Wednesday, March 21, 2018

Learn Geez Through WhatsApp Group

በአውደ ጥናት ዘግእዝ የሚሰጡ የግእዝ ቋንቋ የትምህርት ደረጃዎችና ይዘታቸው


















በአውደ ጥናት ዘግእዝ የሚሰጡ የግእዝ ቋንቋ የትምህርት ደረጃዎችና ይዘታቸው
አውደ ጥናት ዘግእዝ ክፍል ፩ዱ ለወጣንያን(ለጀማሪ)
1.   ፊደልና ስለ ፊደላት አከፋፈል - ድምጽ- ከግእዝ እስከ ሣብዕ በደንብ ግንዛቤን መስጠት
2.   አጫጭር ዐ/ነገራትን በሚከተሉት አርእስት መሠረት የሰላምታ ቃላትና  አጠቃቀማቸው
3.   ደቂቅ አገባቦችን ትርጉማቸውና እና በዐ/ነገር እያስገቡ ማሳየት
4.   የመጠየቂያ ቃላትንና አጠቃቀማቸውን በአጫጭር ዐ/ነገር
5.   የሁለት ቃላትን አነባበብ ለምሳሌ (ሙያንና ባለ ሙያን በማያያዝ የአንድን ሰው ችሎታ ወይም ሙያ መናገር መምህር (ባለ ሙያ) ግእዝ (ሙያ)
6.   አሥሩ መራሕያን እና አጠቃቀማቸው
7.   የግሥ ርባታ ከአቢይ አንቀጽ እስከ ንዑስ አንቀጽ
8.   ቁጥር ከ1 እስከ 19 ያሉ የግእዝን ቁጥሮች
9.   የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል

አውደ ጥናት ዘግእዝ  ማዕከላውያን(ለመካከለኛ)፡
1.   ስምንቱ የንግግር ክፍሎች
2.   ግሥና የግሥ አወራረድ ከንኡስ አንቀጽ እስከ መጨረሻው
3.   ግልጽ የሆኑ(ግልጠ ዘ) ቅጽሎች
4.   ተውላጠ ግሥ
5.   ከግሥ የሚወጡ ዘሮች
6.   ባለቤት፤ ማሠሪያ አንቀ፤ ቅጽል፤ እና ተውሳከ ግሥ ያላቸው ዐ/ነገራትን መፍጠር
7.   የዐ/ነገራትን አካላትና ሙያ ማወቅ
8.   ደቂቅ አገባቦችን ማወቅ
9.   የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል

አውደ ጥናት ዘግእዝ  ፍፁማን(ለከፍተኛ)፡
1.   አገባቦችና አጠቃቀማችው
2.   8ቱ  መራኁት
3.   8ቱ  አርእስት
4.   50ው ሠራዊት
5.   4ቱ  አዕማድ
6.   4ቱ  አሥራው
7.   4ቱ  ፀዋትው
8.   ጽሁፎችን ከግእዝ ወደ አማርኛ መተርጎም እና የሥነ ጽሁፍ ልምምድ
9.   የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መ/ር መላኩ ነኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

ስለ ትምህርት አሰጣጡና አጠቃላይ ማብራርያ የሚከተለውን ቪድዮ ያዳምጡ

ተጨማሪ ማብራርያ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

ልዑል እግዚአብሔር ለዚች ቅጽበት በሰላም ጠብቆ ስላደረሰን የተመሰገነ ይሁን።

የግእዝ ቋንቋ ተከታታይ ትምህርታችን ታህሣስ አንድ ቀን (ታህሣስ 10 በፈረንጆች) ይጀመራል። ስለዚህ ከዚያ በፊት ምዝገባና ክፍያችሁን ማጠናቀቅ አለባችሁ። ክፍያውን እስከ ህዳር 30 (ታህሣስ 9 በፈረንጆች) ትከፍሉና ክፍያው የሚያዝላችሁ ግን ከጥር 1 ቀን በፈረንጆች ጀምሮ ለአንድ ዓመት ነው፤ ስለዚህ ከጥር በፊት ያለው አንድ ወር ነጻ ነው ማለት ነው።

በትምህርቱ የተመዘገባችሁት አብዛኛዎቻችሁ ሁላችሁም ማለት ይቻላል “በጀማሪ” ደረጃ ነው። ስለዚህ ሁለት ሰዎች ቢሆኑ ነው በመካከለኛ ደረጃ ያሉት፤ በከፍተኛ ያለ ግን የለም።

የራሴን አስተያየት ለመስጠት ያህል ከመጀመሪያው መጀመሩ በጣም የተሻለ ነው። ምክንያቱም መሠረቱን ማጥበቁ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ከመጀመሪያው እንጀምራለን፤ መጀመሪያው ደግሞ ፊደል ስለሆነ ከፊደል ነው የምንጀምረው፤ ምን አልባት ፊደል ሁሉም የሚያውቀውና ስለፊደል መማር መደጋገም መስሎ ሊታየን ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን ብዙ የማናውቀውና የጎደለብን ነገር ያለ የማይመስለን ብዙ ሊናውቀው የሚገባ ትምህርት በፊደሎች ውስጥ አለ። በተለይ ለግእዝ ትምህርት ስለፊደላት ሁለንተና በቃል ጭምር ማወቅና መያዝ በጣም ወሳኝ ነው። ስለዚህ የምናውቀው ነው ብላችሁ ሳትዘናጉ መከታተል ይኖርባችሁዋል።

ግሩፑን አንድ ግሩፕ ለጀማሪዎች አድርገን እንጀምረውና እንቀጥላለን ማለትም ክፍል አንድ የሚቀላችሁ ካላችሁ ለመካከለኞች ግሩፕ መክፈት ይቻላል፤ ክፍተኛም ካለ እንደዚሁ በሂደት ይሆናል። ትምህርቱ ለየት ባለና ጠለቅ ባለመልኩ በያንዳንዱ ንዑስ ርእስ ጭምር የልምምድ ጥያቄዎችን በመሥራት የሚሰጥና ቀላል፤ግልጽና በቂ ዕውቀትን የሚያስጨብጥ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ።

 ከናንተ የሚጠበቀው የሚሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ መተግበር ነው። ይህ ትምህርት በተለይ የትምህርቱ የማስተማር ስልት በየትም ቦታ ሊታገኙት እንደማትችሉ ምንም አያጠራጥርም። ይህ ማላት ባለሙያዎች የሉም ማለት ሳይሆን 1ኛ ያለውን ትንሺም ሆነ ብዙ ለሌሎች የማስተላለፉ ዘዴና ችሎታ የያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር የየግል ልዩ ስጦታ ነው። 2ኛው ደግሞ የቦታ፤የጊዜ፤ እና የዘመናዊ መሣሪያዎች አመች ሆነው መገኘታቸውም ሌላው ምክንያት ነው። ስለዚህ እነዚህን ሁሉ እግዚአብሔር ስላመቻቸልን እድሉን መጠቀም የያንዳንዳችን ድርሻ ነው።

የሚሰጠው የትምህርት ንድፍ የሚከተለውን ይመስላል

ለአንድ ዓመት ሰፋ ባለመልኩ የሚሰጡት አበይት የትምህርት ዓይነቶች በዘጠኝ ንዑሳን ክፍሎች የተከፈሉ ሲሆኑ የሚከተሉት ናቸው። (በጣም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ቃላትና ትምህርቶች/ዐ/ነገራት የበለጠ ግልጽ እንዲሆንላችሁና ተጨማሪ ዕውቀትንም ታገኙ ዘንድ ዓለም አቀፍ በሆነው በእንግሊዘኛም እንዴት እንደሚተረጎሙ እንነጋገራለን እንማራለን ይህም እንግሊዘኛን ለሚማሩ ተጨማሪ ጥቅም ነው)

1.   ፊደልና ስለፊደል በሚለው ንዑስ ርእስ
·         ደል ማለት ምን ማለት እንደሆነ እስከ መነሻው፤ ታሪክን ጨምሮ፤ ፊደል የሚጠራባቸው ልዩ ልዩ ስሞች፤ የግል፤የወል፤የደረጃ፤ ወዘተ ስያሜዎች፤ ዓይነት፤ ድምጽ፤ መኩሸ ፊደላትና የሚለያዩባቸው፤ የሚዋሃዱባቸው፤
·         ከፊደላት ውስጥ ከፊደልነት ሥራቸው ሌላ አገልግሎትን የሚሰጡ ፊደላትን አዲስ እና ልዩ በሆነ የአውደ ጥናት ብቻ የማስተማር ዘዴ ለይተን እንማራለን፤(ለበወ) እንዲሁም ሌሎች ከፊደላት ጋር የተያያዙ ዕውቀቶች በጥልቀት ይተነተናሉ።
·         በያንዳንዱ ንዑስ ርእስ የግንዛቤ ጥያቄ ዎች ይሰጣሉ

2.   አጫጭር ዐ/ነገራትን በሚከተሉት አርእስት መሠረት የሰላምታ ቃላትና  አጠቃቀማቸው
·         የሰላምታ ቃላትን መሠረት በማድረግ ልዩ ልዩ ትርጉሞ ያላቸውን ዐ/ነገራት መሥራት
·         ስለራሳችን ማንነት እና ታሪክ ባጭሩ መናገር እና መጻፍ
·         በምንማራቸው ዐ/ነገራት የምንጠቀምባቸውን ቃላት ትርጉም ማወቅ
·         በዐ/ነገራቱ ውስጥ የሚገኙትን ቃላትና የሥራ ድርሻቸውን ማወቅ
3.   ደቂቅ አገባቦችን ትርጉማቸውና እና በዐ/ነገር እያስገቡ ማሳየት
·         ደቂቅ አገባብ ምን ማለት እንደ ሆነ፤ አገልግሎትና ትርጉም
·         መቸና እንዴት ደቂቅ አገባቦችን እንደምንጠቀም ልዩ ልዩ ዐ/ነገራትን በመሥራት ልምምድ ማድረግ
4.   የመጠየቂያ ቃላትንና አጠቃቀማቸውን በአጫጭር ዐ/ነገር
·         የመጠየቂያ ቃላትን ትርጉም እና አጠቃቀም በዐ/ነገራት በማስገባት
·         ቦታን የሚመለከት
·         ጊዜን የሚመለከት
·         ርቀትን የሚመለከት
·         ቁጥርን የሚመለከት ወዘተ በመከፋፈል በሰፊው ልምምድ ማድረግ

5.   የሁለት ቃላትን አነባበብ ለምሳሌ (ሙያንና ባለ ሙያን በማያያዝ የአንድን ሰው ችሎታ ወይም ሙያ መናገር መምህር (ባለ ሙያ) ግእዝ (ሙያ)
·         በግእዝ ቁዋንቋ ህግ ሁለት ቃላት እንዴት ይያያዛሉ(ይናበባሉ)፤ ለምን ይናበባሉ፤
·         ሁለት ቃላትን ለማያያዝ የሚጠቅሙን ፊደላት፤
·         ሁለት ቃላትን በማያያዝ የሚገኙ ጥቅሞች
·         ሙያን፤ ባለሙያን፤ ወይም ሐብትን፤ እና ባለሐብትን ወዘተ እንዴት ማወቅ እንደሚቻል
·         ለምሣሌ፤ የክርስትና ስሞችን፤ የትምህርት ዓይነቶችን፤ ወዘተ ምሣሌ በማድረግ በሰፊው መነጋገር
6.   አሥሩ መራሕያን እና አጠቃቀማቸው
·         መራሕያን ስምና ትርጉም፤ ብዛትና ከሌሎች ቁዋንቁዋዎች ጋር ንፅጽር
·         አሥሩ መራህያን የሥነ ጽሁፍ ሁሉ መሠረቶች ስለሆኑ ሙሉ በሙሉ በቃል ጭምር መያዝ አለባቸው። ስለዚህ በግእዝ፤ በአማርኛ፤ እንዲሁም በእንግሊዘኛ ይብራራሉ።
·         ለምን ስሞችን ትተን ተውላጠ ስሞችን እንደምንጠቀም፤ መቸ እንደምንጠቀም፤ በተግባር በዐ/ነገር በሰፊው እናያለን፤
·         በአሥሩም ተውላጠ ስሞች ልዩ ልዩ ምሳሌዎችን መሥራት
7.   የግሥ ርባታ ከአቢይ አንቀጽ እስከ ንዑስ አንቀጽ
·         ግሥ/አንቀጽ ስያሜ፤ ምድብና ሥራ
·         ሐላፊ ግሥ/አንቀጽ
·         ትንቢት ግሥ/አንቀጽ
·         ዘንድ ግሥ/አንቀጽ
·         ንዑስ ግሥ/አንቀጽ
·         ከሃላፊ እስከ ንዑስ ያሉትን አናቅጽ በዐ/ነገራት እያስገባን በምሣሌ ማስረዳት
8. ቁጥር ከ1 እስከ 19 ያሉ የግእዝን ቁጥሮች
·         ቁጥር ትርጉምና ምድብ
·         ከ1 እስከ 10 ያሉ ቁጥሮች
·         ከ11 እስከ 19 ያሉ ቁጥሮች
·         ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መሠረታውያን ቁጥሮች በልምምድ ማስረዳት
·         ከቁጥር ጋር የተያያዙ አርእስትን ለምሣሌ የሣምንቱ ቀናትን፤ ከግእዝ እስከ ሳብእ ያሉ ሆሄያትን መዳሰስ

9. የልምምድ ውይይት በተማሪዎች መካከል
·         ትምህርቱ ከተጀመረ ከ2 ወራት በሁዋላ ተማሪዎች በውይይት ግሩፕ እርስ በርሳቸው ይወያያሉ፤ ጥያቄ ይጠያየቃሉ፤ መልስ ይሰጣጣሉ፤ መጨረሻ ላይ እኔ አየውና ማስተካከያ እሰጣለሁ።

የትምህርቱ መተላለፊያ መንገዶች

ትምህርቱ በድምጽ፤በጽሁፍና በቪዲዮም ይሰጣል እስካሁን በአውደ ጥናት ይሰጡ የነበሩት የግእዝ ትምህርቶች በአውደ ጥናት ዘግእዝ ቻናል ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህ ቪዲዮዎች ለሁሉም ሰው ነጻ ናቸው። ከአሁን በኁዋላ የሚለቀቁ ቪዲዮዎችም ግሩፑ እንዳይጨናነቅ የሚለቀቁት ወደአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው። ነገር ግን እየከፈሉ የሚማሩ ተማሪዎች ብቻ ሊንክ እየተላከላቸው የሚገኙ እንጂ ለሁሉም የሚታዩ አይደሉም (ፕራይቤት ይሆናሉ)፡ (አልፎ አልፎ ነጻ ትምህርቶችም ስለሚኖሩ) ስለዚህ ሁላችሁም እስካሁን የተለቀቁትን በነጻ ለመከታተል አዲስ የሚለቀቁትንም ለማየት በአውደ ጥናት ዘግእዝ  ሰብስክራይብ አድርጉ
ትምህርት የሚለቀቅባቸው ቀናትና የሚለቀቀው ትምህርት፡
ትምህርቱ የሚለቀቅባቸው ቀናት (አርብና ለቅዳሜና ሰኞ ለማክሰኞ ነው ግን ሰዓቱ እንደየ አገራቱ ይለያያል)
አንድን ትምህርት በሚገባ ለመማርና እውቀቱን ይዞ ለመውጣት ጊዜ ወሳኝ ነው ማለትም ትምህርቱን ደጋግመን ለማጥናት ጊዜ ማግኘት ግድ ነው። ስለዚህ አንዱ ትምህርት በሌላው ላይ መደራረብ ሳይኖር አንዱን አሸንፈን ወደ ቀጣዩ መራመድ አለብን በመሆኑም በሳምንት 2 ጊዜ ትምህርት ይለቀቃል አንዱ ትምህርቱ ነው፣ ሁለተኛው የጥያቄዎች ማብራርያና መልስ ነው። ስለዚህ
·          አንዱ ትምህርቱ ተዘጋጅቶ በድምጽ ይለቀቃል (ተማሪዎች ግን ባላቸው ጊዜያት ሁሉ እየመላለሱ መስማትና ማጥናት አለባቸው)
·         ሁለተኛ የሚለቀቀው ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራርያና መልስ ነው
·         በግል ማብራርያ የሚፈልግና የበለጠ ርዳታ የሚፈልግ ማነኛውም ተማሪ በውስጥ መስመር ሊያነጋግረኝ ይችላል፤ ከቻልሁ ወዲያውኑ እመልሳለሁ ካልቻልኩ ግን መልእክታችሁን ወይም ጥያቂያችሁን ብታስቀምጡ መልሱን ይዠ አነጋግራችሁዋለሁ። ማንም ተማሪ ትምህርቱ ከብዶት፤አልገባው ብሎ የሚቀር አይኖርም።

ክፍያና የክፍያ ሁኔታ
ክፍያው ከዚህ በፊትም ደጋግሜ ገልጨዋለሁ።
·         በኢትዮጵያ ለሚኖሩ 2000(ሁለት ሺህ) በዓመት
·         በአረብ አገራት ለሚኖሩ 3000(ሦስት ሺህ ብር ወይም 125 ዶላር) ባመት
·         በአሜሪካና በሌሎች የአውሮፓና እስያ አገሮች 200(ሁለት መቶ ዶላር) ባመት

አከፋፈል
·         በባንክ የቁጠባ ሂሣብ ቀጥታ የሚያስገቡ ሰዎች ወደ ባንክ ያስገቡበትን ደረሰኝ በስልካቸው ፎቶ አንስተው ለእኔ (በዋትስ አፕ ይልኩልኛል)ደረሰኙ ሲደርሰኝ መክፈላቸውን እመዘገባለሁ ለነሱም ደረሰኙን መቀበሌን መልሸ እጽፍላቸዋለሁ
·         በዌስተርን ዩኒየን(በኃዋላ) መላክ የሚፈልጉ ቀጥታ በስሜ ስለሚልኩት ከደረሰኝ በሁዋላ ከፍለዋል ብየ እመዘግባለሁ ለነሱም ገንዘቡን መቀበሌ ወደ ስልካቸው መልእክት እልክላቸዋለሁ።
·         በአካል የሚከፍሉም ከተቀበልኩ በሁዋላ እንዳይረሻ ወደ ስልካቸው ለመክፈላቸው ማረጋገጫ መልእክት እልክላቸዋለሁ።
የግሩፑ ሕግ
አንድ አስተማሪ የሚያውቀውን ሁሉ ለተማሪዎች የሚያስተምር ወይም የሚናገር ከሆነ አስተማሪ አይባልም አስተማሪ ማለት መጥኖ፤ ለክቶ፤ በሚያስተምራቸው ተማሪዎች ደረጃና መጠን እያዘጋጀ ነው ማስተማር ያለበት፤ የሚያውቀውን ሁሉ ከተናገረ፤ ለአንደኛ ክፍል ተማሪዎች የስድስተኛ ክፍል ትምህርትን ቀላቅሎ የሚናገር ከሆነ ተማሪዎችን ግራ በማጋባት መስመር ያስታቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም።

ስለዚህ በተማሪዎች መጠን የተዘጋጀውን ትምህርት ብቻ ለማስተማር በአስተማሪው ብቻ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ ትምህርቶች ብቻ በአስተማሪው በኩል ይለቀቃሉ:
·         በግሩፑ ውስጥ ከአስተማሪ በስተቀር ማንም ሰው፤ ምንም ነገር፤ መንፈሳዊም፤ ሥጋዊም፤ ስለ ግእዝ ትምህርትም ቢሆን ወደ ግሩፑ መልቀቅ አይችልም።

በተረፈግን የግእዝን ትምህርት በሚገባ ማንበብ መጻፍና መናገርም እንድትችሉ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መ/ር መላኩ ነኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው