Tuesday, June 25, 2019

የጭንቅ ሰቆቃ/ The Depression of Tragedy-Poem


የጭንቅ ሰቆቃ


አንተ ቸር ፈጣሪ አልፋና ዖሜጋ
ሰላም የባሕርይህ ይቅርታም ካንተ ጋ
ነውና ወደ እኛ ቀኝ እጅህን ዘርጋ፤
ሰብሳቢ የሌለው የባዘነ መንጋ
ሆነን በሜዳ ላይ ቀርበናል ላደጋ።

የኃያላን አምላክ የነገሥታት ጌታ
ፈጥነህ ድረስልን እንዳንንገላታ፤

ልባችን ኮብልሎ ከአንተ ሸፍተን
ብዙ ተንገላታን ለረጅም ዘመን፤
የጥበብ ባለቤት መሆንህን ዘንግተን
በምድራዊው እውቀት ስንመካ ቆየን፤
በታንክ በመትረየስ ስናምን በይፋ
እየከዳን ሄደ እየጣለን ጠፋ፤
ያመኑት ሲከዳ ዋ! ታላቅ አበሣ
ወዳጅ ጠላት ሆኖም ሊበላን ተነሣ።

ተጣላን፣ ተብላላን፣ ተገዳደልንሣ!
ምነው አእምሮ አጣን ሆን እንደ እንስሣ! ።

ኀያሉ ፈጣሪ የሰላሙ ጌታ
ኢትዮጵያን ታደጋት ሁንላት መከታ
ወዳንተ እየጮኸች ቃሏን አሰምታ
ማረኝ ትልሃለች እጆቿን ዘርግታ
ዕንባን እያነባች ጸሎቷን ሳትገታ
ደምን ታለቅሳለች ከጧት እስከማታ።

የዘረኞች ክፋት የክፉዎችም ኃል
ከቦ ሲያጣድፋት ሲጎዳት በከፊል
አምላክ ሆይ ገላግላት የምጥ ጣር ይዟታል።

ፈጣሪ በሰጠሽ በቃል ኪዳንሽ
አመጸኛውን ሰው ስምኦንን ያዳንሽ
በዚያው ታላቅ ፀጋሽ በጽኑ ምልጃሽ
ዛሬም በዚህ ዘመን ማልደሽ ልጅሺን
አድኛት ታደጊያት እናት ኢትዮጵያን።

እምዬ ኢትዮጵያ ውቢቷ ሐገሬ
ዘመን ጣለሺና ጠወለግሽ ዛሬ
በልጆችሽ ኀዘን ኑሮሽ ስለከፋ
መልክሽ ተለውጦ ውበትሺም ጠፋ።

በአንበሦች ጉድጓድ እንደሚል መጽሐፍ
ዳንኤልን ያዳንክ ሕይወቱ ሳያልፍ
ኢትዮጵያን አድናት፣ ታደጋት፣ ከገዳዮች ሰይፍ።

ፈጣሪ ሆይ እርዳት ስማት በጽሙና
እምዬ ኢትዮጵያ ተጨንቃ በጠና
ከሞት አፋፍ ሆና ትጣራለችና።

ኢትዮጵያ ተናዘዥ ኃጢአትሺን ንገሪ
ለሊቀ ካህናቱ ለዓለም ፈጣሪ፣
ንስሐ ከገባሽ ምንም ሳትሠውሪ
እርሱ ያድንሻል ነውና መሐሪ።

አምላክ ሆይ አድነን አውጣን ከፈተና
ሕግህን ተላልፈን በድለናልና።

ባደረገቺው ግፍ በሠራቺው ኃጢአት
ከእንግዲህ ፈርጀ ምድርን ላላጠፋት
ለቃል ኪዳን ማጽኛ ለውል ስምምነት
በእኛ መካከል ለእውነት ምልክት
ስየ አሳይሃለሁ ቀስቴን በደመና
ብለህ በነገርከው ለኖኅ በቅድምና
ፈጣሪሆይ ማረን መሐሪ ነህና።
ከፊቷ መትረየስ ከኋላዋ መድፍ
በስተቀኞ ታንክ በግራዋም ሰይፍ
ከበው ሲያስጨንቋት ኢትዮጵያን በሰልፍ
ፈርታ ተንቀጥቅጣ ደንግጣ ተዳክማ
ይኸው ታለቅሳለች መካከል ላይ ቆማ
እምዬ ኢትዮጵያ ባልቴቲቱ እማማ
ይኸው ታለቅሳለች መካከል ላይ ቆማ።

ስለ ዚህ ፈጣሪ ሳትጠፋ ፈጽማ
ፈጥነህ ታወጣት ዘንድ ከጥፋት አውድማ
ልቅሶዋን አዳምጥ ጩኸቷንም ስማ።

ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ ብለህ
የማልክላቸውን ለጥንት ወዳጆችህ
ፈጣሪ ሆይ አስብ ጎብኘን በምህረትህ
አቤቱ አታጥፋን በደላችን ቆጥረህ።

ወንጌልን ለዓለም ዞረው ባበሠሩ
በማያምኑትም ፊት ሳይፈሩ ሳያፍሩ
ስምህን በይፋ ቆመው ባበሠሩ
 በሐዋርያትህ ስም ማረን አንተ ቸሩ።

ኃጢአታችን በዝቶ ዕውን ቢሆን ዛሬ
ምድር ተለውጣ ሆነቺብን አውሬ።

በክፉ አሟሟት በከንቱ እንዳናልቅ
አቤቱ አምላካችን ፍጥረትህን ጠብቅ።

ማረን እራራልን አንተ አምላከ ሰላም
ልትከዳን ነውና ይህች የተውሶ ዓለም።

ወዳንተ እንጮሃለን በልቅሶ በዋይታ
የምሕረት ባለቤት ማረን አንተ ጌታ
አምላከ አብርሃም ወአምላከ ሣራ
አምላከ ኤልያስ ወአምላከ ዕዝራ
ኢትዮጵያን አደራ ኢትዮጵያን አደራ
እንለምንሃለን ልጆቿ በጋራ።

 ይህ ግጥም “የጸጋ ግምጃ ቤት” ከተሰየው የግጥም መድበል መጽሐፌ ተወስዶ መጠነኛ ለውጭ ተደርጎበታል ።
መጽሐፉን ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ(ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ።
 

Monday, June 24, 2019

የጭንቅ ሰቆቃ ሥነ ግጥም/Yechink Sekoka poem by Mhr Melaku




የጭንቅ ሰቆቃ ስነ ግጥም ስለ አገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች 
ግጥሙ ያለበትን መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ሊንክ ይጫኑ

https://amzn.to/2Rvwu5I

Sunday, June 16, 2019

ቃለ - መጠይቅ ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ጋር/Interview with Megabe Hadis Eshetu Alema...




መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር፤ እንዲሁም የመጻሕፍት
ትርጓሜና የቅኔ መምህር እና መም/ር መላኩ አስማማው የአውደ ጥናት እና የአውደ ጥናት ዘግእዝ መሥራችና አስተማሪ ቃለ - መጠይቅ ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ጋር/Interview with Megabe Hadis Eshetu Alemayehu

ስለ ግእዝ ቋንቋ ቅድመ ታሪክ፤ ይዘትና ጥቅም፤ እንዲሁም ስለ አውደ ጥናት ዘግእዝ የትምህር አሰጣጥ ዘዴ ሰፋ ያለ ማብራርያ ይሰጣሉ ፤ ለሌሎችም ሸር ያድርጉ

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተባለውን መጽሐፍ ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ

Saturday, June 15, 2019

“For US and For Them” ለኛም ለነሱም


“For US and For Them” ለኛም ለነሱም 






“ለኛም ለነሱም” 
ለኛም ለነሱም :- 
ማለት እኛ እንግሊዘኛ የምንማርበት፤
 እነሱም አማርኛ የሚማሩበት ማለት ነው።

“ለኛም ለነሱም በተሰኘው”
በዚህ ርእስ መሠረታዊ መግባቢያ
የሚሆን የአማርኛ ቋንቋ 

ለውጭ ዜጎችና በውጭ ለተወለዱ
ኢትዮጵያውያን የሚሰጥ ሲሆን እንዲሁም 

መሠረታዊ የሆነ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትን
 መማር ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን
የእንግሊዘኛ ትምህርት ይሰጥበታል።
 በመሆኑም “በአንድ ወንጭፍ
ሁለት ወፍ”እንደ ማለት ነው።
 (በመልካም መንገድ ሲተረጎም)
 ወይም “ሰይፍ ዘክልኤ አፉሁ”
ማለት ሰይፍ በሁለቱም ጎን በኩል
 ስለት ያለው ነው ማለት በሁለቱም
 የሚሠራ ለማለት ነው።ስለዚህ
ይህም ድረ-ገጽ ሁለት የተለያዩ ቋንቋዎችን
በአንድ ጊዜ ያስተምራል ማለት ነው።

Teaching Amharic Language
 for Amharic and non-Amharic
speakers as well
as Teaching Basic English
 for Amharic speakers
















ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘውን
 ይህንን መጽሐፍ እና ሌሎችንም 
መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት 
የሚከተለውን(መጽሐፉን) ይጫኑ።






English letters/ የእንግሊዘኛ ፊደላት
  For Us/ ለኛ

6ቱ የእንግሊዘኛ ፊደላት ሲሆኑ 5ቱ 
በቀይ የተከበቡት አናባቢዎች፤ "ዋይ" 
የተባለውና በቀይና በቡናማ ቀለም
የተከበበው ሆሄ  ግማሽ አናባቢ
(አንዳንድ ጊዜ አናባቢ
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ተናባቢ)
ሲሆን ቀሪዎቹ  ማለትም
ሃያዎቹ ሆሄያት ደግሞ ተናባቢዎች ናቸው። 
 ማለትም፡ A, E, I, O, U
ሙሉ በሙሉ አናባቢዎች ሲሆኑ "Y" 
ተባለው ሆሄ ግን  አልፎ አልፎ
አናባቢ በመሆን ይሠራል።
ይህ ማለት የእንግሊዘኛ
ፊደላት ትርጉም ሊኖራቸው የሚችለው
አናባቢና ተናባቢ ተቀላቅለው ሲጻፉ ነው። 


















ከዚህ በላይ ያሉትን
 አናባቢዎችና ተናባቢዎች 
ለይታችሁ እወቁ ማለትም
 የያንዳንዱን ፊደል ስም ጻፉ፤
 እንዲሁም  ስንት ትናባቢ ፊደላት አሉ?
ስንት አናባቢ ፊደላት አሉ?
ስንት አናባቢም ተናባቢም ፊደላት አሉ?  
የሁሉም የእንግሊዘኛ ሆሄያት
ድምራቸው ስንት ነው?  
ለአምስቱም ጥያቄዎች መልስ ስጡ


ከዚህ በላይ ባሉት ሁለት 
የእንግሊዘኛ ቃላት  
የእንግሊዘኛ አናባቢዎች
(Vowels) ሁሉ አሉባቸው 
ስለዚህ አናባቢዎቹን 
ለይታችሁ በማውጣት 
ለብቻቸው ጻፉ።



ከዚህ በታች ያሉት ደግሞ
ፊደላቱ በትልቅ እና በትንሽ

(ካፒታል ሌተር እና 
ስሞል ሌተር) ሲጻፉ ነው/ 

Capital or 
small letters

(also called upper
and Lower case)


















For Them/ለነሱ
Comparing Amharic letters

 with English Learn 
the Amharic Alphabet





For Example: 
This letter “ሀ” is Called Ha (He)
  and has the sound of  “H” 
 so, it replaces
 the English letter “H” and
has 7 branches
with similar sounds  
and they replace the vowels.
1.     = He
2.    = Hu
3.    = Hi
4.    = Ha
5.    = Hia
6.    = H
7.    = Ho 

Self-Introducing/
ራስን ማስተዋወቅ
For Us/ለኛ:


ይህንን ድረ-ገጽ የጀመርኩት
ለውጪው ዓለም
 አዲስ የሆኑ ወገኖች
ሊኖሩ ስለሚችሉ
በመጠኑም ቢሆን
መሠረታዊ የእንግሊዘኛ
ቋንቋን ለማጥናትና
በሥራ ቦታም ሆነ
በትምህርት ቤት
በቀላሉ ለመግባባት
ያስችላቸዋል
ብየ በማሰብ ነው።


Hello, my name is 
Melaku; I am from Ethiopia.= 
ሰላም ስሜ መላኩ ይባላል(ነው) 
እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ.

For Them/ለነሱ:

 Selam, Smie Melaku
Yibalal (naw)

Giving Personal Information= 
ስለ ራስ ማንነት መናገር
ወይም ማስተዋወቅ የቃላት ትርጉሞች፤ 

Giving = መስጠት፤ 
Personal = የግል 
Information =መረጃ 


ከዚህ በታች ባሉት 
ቃላት መሠረት ራሳችንን
 ስናስተዋውቅና ሌላውን ስንጠይቅ 

My name is ----
I came from----
What is your name?


Where are you from?
የቃላት ትርጉም
my = የኔ
name=ስም
is= ነው/ናት
My name is ----=
ስሜ/የኔ ስም ----ነው 
(በባዶ ቦታው ላይ 

ስማችንን ማስገባት ነው)

ለምሳሌ፡ እኔ 
My name is Melaku
ብል "ስሜ ወይም
 የኔ ስም መላኩ ይባላል 
ማለት እችላለሁ። እናንተም 
እንደዚሁ ስማችሁን ማስገባት 
ትችላላችሁ።

የቃላት ትርጉም
I = እኔ
Came= መጣሁ፤መጣ፤ 
መጣች፤ መጡ፤ 
መጣን ወዘተ ማለት ነው

From = ከ
I Came from---= እኔ
 ከ----መጣሁ (የመጣሁት) 
ከ---ነው (በባዶ ቦታው ላይ
የመጣንበትን ቦታ/

አገር መናገር ነው) 
ለምሳሌ እኔ እንደሚከተለው
ማለት እችላለሁ።
I came from Ethiopia.

የቃላት ትርጉም
What = ምን
Your name =
ስምህ (ያንተ ስም)
what is your name?=
ስምህ ማነው (ምንድነው፤
 ወይም ማን ይባላል) 

ለምሳሌ What is your name?
 ተብየ ብጠየቅ 


My name is Melaku
በማለት መልስ መስጠት እችላለሁ ።
 ስሜ መላኩ ነው/ ወይም መላኩ

እባላለሁ ወይም ስሜ መላኩ
 ይባላል ማለቴ ነው።

የቃላት ትርጉም

Where= የት/ከየት?

are= ነን፤ናቸው፤ናችሁ

Where are you from?= 
ከየት አገር ነህ/የት ነው አገርህ?

Wher are you from? 

ተብየ ብጠየቅ

"I am from Ethiopia"
 በማለት እመልሳለሁ 

"ከኢትዮጵያ ወገን ነኝ
ወይም ኢትዮጵያዊ ነኝ/

ከኢትዮጵያ ነኝ 
ወዘተ ማለት ነው።







በአማርኛ መሪዎች ወይም
የስም ተለዋጮች እየተባሉ 
ይጠራሉ  ቁጥራቸው
 ስምንት ሲሆኑ
ከግእዝ በ2 ያንሳሉ።
እነሱም
እኔ

እኛ

አንተ

አንቺ
እናንተ
(ወንዶችም፤ሴቶችም)

እሱ

እሷ

እነሱ(ወንዶችም ሴቶችም)
በእንግሊዘኛ ፐርሰናል
ፕሮናውንስ ይባላሉ
ቁጥራቸው 6 ሲሆንከግእዝ
በ4 ከአማርኛ ደግሞ
በ2 ያንሳሉ።
ስማቸውም 
Personal pronouns

We

You (4)

He (it)

She (it)

They

አገልግሎታቸው የአንድን አካል፤
ወይም ነገር ስም ወክለው

ወይም ተክተው መሥራት
ወይም የዐ/ነገር ባለቤት
መሆን ነው።

አንደኛ ምሣሌ፡
መላኩ፡ ብለን በስም መጥራት
 ካልፈለግን

በስም ተለዋጭ ተክተን
 እሱ በማለት እንጠራዋለን

ስለዚህ መላኩ መጣ
በማለት ፈንታ
 “እሱ መጣ” እንላለን።

በመሆኑም“እሱ”
የሚለው“መላኩን”

ተካ ወይም የመላኩን
ድርሻ ያዘ ማለት ነው።

ለዚህም ነው
“የስም ተለዋጭ” የሚባለው።

ሁለተኛ ምሳሌ

“አልማዝ” ብለን በስሟ መጥራት
 ካልፈለግን“እሷ”
 በማለት እንጠራታለን።
 ስለዚህ“
አልማዝ መጣች”
በማለት ፈንታ
“እሷ መጣች” እንላለን።

ሦስተኛ ምሳሌ፡
“መላኩና አልማዝ”
ብለን በስማቸው
 መጥራት ካልፈለግን

“እነሱ” እንላለን።
 ስለዚህ “አልማዝና መላኩ መጡ”

በማለት ፈንታ “እነሱ መጡ”
 እንላለን ማለት ነው።

ተውላጠ ስሞች/
 Personal Pronouns
 እና የአማርኛ ትርጉማቸው

· I = እኔ

· We = እኛ

· You = አንተ

· You = አንቺ

· You = እናንተ

· You = እናንተ

· He = እሱ

· She = እሷ

· It = እሱ
(ለእቃ፤ ለማይሰማ ነገር)

· They = እነሱ
በሚከተለው መልኩ
ዐ/ነገር ይሠራባቸዋል

· I am = እኔ ነኝ

· We are = እኛ ነን

· You are = አንተ ነህ

· You are = አንቺ ነሽ

· You are = እናንተ ናችሁ

· You are = እናንተ ናችሁ

· He is = እሱ ነው

· She is = እሷ ናት

· They are = እነሱ ናቸው

· They are =
 እነሱ ናቸው
ባለቤትነትን
የሚያመለክቱ ቃላት
/Possessive Pronouns =

ባለቤትነትን የሚያመለክቱ ቃላት
ከዚህ በታች ያሉት ቃላት
ሁለት ሁለት ናቸው
ሁለቱ ባለቤትነትን
የሚያመለክቱ ናቸው
ላሁኑ ሁለቱም
አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው
በሚቀጥለው ትምህርት

ሁለቱን ማለትም
 የያንዳንዳቸውን
 ልዩነት እናያለን።

ላሁኑ አንድ ምሳሌ እንሆ :
ከጽሁፉ መጨረሻ ላይ

አንድ መጽሐፍ አለ
 ይህ መጽሐፍ የማን
መሆኑን ለመግለጽ

አንድ አመልካችን እንጠቀም
 (የሷ መጽሐፍ ለማለት)*

1st person singular
 and plurals

Ø My = የኔ
 (need subject
or object)

Ø mine = የኔ

Ø የኔ

Ø -------------

2nd person singular
and plurals

Ø Our =

Ø ours =

Ø የኛ

Ø የኛ

Ø ----------

3rd person singular
 and plurals

Ø Your =

Ø yours =

Ø ያንተ፤

Ø የናንተ፤

Ø ያንቺ፤

Ø የናንተ

----------

Ø Their =

Ø theirs =

Ø የነሱ፤

Ø የነሱ

-----------

Ø His =

Ø It's =

Ø የሱ፤

Ø የሱ

----------

Ø Her =

Ø Hers

Ø የሷ፤

Ø የነሱ

Example/ምሳሌ፡
---Her book =

የሷ መጽሐፍ ማለታችን ነው፡

ላሁኑ ቃላቱን ብቻ አጥኑ

(ማለትም የተጻፈውን ትርጉም
 በቃል መያዝ ነው)

በሚቀጥለው በዐረፍተ ነገር

እያስገባን እንማራለን።







Thursday, June 13, 2019

እምነትሽ ያድንሽ-ግጥም/Let your faith saves you-poem



“… በልጅ የመደሰት ዕድሉም ከሌለሽ፣
ትካዜ ጩኸቱን ስሞታውን ትተሽ
ጸሎት አቅርቢና ወደ ቸሩ አምላክሽ
በልቡናሽ ያለው እምነትሽ ያድንሽ”

መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ

Saturday, June 8, 2019

Megabe Hadis about the Orthodox Church song contents/ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች ይዘት

Megabe Hadis Eshetu Alemayehu teaches about what the Orthodox Church songs should includes/ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች ይዘት 

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የሰዋስወ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር፤ የመጻሕፍት ትርጓሜና የቅኔ ምሁር  ናቸው 
መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ስለ ቅዱስ ያሬድ መዝሙራት እና በአጠቃላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙራት ምን ምን መሠረታውያን ነጥቦችን በውስጣቸው ማካተት እንዳለባቸውና ከሌሎች ሃይማኖታዊ መዝሙራት መለየት እንደሚገባቸው ሰፋ አድርገው ይገልጻሉ። 
ቪዲዮውን ለመስማት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ፤ ሌሎችንም ልዩ ልዩ ትምህርቶችን ለማግኘት ሰብስክራይብ አድርጉ፤ ሸርም አድርጉት። እግዚአብሔር ይባርከዎ።
ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን እና “ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” የሚባለውን ሌሎችንም መጻሕፍት ለመግዛት የመጻሕፍቱን ሥዕል ይጫኑ
ሁለቱ  ተወዳጆቹ መጻሕፍቶቼ!!
እነዚህን መጻሕፍት ልታገኞቸው ይገባል፤ በውነትም ይረኩባቸዋል።


ስለ መጻሕፍቶ ማብራርያና ይዘት የሚከተለውን ያንቡ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ

የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ሦስት ምዕራፎችንናአሥር አበይት ክፍሎችን የያዘ ሲሆንበመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ በአማርኛ ቋንቋከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ባቀራረቡና በይዘቱፍፁም የመጀመሪያው ነው ።

ስለመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስውስጥ ስላለው ሁሉ በዚህ መጽሐፍ ተካቶይገኛል ። በቂ ግንዛቤ ከሌላቸው ጀማሪዎችእስከ መጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ድረስከዚህ መጽሐፍ የማይለካ ዘርፈ-ብዙእውቀትን ያገኛሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታልም ። ስለዚህ ስለእምነትዎ በሚገባ በማወቅም ሆነ በማሳወቅ ራሰዎን ፤ ቤተሰበዎንና ሕብረተሰቡን ሕያው

በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ቃል ማነጽ ከፈለጉ ፤ ስለ እያንዳንዱ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ፤የተለያዩ የሃይማኖትተቋማት የሚቀበሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሰዎ ከያዙት ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚለያይ መሆኑን ማወቅ የሚሹ ከሆነ ፤ስለመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማርና የመስበክ ሃላፊነት ካለብዎ ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪ ፤ ዲያቆን ፤ ቄስ ፤ መነኩሴ ፤ ጳጳስ ፤ኤጲስ ቆጶስ ወዘተ ከሆኑ፤ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂዱ ከሆነ ፤ በአጠቃላይ ፍፁም የሆነውን

ሃይማኖታዊውንና ማኅበራዊውን ሕገ-መንግሥት ሊመሩበት ከወደዱ ፤ ከዘፍጥረት እስከ ራእየ-ዮሐንስ እንዲሁም 2ኛ የቀኖናመጻሕፍትን ጨምሮ በ81ዱ ፤ በ76ቱ ፤ በ73ቱ ፤በ66ቱና በ24ቱ የዕብራውያን ብሉይ ኪዳን የሚገኙ መጻሕፍት ሁሉ በቀላልና ልዩበሆነ ዘመናዊ አቀራረብ የመጽሐፉ ጸሐፊ ፤ የተጻፈበት ዘመንና ቦታ ፤ የመጽሐፉ ፍሬ-ሐሣብ ባጭሩ ፤ የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘትባጭር ትንታኔ፤

ምርጥ ጥቅሶች ፤ ልዩና ያልተለመዱ ፤ እንዲሁም የመጽሐፉ መልዕክት በሚሉ መሠረታውያን አርእስት የያንዳንዱ መጽሐፍ ይዘትማራኪ በሆነ መንገድ የመጽሐፉን ጠቅላላ ሐሣብ ባጭሩ ተምሮ በሰፊው መረዳት በሚያስችል ዘዴ ቀርቧል ።

በእኔ እይታ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከልጅ እስካዋቂ ይህንን መጽሐፍ ሊይዝ ይገባል እላለሁ ። በመሆኑም እርሰዎም ከመጽሐፍ ቅዱሰዎ ጋር ተዋውቀው ያስተዋውቁት እላለሁ

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን 
ይህ መጽሐፍ በመሠረታዊነት የተዘጋጀው ቋንቋውን ምንም ለማያውቁ ጀማሪዎችና መጠነኛ ግንዛቤ ኖሯቸው ሰዋስዋዊ አካሄዱን ግን ለማያውቁ ሲሆን ከዚያም በላይ የእውቀት ደረጃ ላሉም ቢሆን በተለይ የአገባብ መዋቅሮችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤን እንዲሰጥ ታስቦ ነው።  


መጽሐፉን ካህናት፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፤ በየአብያተ ክርስቲያናት ሕጻናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ የእምነትንና የሥነ ምግባርን ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ለማስተማሪያነትም ሆነ የግል እውቀትን ለማዳበር እንዲሁም በማነኛውም የቋንቋ ጥናት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የቋንቋን አካሄድ፤ የቃላትን ቅንብርና አገባብ ለመገንዘብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። 


 መጽሐፉ ቀላልና ግልጽ በሆነ የአጻጻፍ ስልት ቢጻፍም “ያለ መምህር መማሪያ” ለመሆን ከበድ ሊል ይችላል ብየ አምናለሁ። በመሆኑም “አውደ ጥናትን መጎብኘት አይዘንጉ። 

ከዚህ መጽሐፍ ላቅ ያለ ዕውቀት ያላችሁ አንባብያን ለወጣንያንና ለማዕከላውያን1 የተዘጋጀ 1ኛ መጽሐፍ እንደ መሆኑ መጠንም በውስጡ የሚገኘው እያንዳንዱ ርእስ የተሰጠው ትርጉም፤ አገልግሎትና ትንታኔ ያለቀለት ሳይሆን ለክፍል አንድ የተመጠነ ብቻ ነው። ማለትም በክፍል ሁለትና በቀጣዮቹም ክፍሎች ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ወይም እየጨመረ የሚሄድ ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ወይም አገባብ እናንተ የምታውቁትን ሁሉ አካቶ ባለመገኘቱ የተረሣ ወይም ሳይታወቅ የታለፈ እንዳይመስላችሁ፤ ለክፍል አንድ ተመጥኖ የቀረበ ስለሆነ ብቻ ነው።  


ሌላው ተማሪዎች ለጥናት የበለጠ እንዲተጉ በማሰብ በመጽሐፉ ውስጥ የቀረቡት ጥያቄዎች እየተመለስን መጽሐፉን እያነበብን የምንመልሳቸው ናቸው እንጅ መልሳቸው አልተሰጠም። 











Megabe Hadis Eshetu Alemayehu Et/Orthodox song/መ/ሐ እሸቱ አለማየሁ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ...



መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የትርጓሜ መጻሕፍትና

የቅኔ መምህር፤ እንዲሁም በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሣዊ ኮሌጅ መምህር የሆኑት በዚህ ቪዲዮ  ስለ ቅዱስ ያሬድ መዝሙርና በአጠቃላይ የእምነት መዝሙራት በይዘታቸው ሊያሟሏቸው ስለ ሚገቡ መሠረታውያን ነጥቦች በስፋት ማብራርያ ይሰጣሉ።
 በአትኩሮት ልትሰሙት የሚገባ መሠረታዊ ትምህርት ነው። ከሰሙ በኋላ ለሌሎች
ማስተላለፉን አይርሱ። 

እነዚህን ሁለት መጻሕፍቶቼን  እና ሌሎችንም መጻሕፍት ለመግዛት የመጻሕፍቶቹን ሥዕል በመጫን ይጠቀሙ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ

የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ሦስት ምዕራፎችንና አሥር አበይት ክፍሎችን የያዘ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ በአማርኛ ቋንቋ ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ባቀራረቡና በይዘቱ ፍፁም የመጀመሪያው ነው 
ስለመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው ሁሉ በዚህ መጽሐፍ ተካቶ ይገኛል  በቂ ግንዛቤ ከሌላቸው ጀማሪዎች እስከ መጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ድረስ ከዚህ መጽሐፍ የማይለካ ዘርፈ-ብዙ እውቀትን ያገኛሉ

ይማሩበታል ያስተምሩበታልም 

 ስለዚህ ስለእምነትዎ በሚገባ በማወቅም ሆነ በማሳወቅ ራሰዎን  ቤተሰበዎንና ሕብረተሰቡን ሕያው
 በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ቃል ማነጽ ከፈለጉ  ስለ እያንዳንዱ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የሚቀበሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሰዎ ከያዙት ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚለያይ መሆኑን ማወቅ የሚሹ ከሆነ  ስለመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማርና የመስበክ ሃላፊነት ካለብዎ  የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪ  ዲያቆን  ቄስ  መነኩሴ  ጳጳስ  ኤጲስ ቆጶስ ወዘተ ከሆኑ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂዱ ከሆነ  በአጠቃላይ ፍፁም የሆነውን 
ሃይማኖታዊውንና ማኅበራዊውን ሕገ-መንግሥት ሊመሩበት ከወደዱ  ከዘፍጥረት እስከ ራእየ-ዮሐንስ እንዲሁም  2 የቀኖና መጻሕፍትን ጨምሮ 81  76  73 66ቱና 24  የዕብራውያን ብሉይ ኪዳን የሚገኙ መጻሕፍት ሁሉ በቀላልና ልዩ በሆነ ዘመናዊ አቀራረብ የመጽሐፉ ጸሐፊ  የተጻፈበት ዘመንና ቦታ  የመጽሐፉ ፍሬ-ሐሣብ ባጭሩ  የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት ባጭር ትንታኔ፤
ምርጥ ጥቅሶች  ልዩና ያልተለመዱ  እንዲሁም የመጽሐፉ መልዕክት በሚሉ መሠረታውያን አርእስት የያንዳንዱ መጽሐፍ ይዘት ማራኪ በሆነ መንገድ የመጽሐፉን ጠቅላላ ሐሣብ ባጭሩ ተምሮ በሰፊው መረዳት በሚያስችል ዘዴ ቀርቧል 

በእኔ እይታ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከልጅ እስካዋቂ ይህንን መጽሐፍ ሊይዝ ይገባል
እላለሁ  በመሆኑም እርሰዎም ከመጽሐፍ ቅዱሰዎ ጋር ተዋውቀው ያስተዋውቁት እላለሁ 


Wednesday, June 5, 2019

“እስመ ሰማዕከ ቃለ ብእሲትከ/Because you listen the word of your wife

መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ
https://amzn.to/2MrZRXH
https://amzn.to/2MEcVZU

 ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ ወቅታዊ ታሪክን መሠረት ያደረገ የግእዝ ቋንቋ ጥቅስ ትምህርታችን
 ክፍል 3 

ይቀጥላል እንከታተል።


 የዛሬውም ጥቅስ በቀዳማይ ምዕራፈ ታሪክ ውስጥ በሕገ ልቡና የተነገረ ነው። ዛሬ ሁለት ጥቅሶችን ነው የምናየው። ባለፈው እንዳየነው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ነጻነት የተገደበ አይደለም በመሆኑም አዳምና ሔዋን በሞትና በሕይወት መካከል የመምረጥ ሙሉ ነጻነት ተሰጣቸው። እነሱም የወደዱትን መረጡ።

ስለዚህ በምርጫቸው መሠረት የመረጡትን አገኙ ማለት ነው። ለሰው ልጅ የተሰጠውን ሙሉ ነጻነትና ምርጫ ለመግለጽ ሊቃውንቱ የሚከተለውን ጥቅስ በግእዝ ቋንቋ ይጠቅሳሉ። “አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ” የሚለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ።
 መጽሐፈ ሢራክ 15፡16

 = እሳትና ውኃን አቅርቤልሃለሁ ወደ ወደድከው እጅህን አስገባ” ማለት ነው። (ሞትና ሕይወትን አቅርቤልሃለሁ የመረጥከውን ውሰድ) አሁን እያንዳንዱን ቃል የሚነሣውን እና የሚወድቀውን እየጠቀስኩ እነግራችኋለሁ •

 “አቅረብኩ • ለከ • እሳተ • ወማየ • ደይ • እዴከ • ኀበ ዘፈቀድከ” በትቅሱ ውስጥ አሥራ አንድ ቃላትና ሆሄያት ይገኛሉ ሆሄያቱ አገባቦች ናቸው
1. “አቅረብኩ
 2. ለ
3. ከ
 4. እሳተ
 5. ወ
6. ማየ
 7. ደይ
 8. እዴከ
9. ኀበ
 10. ዘ
11. ፈቀድከ”  

2ኛው ጥቅስ ይቀጥላል አዳምና ሔዋን አሁን ምርጫቸውን መርጠዋል፡ እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት የሚከተለውን አስተላለፈ
 “እስመ ሰማዕከ ቃለ ብእሲትከ ወበላዕከ እም ውእቱ ዕፅ ባሕቲቱ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ ርግምተ ትኩን ምድር በተግባርከ ወበጻዕር ብላዕ ኵሎ መዋዕለ ሕይወትከ” ዘፍ. 3፡17
 = የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፤ እንዳትበላ ካዘዝኩህ ከዚያ አንድ ዛፍ በልተሃልና ምድር በሥራህ (በኃጢአትህ) የተረገመች ትሁን፤ በሕይወትህ ዘምን ሙሉም በጭንቀ(በድካም) ብላ።

 የቃላቱ የአነባበብ ስልትና የንባብ ስልት ስማቸው እንዲሁም የቃላቱ ምድብና አከፋፈል። አነባበብ •

 “እስመ ሰማዕከ
 • ቃለ ብእሲትከ
• ወበላዕከ
 • እም ውእቱ ዕፅ
 • ባሕቲቱ ዘአዘዝኩከ
 • ከመ ኢትብላዕ
 • ርግምተ ትኩን ምድር በተግባርከ
 • ወበጻዕር ብላዕ ኵሎ መዋዕለ ሕይወትከ”

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ፡
 የተሰኘውንና በአማርኛ ከተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መጻሕፍ የመጀመሪያው የሆነውን ሙሉ የ81ዱን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች የሚቀበሏቸውን የማይቀበሏቸውን ምክንያት ሁሉ የያዘን መጽሐፌን ከአማዞን ይግዙ!

/>

 ልዑል አምላክ ለብዎቶ የሐበነ
 እም አውደ ጥናት ዘግእዝ andegha