Monday, February 2, 2015

ግእዝ ክፍል 20

Learn Ge'ez Language part 20 Sentences structures and vocabularies 


ንዋያተ ቅድሳት(ለብዙ)
ጻድቅ = እውነተኛ
ጻድቃን (ለብዙ)
ሰማዕት =ምስክር
ሰማእታት (ለብዙ)
ተሰጥዎ = መልስ፤ ስጦታም ይሆናል።
መዝሙር = ምስጋና   
ቁርባን = የሚቀበሉት፤ የሚያቀብሉት(ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ)
ጽንሰታ = መወለድ (መወለዷ)
ልደታ =መወለዷ
በዓታ = መግባቷ(መግባት)
ፍልሰታ =መሰደድ፤መዛወር
ንስሐ =ጸጸት
ተዝካር = መታሰቢያ
ዝክር =መታሰቢያ
ምግባር = ሥራ
ኃጢአት = ወንጀል
ክህነት =አገልግሎት
ካህን=አገልጋይ
ዲያቆን=ተላላኪ(ለመንፈሳዊ አገልግሎት)
ክርስቲያን= ክርስቶሳዊ
ኦርቶዶክስ=ቀጥተኛ ምስጋና (አምልኮት) (ግሪክ)
ተዋሕዶ= ያለመቀላቀል፤ያለመለያየት፤ያለመጠፋፋት፤ ያለመለዋወጥ አንድ መሆን
ሥጋዌ = ሰው መሆን
ትንሣኤ ሙታን = የሙታን መነሣት
መድኃኔ ዓለም =የዓለም መድኃኒት
በአለ ወልድ = የወልድ በአል፤ክብር
አብ =አባት
ወልድ=ልጅ
ልሳን=ቋንቋ
ወንጌል=የምሥራች
ሐዋርያት=ሐጅዎች የሚሄዱ
ነቢያት= ትንቢት ተናጋሪዎች
ደቀመዝሙር=ተማሪ
ጸሎት =ልመና (ወደ እግዚአብሔርና ወደ ቅዱሳን)
 ትእግሥት =መቻል
ወላዲተ አምላክ = አምላክን የወለደች
እመብርሃን = የብርሃን እናት
መንግሥተ ሰማይ = የሰማይ መንግሥት
መልአክ = ተላላኪ፤አለቃ፤አስተዳዳሪ






የዐረፍተ ነገር ወይም የአገላለጽ እድገት ይህ ልምምድ ግእዝን ከማጥናት አልፎ
የሥነ ጽሁፍ ፍላጎት ላለው ሁሉ እጅግ ጠቃሚ ነው።

ከዚህ በታች የሚገኙትን የዐረፍተ ነገራቱን አቀማመጥ፤ ትርጉምና እንዴት ዐረፍተ ነገራቱ ሊስፋፉ ወይም ሊያድጉ እንደ ቻሉ ያስተውሉ። የራሰዎን ዐረፍተ ነገራት በመፍጠር ልምምድም ያድርጉ፡ በግእዝ ካቃተዎ በአማርኛ እየሠሩ ወደ ግእዝ ይቀይሩት።
1ኛ ምሳሌ
1.       መርድእ አእመረ= ተማሪ አወቀ
2.      መርድእ አእመረ ልሳነ =ተማሪ ቋንቋን አወቀ
3.      መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ
=የግእዝ ተማሪ የግእዝ ቋንቋን አወቀ
4.      መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ ተምሂሮ
=የግእዝ ተማሪ የግእዝ ቋንቋን ተምሮ አወቀ
5.      መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ ተምሂሮ እምነ አውደ ጥናት
=የግእዝ ተማሪ የግእዝ ቋንቋን ከአውደ ጥናት ተምሮ አወቀ
6.     መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ ተምሂሮ እምነ አውደ ጥናት ዘግእዝ
=የግእዝ ተማሪ የግእዝ ቋንቋን ማጥኛ ከሆነቺው ከአውደ ጥናት (ከግእዝ ትምህርት ቤት) የግእዝ ቋንቋን ተምሮ አወቀ
7.      መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ ወ ቅኔ ተምሂሮ እምነ አውደ ጥናት ዘግእዝ
=የግእዝ ተማሪ የግእዝ ቋንቋን ማጥኛ ከሆነቺው ከአውደ ጥናት (ከግእዝ ትምህርት ቤት) የግእዝ ቋንቋን እና ቅኔን ተምሮ አወቀ

2ኛ ምሳሌ
የዐረፍተ ነገር ወይም የአገላለጽ እድገት ይህ ልምምድ ግእዝን ከማጥናት አልፎ የሥነ ጽሁፍ ፍላጎት ላለው ሁሉ
               እጅግ ጠቃሚ ነው።
·         መርድእ መጽአ
 =ተማሪ መጣ
·         መርድአ ቅኔ መጽአ
 = የቅኔ ተማሪ መጣ
·         መርድአ ቅኔ መጽአ እምነ ጎጃም
 = የቅኔ ተማሪ ከጎጃም መጣ
·         መርድአ ቅኔ መጽአ እምነ ጎጃም በእግሩ
= የቅኔ ተማሪ ከጎጃም በእግሩ መጣ
·         መርድአ ቅኔ መጽአ እምነ ጎጃም  እንዘ ይረውጽ በእግሩ
 = የቅኔ ተማሪ ከጎጃም በእግሩ እየሮጠ መጣ።


ከዚህ በላይ በ “1ኛ ምሳሌ” 1- 7 በተጠቀሱት ዐረፍተ ነገራት ውስጥ ለሚገኙት ቃላት ሙሉ ማብራርያ የያንዳንዱን ቃል ሙያ በአትኩሮት ይመልከቱ በ2ኛ ምሳሌ ሥር ያሉትም ከ1ኛ ምሳሌ ጋር ተመሳሳይ ናቸው በቃላት ትርጉም ብቻ ነው የሚለያዩት ።

1 ባለቤትና ማሠሪያ  አለው( 2 አካላትን ይዟል) (Subject and Verb)
·         መርድእ = የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት (Subjet)
·         አእመረ = ማሠሪያ አንቀጽ(Verb)
2. ባለቤት፤ ማሠሪያ አንቀጽ፤ እና ተሳቢ (3 አካላትን ይዟል)( Subject; Verb, and Direct Object)
·         መርድእ = የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት (ዐረፍተ ነገሩ የሚነገርለት) ( Subject)
·         አእመረ = ማሠሪያ አንቀጽ(Verb)
·         ልሳነ = ተሳቢ (Direct Object)
3. ባለቤት፤ ማሠሪያ ቅንቀጽ፤ ዘርፍ፤ ተሳቢ፤የተሳቢ ዘርጅፍ (4 አካላትን ይዟል)
·         መርድአ = ባለቤት(Subjet)
·         ግእዝ = ዘርፍ (የመርድእ ዘርፍ ማለትም የባለቤቱ)
·         አእመረ = ማሠሪያ አንቀጽ(Verb)
·         ልሳነ = ተሳቢ ( የአእመረ ወይም የማሠሪያ አንቀጹ ተሳቢ)(Direct Object)
·         ግእዝ = የልሳነ ዘርፍ
4. ባለቤት፤ ማሰሪያ አንቀጽ፤ ዘርፍ፤ተሳቢ፤ ዘርፍ፤ ቦዝ አንቀጽ (6 አካላትን ይዟል)
·         መርድአ = የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት(Subjet)
·         ግእዝ = ዘርፍ ( የመርድ እዘርፍ)
·         አእመረ = ማሠሪያ አንቀጽ(Verb)
·         ልሳነ = ተሳቢ(Direct Object)
·         ግእዝ = የልሳን ዘርፍ
·         ተምሂሮ = ቦዝ አንቀጽ(የማያሥር)
5. ባለቤት፤ ማሠሪያ አንቀጽ፤ ዘርፍ፤ተሳቢ፤ ዘርፍ፤ቦዝ አንቀጽ፤ አገባብ(ከ)፤ አገባብ የወደቀበት፤ ዘርፍ፤ (8 ወይም 9 አካላትን ይዟል)
·         መርድአ = የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት(Subjet)
·         ግእዝ = ዘርፍ (የመርድእ ዘርፍ)
·         አእመረ = ማሠሪያ አንቀጽ(Verb)
·         ልሳነ = ተሳቢ(Direct Object)
·         ግእዝ = የልሳነ ዘርፍ
·         ተምሂሮ = ቦዝ አንቀጽ
·         እምነ = አገባብ ሲሆን ትርጉሙ “ከ” ማለት ነው
·         አውደ ጥናት = አገባብ የወደቀበት ማለትም እምነ ወይም ከ የወደቀበት
·         (ጥናት) = የአውድ ዘርፍ፤ “አውደ ጥናት” የሚለውን እንደ አንድ ስም ልንወስደውም እንቺላለን ግን ሁለት ቃላት ስለሆኑ ለያይቶ ማወቁ መልካም ነው።
6. ባለቤት፤ ዘርፍ፤አንቀጽ፤ተሳቢ፤ ዘርፍ፤ቦዝ አንቀጽ፤ አገባብ(ከ) አገባብ የወደቀበት፤ ዘርፍ፤አገባብ፤ የዘርፍ ዘርፍ (10 ወይም 11 አካላትን ይዟል)
·         መርድአ = ባለቤት(Subjet)
·         ግእዝ = ዘርፍ
·         አእመረ = ማሠሪያ(Verb)
·         ልሳነ = ተሳቢ(Direct Object)
·         ግእዝ = ዘርፍ
·         ተምሂሮ = ቦዝ አንቀጽ
·         እምነ= (አገባብ)
·         አውደ(ጥናት) = አገባብ የወደቀበት
·         ጥናት = ዘርፍ
·          ዘ = ትርጉሙ “የ” ማለት ሲሆን አገባብ ነው፤ ( የ”ዘ” ሥራ ብዙ ነው ለወደፊቱ ቀስ በቀስ እንማረዋለን ለአሁኑ ግን  “የ” የሚል ትርጉምን ብቻ ካወቅን ይበቃል።)
·         ግእዝ = አገባብ ያረፈበት ወይም የወደቀበት (ዘ ማለት ነው አገባብ ያልነው)

7. ባለቤት፤ ዘርፍ፤አንቀጽ፤ተሳቢ፤አጫፋሪ አገባብ፤ተሳቢ፤ ዘርፍ፤ቦዝ አንቀጽ፤ አገባብ(ከ) አገባብ የወደቀበት፤ ዘርፍ፤አገባብ፤ የዘርፍ ዘርፍ( 11 አካላትን ይዟል)
·         መድአ = ባለቤት(Subjet)                      
·         ግእዝ = ዘርፍ
·         አእመረ = ማሠሪያ (Verb)
·         ልሳነ = ተሳቢ(Direct Object)
·         ግእዝ = ዘርፍ
·         ወ = አገባብ ሲሆን አጫፋሪ ይባላል ሁለት ነገሮችን በአንድ ላይ ስለሚያያይዝ ነው
·         ቅኔ = ተሳቢ(Direct Object)
·         ተምሂሮ = ቦዝ አንቀጽ
·         እምነ =
·         አውደ (ጥናት) = አገባብ የወደቀበት
·         ጥናት = ዘርፍ
·         ዘ= (አገባብ)
·         ግእዝ = አገባብ የወደቀበት



4 comments: