Sunday, July 26, 2020

#PartsOfSpeech~The Eight Parts of Speech part 5/ ፰ቱ(ስምንቱ) የንግግር ክፍሎች የእን...



The Eight parts of speech
ሰላም ጠና ይስትልኝ ከአውደ ጥናት ነው፤ ዛሬ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል አምስትን ነው የምንማረው።

ስለ ቋንቋና ስለ ሆሄያት ቅድመ ታሪክ ከተማርናቸው አራት የመግቢያ ክፍሎች ሌላ ከክፍል አንድ ጀምረን ስለ ፊደላት ስለ አናባቢና ተናባቢ ፊደላት እንዲሁም አናባቢ ፊደላት እና ተናባቢ ፊደላት ተቀናጅተው እንዴት ቃልን ወይም ቃላትን እንደሚፈጥሩ ተምረናል።

በዛሬው በክፍል አምስት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ደግሞ ስለ ቃላት አከፋፈል እንማራለን ማለት ነው። ለመሆኑ የቃላት አከፋፈል ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ ነው የሚከፈሉት?
በአውደ ጥናት የግእዝ ቋንቋ ትምህርታችን የምትከታተሉ ሰዎች ስለ ቃላት አከፋፈል በሚገባ እንደምታውቁ አልጠራጠርም። ምክንያቱም በማነኛውም ቋንቋ ተመሳሳይ ይዘት አለው።

በእንግሊዘኛም ቋንቋ ያው የተለየ አይደለም። በመሆኑም
ቃላት በሚሠሩት ሥራ ወይም በሚሰጡት አገልግሎት በ8 ይከፈላሉ። ይህ ማለት ሰዎች በሙያቸው ወይም በሚሠሩት የሥራ ዓይነት ዶክተር፤ነጋዴ፤ ገበሬ፤ ወዘተርፈ በመባል እንደሚለያዩ ሁሉ ቃላትም የራሳቸው  ሙያ፣ ወይም የሥራ ድርሻ አላቸው።

በእንግሊዘኛ “The Eight parts of speech” ዚ(thi) 8 ፓርትስ ኦፍ ስፒች ይባላሉ ስምንቱ የንግግር ክፍሎች ማለት ነው። ዘ ለታወቀ ነገር የሚነገር ነው ወደፊት እንማረዋለን
  • ·        ፓርት ማለት ክፍል
  • ·        ኦፍ ማለት የ
  • ·        ስፒች ማለት ደግሞ ንግግር ማለት ነው

ስለዚህ በአንድ ላይ ሲተረጎም “ስምንቱ የንግግር ክፍሎች” ማለት ይሆናል። ስምንቱ የንግግር ክፍሎች የምንላቸውም በእንግሊዘኛ የሚከተሉት ናቸው
1.  Nouns = ስሞች
2.  Pronouns = የስም ተለዋጮች
3.  Verbs = ማሠሪያ አንቀጾች/ግሶች
4.  Adjectives = ገላጮች/ቅጽሎች
5.  Adverbs = የግስ ረዳቶች
6.  Prepositions = መስተዋድዳን/ የሚያዋድዱ/የሚያስማሙ
7.  Conjunctions (ኮንጃንክሺን)= መስተጻምራን/የሚያያይዙ
8.  Interjections(ኢንተርጀክሺንስ) = የማጋነን የማሳዘን ቃላት

እነዚህ ስምንት የንግግር ክፍሎች የሚባሉት በእንግሊዘኛው በአጭር ባጭሩ ስለእያንዳንዱ የሥራ ድርሻ ሲገለጽ የሚከተለውን ይመስላል።

Nouns - persons or people, places, things, ideas
Example: Abel, Adam, Hewan,Teacher
Ethiopia, Canada, Addis Abeba,
Book, pen, paper
Love, happiness, sadness

Pronouns - Replace nouns
Example: I, We, You, They, he, she, It me,my, that, this,

Verbs - show actions and being
Example: Run, go, have, invite

Adjectives - Describe nouns and pronouns
Example: angry, healthy, old, red, smart,

Adverbs – describe or help verbs
Example: quickly, hardly, nearly

Prepositions – Show relationship between words or sentences
Example: above, before, from, in, of, at ,to

Conjunctions – Connect words, phrases, clauses or sentences
Example: and, or, but, so, after,

Interjections - Exclamations that express strong feelings
Example: Ouch, well, aha, wow!

ይህ ባጭሩ የተገለጸው የያንዳንዱ የንግግር ክፍል የሥራ ድርሻ ሲሆን በሚቀጥለው በክፍል ስድስት ትምህርት እያንዳንዱን የንግግር ክፍል በዐረፍተ ነገር ወይም በሰንቴንስ እያስገባን እናየዋለን።


መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት ራሳቸው መጻሕፍቶቹን ይጫኑ ወይም ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ



No comments:

Post a Comment