Friday, June 20, 2014

ለልምምድ ጥያቄዎች የሚያገለግል የክለሣ ትምህር/Revising the lessons for practical exam

Learn Geez language Part 10 review, Ge'ez text, and vocabularies


ክፍል 10
ዛሬ በክፍል 10 ትምህርታችን እስከ ዛሬ ከተማርናቸው አርእስት አለፍ አለፍ እያልኩ በማስታዎስ ክለሳ አደርግላችኋለሁ። ምክንያቱም ቀደም ብዬ እንዳስታወስኳችሁ ክፍል 11 የመመዘኛ ጥያቄዎች የሚሰጡበት ክፍል ስለሆነ ለዚሁ መመዘኛ እንድንዘጋጅ ነው።
በክፍል 1 የመግቢያ ትምህርታችን ግእዝ ማለት ሁለት አበይት ትርጉሞች እንዳሉትና እነዚህም ነጻነት እና 1ኛ የሚሉት እንደሆኑ፤ እንዲሁም ግእዝ የኢትዮጵያውያን የጋራ ቋንቋ ወይም ኢትዮጵያዊኛ እንጂ በማንም ልዩ ጎሳ የማይጠራ መሆኑን በዚህም ምክንያት ግእዝን ለመማር የጎሳም ሆነ የሃይማኖት የሌላም ልዩነት ሊገታን እንደማይችል ተምረናል።
በክፍል 2 መግቢያ ከክፍል አንድ በመቀጠል የግእዝን ታሪክና ጥቅም በመተረክ ግእዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች ተብለው ከሚጠሩት የዓለም ቋንቋዎች አንዱ መሆኑን የዓለም ምሁራን እንደሚያምኑበት፤ ከኢትዮጵያ ውጭ በቲኦሎጂ ተቋማትም እንደሚያስተምሩት፤ከሁሉም በላይ የዓለም ሕዝብ ስለ መጽሐፈ ኩፋሌ እና መጽሐፈ ሄኖክ ሊያውቅ የቻለው በግእዝ ቋንቋ ተጽፎ ከተገኘው ጥንታዊ ጽሁፍ በየቋንቋው በማስተርጎም እንደ ሆነ የዓለም የታሪክ፤ የሥነ ምድርና የቲዮሎጂ ምሁራን ሙሉ በሙሉ የሚያምኑበትና የሚያስተምሩት እውነት እንደሆነም ተምረናል።
ከዚህ በላይ ክፍል አንድና ሁለት በማለት የጠቀስኳቸው እንደ መግቢያ ባጭሩ ስለግእዝ ምንነትና ጥቅም ያየናቸው ሲሆኑ የሚቀጥሉት የዋናው ትምህርታችን ክፍሎች ናቸው።

በክፍል 1 የግእዝ ትምህርት፤ ስለ 10ቱ መራሕያን
በክፍል 2 ስለ 1ኛ መደብ መራህያን ለነጠላ ቁጥር
በክፍል 3 ስለ 1ኛ መደብ ብዙ ቁጥር ንሕነ (ንግበር ሰብአ በአርያያነ ወበአምሳሊነ የሚለውን እንደ ምሳሌ በመውሰድ)
በክፍል 4 ስለ 2ኛ መደብ መራሕያን እና ዐረፍተ ነገር በመሥራት ልምምድ አድርገናል
በክፍል 5 ስለ 3ኛ መደብ መራሕያን ልምምድ
በክፍል 6 ስለ 5ቱ አእማድ እና “ክርስቶስ ተንሥ አእሙታን --” የሚለውን ምንባብ በመውሰድ ትርጉምና ልምምድ
በክፍል 7 ስለ መጠየቂያ ቃላት ትርጉምና የአጠቃቀም ልምምድ
በክፍል 8 ስለ 26ቱ የግእዝ ፊደላት ዝርዝርና ትርጉም እንዲሁም ስለተጨማሪ ዲቃላ ፊደላት ክለሳ ተምረናል።
በክፍል 9
ሀ. አበይት አናቅጽ (ከሃላፊ እስከ ትእዛዝ)
ለ. የ10ቱ መራሕያን ግሦች የሚጨርሱባቸው ሆሄያት
ሐ. 10ቱ መራሕያን እንደ ነባር አንቀጽ ወይም ግሥ ሲያገለግሉ፤

የሚሉትን በሰፊው የተማርን ሲሆን ከክፍል 1 እስከ ክፍል 5 ድረስ ለነበሩን ትምህርቶች አንድ የክለሳ ትምህርት ሰጥቻለሁ። በመሆኑም በመጠኑ እስካሁን በተማርናቸው ክፍሎች ላይ በቂ የሆነ ግንዛቤ ይኖራችኋል ብዬ አምናለሁ።

ክፍል 11 የመመዘኛ ትምህርታችን የሚከተለውን ይመስላል
ምሳሌ፡
 1.ዓለም ስለ-----ማወቅ የቻለው በግእዝ ቋንቋ ተጽፎ ከተገኘው ጥንታዊ ጽሁፍ በማስተርጎም ነው
1.      የዘፍጥረትና የኩፋሌ መጽሐፍ
2.     መጽሐፈ እዝራ እና መጽሐፍ ጦቢት
3.     መጽሐፈ ሄኖክና መጽሐፈ ኩፋሌ
መልስ፡3

ምሳሌ ሁለት
 2አንቲ
1.      1ኛ መደብ ለወንድ
2.     2ኛ መደብ ለአንዲት ሴት
3.     ሦስተኛ መደብ ለብዙ ሴቶች
መልስ፡2

ስለዚህ በዚህ ዓይነት መልኩ እናንተ የሚጠበቅባችሁ
የመልሱን ቁጥር ብቻ በኮሜንት ቦታ መጻፍ ነው። ከዚህ በታች እንዳለው አይነት

Q.1 A.3 (ለጥያቄ 1(አንድ) መልሱ 3(ሦስት ቁጥር ነው ማለቴ ነው)
Q2. A.2===========================================

Q=Question
A=Answer

ሰላም ለክሙ አኃውየ ወአኃትየ አርድእተ ልሳነ ግእዝ ኩልክሙ፤ ዮም እፈቅድ ከመ እንብብክሙ ወአለብወክሙ በይነ አሰርቱ ወአሃዱ ክፍላተ ትምህርትነ ዘመሐርኩክሙ በቅድም። ወእምኔሆሙ እጤይቀክሙ አሠርተ ጥያቄያተ። ወናሁ ይደልወክሙ ታንብቡ ወትስምኡ ኩሎሙ አርእስተ ትምህርት ዳግመ።

ዛቲ ጦማረ መልእክት ትብጻሕ ኀበ አርድእትየ አርድእተ ልሳነ ግእዝ ዘበኀበ ኵሉ ተፈቅረ። ኦ አርድእት አፍቀርኩ ከመ እምሐርክሙ በይነ ዜና ፍጥረት ዘእግዚአብሔር አምላክነ፡

በቀዳሚ  ዕለት (በእሁድ ዕለት) ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ
በሰኑይ ዕለት ገብረ(ፈጠረ) ባሕረ ወየብሰ
በሠሉስ ዕለት ገብረ ሐመልማለ ሣዕር ወዕፀወ፤ ወአዝርእተ
በረቡዕ ዕለት ገብረ ፀሓየ ወወርኀ ወከዋክብተ
በኀሙስ ዕለት ገብረ እንስሳ ወአራዊተ፤ ወአእዋፈ ወኩሎ
በሰዱስ ዕለት ገብሮሙ/ ፈጠሮሙ ለአዳም ወሔዋን  ብእሴ ወብእሲተ
ወበሳብዕት ዕለት አዕረፈ እግዚአብሔር እምኵሉ ግብሩ።



የቃላት ትርጉም፡ ለመጀመሪያው ምንባብ

አኃውየ =ወንድሞቼ
አኃትየ=እኅቶቼ
ወ=እና
ልሳን=ቋንቋ
ኩልክሙ=ሁላችሁ(ሁላችሁም)
ዮም=ዛሬ
እፈቅድ=እወዳለሁ
በቅድም = በመጀመሪያ/በፊት/ከዚህ በፊት
ከመ=ዘንድ(እንደ)
እንብብክሙ=እነግራችሁ ዘንድ
አለብወክሙ=አስታውሳችሁ ዘንድ
በይነ=ስለ
10ቱ=አሥሩ
ወሠርቱ ወአሐዱ=አሥራ አንዱ
እምኔሆሙ=ከነሱ
እጤይቀክሙ=እጠይቃችኋለሁ
አሠርተ ጥያቄያተ=10 ጥያቄዎችን
ናሁ=አሁን
ይደልዎክሙ=ይገባችኋል
ታንብቡ=ታነቡ ዘንድ
ወታጽምኡ=ትሰሙ/ታዳምጡ ዘንድ
ኩሎሙ=ሁሉንም
አርእስተ ትምህርት= የትምህርት አርእስት/ክፍሎች
ዳግሞ=እንደገና/ሁለተኛ/ዳግሞኛ







የቃላት ትርጉም ለሁለተኛው ምንባብ

ጦማር=ጽሁፍ /ደብዳቤ
ገብረ=ፈጠረ/ሠራ/አደረገ
መል እክት=በቁሙ መልእክት
ትብጻሕ =ትድረስ
ዘበኀበ ኩሉ=በሁሉ ዘንድ
ኦ=ሆይ
በቀዳሚ ዕለት=በመጀመሪያው ቀን
ዕለት=ቀን
በሰኑይ=በሁለተኛው
በሰሉስ=በሦስተናው
በረቡዕ=በአራተኛው
በሐሙስ=በአምስተኛው
በሳድስ=በስድስተኛው
በሳብዕት=በሰባተኛዋ
ማስታዎሻ፦
የመጀመሪያ ቀን የተባለው ዕሁድ
ሰኑይ =ሰኞ
ሰሉስ=ማክሰኞ
ረቡዕ =ረቡ ዕ
ሐሙስ=ሐሙስ
ሳድስ=አርብ
ሳብዕት=ቅዳሚት/ቅዳሜ

Sunday, June 8, 2014

Geez/ኢትዮጵያዊኛ

Thank you for Visiting "Andegna"(ግእዝ) the Place for Learning Geez Language, The Language of Wisdom.And Wellcome!
ግእዝ = ዮጵያዊኛ 

ሰላም ለክሙ አኃውየ ወአኃትየ፤አበውየ ወእማትየ ዮምንትመሐር በልሳነ ግእዝ በይነ አሠርቱ መራህያነ ኩሉ ልሳን.

Learn Geez Language from the source!

አገራችን ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ባሕሎች ባሏቸው ልዩ ልዩ ብሔረ ሰዎች የተዋበች አገር በመሆኗ በነዚሁ ልዩ ልዩ ብሔረ ሰዎች ከጥቅም ላይ የዋሉ ከ75 በላይ የሚሆኑ ቋንቛዎች ይገኛሉ ። እነዚህ ቛንቛዎች የአማራ አማርኛ የትግራይ ትግርኛ የኦሮሞ ኦሮሚኛ የጉራጌ ጉራግኛ ወዘተርፈ እየተባሉ ይጠራሉ ።

ከብዙዎቹ ቋንቋዎች መካከል አንዱና የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ቋንቋ እንደነበረ የሚነገርለት የግ እዝ ቋንቋ ግን በተለየ ብሔረሰብ ያልተወሰነ የኢትዮጵያውያን ሁሉ የጋራ ቋንቋ በመሆኑ በምሁራኑ አገላለጽ 
ዮጵያዊኛ እየተባለ ይጠራል ። እንዲሁም ከስፋቱና ከምሥጢር ቋንቋነቱ እንዲሁም ማነኛውንም ትምህርት ለመማር በርከፋችና ብሩህ አእምሮን የሚሰጥ መሆኑን ለመግለጽ መጽሔተ አእምሮ ወይም የእውቀት መስታወት በመባል በሊቃውንቱ ይጠራል ።

ርግጠኛ ነኝ እርሰዎም ዓለምን በሙሉ ልበዎ ለማየት ይህንን የእውቀት መስታወት ይፈልጉ ይሆናል ብየ አምናለሁ ! ከሆነ ያለምንም ክፍያ እንሆ !!!
Click here to watch video for this part


Please visit the following
Awde Tinat on youtube
Awde Tinat on blog
Awde Tinat on Amazon
Ethio By God
My Poems Speak!