Sunday, February 28, 2021

ለወደፊቱ በሰው የማይሰሩ ሥራዎች/Jobs jobs will disappear in the future: እነዚህ ሥራዎች ...


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው፣ አምላካችን እግዚአብሔር ለዚች ሰዓት ስላደረሰን የተመሰገነ ነው።

 መጻሕፍት ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ

ዛሬ የማቀርብላችሁ በጣም ወሳኝና ወቅታዊ እስካሁን ከማዘጋጃቸው መልእክቶችና ትምህርቶ ለየት ያለ ርእስ ነው፣ እያንዳንዳችን ቢያንስ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተን ሰዎች፡ ልዩ ትኩረት ልንሰጠውና መረጃውን ተገንዝበን ከመረጃው ተጠቃሚ ልንሆን ይገባል ብየ አምናለሁ፣ እንከታተል።

 

ይህ ዝግጅት ለመረጃ ለአጠቃላይ ግንዛቤ ብቻ የሚሆን ነው። እኔ የዚህ ጉዳይ ባለሙያ አይደለሁም ይህንን የምነግራችሁ ከባለሙያዎቹ በመስማት የጻፉትን የጥናት ጽሁፍ በመመልከት፤ ራሴም ጥናት በማድረግ ነው፤ ስለዚህ ለመረጃነት የሚሆን ነው፤ ውሳኔ ለመወሰን ግን ምንም ነገር ከማድረጋችሁ በፊት ባለሙያዎችን ማነጋገር፤ ራሳችሁም ተከታትላችሁ መረጃዎችን በመሰብሰብ ሙሉ በሙሉ ሲገባችሁና ስታምኑበት መሆን አለበት።

 

 

ሁላችንም እንደምናውቀው አሁን ያለንበት 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አሉታ ወይም መጥፎ ጉኑ እንዳለ ሆኖ በሥልጣኔ እጅግ የመጠቀና አስደናቂ አዲስና ሕይወታችንን በተለይ ሥጋዊ ሕይወታችንን ቀላልና አመች ሊያደርጉ የሚችሉ ወይም የቻሉ የጥበብ ውጤቶች የሚታዩበት ጊዜ ነው።

 

ለምሳሌ

ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ቀላልና አመች በመሆኑ ዓለም ጠባብ መንደር ሆናለች፤ የትም ዓለም ሆነን በሰባቱም ዓለማት የሚገኙ ወገኖቻችንን ጓደኞቻችንን ሁሉ በየቅጽበቱ በእጃችን መዳፍ ባለ ዘመናዊ ስልክ በጽሁፍ በድምጽ እናነጋግራቸዋለን ከዚያም አልፎ በቪድዮ በአካላዊ ዓይን እየተያየን መወያየት እንችላለን፤ ያውም አብዛኛውን ጊዜ በነጻ ነው።

 

ከቤታችን ሳንወጣ ከአልጋችንም ቢሆን ሳንነሣ ያለምንም ገደብ በመላው ዓለም ተሰራጭቶ ጥቅም ሊያስገኝልን የሚችል ሥራን እየሠራን ገቢ እናገኝበታለን፤ አንድ ጊዜ ያዘጋጀነው ቪድዮ፣ የጻፍነው ጽሁፍ የለቀቅነው ድምጽ እኛ ተኝተን እያንቀላፋን ሥራችን በቀንም በሌሊትም በየትም ዓለም በማነኛውም ሰዓት ገንዘብ እየሰበሰበ ወደ ኪሳችን ያስገባል።

 

አሁን አሁን የሥራ ልብስ ለብሶ ቢሮ መግባት ከሰዎች ጋር በአካለ ሥጋ የተገናኙ አብሮ መሥራት፤ ወደ ምግብ ቤት ገብቶ በአስተናጋጆች መገልገል እየቀረ ነው።  በቴክኖሎጅ ወይም ዘመኑ ባመጣው የሥልጣኔ ውጤት ተጽእኖ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፉ ገዳይ ቫይረስ ምክንያት ተጨማምሮ ሰዎች በያሉበት ሆነው ዘመን ባፈራቸው የጥበብ ውጤቶች በመታገዝ መሥራት እንደ ግዴታ ሆኗል።

 

ሌላው ቀርቶ ሥርዓተ አምልኮቱም ቭርቹዋል የርቀት ከሆነ ውሎ አድሯል።

·        ኦንላይ

·        ድጅታል

·         ቭርቹዋል ወዘተ የሚባሉት ቃላትም የሚነግሩን የርቀት ወይም በአካለ ሥጋ በአንድ ውሱን ቦታ ሳንገናኝ በጽሁፍ፤በቃል በቪድዮ በመግባባት ስለሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ነው።

ታዲያ ይህ ሁኔታ ለብዙዎች አመችና የበለጠ ምርታማ ቢሆንም ለተወሰነው ምርታማ ላይሆን ይችላል በመሆኑም ዛሬ የምንነጋገረው በነዚህ ከዚህ በላይ በጠቀስኳቸው ነገሮች ወይም ክስተቶች እድገቶችም ልንላቸው እንችላለን ምክንያት ጥቅም ብቻ ሳይሆን ጉዳቱንም በተለያየ መልኩ እየተጋራን ነው።

ከዚያም አለፍ ባለ ሁኔታ ለተወሰነው ልዩ ዝግጅት ማድረግ ግዴታ የሚሆንበት ወቅት እንደሚመጣ ባለሙያዎች ደጋግመው እየተናገሩ ነው።

ስለዚህ የተለያዩ ምሁራን የሚተነብዩትን ማለትም በጥናትና በተጨባጩ እይታ ላይ በመመሥረት ወደፊት በሰብአዊ ፍጡር መሠራታቸው ይቀራል ከሚሏቸው ሥራዎች መካከል የሚከተሉት 14ቱ ተቀዳሚዎቹ እንደሆኑ ይናገራሉ፤ በመሆኑም በነዚህ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ሰዎች ከአሁኑ ሙያቸውን ሊቀይሩ ወይም ተጨማሪ ሙያ ሊቀስሙ ይገባል በማለት ይመክራሉ። ስለዚህ የትኞቹ የሥራ ዓይነቶች እንደሆኑ እናያለን።

1.  Drivers/ (ሹፌሮች ወይም ሹፌርነት)

2.  Farmers (ገበሬዎች ወይም የግብርና ሥራ)

3.  Printing and publishing (ፕሪንቲንግ ወይም የሕትመት ሥራዎች)

4.  Cashers (ካሸርስ የገንዘብ መቀበያ ማሽን ላይ የሚሠሩ)

5.  Travel agencies (የጉዞ ወኪሎች)

6.  Manufacturing workers (የፋብሪካ ሠራተኞች)

7.   Dispatchers (ዲስፓቸርስ በታክሲ፣ በእሳት አደጋ፣ በፖሊስ ወዘተ መሥሪያ ቤቶች የስልክ ጥሪ የሚያደርጉና የሚቀበሉ)

8.  Waiters and waitress (የሆቴሎችና የምግብ ቤት ሠራተኞች)

9.  Bank Tellers(የባንክ ገንዘብ ተቀባዮች ወይም ከፋዮች)

10. Airforce pilots (የአየር ሃይል አብራሪዎች ወይም ፓይለቶች)

11. Tele marketing (በስልክ የሚያስተዋውቁ የሚሸጡና የሚገዙ ወዘተ)

12. Accounting and Tax Preparers (የሂሳብና የግብር አሰባሰብ ሥራ ወይም  ሠራተኞች)

13. Stock market Traders (የስታክ ማርኬት ወይም አክሲዮን አሻሻጮችና አጋዥዎች)

14. Constriction workers (የሕንጻና የመንገድ ሥራዎች ሠራተኞች)

አሁን እያንዳንዳቸውን ባጭሩ እንመልከት

በ1ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰው የሹፌርነት ሥራ ነው፤ የሹፌርነት ሥራ የግል መኪናን  የጭነት መኪናን  ታክሲን፣ ለምሳሌ እንደ ኡቨር፣ ሊፍት ሌሎችም ልዩ ልዩ የታክሲ ድርጅቶች አሉ፡ በአጠቃላይ የሹፌርነት ሥራ በሰብአዊ ፍጡር ወይም በሰው መነዳቱ ይቀራል፤ ራሳቸው የሚሽከረከሩ (ሰልፍ ድራይቪንግ ቪክልስ) እየተሰሩ ነው አሁንም በልዩ ልዩ ቦታዎች ልዩ ልዩ ካምፓኒዎች እየተገለገሉባቸው ነው፤

በ2ኛ ደረጃ የተጠቀሰው የግብርና ሥራ ነው፤ (Farmers) እንደምታውቁት በሠለጠነው ዓለም ብግብርና ሥራ በበሬና በገበሬ መጠቀም ከቆመ ሰነባብቷል ባላደጉ አገሮች ግን እስካሁንም  በልዩ ልዩ እንስሳት ይታረሳል፤ አሁንም በአገራችን በበሬ ማረስ የተለመደ ነው፤ ዓለም በሥልጣኔ እየመጠቀ ሲመጣ ግን በመኪና በልዩ ልዩ ትራክተሮች ማረስ ተጀመረ

 በአሁኑ ጊዜ የሚያርሱ የሚዘሩ አዝመራውን የሚሰበስቡ ማሽኖች ተፈጥረዋል እስካሁን ማሽኖቹ “ፋርም ዩቲሊቲ” ቪክልስ” የሚባሉ የሚሰሩት በሰዎች ነጅነት ማለትም በሹፌር ነው የሚነዱት፤ አሁን ግን በሮባት የሚሠሩ ወይም ራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ሆነው የተሰሩ ናቸው፡ ስለዚህ በሬንም ሆነ ሰብአዊ ገበሬን ወይም ሹፌርን አይፈልጉም። ስለዚህ በግብርና ሥራ የተሰማራን ሰዎች ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን፤

የግብርና ሥራ ገበሬን ብቻ ሳይሆን መሬት ከማረስ ጀምሮ እህል ወይም ሌላ የመሬት ወይም የግብርና ውጤቶችን አምርቶ እስከ መሰብሰብ ድረስ ባለው የሥራ መስክ የተሰማራውን ኅብረተሰብ ሁሉ ያጠቃልላል።

በ3ኛ ደረጃ የተጠቀሰው “ፕሪንቲንግ እና ፐብሊሺንግ”(Printing and Publishing) ወይም ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ወይም የሕትመት ሥራ ነው። ይህም የጋዜጣ የመጽሔት የመጻሕፍት የሌሎችንም የሕትመት ሥራዎችን ይመለከታል። ወደፊት ጋዜታ መጽሔት መጻሕፍት ገዝቶ መአካል እያገላበጡ ማንበብ ይቀራል፤ ሁሉንም ኦን ላይን በኢንተርኔት እናሳትማለን በዚያ በኢቡክ ለምሳሌ እንደ ኪንድል ኑክ በተባሉት ድጅታል መሳሪያዎች እናነባለን ወይም ጉግል ፕሌይ፣ በአፕል ቡክ ወዘተ ፕላት ፎርሞች እናነባለን። እኔ ራሴ አብዛኛዎቹን መጻሕፍቶችን በጉግል ፕሌይ ስቶር ነው የምሸጠው፤ ጉግል ፕሌይ የሚባለው መጻሕፍቱን ስካን በማድረግ በፒዲኤፍ እና በሌሎችም ሴብ በማድረግ በጉግል ድጅታል ስቶር በማስቀመጥ ሰዎች በስልካቸውና በተለያዩ መሣሪያዎች እንዲያነቡ የሚያስችል ነው።

 

4ኛው የካሸርነት ሥራ ነው፤(Cashers) የካሸርነት ሥራ አሁንም እንደምታውቁት በታላላቅ ሱፐር ማርኬቶች የካሸርነት ሥራ የሚከናወነው በአውቶ ማቲክ ማሽኖች ነው፤ ምን አልባት የምታዩት የማሽኖቹን አጠቃቀም የማያውቁ ሰዎችን የሚረዱ አልፎ አልፎ የቆሙ ሰዎችን ነው። ስለዚህ የካሸርነት ሥራ ለወደፊቱ ሙሉ በሙሉ የሚሰራው በሚናገሩ ማሽኖች ብቻ ይሆናል ይባላል።

5ኛ የጉዞ ዎኪልነት ሥራ ነው፤(Travel agencies) ማለትም የአገር አቋራጭ የመኪና የአይሮፕላን የትሬይን ወዘተ ጉዞ ወኪሎች ወይም ባለ ንብረቶች ትኬት የሚቆርጡ ወይም የሚሸጡ ሥራተኞችን መቅጠር አያስፈልጋቸውም ሁሉም ነገር በኢንተርኔእት በሥልካችን በየቤታችን ሆነን ትኬት መቁረጥ በክሬዲት ካርድ መክፈል እንችላለን ትኬት ብቻ ሳይሆን ሆቴል ታክሲ ሁሉንም በአንድ ላይ በሥልካችን እንጨርሳለን።

6ኛ ፋብሪካዎች ናቸው(Manufactures) የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ሰዎች በሚያንቀሳቅሷቸው ማሽኖት መሥራታቸው ቀርቶ በሮባት የሚሠሩ ይሆናሉ ሮባት ፕሮግራም የሚደረግ ማሺን ስለሆነ ይናገራል ይንቀሳቀሳል ያዛል ይሠራል። ስለዚህ ሰብአዊ ፍጡርን ተክቶ መሥራት ይችላል ማለት ነው።

7ኛው ዲስፓቸርነት ነው። (dispatchers) ዲስፓቸር ማለት ልዩ ልዩ መልእክትን ትዕዛዝን እየተቀበለ አገልግሎት የሚያስፈጽም (sender) ማለት ነው ለምሳሌ በታክሲ ካምባኒዎች የሚሰሩ ዲስፓቸሮች ታክሲ የሚፈልግ ሰው ሲደውል ስልክ ያነሱና ምን አይነት ታክሲ እንደሚፈልግ፣ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሚሄድ በመጠየቅ በአቅራቢያው ያሉ ታክሲ ነጅዎችን በማናገር ወደ ተጠቃሚው ይልካሉ፤

በእሳት አደጋ መከላከያ በሥሪያ ቤት፤ በፖሊስ ጣቢያ ወዘተ በስልክ ተቀባይነት የሚሠሩ ሠራተኞችም “ዲስፓቸሮች “ ይባላሉ የእሳት አደጋ ሲከሰት በምንደውል ጊዜ የሚያነሱት ዲስፓቸሮች ናቸው። ችግሩን ጠይቀው በአፋጣን ፖሊስ ወይም የእሳት ማጥፊያ መኪና እንዲላክ ያደርጋሉ። አሁን የተለያዩ ሶፍት ዌሮች አፕሊኬሽኖች በስልካችን አሉ እነሱን ክሊክ ማድረግ ነው፤ ወይም ጉግል አሲስታንት፤ ሲሪ ወዘተ የሚባሉትን ማነጋገርና ሎኬሽናችንን ኦን ማድረግ ነው።

8ኛው የአስተናጋጅነት ሥራ ነው፤(waiters and waitress) ለምሳሌ የሆቴል የምግብ ቤት ፋስት ፉድ ወዘተ በነዚህ የሚያስተናግዱ ሰዎች ወደፊት አይኖሩም እንደሰው የሚታዘዙ ሮባቶች አርቲፊሻል ሰዎች ይታዘዛሉ የሚፈለገውን ያቀርባሉ።  እንዲያውም ቲፕ መስጠት አይጠበቅብንም።

9ኛው የባንክ ሥራ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ እንደ ድሮውም ባይሆን አልፎ አልፎ ወደ ባንክ እየሄድን በሰዎች እንገለገላለን፤ ገንዘብ እናስገባለን፤ እናወጣለን።

ለወደፊቱ ይህ ሁሉ ይቀራል ገንዘባችንን በሚከተሉት መንገዶች ማስገባት ማስወጣትም ወይም ማዘዋወር ወይም መጠቀም እንችላለን፡

·        ከምንሠራበት መሥሪያ ቤት ደሞዛችን ወደ አካውንታችን ይገባል

·        ቸክ የምንቀበል ከሆነ የባንኮችን አፕሊኬሽኖች በስልካችን በማውረድ ቸኩን በስልካችን ወደ አካውንታችን ዲፖሲት ማድረግ እንችላለን

·         ካሽ የምንፈልግ ከሆነ ከአውቶ ማቲክ ማሽን ወይም ኤይቲኤም  ማሽን ራሳችን ማውጣት እንችላለን

·        ማነኛውንም ነገር መግዛት ስንፈልግ ክሬዲት ካር እንጠቀማለን ወደ ባንክ ቤቶች መሄድ አያስፈልገንም፤ ይህም ከሆነ ባንኮች ገንዘብ የሚቀበልና የሚሰጥ ሰው መቅጠር አያሻቸውም

10ኛ ፓይለቶች፤ የግል፤ የድርጅት የወታደር አየር ሃይል አብራሪዎች ወዘት፡ አሁን ራሳቸው የሚበሩ ወይም ሰው አልባ ተዋጊ አይሮ ፕላኖች ተፈጥረዋል አሁን በተወሰነ መልኩ ቢሆንም ለወደ ፊቱ ሙሉ በሙሉ አይሮፕላኖች ሰው አልባ ይሆናሉ ፤ እንደ ጥንቱ በፈረስ በእግር ወዘተ እየዘመተ አገርን ከጠላት የሚጠብቅ ወታደር፣ ወታደሮችን የሚሸከም ፈረስ ወይም መኪና አይሮፕላን ወዘተ ሳያስፈልግ ሰው አልባ አይሮፕላኖችን መሳሪያ አስታጥቆ መላክ ወይም በርቀት በሪሞት ኮንትሮል ማሽከርከር ብቻ ነው።

11ኛ ቴሌ ማርኬቲንግ ( በስልክ የሚያስተዋውቁ የሚያሻሽጡ ወዘተ) ሠራተኞች እስከሁን አሁንም ጭምር ብዙ ጊዜ አጋጥሟችሁ ይሆናል በስልክ እየደወሉ የመኪና ኢንሹራንስ የጤና ኢንሹራንስ ወይም የተለያዩ ነገሮችን በቅናሽ ግዙ ተበደሩ ወዘተ እያሉ የሚደውሉ ሰዎች ተሌ ማርኬተር ይባላሉ። አሁን በድጅታል ማርኬቲንግ በነፌስ ቡክ በነጉግል ወዘተ በደቂቃ ውስጥ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲያነቡትና እንዲሰሙት በማድረግ ማስተዋወቅ ተችሏል፤ ስለዚህ በስልክ መሥራት ማስተዋወቅ የሚባለው ሥራ ቦታ አይኖረውም ይላሉ።

12ኛው አካውንታንት እና ታክስ አዘጋፎች ናቸው፤ እንደምታውቁት በተለይ በየ አመቱ ባለሙያ ወችን  እየከፈልን አመታዊ ግብር የከፈልነውን በማነጻጸር ወይም ይመለስልና አልያም እኛ ተጨማሪ እንከፍላለን፤ እና ታክስ ረተርን የሚያዘጋጁ ሰዎች ወደፊት ተጠቃሚዎችን ማግኘት ከባድ ይሆንባቸዋል፤ ምክንያቱም በጣም ቀላል እና ፈጣን ነጻም የሆኑ በኢንተርኔት የምናገኛቸው ሶፍት ዌሮች ተዘጋጅተው ቀርበዋል፤ መንግስትም የሚያበረታታን በነዚህ ሶፍት ዌሮች ተጠቅመን ራሳችን መሥራት እንድንችል ነው። ስለዚህ ለወደፊቱ ሰው ሙሉ በሙሉ የነዚሁ የኦንላየን አገልግሎቶች ተጠቃሚ ይሆናል።

13ኛው የሕንጻና የመንገድ ሥራዎች ናቸው እነዚህም ሥራዎች ወደ ፊት በሮባት ወይም በአርቲፍሻል ሰዎች  ሊሠሩ እንደሚችሉ ይተነበያል

14ኛው ስታክ ማርኬት ሠራተኞች ናቸው። (Stock market treders) ስታክ ማርኬት የሚባለው በአገራችን የአክሲሆን አገልግሎት ወይም የአክሲዮን ገበያ ማለት ነው። ይህ የስታክ ማርኬት ሥራ የአለምን ኢኮኖሚ የሚያነሳ እና የሚጥል ከፍተኛ ሃይል ያለው የኢንቨስትመንት(investment) ሥራ ነው። ለወደፊቱ አንድ ስለስታክ ማርኬት መረጃዎችን እሰጣችኋለሁ።

እስካሁን ወይም ትንሽ ቀድም ብሎ የስታክ ማርኬት ሥራ የሚሰራው በባለሙያዎች ብቻ ነበር ተጠቃሚው ስታክ ማርኬት ውስጥ invest ማድረግ ሲፈልግ ባለሙያውን ያነጋግራል፤ የአገልግሎት ዋጋ እየከፈለ “ሸር” ወይም አክሲሆን የሚባለውን ይገዛለታል ይሸጥለታል። በዚህ ዓይነት መልኩ ነበር የሚሰራው።

አሁን ግን ቴክኖሎጅ እያደገ ተጠቃሚው እየበዛ፤ ሲሄድ ነጻ, ለአጠቃቀምም ቀላል የሆኑ  (Apps) አፕሊኬሽኖች ተፈጠሩ፤ ስለዚህ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግ አፕሊኬሽኖቹን ወደ ስልኩ ኢንስቶል (instale) ያደርጋል፤ አካውንት ይከፍታል ራሱ በነጻ ከተለያዩ ካምፓኒዎች “ሼር” እየገዛ መሸጥና መለዋወጥ ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ የስታክ ማርኬት ባለሙያዎች ከተጠቃሚው የማግኘቱ ሁኔታ ስለሚቀር ሥራ ሊያጡ ይችላሉ፤ ሆኖም ግን ራሳቸው ባለሙያዎች ስለሆኑ ለራሳቸው ከሠሩ ከበቂበላይ ማግኘታቸው አይቀርም።

እነዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሁሉ በፍጥነት በአንድ ጊዜ የሚጠፉ ወይም የሚወገዱ ሳይሆኑ ሙሉ በሙሉ ለመጥፋት ዓመታት ይፈጃል እስከዚያውም ሠራተኛ ይቀንሳሉ እንጅ ሙሉ በሙሉ ሰው አልባ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ማሽኖቹ ወይም ሮባቶቹ አልፎ አልፎ ሰው ሊያስፈልጋቸው ይችላ

Wednesday, February 24, 2021

How to study effectively? Basic studding rules/ማነኛውንም ነገር እንዴት ማጥናት አንችላ...


መሠረታዊ የአጠናን ጥበብ፥ በዚህ ዓይነት መንገድ ካጠናችሁ በእውነትም ስኬት ታገኛላችሁ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው።

 ዛሬ ለየት ያለ ዝግጅት ነው ያለኝ፤ እንደምታውቁት አውደ ጥናት የእምነት ወይም የአማርኛ እና የግእዝ ትምህርቶችን ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊ ሕይወታችን በሥጋዊ ጉዟችን ሁሉ የሚጠቅሙን ልዩ ልዩ ትምህርቶች የሚሰጡበት ቻናል ወይም ድረ ገጽ ነው።

በመሆኑም የሥነ ምግባር፤ የቋንቋ፤ የትምህርት ሌሎችንም ትምህርቶች ከምሁራን በመጠየቅ ከመጻሕፍት በማንበብ በጥናት ላይ የተመረኮዙ አርእስትን እያዘጋጀሁ ወደ እናንተ አደርሳለሁ ማለት ነው። የእኔ ዕቅድ በተቻለ መጠን ሰዎች ወደ አውደ ጥናት መጥተው በሥጋዊውም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የሚፈልጉትን ሁሉ ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ነው፤ ለዚህም ነው የተለያዩ ሊቃውንትን በተለያዩ አርእስት ቃለ መጠይቅ እያደረግሁ ሳቀርብ የምትመለከቱት።

የበለጠ ለመሥራት ግን የሁላችሁም ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ አውደ ጥናትን በተለያየ መንገድ በምትችሉት ሁሉ መደገፍና ተሳትፎም ማድረግ ትችላላችሁ።

 መጻሕፍት ለመግዛት የሚከተሉትን የመጻሕፍቱን ሥዕሎች ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 በመደወል ያነጋግሩኝ በአድራሻዎ ይላክለዎታል፤ I am directing you to amazon market place. buy my books on amazon.

 

የአጠናን ጥበብ

መሠረታዊ የአጠናን ጥበብን በአጭሩ ነው የምንመለከተው፤

በቀላሉ በሚከተሉት ስድስት አርእስት ልንከፍለው እንችላለን

1.  ለጥናት የሚያነሣሳ ኃይል ወይም ምክንያት መኖር (ለምን አጠናለሁ?)
2.  የአጠናኑን መንገድ መቀየስ (ጊዜና ቦታ)
3.  የጥናት ልክ (የጊዜ ውሱንነት)
4.  ቅኝት(መቃኘት)
5.  ጥናት
6.  ክለሳ

በነዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ነጥቦች መሠረት በአጭሩ እንነጋገራለን።

የጥናት ምክንያት (ለማጥናት የሚያነሣሳ ኃይል ወይም ምክንያት (ለምን አጠናለሁ)

·        ራሴን ለማሻሻል

·        ገንዘብ ለማግኘት

·        ዝናን ለማግኘት

·        ለዕድገት ወዘተ

ለምን እንደምናጠና በቂ ምክንያት ካገኘን በኋላ ደግሞ እንዴት እና በየት ማጥናት እንዳለብን ማቀድ ይኖርብናል። ማቀድ ግዴታ ይኖርብና “ለመሥራት የማያቅድ ሰው ላለመሥራት ያቀደ ነው” ይባላል። ምክንያቱም ያለ እቅድ መሥራት የትም ሊያደርሰን አይችልም ልክ የት መሄድ እንደሚፈልግ ሳያውቅ መኪናውን አሥነሥቶ በትልቅ ጎዳና ላይ የሚያሽከረክር ሰውን ይመስላል።

እንዴት አጠናለሁ? (የጊዜ አጠቃቀምና የቦታ ምርጫ፤ መቼና ምን ያህል ደቂቃ ወይም ሰዓት)

በክፍል ውስጥ ወይም በሌላ መንገድ የምንማርበትን ጊዜ ወይም ሌሎች የግልም ሆኑ የጋራ ጉዳዮችን የምናከናውንበትን ጊዜ የማይሻማ ለጥናት የተለየ ጊዜን መምረጥ ነው።

·        ማታ፡ ከትምህርት ወይም ከሥራ መልስ

·        ጠዋት፡ ከትምህርት ወይም ከሥራ በኋላ

·        ቀን፡ በረፍት ሰዓት ወይም ሥራ ስንጨርስ

·        ሌሊት፡ ከእንቅልፋችን ቀንሰን ወዘተ(የሚስማማንን ጊዜ መፍጠር)

ለምን ያህል ጊዜ ማጥናት እንችላለን(ያለን ጊዜ ምን ያህል ነው?)

·        30 ደቂቃ፤ 1 ሰዓት፣ 2 ሰዓት ወዘተ

የምናጠናውስ በየት ነው? (ጸጥታ ያለው፣ ሊረብሸንና ሐሣባችንን ሊበትን የሚችል ድምጽና ዕይታ የሌለው ሠወር እና ጸጥ ያለ ቦታ ወይም ክፍል ማግኘት ይጠበቅብናል።

አሁን ለምን እንደምናጠና፤ በየት እንደምናጠና፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደምናጠና አውቀናል ተዘጋጅተናል ማለት ነው፤ በሌላ አባባል የተሟላ እቅድ አውጥተናል።

ትልቁ ፈተና የአላማ ጽናት ነው፤ ማለትም ላወጣነው እቅድ ወይም መርሐግብር ተገዥ ለመሆን ቃል መግባት ይጠበቅብናል።

 ካልሆነ ግን እቅዳችን ግብ ሳይመታ ሊቀር ይችላል። ይህ ታላቁ ሥራ ነው፤ (የሚያቅደው ሰው ብዙ ነው ነገር ግን እቅዱን በሥራ ላይ የሚያውለው ግን በጣም አናሣ ቍጥር ያለው ነው) ባለሙያዎች ዕቅድ ከሚያወጣው ሕዝብ መካከል ለእቅዱ ተገዥ በመሆን ለስኬት የሚበቃው ከመቶ 8 ሲሆን አቅዶ ሳይሳካለት የሚቀረው ከመቶ 92% ነው ይላሉ። ስለዚህ እኛ ከ8ቱ ውስጥ ራሻችንን ለመመደብ መጣር አለብን።

በዕቅድ መመራትና በዕቅዳችን መጽናት የሚጠቅመን በሁሉም የሕይወት አቅጣጫ ነው፤ ለሥጋም፤ ለነፍስም፤ ለጤናም፤ ለብልጽግናም፤ ለደስታም፤ ባጭሩ ለሁሉም። ስለዚህ በእቅዳችን መጽናትና ላወጣነው መመሪያ ወይም መርሐግብር ተገዥዎች መሆን አለብን።

የአጠናን ዘዴ (እንዴት እንጀምር)

አሁን እቅዳችንን ጨርሰን መርሐግብር አውጥተን፤ ማስታዎሻ የምንይዝበት ደብተርና ስክብሪቶ ይዘን በመረጥነው ጊዜ፣ በወሰነው ቦታ፣ ተሰይመናል ወይም ተቀምጠናል፤ የምናጠናው መጽሐፍ በእጃችን ገብቷል፤ አሁን መቃኘት ወደሚለው ክፍል ልናልፍ ነው።

መቃኘት

መጽሐፉን ወይም የሚጠናውን ነገር በእጃችን ይዘን እናየዋለን፣ እናስተውለዋለን፤ ምንድነው የምናየውና የምናስተውለው

  • ·        ርእሱ ምን ይላል?
  • ·        ቅርጹ ምን ይመስላል?
  • ·        ቀለሙ ምን ዓይነት ነው?
  • ·        በሽፋኑ ላይ ምን ያህል ሥዕሎች አሉ? ምን ዓይነትስ ናቸው?
  • ·        ምንያህል ገጽ ነው? ወዘተ…

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ መልእክትን የሚያስተላልፉ ናቸው። መልእክታቸውም በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን መሠረታዊ ሐሣብ የሚገልጡ፤ የትምህርቱን ይዘት፣ ስፋት እና ጥበት የሚናገሩ ናቸው።

እነዚህን ሁሉ ካየን በኋላ ራሳችንን ለሰከንዶች(ለደቂቃዎች) መጠየቅ አለብን፤ ማለትም መገመት (ይህ ርእስና በሽፋኑ ያሉት ጽሁፎችና ሥዕሎች ምንን ሊወክሉ ይችላሉ ወዘተ እያሉ መመራመር) ይኖርብናል።

 

አሁን ወደ መጽሐፉ ገብተን ማጥናት ልንጀምር ነው፤ መጀመሪያ የምናገኛቸው የአርእስት ማውጫ፤ መግቢያ፤ እና መግለጫ የሚባሉት የመጽሐፉን ምዕራፍ አንድን ከመጀመራችን በፊት የምናያቸው ዋና ዋናዎቹ ክፍሎች ናቸው።

ሦስቱንም መመልከት ይኖርብናል፤ የአርእስት ማውጫ፣ በያንዳንዱ ምዕራፍ ወይም ክፍል የሚገኙትን ንዑሳን አርእስት የሚያስተዋውቀን፤ የምግብ ሜኑ ማለት ነው፤ የአርእስት ማውጫውን ማየት ጠቅላላ የመጽሐፉን ሐሳብና ይዘት ለማወቅ ብቻ ሳይሆን፤ የምንቸኩልና ከመጽሐፉ ውስጥ የተወሰነ ነገር ብቻ ማጥናት የምንፈልግ ከሆነ የምንፈልገውን በቶሎ አውጥተን ለመመልከት ወይም ለማጥናት ይረዳናል።

መግቢያን መግለጫ

መግቢያ እና መግለጫ ማንበብ ስለ መጽሐፉ ይዘትና አጠቃቀም ግልጽ የሆነ ግንባቤን ይሰጣል፤ ምክንያቱም ከስያሜያቸው እንደምንረዳው “መግቢያ” ማለት የመጽሐፉን ይዘት ወይም መልእክት ለመመርመር ከመጀመራችን በፊት በሩን የሚከፍትልንና አጠቃላይ ማብራርያ የሚሰጠን ክፍል ነው። መግቢያ ሳያነብ ዋናውን ምዕራፍ ወይም ክፍል የሚጀምር ሰው፣ በሩን በመክፈቻ ከፍቶ ሳይሆን መክፈቻውን ሰብሮ የገባን ወይም አንድን የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት የሚገኝበት በየት እንደሆነ ሳያውቅ በየቦታው እየገባ የሚፈልግን ሰው ይመስላል።

መግለጫው ደግሞ ከስሙ እንደምንረዳው ስለመጽሐፉ አከፋፈልና አጠቃቀም የሚነግረን ክፍል ነው። (መጽሐፉ ስንት ምዕራፎችና ክፍሎች እንዳሉት የትኛው ትምህርት በየትኛው ምዕራፍ ወይም ክፍል እንደሚገኝ ወዘተ) የሚነግረን ክፍል ነው።

በመቀጠልም በየምዕራፉ መጨረሻ የሚገኙ ማጠቃለያዎችንና ጥያቄዎችን ቀድመን መመልከትና ሐሳባዊ መልስ ለመስጠት መሞከር

ዋናውን ጥናታችንን ስንጀምር

  • ለምን?
  • እንዴት?
  • መቼ?
  • በየት?

ማን? ወዘተ በሚሉት ወሳኝ ጥያቄዎች መሠረት ራሳችንን እየጠየቅን መልሱን እያገኘን ማጥናት መቻል አለብን።

የምናነበውን ወይም የምናጠናውን ሐሣብ ወይም ትምርት ቃልም ሊሆን ይችላል በአእምሯችን እንዲቀረጽ ከምናውቀው ነገር ጋር በማያያዝ ወይም በማዛመድ የማይረሳ ማድረግ መቻል።

ለምሳሌ፡

እንግሊዘኛ የምናጠና ከሆነ እና ቃላትን እንዲሁ ያለምንም ዘዴ ለመሸምደድ ከመሞከር ይልቅ ከአማርኛ ከግእዝ ከሌሎችንም ከምናውቃቸው ቋንቋዎች ጋር በማዛመድ ለማስታዎስ መጣር፤

“ማይ” ማለት በእንግሊዘኛ “የእኔ” ማለት ነው፤ መግእዝ “ማይ” ማለት “ውሀ” ማለት ነው፡(ትግርኛና ግእዝ የሚያውቅ ተማሪ “ማይ” የሚለውን የእንግሊዘኛ ቃል በቀላሉ በአእምሮው ቀረጸው ማለት ነው።

“ጉድ” ማለት በአማርኛ አስደንጋጭ ቃል ነው፤ በእንግሊዘኛ ግን “መልካም” ማለት ነው፤ ስለዚህ እነዚህን ቃላት በማዛመድ የማይረሱ ማድረግ እንችላለን፤ ከዚህም ሌላ ብዙ ነገሮችን ማግኘት እንችላለን፤ ግዴታ ቀጥታና ግልጽ ተመሳሳይነት ባይኖራቸውም ብዙ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን በመፍጠር ከባሕላችን ከታሪካችን ወዘተ ጋር በተዘዋዋሪ ማዛመድ እንችላለን፤ (በሌላ ርእስ በበለጠ ልንመለከተው እንችላለን)

 

የመጨረሻው መከለስ(መደጋገም) ልምምድ ማድረግ ወዘተ የሚለው ክፍል ነው። “መደጋገም የማወቅ እናት ናት” ይባላል። አንድን ነገር መልሰን መልሰን መላልሰን ከሠራነው አንዱ የሕይወታችን ክፍል ስለሚሆን ልክ እንጀራ ለመጉረስ አፋችን ያለበትን መፈለግ እንደማንሻና በብራትም ሆነ አመልካች እንደማያስፈልገን ሁሉ የለመድነው ሥራም ዐይናችንን ጨፍነን እንኳን መሥራት የምንችለው ይሆናል።

ይቆየን


Saturday, February 20, 2021

ጥንታዊ ምሳሌዎች ክፍል 2

የወላጆቻችን ጥንታዊ ምሳሌዎች ክፍል 2

እነዚህን የተደበቀ ምሥጢርን የያዙ ምሳሌዎች በመስማት ይመራመሩ ኅሊናዎንም በጥበብ ይመግቡ ያነቃቁም

መጻሕፍት ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን በመጫን ወደ አማዞን ሄደው መግዛት ይችላሉ ወይም በ+1 703 254 6601 ደውለው ያነጋግሩኝ ባድራሻዎ ይላክለዎታል።

Sunday, February 14, 2021

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴ ንባቡና ትርጓሜው ቅዱስ ኤፍሬም እንደደረሰው ክፍል 1 መግቢያ


የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ውዳሴ ቅዱስ ኤፍሬም እንደተናገረው ንባቡና ትርጓሜው(አንድምታ)
ዘወትር ዕሁድ በአውደ ጥናት ይቀርባል ይከታተሉ። ሼርና ላይክ በማድረግ ላልሰሙት አሰሙ።

መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት ከዚህ በታች ያለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ፡ ከአማዞን መግዛት የማትችሉ በአድራሻችሁ እንዲላክላችሁ በ+1 703 254 6601 በመደወል ያነጋግሩኝ ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን ከአውደ ጥናት።
I am directing you to Amazon market place.

Saturday, February 13, 2021

The Old Saying of Ethiopian/የጥንት ኢትዮጵያውያን አባባሎች ክፍል አንድ


የጥንት ኢትዮጵያውያን ምሳሌያዊ ንግግሮች አዳምቱ፣ ተመራመሩ፣ ምን ማለት እንደሆነ ተናገሩ፣ በዝህም የወላጆቻችንን ማንነት፣ እምነት፣ ባሕልና ጥበብ እናውቃለን፡ ሕሊናችንም ፈጣንና ተመራማሪ ይሆናል።

ከዚሁ ቪድዮ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ሰምና ወርቅ የአማርኛ፣ የግእዝና፣ አና የእንግሊዘኛም ሰምና ወርቅ ግጥሞችን የያዘ መጽሐፊን፣ ሌሎችንም መጻሕፍት መግዛት የምትሹ የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን በመጫን ወደ አማዞን በመሄድ መግዛት ትችላላችሁ፡ ከአማዞን መግዛት የማትችሉ በ+1 703 254 6601 በነጻ ስልክ (በዋትስአፕ፣ ቫይበር፣ ኢሞ፣ ቴሌግራም ወዘተ በመሳሰሉት) በመደዎል ያነጋግሩኝ በአድራሻዎ ይላክለዎታል።

Wednesday, February 10, 2021

#ObjectivePronouns~Part/እንግሊዘኛ በአውደ ጥናት ክፍል 10


English for Amharic Speakers part 10 Objective Pronouns

Objective  Pronouns

 

ባለፈው ትምህርታችን ስለ Subject Pronouns ተምረን ነበር፤ ለማስታዎስ ያህልም ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስ የሚባሉት በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ የሚገኘውን የዐረፍተ ነገር ባለቤት የሚተኩ የስም ተለዋጮች ወይም “ፕሮናውንስ”  በእንግሊዘኛ፣ ተውላጠ ስም በግእዝ፤ በአማርኛ ደግሞ የስም ተለዋጮች የምንላቸው ናቸው። ብዙ ጊዜ እነዚህ ለሰብአዊ አካል የሚሆኑ ናቸው። ምሳሌያቸውንም አይተናል።

Subject Pronouns are pronouns that replace the subject in the sentence.  ማለትም “ሰብጀክት”ወይም ሰብጀክት የሚባለው የአንድ ዐረፍተ ነገር ባለቤት ወይም ድርጊት ፈጻሚ/ድርጊቱ የሚነገርለት ወዘተ ማለት ነው። ስለዚህ  ባጭሩ ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስ የሚባሉት የዐረፍተ ነገር ባለቤት የነበረውን አካል ተክተው የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት የሚሆኑ ቃላት ናቸው።

 

ወደ ዛሬው ትምህርታችን እንሸጋገርና የዛሬው ትምህርት ስለ “ኦብጀክቲቭ ፕሮናውንስ” ስለሚባሉት ነው።

Objective  Pronouns

 Objective  Pronouns /ኦብጀክት ማለት ደግሞ  ተደራጊ /ወይም የሚፈጸመው ድርጊት ወይም ነገር ነው።

The object is the part of the sentence that is being done to, from or with the action.

የሚከተሉት “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስን” እና ኦብጀክቲቭ ፕሮናውንስን” ለማነጻጸር የሚጠቅሙን ዐረፍተ ነገሮች ናቸው እንከታተል። “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስ” በቀይ፣ “ኦብጀክቲቭ ፕሮናውንስ” ደግሞ በሰማያዊ ቀለም ተጽፈዋል።

The following are subjective and Objective pronouns together. subjective pronouns are written in red and objective pronouns are written in blue.

1.   I  will call you tomorrow or (you can) call me

ዐይ ዊል ኮል ዩ ትሞሮ ወይም ደውልልኝ/ልትደውልልኝ ትችላለህ

ነገ እደውልልሃለሁ(እደውልልሻለሁ) ወይም ደውልልኝ(ልትደውልልኝ ትችላለህ)

 

2.   We will tell you before you leave the country but, let us know before you go.

ዊ ዊል ቴል ዩ ቢፎር ዩ ሊቭ ዘ ካንትሪ፣ ባት ሌት አስ ነው ቢፎር ዩ ገው፤

ከአገር ከመውጣትህ በፊት እንነግርሃለን፤ ነገር ግን ከመሄድህ በፊት አስታውቀን

 

3.   You will see me tomorrow or I will email you

ዩ ዊል ሲ ሚ ትሞሮ ኦር ዐይ ዊል ኢሜይል ዩ

ነገ ታገኘኛለህ/ታየኛለህ ወይም እሜይል አደርግልሃለሁ.

 

4.   He gave me the book to read it.

ሒ ጌቭ ሂም ዘ ቡክ ቱ ሪድ እት

(እሱ) መጽሐፉን እንዳነበው ሰጠኝ።

 

5.   She went with her boyfriend yesterday before I told her about the class.

ሺ ዌንት ዊዝ ኸር ቦይፍሬንድ የስተርደይ ቢፎር ዐይ ቶልድ ኸር አባውት ዘ ችላስ

(እሷ) ስለ ትምህርቱ ሳልነግራት በፊት ትናንት ከወንድ ጓደኛዋ ጋር ሄደች።

 

6.   It is my book just leave it there.

እት ኢዝ ማይ ቡክ! ጀስት ሊቭ እት ዜር.

(እሱ) የኔ መጽሐፍ ነው እዛው ተወው።

 

7.   They left me a message last sundy before I called them.

ዘይ ሌፍት ሚ ኤ መሴጅ ላስት ሰንደይ ቢፎር ዐይ ኮልድ ዘም.

ሳልደውልላቸው በፊት የለፈው እሁድ መልክት ትተውልኝ ነበር።

The following are the Objective pronouns by theirself /ኦብጀቲቭ ፕሮናውንስ የሚባሉት ራሳቸውን  ችለው ሲጻፉ የሚከተሉት ናቸው፤

  1. Me -ሚ
  2. You - ዩ
  3.  Him -ሒም
  4. Her- ኸር
  5.  It -እት
  6. Us - አዝ
  7. Them -ዘም

የስም ተለዋጮች ወደ ተሳቢ ወይም ፕሮናውንስ ቱ ኦብጀክት(from Subjective pronouns to Objective pronouns)

·         I = Me (ዐይ ይሆናል ሚ)  ማለትም  የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን    I  ይሆናል

·         We = Us ማለትም  የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን    We ይሆናል

·         You = You ማለትም  የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን    You ይሆናል

·         He = Him ማለትም  የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን    He ይሆናል

·         She = Her ማለትም  የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን    She ይሆናል

·         It = It ማለትም  የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን    It ይሆናል

·         They =Them ማለትም  የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን    They  ይሆናል