Tuesday, June 4, 2019

አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ

አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ 

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ ወቅታዊ ታሪክን መሠረት ያደረገ የግእዝ ቋንቋ ጥቅስ ትምህርታችን ክፍል 3 ይቀጥላል እንከታተል።
የዛሬውም ጥቅስ በቀዳማይ ምዕራፈ ታሪክ ውስጥ በሕገ ልቡና የተነገረ ነው። ዛሬ ሁለት ጥቅሶችን ነው የምናየው።

ባለፈው እንዳየነው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ነጻነት የተገደበ አይደለም በመሆኑም አዳምና ሔዋን በሞትና በሕይወት መካከል የመምረጥ ሙሉ ነጻነት ተሰጣቸው። እነሱም የወደዱትን መረጡ። ስለዚህ በምርጫቸው መሠረት የመረጡትን አገኙ ማለት ነው።
ለሰው ልጅ የተሰጠውን ሙሉ ነጻነትና ምርጫ ለመግለጽ ሊቃውንቱ የሚከተለውን ጥቅስ በግእዝ ቋንቋ ይጠቅሳሉ።

መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ
https://amzn.to/2MrZRXH
“አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ” የሚለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ። መጽሐፈ ሢራክ 15፡16 =
እሳትና ውኃን አቅርቤልሃለሁ ወደ ወደድከው እጅህን አስገባ” ማለት ነው።(ሞትና ሕይወትን አቅርቤልሃለሁ የመረጥከውን ውሰድ)
አሁን እያንዳንዱን ቃል የሚነሣውን እና የሚወድቀውን እየጠቀስኩ እነግራችኋለሁ
·         “አቅረብኩ
·         ለከ
·         እሳተ
·         ወማየ
·         ደይ
·         እዴከ
·         ኀበ ዘፈቀድከ”
በትቅሱ ውስጥ አሥራ አንድ ቃላትና ሆሄያት ይገኛሉ ሆሄያቱ አገባቦች ናቸው
1.   “አቅረብኩ
2.  
3.  
4.   እሳተ
5.  
6.   ማየ
7.   ደይ
8.   እዴከ
9.   ኀበ
10.
11. ፈቀድከ”
2ኛው ጥቅስ ይቀጥላል
አዳምና ሔዋን አሁን ምርጫቸውን መርጠዋል፡ እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት የሚከተለውን አስተላለፈ
 “እስመ ሰማዕከ ቃለ ብእሲትከ ወበላዕከ እም ውእቱ ዕፅ ባሕቲቱ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ ርግምተ ትኩን ምድር በተግባርከ ወበጻዕር ብላዕ ኵሎ መዋዕለ ሕይወትከ” ዘፍ. 3፡17
=
የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፤ እንዳትበላ ካዘዝኩህ ከዚያ አንድ ዛፍ በልተሃልና ምድር በሥራህ (በኃጢአትህ) የተረገመች ትሁን፤ በሕይወትህ ዘምን ሙሉም በጭንቀ(በድካም) ብላ።
የቃላቱ የአነባበብ ስልትና የንባብ ስልት ስማቸው እንዲሁም የቃላቱ ምድብና አከፋፈል።
አነባበብ
·         “እስመ ሰማዕከ
·         ቃለ ብእሲትከ
·         ወበላዕከ
·         እም ውእቱ ዕፅ
·         ባሕቲቱ ዘአዘዝኩከ
·         ከመ ኢትብላዕ
·         ርግምተ ትኩን ምድር በተግባርከ
·         ወበጻዕር ብላዕ ኵሎ መዋዕለ ሕይወትከ”

ልዑል አምላክ ለብዎቶ የሐበነ
እም አውደ ጥናት ዘግእዝ

No comments:

Post a Comment