"ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለቺ ::
መዝሙር 67፡31
ትርጉምና ሙያ፦
መደብ፦3ኛ ለሴት ፆታ ለነጠላ፡
ተውላጠ ስም፦ይእቲ
ታበጽሕ:- ማሠሪያ አንቀጽ፤
የግሥ ዓይነት:- ትንቢት (አዘውትሮ የሚደረግም ይሆናል)
እደዊሃ:- የታበጽህ ተሳቢ፡
ኀበ:- ወደ ደቂቅ አገባብ፡
እግዚአብሔር :- የአገባብ ባለቤት(የኀበ)
መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን (መጽሐፉን) ይጫኑ።
"Ethiopia will stretch out her hands to God.." Psalm 67:31
የቃላት ትርጉም፡
ታበጽህ = ታደርሳለች፤ ትዘረጋለቺ ማለት ሲሆን ዋናው ግሥ "አብጽሐ" የሚለው ነው።
እድ ማለት እጅ ማለት ሲሆን ሲበዛ እደው ይባላል።
እድ ያለውን አእዳው በማለትም ይበዛል እንዲያውም ብዙ ጊዜ እድ ሲበዛ አእዳው ነው የሚሆነው።
ዕደው ወንዶች ማለትም ይሆናል
እደዊሃ=ሃ የሚለው የሦስተኛ መደብ አንዲት ሴት የባለቤት ዝርዝር የሚሆን ነው። (ባለቤትነትን የሚያሳይ) ማለት ነው።
ኀበ; አገባብ ሲሆን ወደ ማለት ነው።
No comments:
Post a Comment