የቃላት አከፋፈል ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ ነው የሚከፈሉት?
በአውደ ጥናት የግእዝ ቋንቋ ትምህርታችን የምትከታተሉ ሰዎች ስለ ቃላት አከፋፈል በሚገባ እንደምታውቁ አልጠራጠርም። ምክንያቱም በማነኛውም ቋንቋ ተመሳሳይ ይዘት አለው።

በእንግሊዘኛም ቋንቋ ያው የተለየ አይደለም። በመሆኑም
ቃላት በሚሠሩት ሥራ ወይም በሚሰጡት አገልግሎት በ8 ይከፈላሉ። ይህ ማለት ሰዎች በሙያቸው ወይም በሚሠሩት የሥራ ዓይነት ዶክተር፤ነጋዴ፤ ገበሬ፤ ወዘተርፈ በመባል እንደሚለያዩ ሁሉ ቃላትም የራሳቸው  ሙያ፣ ወይም የሥራ ድርሻ አላቸው።

በእንግሊዘኛ “The Eight parts of speech” ዚ(thi) 8 ፓርትስ ኦፍ ስፒች ይባላሉ ስምንቱ የንግግር ክፍሎች ማለት ነው። ዘ ለታወቀ ነገር የሚነገር ነው ወደፊት እንማረዋለን
  • ·        ፓርት ማለት ክፍል
  • ·        ኦፍ ማለት የ
  • ·        ስፒች ማለት ደግሞ ንግግር ማለት ነው

ስለዚህ በአንድ ላይ ሲተረጎም “ስምንቱ የንግግር ክፍሎች” ማለት ይሆናል። ስምንቱ የንግግር ክፍሎች የምንላቸውም በእንግሊዘኛ የሚከተሉት ናቸው
1.  Nouns = ስሞች
2.  Pronouns = የስም ተለዋጮች
3.  Verbs = ማሠሪያ አንቀጾች/ግሶች
4.  Adjectives = ገላጮች/ቅጽሎች
5.  Adverbs = የግስ ረዳቶች
6.  Prepositions = መስተዋድዳን/ የሚያዋድዱ/የሚያስማሙ
7.  Conjunctions (ኮንጃንክሺን)= መስተጻምራን/የሚያያይዙ
8.  Interjections(ኢንተርጀክሺንስ) = የማጋነን የማሳዘን ቃላት

እነዚህ ስምንት የንግግር ክፍሎች የሚባሉት በእንግሊዘኛው በአጭር ባጭሩ ስለእያንዳንዱ የሥራ ድርሻ ሲገለጽ የሚከተለውን ይመስላል።

Nouns - persons or people, places, things, ideas
Example: Abel, Adam, Hewan,Teacher
Ethiopia, Canada, Addis Abeba,
Book, pen, paper
Love, happiness, sadness

Pronouns - Replace nouns
Example: I, We, You, They, he, she, It me,my, that, this,

Verbs - show actions and being
Example: Run, go, have, invite

Adjectives - Describe nouns and pronouns
Example: angry, healthy, old, red, smart,

Adverbs – describe or help verbs
Example: quickly, hardly, nearly

Prepositions – Show relationship between words or sentences
Example: above, before, from, in, of, at ,to

Conjunctions – Connect words, phrases, clauses or sentences
Example: and, or, but, so, after,

Interjections - Exclamations that express strong feelings
Example: Ouch, well, aha, wow!

ይህ ባጭሩ የተገለጸው የያንዳንዱ የንግግር ክፍል የሥራ ድርሻ ሲሆን በሚቀጥለው በክፍል ስድስት ትምህርት እያንዳንዱን የንግግር ክፍል በዐረፍተ ነገር ወይም በሰንቴንስ እያስገባን እናየዋለን።


መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት ራሳቸው መጻሕፍቶቹን ይጫኑ ወይም ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ



Tuesday, July 21, 2020

በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ምድረ/In the beginning God created Heaven&Earth(በግእዝ ...



በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ምድረ/In the beginning God created
Heaven&Earth(በግእዝ ድምፅ ግእዝና አማርኛ ለማያነቡም)
መጻሕፍቶቼን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ   https://amzn.to/32JQHMD       ወይም በ+17022546601 ይደውሉ
ሥነ ፍጥረት

#EnglishWordFormation~The 5 vowels&the 1 special vowel in action/የአናባቢዎች...

#HeavenAndEarth~በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ/In the begning God created...



በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ/In the begning God created
Heaven&Earth(በአማርኛ ድምፅ አማርኛ ለማያነቡም)
መጻሕፍቶቼን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ https://amzn.to/32JQHMD  ወይም በ+17022546601 ይደውሉ

Sunday, July 12, 2020

እክሕደከ ሰይጣን ስምዕየ ማርያም አላ አድኅነነ/The three words that read wrongly by peopl...





 አነዚህን መጻሕፍት በስልካችሁ አንቡ 


እነዚህ ከዚህ በታች ያሉ ሦስት ቃላት በተወሰኑ ግእዝን በማያውቁ ሰዎች በተሳሳተ ቃል እየተተኩ ይነበባሉአ በመሆኑም 
ትክክለኛውን ቃል ከምሥጢሩ ጋር መማዛመድ ወይም በማስረዳት ማብራርያ ከቢድዮው ያገኛሉ ይከታተሉ።

“…እክሕደከ ሰይጣን በቅድመ ዛቲ እምየ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን…”

“… እንተ ይእቲ ስምዕየ ማርያም…”

“… ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነ…”

ቃላቱ ተለይተው ሲቀመጡ የሚከተሉት ናቸው


 “እክሕደከ ሰይጣን” እንጅ እከደከ ሰይጣን አይደለም
“ስምዕየ ማርያም” እንጅ ስምየ ማርያም አይደለም
“አላ አድኅነነ” እንጅ አላሕ አድኅነነ አይደለም

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተባለውን መጽሐፌን እና ሌሎችንም መጻሕፍት ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑት ወይም በ +1 703 254 6601 ደውለው ያነጋግሩኝ

Friday, July 10, 2020

#LisaneGeez~ልሣነ ግአዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘው መጽሐፌ ይዘትና ማብራርያ ክፍል 2




የግአዝ መማርያ መጽሐፉን ለመግዛት ከዚህ በታች ያለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑት ወይም በ +1 703 254 661 ይደውሉ፤
ልሣነ ግ አዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘውን መጽሐፍ ይዘቱን አና ታሪኩን ማወቅ ከፈለጉ የሚከተለውን ሊንክ በመጫነ ከኣማዞን ይግዙ ወይም በ +1 703 254 661 ይደውሉ፥ https://amzn.to/2ZUZubH