ጸሎተ ሃይማኖት
ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ገባሬ ሰማያት
ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።
ወነአምን በአሐዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ዋሕድ ዘህልው
ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ብርሃን ዘእምብርሃን አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ።
ዘቦቱ ኵሉ ኮነ ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ
ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ። ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኀኒትነ ወረደ እምሰማያት። ተሰብአ ወተሠገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል ።
ኮነ ብእሴ ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጴንጤናዊ
። ሐመ ወሞተ ወተቀብረ ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት በከመ ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት። ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት
ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ።
ወነአምን በመንፈስ
ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረጸ እምአብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ
ዘነበበ በነቢያት። ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት።
ወነአምን በአሐቲ
ጥምቀት ለስርየተ ኀጢአት። ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም።
ይህ "ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘው መጽሐፍ በአቀራረቡ ለየት ያለ ቀላልና በጣም ዘመናዊ የሆነ አቋራጭ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴን የተከተለ ነው።
ከዚህ መጽሐፍ የግእዝን ቋንቋ በአማርኛ የሚማሩ ሲሆን መጠነና የሆነ የእንግሊዘኛ ቃላትንና አገባቦችንም ያስተምራል። ይህ መጽሐፍ በመሠረታዊነት የተዘጋጀው ቋንቋውን ምንም ለማያውቁ ጀማሪዎችና መጠነኛ ግንዛቤ ኖሯቸው ሰዋስዋዊ አካሄዱን ግን ለማያውቁ ሲሆን ከዚያም በላይ የእውቀት ደረጃ ላሉም ቢሆን በተለይ የአገባብ መዋቅሮችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤን እንዲሰጥ ታስቦ ነው።
መጽሐፉን ካህናት፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፤ በየአብያተ ክርስቲያናት ሕጻናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ የእምነትንና የሥነ ምግባርን ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ለማስተማሪያነትም ሆነ የግል እውቀትን ለማዳበር እንዲሁም በማነኛውም የቋንቋ ጥናት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የቋንቋን አካሄድ፤ የቃላትን ቅንብርና አገባብ ለመገንዘብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ለወጣንያንና ለማዕከላውያን የተዘጋጀ 1ኛ መጽሐፍ እንደ መሆኑ መጠንም በውስጡ የሚገኘው እያንዳንዱ ርእስ የተሰጠው ትርጉም፤ አገልግሎትና ትንታኔ ያለቀለት ሳይሆን ለክፍል አንድ የተመጠነ ብቻ ነው።
ማለትም በክፍል ሁለትና በቀጣዮቹም ክፍሎች ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ወይም እየጨመረ የሚሄድ ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ወይም አገባብ እናንተ የምታውቁትን ሁሉ አካቶ ባለመገኘቱ የተረሣ ወይም ሳይታወቅ የታለፈ እንዳይመስላችሁ፤ ለክፍል አንድ ተመጥኖ የቀረበ ስለሆነ ብቻ ነው። ለወደፊቱ በእኔ የሚዘጋጁ የግእዝ መማሪያ መጻሕፍት ከዚህ መጽሐፍ የሚቀጥሉ እንጅ ይህንን ክፍል የማያካትቱ ስለሚሆኑ የቋንቋው ሙሉ ፍላጎት ያለው ሁሉ ከዚህ ከመሠረታዊው ትምህርት መጀመር አማራጭ የሌለው በመሆኑ ይህን መጽሐፍ ማግኘት ይኖርበታል ብየ አምናለሁ። እንደዚህ ከሆነ ማለትም መሠረቱን በሚገባ መገንዘብ ከቻላችሁ ጽኑ እና በአለት ላይ የተመሠረተ መሠረት ስለሚኖራችሁ ቀጣዩ ትምህርት በጣም ቀላል እና ግልጽ እንደ ሚሆንላችሁ አልጠራጠርም።
መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ
የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ሦስት ምዕራፎችንና አሥር አበይት ክፍሎችን የያዘ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ በአማርኛ ቋንቋ ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ባቀራረቡና በይዘቱ ፍፁም
የመጀመሪያው ነው ። ስለመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው ሁሉ በዚህ መጽሐፍ ተካቶ ይገኛል ። በቂ ግንዛቤ ከሌላቸው ጀማሪዎች እስከ መጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ድረስ ከዚህ መጽሐፍ የማይለካ ዘርፈ ብዙ እውቀትን ያገኛሉ ፤ ይማሩበታል ያስተምሩበታልም ።
ስለዚህ ስለእምነትዎ በሚገባ በማወቅም ሆነ በማሳወቅ ራሰዎን ፤ ቤተሰበዎንና ሕብረተሰቡን ሕያው በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ቃል ማነጽ ከፈለጉ ፤ ስለ እያንዳንዱ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ፤ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የሚቀበሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሰዎ ከያዙት ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚለያይ መሆኑን ማወቅየሚሹ ከሆነ ፤ ስለመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማርና የመስበክ ሃላፊነት ካለብዎ ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪ ፤ ዲያቆን ፤ ቄስ ፤መነኩሴ ፤ ጳጳስ ፤ ኤጲስ ቆጶስ ወዘተ ከሆኑ፤ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂዱ ከሆነ ፤ በአጠቃላይ ፍፁም የሆነውን ሃይማኖታዊውንና ማኅበራዊውን ሕገ-መንግሥት ሊመሩበት ከወደዱ ፤ከዘፍጥረት እስከ ራእየ-ዮሐንስ እንዲሁም 2ኛ የቀኖና መጻሕፍትን ጨምሮ በ81ዱ ፤ በ76ቱ ፤ በ73ቱ ፤በ66ቱና በ24ቱ የዕብራውያን ብሉይ ኪዳን የሚገኙ መጻሕፍት ሁሉ በቀላልና ልዩ በሆነ ዘመዊ አቀራረብ የመጽሐፉ ጸሐፊ ፤ የተጻፈበት ዘመንና ቦታ ፤ የመጽሐፉ ፍሬ-ሐሣብ ባጭሩ ፤ የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት ባጭር ትንታኔ ምርጥ ጥቅሶች ፤ ልዩና ያልተለመዱ ፤ እንዲሁም የመጽሐፉ መልዕክት በሚሉ መሠረታውያን አርእስት የያንዳንዱመጽሐፍ ይዘት ማራኪ በሆነ መንገድ የመጽሐፉን ጠቅላላ ሐሣብ ባጭሩ ተምሮ በሰፊው መረዳት በሚያስችል ዘዴ ቀርቧል ።
በእኔ እይታ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከልጅ እስካዋቂ ይህንን መጽሐፍ ሊይዝ ይገባልእላለሁ ። በመሆኑም እርሰዎም ከመጽሐፍ ቅዱሰዎ ጋር ተዋውቀው ያስተዋውቁት እላለሁ ።
"ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን
"Lisane Ge'ez Yegara Quanquachin" is a study book for Ge'ez Language. This book is part one and teaches Ge'ez language for Amharic speakers however, includes also some basic English grammars and vocabularies to help the people who are interested to learn some basic Ge'ez words.ከዚህ መጽሐፍ የግእዝን ቋንቋ በአማርኛ የሚማሩ ሲሆን መጠነና የሆነ የእንግሊዘኛ ቃላትንና አገባቦችንም ያስተምራል። ይህ መጽሐፍ በመሠረታዊነት የተዘጋጀው ቋንቋውን ምንም ለማያውቁ ጀማሪዎችና መጠነኛ ግንዛቤ ኖሯቸው ሰዋስዋዊ አካሄዱን ግን ለማያውቁ ሲሆን ከዚያም በላይ የእውቀት ደረጃ ላሉም ቢሆን በተለይ የአገባብ መዋቅሮችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤን እንዲሰጥ ታስቦ ነው።
መጽሐፉን ካህናት፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፤ በየአብያተ ክርስቲያናት ሕጻናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ የእምነትንና የሥነ ምግባርን ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ለማስተማሪያነትም ሆነ የግል እውቀትን ለማዳበር እንዲሁም በማነኛውም የቋንቋ ጥናት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የቋንቋን አካሄድ፤ የቃላትን ቅንብርና አገባብ ለመገንዘብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ለወጣንያንና ለማዕከላውያን የተዘጋጀ 1ኛ መጽሐፍ እንደ መሆኑ መጠንም በውስጡ የሚገኘው እያንዳንዱ ርእስ የተሰጠው ትርጉም፤ አገልግሎትና ትንታኔ ያለቀለት ሳይሆን ለክፍል አንድ የተመጠነ ብቻ ነው።
ማለትም በክፍል ሁለትና በቀጣዮቹም ክፍሎች ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ወይም እየጨመረ የሚሄድ ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ወይም አገባብ እናንተ የምታውቁትን ሁሉ አካቶ ባለመገኘቱ የተረሣ ወይም ሳይታወቅ የታለፈ እንዳይመስላችሁ፤ ለክፍል አንድ ተመጥኖ የቀረበ ስለሆነ ብቻ ነው። ለወደፊቱ በእኔ የሚዘጋጁ የግእዝ መማሪያ መጻሕፍት ከዚህ መጽሐፍ የሚቀጥሉ እንጅ ይህንን ክፍል የማያካትቱ ስለሚሆኑ የቋንቋው ሙሉ ፍላጎት ያለው ሁሉ ከዚህ ከመሠረታዊው ትምህርት መጀመር አማራጭ የሌለው በመሆኑ ይህን መጽሐፍ ማግኘት ይኖርበታል ብየ አምናለሁ። እንደዚህ ከሆነ ማለትም መሠረቱን በሚገባ መገንዘብ ከቻላችሁ ጽኑ እና በአለት ላይ የተመሠረተ መሠረት ስለሚኖራችሁ ቀጣዩ ትምህርት በጣም ቀላል እና ግልጽ እንደ ሚሆንላችሁ አልጠራጠርም።
No comments:
Post a Comment