Showing posts with label 8ቱን የንግግር ክፍሎች በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ the 8 parts of speech in one sentences. Show all posts
Showing posts with label 8ቱን የንግግር ክፍሎች በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ the 8 parts of speech in one sentences. Show all posts

Thursday, August 27, 2020

Personal pronouns part 8

 Personal pronouns part 8

Personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውን/ ሰብአዊ ወይም አካላዊ የስም ተለዋጮች

 

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው፤ በዛሬው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ስለ personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ ነው የምንማረው። ባለፈው እንደመግቢያ እንዳየነው pronounse/ፕሮናውንስ ብዙ ዓይነት እንደሆኑ፤ ከብዙዎቹ መካከልም አንድዱ “ፐርሰናል ፕሮናውን/personal pronoun” የሚባለው እንደሆነና “ፐርሰናል ፕሮናውንስ” ራሳቸው በ3 እንደሚከፈሉ። ተነጋግረን ነበር።

ስለዚህ ዛሬ ስለ ሦስቱ የስም ተለዋጭ/personal pronouns ዓይነቶች በምሳሌ እናያለን እንከታተል። ሰብስክራይብ እና ሽር ማድረግን አትርሱ።

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ


መጻሕፍት ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ በአድራሻዎ ይላክለዎታል።





 

ባለፈው ባጭሩ እንደጠቀስኩት Personal Pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ በ3 ዐበይት ክፍሎች ይከፈላሉ፤ እነሱም

1.   Subjective/ስብጀክቲብ (ባለቤት የሚሆኑ)

2.   Objective/ኦብጀክቲቭ(ተሳቢ የሚሆኑ) እና

3.   Possessive pronouns/ፖሰሲብ (ባለቤትነትን አመልካች) ፕሮናውንስ የሚባሉት ሲሆኑ Subjective/ሰብጀክቲቭ የዐ/ነገር ባለቤት፣ Objective/ኦብጀክቲቭ ተሳቢ፣ Possessive/ፖሰሲብ ደግሞ ባለቤትነትን የሚጠቁም ወይም የሚያመለክቱ ተውላጠ ስሞች ናቸው።

 

ከዚህ በታች ባሉት 4 የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ዐረፍተ ነገራት ሦስቱን የስም ተለዋጮችና እንዴት ዓይነት አገልግሎትን እንደሚሰቱ እንመለከታለን ተከታተሉ። በተጓዳኝም ስለ ዐረፍተ ነገራቱ መዋቅር እና ስለ እያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ ባጭሩ እንዳስሳለን።

 



















በመጀመሪያ በአማርኛችን ግልጽ እንዲሆንልን የአማርኛውን ዐ/ነገራት አንድ በአንድ አስረዳና ወደ እንግሊዘኛው አልፋለሁ። በቀይ በተጻፉት ወይም ቀስቱ የተመለከተባቸውን ቃላት ላይ የበለጠ አትኩሮት ስጡ።

 

ምሳሌዎቹ የሚናገሩት ስላለፈ ጊዜ ነው፤ ትምህርታችን ግን የሚያተኩረው ስለ ጊዜው ሳይሆን ስለ ዐረፍተ ነገር ባለቤቶች እና ተሳቢዎች ነው። ማለትም “ፐርሰናል ፕሮናውንስ” ስለሚባሉት አርእስት ነው።

በተሰጡት 4 ዐ/ነገራት ውስጥ ሰብጀክቲብ/Subjective፤ኦብጀክቲብ/ Objective እና ፖሰሲቭ/Possessive ፕሮናውንስ/Pronouns የሚባሉት አገባቦች ይገኛሉ። ይህ ማለት ሦስቱም የስም ተለዋጭ ዓይነቶች ወይም ፕሮናውንስ ይገኙበታል ማለት ነው።

 

በመጀመሪያው ዐ/ነገር “እኔ” እና “አቤል” የሚባሉት ሁለት ቃላት ናቸው የሚፈለጉት። “እኔ” የሚለው የስም ተለዋጭ ሲሆን በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም ሥራውን የሠራው አካል ነው። በእንግሊዘኛው “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን/Subjective Pronoun” ይባላል። ባለቤታዊ የስም ተለዋጭ ማለት ነው። ወይም በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ በባለቤትነት የተጠቀሰውን ሰው ወይም አካል ተክቶ የሚሠራ የስም ተለዋጭ ነው።

“አቤል” የሚለው ቃል ግን የስም ተለዋጭ ሳይሆን ራሱ የሰው ስም ነው። የሥራ ድርሻውም ተሳቢ “ኦብጀክት” መሆን ነው። ስለዚህ በስም ተለዋጭ ሲተካ “እሱን” ማለት ይሆናል፤ በሁለተኛው ዐ/ነገር ላይ ተጠቅሷል። “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን” “who/ማን”? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ የስም ተለዋጭ ነው።

 

በሁለተኛው ዐ/ነገር “እኔ” እና “እሱን” የሚባሉት ሁለት ቃላት ናቸው የሚፈለጉት። “እኔ” የሚለው የስም ተለዋጭ ሲሆን በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም ሥራውን የሠራው አካል ነው። በእንግሊዘኛው “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን/Subjective pronoun” ይባላል ባለቤታዊ የስም ተለዋጭ ማለት ነው።

“እሱ” የሚለው ቃል ከላይ “አቤል” ብለን የጠቀስነው “ኦብጀክቲቭ ናውን/Objective” እሱን” በሚለው የስም ተለዋጭ ተተክቷል። ይህም “ኦብጀክቲቭ ፕሮናውን/Objective” የሚባለው ነው። ኦብጀክቲብ ፕሮናውንስ “ምንን whom”? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው።

 

በሦስተኛው ዐ/ነገር “የእኔ” የሚለው ቃል ብቻ ነው በዚህ ትምህርታችን የሚፈለገው። ይህ ባለቤትነትን የሚያመለክት የስም ተለዋጭ ወይም ፖሰሲብ ፕሮናውን ይባላል። ምክንያቱም መጽሐፉ የእኔ መሆኑን የሚገልጽ ወይም የሚናገር ስለሆነ ነው። ይህም “የማን/whose” ? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ  አመልካች ነው።

 

በአራተኛው ዐ/ነገር “የእኔ” የሚለው ቃል ብቻ ነው በዚህ ትምህርታችን የሚፈለገው። ይህ የስም ተለዋጭ እንደ ሦስተኛው የስም ተለዋጭ ባለቤትነትን የሚያመለክት ሲሆን ሁለቱ የሚለዩት የሚመለከተውን ወይም በዚህ ዐረፍተ ነገር “መጽሐፍ” የሚለውን ንብረት ከፊት ለፊታቸው ወይም ከኋላቸው በማስቀመጥ ነው።

 

ስለዚህ 3ኛው የስም ተለዋጭ  “ፖሰሲብ አድጀክቲቭ/Possessive Adjective” ይባላል (ቅጽላዊ አመልካች ማለት ነው)

 

በ4ኛው ዐ/ነገር የሚገኘው የስም ተለዋጭ ደግሞ “ፖሰሲብ ፕሮናውን/Possessive Pronoun”(ባለቤታዊ አመልካች) ይባላል። ወደፊት የሁለቱን ልዩነት በሰፊው እንማራለን።

 

ዐረፍተ ነገራቱን እናንብ ።

1.   እኔ  ትላንት አቤልን ዐየሁት

2.   እኔ  ትላንት እሱን ዐየሁት

3.   ይህ የእኔ መጽሐፍ ነው

4.   ይህ መጽሐፍ የእኔ ነው

 

·         I saw Abel yesterday

አይ ሳው(ሳ) አቤል የስተርደይ

እኔ አቤልን ትናንት አየሁት

·         I saw him yesterday

አይ ሳው ሒም የስተርደይ

እኔ እሱን ትላንት አየሁት

·         This is my book

ዚስ ኢዝ ምይ ቡክ

ይህ የእኔ መጽሐፍ ነው

·         This book is mine

ዚስ ቡክ ኢዝ ማይን

ይህ መጽሐፍ የእኔ ነው



Read on you phone this English E book


መጽሐፉ አካላዊ ሳይሆን በስልክ ወይም በሌላ ኤሌክትሮኒስ መሳሪያ የሚነበብ (ኪንድል ቡክ ነው) በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንደኝነት አልፈው ሽልማትን ያስገኙ የእንግሊዘኛ ግጥሞቼ ናቸው



ቃላት/wors

Subject/Subjective = ርዕስ፣ ርዕሰ ጉዳይ (በዚህ ትምህርታችን የዐረፍተ ነገር ባለቤት)

Object/Objective = ነገር፣ አካል፣ (በዚህ ትምህርታችን ተሳቢ)

Possessive = የባለቤት አመልካች (ንብረትን እና ባለ ንብረትን የሚያመለክት)

To see – saw = ማየት፣ ሃላፊ ጊዜ(አየሁ)

1ኛ መደብ/አካል = First person(s)

2ኛ መደብ/አካል = second person(s)

3ኛ መደቦች/አካል = Third Person(s)

 

ለዛሬው ከዚህ ላይ ይበቃናል

 

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ


Monday, August 3, 2020

Nouns/ስሞች

Noun and Parts of nouns/ ስሞች እና የስሞች አከፋፈል

Nouns/ ስም-ስሞች

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ ነው፤ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ይቀጥላል።

መጻሕፍቶቼን ከአማዞን ለመግዛት ይህንን ሊንክ ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ

https://amzn.to/3fqWcCs

ባለፈው በክፍል 5 የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ስለ ስምንቱ(8) የንግግርክፍሎች ባጭሩ የያንዳንዱን የስም ዓይነት ምንንነት አይተን ነበር። በመቀጠል የምናየው እያንዳንዱን በተናጠል ሲሆን ዛሬ በክፍል 6 ትምህርታችን ከ8ቱ አንዱ ስለ ሆነው ስለ ስም ሰፋ አድርገን በምሳሌ ጭምር እንማራለን ተከታተሉ።

ስለ ስም የሚከተሉትን ሦስት ነጥቦች እንማራለን

1ኛ ለመሆኑ ስም ምንድነው? (ስለ ስም ምንነት)

2ኛ የስም አከፋፈል (ስንት ዓይነት ክፍል አለው)

3ኛ ስም ከስምንቱ(8ቱ) የንግግር ክፍሎች መሠረታዊ ሥራው ምን መሆን ነው?

 

ማነኛውም ነገር መጀመሪያ በራሳችን ቋንቋ ግልጽ እንዲሆንልን ማድረግ አለብን፡ በራሳችን ቋንቋ ስያሜውን ማንነቱን፣ ሥራውን ወዘተ ያለምንም ጥርጥር ከተረዳን በእንግሊዘኛው አንድ ነገር ብቻ ነው ለማወቅ የሚጠበቅብን ይኸውም ምንድነው? ትርጉም።

1ኛ ለመሆኑ ስም ምንድነው? (ስም ምንነት)

What is a noun?

A Noun is a name of person, place, thing, feeling, and idea. =

ስም የሰው፣ የቦታ፣ የነገር፣ የስሜትና የሐሳብ መጠሪያ ነው። ስለዚህ ስም አንዱን ከሌላው ለመለየት የሚሰጥ ልዩ ስያሜ ነው፤ ስም ባይኖር አንዱን ከሌላው ለይቶ ማወቅ ስለማይቻል ነገሮች የተደበላለቁ ወይም የተሳከሩ ይሆኑ ነበር ማለት ነው።

 

2ኛ የስም አከፋፈል/parts of Noun (ስንት ዓይነት ክፍል አለው)

 

ስም በጣም ብዙ ዓይነት ክፍሎች ቢኖሩትም በሚከተሉት  አበይት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን፤ እነዚህም በአማርኛ

·        Concrete and Abstract Nouns/ ቁሳዊና መንፈሳዊ ስሞች

·        Common and Proper Nouns/ የወል እና የግል ስሞች

·        Countable and Uncontable Nouns /የሚቆጠሩና የማይቆጠሩ ስሞች

 

1.  Concrete Nouns: (ካንክሪት ናውንስ)

ካንክሪት ናውንስ የሚባሉት ለሚዳሰሱ ነገሮች የሚሰጡ ስያሜዎች ሲሆኑ

 

በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቶቻችን የሚገለጹ ናቸው ማለትም

በማየት፣ መንካት፣ ማሽተት፣ መቅመስ፣ መስማት የምንችላቸው ነገሮች ናቸው

Seen, touched, smell, taste, hear,

2.  abstract = አብስትራክት ናውን የሚባሉት ግን

የሐሣብ እና የስሜት ስሞች ሲሆኑ የማይዳሰሱ፣ የማይታዩ፣ የማይቀመሱ፣ የማይሸተቱ፣ እና የማሰሙ ናቸው። በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት የማይገለጹ ማለትም

የማይታዩ፣ የማይዳሰሱ፣ የማይቀመሱ፣የማይሸተቱ፣ እና የማይሰሙ ናቸው።

 

ምሳሌዎቹን እንመልከት

Example: 1 ለሚዳሰሱ ነገሮች

Ephrem likes to go to the park and see the birds.

 

ይህ ዐረፍተ ነገር  ወደ አማርኛ ሲመለስ

ኤፍሬም ወደ መናፈሻ መሄድና ወፎችንም ማየትን ይወዳል። ማለት ሲሆን በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ ሦስት ካንክሪት ወይም ቁሳውያን ስሞች አሉ፤ እነሱም “ኤፍሬም” የሰው ስም፤ “ፓርክ” የቦታ ስም፤ እና “በርድ” የእንስሳት ስም”

 

Example: 2 ለማይዳሰሱ ነገሮ

 

Love is one of the ten commandments (ከማንድመንትስ). Or “Honesty is the best Policy

 

ፍቅር ከዐሥሩ ትእዛዛት አንዱ ነው። ወይም “ሐቀኝነት እጅግ መልካሙ ሥርዓት ነው” ማለት ሲሆን በነዚህ ዐረፍተ ነገራት ዐራት የአብስትራክት ስሞች አሉ፤ እነሱም “ፍቅር” እና “ትእዛዛት” “ሐቀኝነት እና ሥርዓት” የሚባሉት ናቸው። ምክንያቱም ፍቅር እና ትእዛዝ የሚታይ፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፤ የሚሰማ፣ የሚቀመስ፣ ወይም የሚሸተት አይደለም።

 

3.  Common (ካመን ናውን)

Common nouns (ካመን ናውንስ) የሚባሉት የጋራ መጠሪያዎች ናቸው፤ እነዚህም ለምሳሌ

Human, man, woman, animals, plants, city, country, month, day/ሰው፣ ወንድ፣ ሴት፣ እንስሳት፣ እፀዋት፣ ከተማ፣ አገር፤ወር፣ ቀን፤ ወዘተ የሚባሉት ናቸው።

4.  Proper፡ ፕሮፐር ናውን፡ የግል መጠሪያ ወይም መጠሪያ ስም ማለት ነው

Proper nouns:(ፕሮፐር ናውንስ)

የሚባሉት ደግሞ የግል መጠሪያዎች ወይም ስያሜዎች ናቸው ለምሳሌ

Abera, Alemitu, Ethiopia, Addis ababa, January, and Friday/ አበራ፣ አለሚቱ፣ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣  ጥር፣ አርብ፣ የመሳሰሉት ናቸው።

5.  Collective and Group (ከለክቲብ ኤንድ ግሩፕ ናውንስ)

Collective noun:(ከለክቲብ ናውን)

ከለክቲብ ናውንስ እና ግሩፕ ተቀራራቢዎች ናቸው በተወሰነ ደረጃ ነው የሚለዩት

ብዙ ተጫዋቾች በአንድ ላይ Players/ፕለየርስ ይባላሉ፤(ግሩፕ) የፕለየሮቹ ስብስብ ደግሞ Team/“ቲም” ይባላል(ከለክቲብ)

Group noun: (ግሩፕ ናውን)

Employee/ኢምፕሎይ ማለት ሠራተኛ ማለት ሲሆን Employees/ “ኢምፕሎይስ” ለብዙ ሠራተኞች ማለት ነው፤ ስለዚህ Employees/“ኢምፕሎይስ” (ግሩፕ) ሲሆን “የኢምፕሎይስ” ስብስብ ደግሞ Staff/ “ስታፍ” ይባላል፤ ስለዚህ Staff/“ስታፍ” Collective noun/ “ኮለክቲብ ናውን” ይባላል።

6.  Countable (count- able) – Uncountable (un-count-able) (የሚቆጠር እና የማይቆጠር) “ካውንት” መቁጠር ሲሆን “አን” የሚለው ቃል “ኢ” ወይም አፍራሽ ነው።

Countable: የሚቆጠሩ ነገሮች ለምሳሌ

Book, pen, spoon, መጽሐፍ፣ ስክብሪቶ፣ ሹካ፣

Un-countable: የማይቆጠሩ ነገሮች ደግሞ ለምሳሌ፡

Water, air, sugar, milk /ውሀ፣ አየር፣ ሱካር፣ ወተት፣ ወዘተርፈ የሚባሉት ናቸው።

 

·         ስሞች በዐረፍተ ነገር ውስጥ መሠረታዊ ሥራቸው የዐረፍተ ነገር ባለቤት(subject) መሆን ነው። በተጨማሪ ደግሞ ተሳቢ(object)  እና ዘርፍም ይሆናሉ።

ከዚህ በታች ያሉትን ቃላት አጥኑ፡ ከዚህ በላይ ካለው ትምህርት ጋር የተያያዙ ናቸው።


·         Noun = ስም

·          Concrete =የሚዳሰስ(ቁስ ነገር)

·          Human = ሰው(ሰብአዊ ፍጡር)

·         Man = ወንድ (ሰው)

·         Woman = ሴት

·         Place = ቦታ

·         Thing = ነገር

·         Abstract = የማይዳሰስ)

·          Idea = ሐሣብ/ አመለካከት

·         Thought = ሐሣብ

·         To see = ማየት

·         To hear = መስማት

·         To smell = ማሽተት

·         To touch  መንካት

·         Common = የጋራ(የወል)

·          Proper = ትክክለኛ፣ ተገቢ

·          Proper noun = የግል መጠሪያ

·         Collective = ስብስብ

·         Group = ግሩፕ/አንድነት

·         Team = ግሩፕ

·          Employee = ሠራተኛ(ተቀጥሮ የሚሠራ)

·         To count = መቍጠር

·         Able = መቻል

·         Un = ኢ

·          Suffix = ድኅር (ከቃል መጨረሻ ላይ የሚገባ)

·         Prefix = ቅድም/መቅድም (ከቃል መጀመሪያ ላይ የሚገባ ቀዳሜ ቃል)

 

 

 Pronoun/ፕሮ ናውን ማለት ምን ማለት ነው?

መጻሕፍት ለመግዛት ይህንን ይጫኑ ወይም በ +1 703 254 6601 ደውሉ 



Pronouns

 

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው፤

በዛሬው በክፍል 7 የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን የምንማረው ከ8ቱ የንግግር ክፍሎች በሁለተኛ ደረጃ የጠቀስነውን Pronoun/ፕሮናውን የተባለውን ርእስ ነው።  Pronouns/ፕሮናውንስ የሚባሉት በጣም ብዙ ዓይነት ናቸው እኛ ግና ለጊዜው የተወሰኑትን ብቻ ነው የምንማረው። በመጀመሪያ

 

·         Pronoun/ፕሮ ናውን ማለት ምን ማለት ነው?

·         የፕሮናውን ሥራ ምንድ ነው?

·         ፕሮ ናውን ስንት ዓይነት ነው?

 

የሚሉትን ሦስት መሠረታውያን ጥያቄዎች ከመለስን በኋላ Pronouns/ፕሮ ናውንስ በተግባር በዐረፍተ ነገር ሲገቡ ምን እንደሚመስሉ አንድ በአንድ እንማራለን። መልካም ትምህርት።

 

Pronoun/ፕሮናውን ምን ማለት ነው፡ (ስያሜን የሚመለከት ማብራርያ)

Pronoun: A word that replaces a noun in a sentences or takes the place of noun in a sentence. = ፕሮ ናውን የሚባለው በዐረፍተ ነገር ውስጥ ስምን ተክቶ የሚገባ ወይም የስምን ቦታ የሚይዝ ነው

 

ባለፈው በክፍል 6 ትምህርታችን Noun/“ናውን” ማለት “ስም” ማለት እንደሆነና የተለያዩ የስም ዓይነቶችን በመጥቀስ ተምረን ነበር።

ስለዚህ የዛሬው ደግሞ Pro/“ፕሮ” የሚለውን Prefix/ “ፕሪፊሽ” ከማስቀድሙ በስተቀር Noun/“ናውን” የሚለው ስያሜ አይቀየርም፤ Pro/ፕሮ የሚለው ተቀጽላ ስላለ ግን ለየት ያለ ማብራርያን እሰጣለሁ ።

 

·         Pro/ፕሮ = ምትክ/ፈንታ

·         Noun/ናውን = ስም

·         ስለዚህ በአንድ ላይ Pronoun/“ፕሮ ናውን” ወይም በብዙ Pronouns/“ፕሮናውንስ” = በስም ፈንታ ወይም ምትክ ማለት ይሆናል።  በግእዝ “ተውላጠ ስም” በአማርኛ “የስም ተለዋጮች” የሚባሉት ሲሆኑ  ስምን ወይም ስሞችን ተክተው የሚገቡ ናቸው። በእንግሊዘኛው “in place of noun” ማለት ነው። ይህም ማለት በስም ምትክ ማለት ነው።(በስም ምትክ የሚገቡ ለማለት ነው)

 

 

የፕሮ ናውንስ ሥራ ምንድነው? (የሚሠጡትን አገልግሎት የሚመለከት)

 

ፕሮናውንስ ሥራቸው በስም ምትክ መግባትና ስም የሚሠራውን መሥራት ነው። (The word that replaces noun in sentence is called “pronoun”) በዐረፍተ ነገር ውስጥ ስምን የሚተካ ቃል ፕሮናውን ይባላል። ስለዚህ ፕሮናውንን ወይም ተውላጠ ስሞችን መቸና እንዴት እንደ ምንጠቀም በሚከተሉት ምሳሌዎች እንመልከት።

 

ምሳሌ፡ በመጀመሪያ በአማርኛ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው በትክክል ሊገባን ይገባል፤ ስለዚህ በመጀመሪያ በእንግሊዘኛ ዐረፍተ ነገር ከመሥራታችን በፊት በአማርኛ እናያለን።

·         አበራ ከአልማዝ ጋር ይሠራል

·         አበራ ከአልማዝ ጋር መሥራት ይወዳል

·         አበራ እና አልማዝ አብረው መሥራት ይወዳሉ። በነዚህ ሦስት ዐረፍተ ነገራት ሁለት ስሞች አሉ ስሞቹ 6 ጊዜ ተደጋግመው ተጠቅሰዋል። ስለዚህ የስሞች መደጋገም ደግሞ ንግግርን የማይማርክ  ወይም አሰልች ያደርጋል። በመሆኑም ድግግሞሺን ለማስቀረት “ተውላጠ ስሞችን” መጠቀም አለብን።

 

አበራ ከአልማዝ ጋር ይሠራል፤

እሱ እርሷ ጋር መሥራትን ይወዳል፤

እነሱ አብረው መሥራት ይወዳሉ።


አሁን የፕሮናውንን ወይም የስም ተለዋጮችን ሥራ አስተውሉ፤ አበራ ከአልማዝ ጋር ይሠራል ካልን በኋላ እንደ ገና ተመሳሳይ ስሞችን ከመደጋገም ማለትም “አበራ” በማለት ፈንታ “እሱ” “አልማዝ” በማለት ፈንታ “እርሷ”፣ አበራና አልማዝ በማለት ፈንታ “እነሱ” የሚባሉትን ተውላጠ አስማት ወይም የስም ተለዋጮች በመጠቀም 1ኛ ስማቸውን ከመደጋገምና አስልች ድግግሞሽ ከማድረግ ተቆጠብን፤ ሁለተኛ 4 ቃላትን (አበራና አልማዝን ሁለት ጊዜ) ከመጻፍ “እሱ” “እሷ” “እነሱ” በሚሉት ቃላት በማጠቃለል ወረቀትና ጊዜን መቆጠብ ቻልን ማለት ነው።

 

እነዚህ ሦስት ከላይ የሠራናቸው ዐረፍተ ነገራት በእንግሊዘኛ ደግሞ እንደሚከተለው ይቀመጣሉ።

·         Abera works with Almaz (አበራ ወርክስ ዊዝ አልማዝ)

·         Abera likes working with Almaz(አበራ ላይክስ ወርኪንግ ዊዝ አልማዝ)

·         Abera and Almaz like working together (አበራ ኤንድ አልማዝ ላይክ ወርኪንግ ትጌዘር)

 

አሁንም ከላይ በአማርኛው እንዳየነው በሦስቱም የእንግሊዘኛ ዐረፍተ ነገራት የተደጋገሙ ስሞች አሉ። ስለዚህ ዐረፍተ ነገሩ የማይስብና የሚያሰለች ድግግሞሽ እንዳይሆን “ተውላጠ ስሞችን/ፕሮናውንን እንጠቀማለን” ስለዚህ.

 

·         Abera works with Almaz.

·         He likes working with her.

·         They like working together.

 

በመሆኑም ተውላጠ ስሞችን የምንጠቀመው አንደኛ የስሞች ድግግሞሽን ለመቀነስና ዐረፍተ ነገሩን ማራኪ የማይሰለች ለማድረግ፤ ሁለተኛ ደግሞ ስም መጥራት የማንፈልግ ከሆነ ተውላጠ ስሞችን እንጠቀማለን። ተውላጠ ስሞችን በመጠቀም ወረቀትና ጊዜን መቆጠብ እንደምንችልም አትዘንጉ

 

ፕሮናውንስ ስንት ዓይነት ነው/ናቸው?(አከፋፈላቸውን የሚመለከት)

 

ከላይ ስጀምር እንደነገርኳችሁ pronouns/ፕሮናውንስ የሚባሉት ብዙ ዓይነት ናቸው ለምሳሌ

1.   Personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ

2.   Relative pronous/ረለቲብ ፕሮናውንስ

3.   Reflexive pronouns/ረፍለክሲብ ፕሮናውንስ

4.   Interrogative pronouns/ኢንተሮጌቲብ ፕሮናውንስ

ወዘተርፈ ይገኙበታል።

 ለዛሬው የመጀመሪያውን “ፐርሰናል ፕሮናውን” የሚባለውን እንማራለን ማለት ነው።

 

Personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውን/ ሰብአዊ ወይም አካላዊ የስም ተለዋጮች

ፐርሰናል ፕሮናውን “ፐርሰን” ማለት ሰው ወይም አካል ማለት ሲሆን “ፐርሰናል ፕሮናውን” የሚለው = ሰብአዊ ወይም አካላዊ ተውላጠስም ማለት ነው። ፐርሰናል ፕሮናውኖች ለሰዎች እና ለቤት እንሥሳት የምንጠቀምባቸው ናቸው። በሦስት አበይት ክፍሎች ይከፈላሉ። እነሱም የዐረፍተ ነገር ባለቤቶች፣ ተሳቢዎች፣ እና ባለቤትነትን የሚያመለክቱ ተውላጠ ስሞች ይባላሉ በእንግሊዘኛው እንደሚከተለው ይገለጻሉ።

·         Subjective pronouns/ባለቤት የሚሆኑ ተውላጠ ስሞች

·         Objective pronouns and /ተሳቢ የሚሆኑ ተውላጠ ስሞች እና

·         Possessive pronouns/ ባለቤትነትን የሚያመለክቱ ተውላጠ ስሞች

የሚባሉት ሲሆኑ በሚቀጥለው በክፍል 8 ትምህርታችን እያንዳንዳቸውን በተናጠል በምሳሌ እንመለከታለን።

Words in this video to be learned/ በዚህ ቪድዮ ውስጥ የሚገኙ መጠናት ያለባቸው ቃላት

·         Pronoun = የስም ተለዋጭ

·         Subject = ባለበት/የዐረፍተ ነገር ባለቤት

·         Object = ተሳቢ ወይም ተደራጊ

·         Possessive = አመልካች(ባለቤትነትን፤ባለንብረትነትን የሚያመለክት)

·         Person = ሰው/አካላዊ ሰው

·         Relative = ተዛማጅ/ዘመድ

·         Reflexive = መልሶ የሚያንጸባርቅ/ወደራሱ የሚያመለክት

·         Interrogative = መጠየቂያ/መመርመሪያ

·         To like = መውደድ

·         To work = መሥራት(ግስ)

·         Working =መሥራት(ስም ከ አር፣ ወይም ኢዝ ከሚባሉት ግሶች ጋር ግስ የሚሆንበትም ጊዜ አለ)

·         With = ጋር ወይም ጋራ/አብሮ..

·         He = እሱ

·         She = እሷ

·         Her = እሷን/የሷ..

·         They = እነሱ

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ