Wednesday, June 21, 2017

ልሣነ ግእዝ ፈተና 1


የክፍል አንድ ማጠቃለያ የመመዘኛ ፈተና 1


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው። “ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” በሚለው የግእዝ ቋንቋ ትምህርታችን ይህ የዛሬው ክፍል አሥራ አንድ ነው። በክፍል 11 ደግሞ ምዕራፍ ሁለት “የንግግር ክፍሎች” የሚለውን ምዕራፍ እንጀምራለን ብየ ነበር ግን በያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ የመመዘኛ ጥያቄዎችን ማዘጋጀቱ የሚሰጠው ትምህርት ምን ያህል እንደገባችሁ ራሳችሁን ለመመርመር ይረዳችኋል ብየ ስላመንኩ ይህንን ክፍል አሥራ አንድ ትምህርታችንን የመመዘኛ ጥያቄዎችን እንድንሠራ 50 ጥያቄዎችን አዘጋጀሁላችሁ ማለት ነው።
በዚህ ምክንያት፤ ክፍል 12ም ለክፍል 11 ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበት ነው የሚሆነው።  በመሆኑም የምዕራፍ 2 መጀመሪያ የሚሆነው ክፍል 13 ነው።
ጥያቄዎቹ 50 ናቸው፤ እያንዳንዱ ጥያቄ ሁለት፤ሁለት ነጥብ ወይም ማርክ ስላለው ከመቶ የሚወሰድ ነው። አንድ ተማሪ ከመቶ 70ውን/70% ከመለሰ ትምህርቱን እንዳለፈ ይቆጠራል።
ጥያቄዎቹን ለመመለስ ሁለት ሣምንታትን እሰጣችኋለሁ ከዚያ በኋላ ቪዲዮውን አንድ ሺ ሰዎች ካዩት በኋላ የጥያቄዎቹ ሙሉ መልስ በክፍል 12 ዝግጅት ይሰጣል።
የጥያቄዎቹን መልሶች በሦስት መንገዶች መመለስ ትችላላችሁ
1.      ከዚሁ ቪዲዮ ስር በኮሜንት ወይም በአስተያየት መስጫ ቦታ መልሶቹን መጻፍ
2.     learngeez@outlook.com በሚለው ኢሜይል በኩል ወይም
3.     በቪዲዮ አዘጋጅታችሁም መልሳችሁን መላክ ትችላላችሁ መልካም ፈተና!
ሌላው፡
የግእዝ መማሪያ መጽሐፉን ግዙ ምክንያቱም መጽሐፉ የታተመው ለናንተ ነው። 1ኛ እናንተ ትምህርቱን የምትማሩበት ነው፤ ግእዝን ከአውደ ጥናት ለማወቅ ሙሉ ፍላጎት ካላችሁ መጽሐፉን መግዛት ግድ ነው።
የመጽሐፉ መሸጥ ለኔም ትምህርቱን በተሻለ መንገድ ለማስተማር፤ በተሻለ የድምጽ መቅረጫ፤ በተሻለ የቪዲዮ ካሜራ ትምህርቱን ለማዘጋጀት ይረዳኛል።
እኔ ትምህርቱን የማስተምራችሁ በበጎ ፈቃድ በነጻ ነው ስለዚህ ቢያንስ ትምህርቱ የምትማሩበትን መጽሐፍ ሳዘጋጅላችሁ ሁላችሁም መጽሐፉን መግዛት ይጠበቅባችኋል ብየ አምናለሁ።
ስለዚህ በዚህ እኔ በምኖርበት በሰሜን አሜሪካ ለምትኖሩ ሰዎች መጽሐፉን ለማግኘት በጣም ቀላል ነው፤ ምክንያቱም ከአማዞን ብትገዙ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ መጽሐፉ በፖስታ ይደርሳችኋል። ወይም ከእኔ በአካል መግዛትም ትችላላችሁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የምትኖሩና በአውሮፓ በእስያ፤ በሌሎችም አገሮች እየኖራችሁ በኢትዮጵያ በኩል መጽሐፉን ማግኘት ለምትፈልጉ መጽሐፉን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ዝግጁ ነኝ። ከዚህ በፊት ወደ አዲስ አበባ ተልኮ የነበረው  ትሽጦ ስላለቀ አሁን ወደ አዲስ አበባ እንዲላክላችሁ የምትፈልጉ ሁሉ በሚከተሉት መንገዶች ስማችሁን፤ የስልክ ቁጥራችሁን(የአዲስ አበባ)፤ እና የምትፈልጉትን የመጻሕፍት ብዛት በመናገር ከአሁኑ ተመዝገቡ ከዚያ በኋላ በሚፈልገው ሰው ልክ መላክ ይቻላል።
0911 866346
703 254 6601 ወይም
 learngeez@outlook.com 

መጽሐፉን ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ

Lisane Geez Yegara Quanquachin


ሌላው ጥያቄን በተመለከተ ነው ፤
ካለኘ የጊዜ እጥረት የተነሣ የምቀበለው ጥያቄ ግእዝን የሚመለከትና በማስተምራችሁ ትምህርት መሠረት ላይ የተመሠረተ ብቻ ሲሆን ነው። ከሌላ ቦታ በማምጣት ከቃላት፤ከዐረፍተ ነገራትም አልፎ በገጽ የሚለካ ጽሁፍ ተርጉምልን የምትሉ ወይም የተለያዩ የእምነት ጥያቄዎችን የምትጠይቁም አላችሁ። እውነቱን ለመናገር ለኔ የማስተምራችሁ የግእዝ ትምህርት በቂ ነው። ሌላውን ደግሞ በአካባቢያችሁ የሚገኙ መምህራንን ብትጠይቁ ለናንተም በአካል መረዳቱ መልካም ነው። ወይም እምነትን በተመለከተ በአውደ ጥናት ያስተላለፍኳቸው ልዩ፤ ልዩ ዝግጅቶች አሉ እነሱን በመመልከት ጥያቄዎቻችሁ ሊመለሱ ይችላሉ ብየ አምናለሁ ። በአውደ ጥናት ውስጥ ከሚገኙት አርእስት መካከል
·         ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ
·         የዘመን አቋጣጠር ታሪክና ልዩነት በዓለም ዙሪያ
·         ይህንን ያውቃሉ
·         ምን ማለት ነው
·         ፍትሐ ነገሥት
የሚሉትና ሌሎችም ናቸው እና እነዚህን ተመልከቱ ጥያቄዎቻችሁን በነዚሁ አርእስት ውስጥ ልታገኙ ትችላላችሁ።
ጥ፡1-14 የቃላት ትርጉም፦የሚከተሉትን ቃላት ወደ አማርኛ ቋንቋ ቀይሩ።
1.      “ስባሔ”  ማለት ምን ማለት ነው?
2.      “እመ” ማለት ምን ማለት ነው?
3.     “ኅየንተ” ማለት ምን ማለት ነው?
4.     “ቦ” ማለት ምን ማለት ነው?
5.     “ቢጽ” ማለት ምን ማለት ነው?
6.     “ዮም” ማለት ምን ማለት ነው?
7.     “ሙባእ” ማለት ምን ማለት ነው?
8.     “መጽሔተ አእምሮ” ማለት ምን ማለት ነው?
9.     “ልሣን” ማለት ምን ማለት ነው?
10.    “ሣልስ” ማለት ምን ማለት ነው?
11.     “ፊደል” ማለት ምን ማለት ነው?
12.    “እፎ” ማለት ምን ማለት ነው?
13.    “ራብዕ” ማለት ምን ማለት ነው?
14.    በፊደላት የደረጃ ስም መሠረት  “ሣብዕ” ማለት ምን ማለት ነው?
ጥ፡15-25 የዐረፍተ ነገር ትርጉም፦የሚከተሉትን አባባሎች ወደ አማርኛ ተርጉሙ
15.    “አውሥኡ ጥያቄያተ” ማለት ምን ማለት ነው?
16.   “አድንኑ አርእስቲክሙ” ማለት ምን ማለት ነው?
17.     “ምክር ሠናይት ለዘይገብራ” ማለት ምን ማለት ነው?
18.    “ከመ ይቤሉ አበዊነ ጠይቆት ይገብር ሊቀ” ማለት ምን ማለት ነው?
19.    “ባኡ በሰላም ኀበ ጽርሐ አውደ ጥናት ከመ ታእምሩ ፈሪሐ እግዚአብሔር ቅድመ ወልሣነ ግእዝ ድኅረ” ማለት ምን ማለት ነው?
20.   “ተናገራ ስመ አበ አቡክን” ማለት ምን ማለት ነው?
21.    “መኑ አንተ ወምንት ግብርከ” ማለት ምን ማለት ነው?
22.   አነ ኢኮንኩ ዐይኑ “ዐ” አላ አልፋው “አ” ማለት ምን ማለት ነው?
23.   “ብየ ምክንያት ለዘእገብር ኵሉ” ማለት ምን ማለት ነው?
24.   “ፌስቡክ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።
25.   “መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።
ጥ፡26-37 ተጨማሪ ማብራርያን የሚሹ፦ተጨማሪ ማብራርያ በመስጠት ጥያቄዎቹን መልሱ
26.  መስተዋድድ እና መስተጻምር ለሚባሉት ቃላት የአማርኛ ትርጉማቸውን ተናገሩ፤ ከያንዳንዱ አንድ ምሳሌንም ስጡ።
27.   አይቴ ውእቱ ብሔሩ ለአቡነ ሰላማ ማለት ምን ማለት ነው? (ጥያቄውን ወደ አማርኛ ከተረጎማችሁ በኋላ መልሱን መልሱ)
28.   “እምነ አስተጋባኢ” ማለት እና “እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉማቸውን እና ልዩነታቸውን ጻፉ።
29.  22 (ሃያ ሁለት) ቍጥርን በግእዝ አኃዝ (ቍጥር) እና በፊደልም ጭምር ጻፉ።
30.   “መምህራን ኮኑ በበ ደወሉ ፊደላተ ዘኆለቍ ኵሉ” የሚለው አባባል  ምን ለማለት ነው? ትርጉሙን እና ምሥጢሩን ተናገሩ።
31.    ስለ ሞክሼ ሆሄያት ስንማር “ፊደላት በስማችን ጥሩን ይላሉ” በሚለው ርእስ ሥር በተማርነው መሠረት “ይቤ “ጸ”(ጸልሎቱ ጸ) ጸውአኒ እንዘ ትጼሊ” የሚለው ዐ/ነገርን ተርጉሙ  ምን ዓይነት ምሥጢር እንዳለውም አስረዱ።
32.   “ይቤ “ሠ”(ንጉሡ ሠ) ሴመኒ ብሂሎ ንጉሡ “ሠ” ዘወለደኒ” ይህን ዐ/ነገር እስከ ማብራርያው ተርጉሙና አስረዱ።
33.   ስም የሚለው ቃል ግእዝ ነው ብለናል  ስለዚህ ወደ ብዙ ቍጥር ቀይሩት ማለትም “ስሞች” ለማለት በግእዝ እንዴት ነው? በአገራችን የሚሰጠውን ከቋንቋ ትርጉም ወይም ይዘት የተለየ ትርጉምስ ምንድነው?
34.    “ተንሥኡ ለጸሎት” ይህንን ወደ አማርኛ ተርጉሙ፤የተናጋሪውንና የሰሚውን የስም ተለዋጭም በግእዝ ጻፉ።
35.   ሆረ ማለት ምን ማለት ነው? ግሡስ ምን ዓይነት ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፣ ወይስ ትእዛዝ)?
36.  “አርኅዉ” ማለት ምን ማለት ነው? አንቀጹስ ወይም ግሡስ ምን ዓይነት ግሥ ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፤ ወይስ ትእዛዝ)?
37.   “መድኃኒ” የሚለውን ቃልና “ዓለም” የሚለውን ቃል 2ቱን ቃላት አያይዞ ለመጻፍ ምን ማድረግ አለብን? አያይዛችሁም ጻፉ።
ጥ፡ 38-47 ትርጉምን የማይሹ ጥያቄዎች፦ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ
38.    በከርሰ ምድር ውስጥ በፍለጋ የተገኙትና ሙሉ ይዘታቸው በግእዝ ቋንቋ ብቻ ተጽፎ የተገኘውን የ2ቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ስሞች ጥቀሱ።
39.  የግእዝ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
40.   የአማርኛ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
41.    ከአረብኛ የተደቀሉ የሚባሉት ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
42.   የአረብኛ ዲቃላዎች ከሚባሉት ሆሄያት ውስጥ የማይገኙት ሆሄያት--እና---ናቸው።
43.   በጉሮሮ የሚነበቡ ሆሄያት ስንትና የትኞቹ ናቸው?
44.   መኵሸ ሆሄያት የሚባሉት ስንት ናቸው?
45.   እያንዳንዳቸው ሞክሼ ሆሄያት ስንት ስንት ስሞች አሏቸው?
46.  ከሞክሼ ፊደላት የሁለት ፊደላትን ሁለት ሁለት ስሞች ብቻ ጥቀስ
47.   በክፍል 10 ትምህርት መሠረት የሆሄያትን የጋራ መጠሪያ ስም ተናገሩ?
ጥ፡ 48-50 እውነት፤ ሐሰት፦ እውነት ሐሰት በማለት መልሱ
48.   “ግ” ሳድስ ወይም የ”ገ” 6ኛ ሆሄ ነው “ሳድስ” ሆሄ ስንል ግን በጠቅላላ የሆሄያትን ሁሉ 6ኛ ፊደል መጥራታችን ነው። ይህ ዐ/ነገር እውነት ነው ወይስ ሐሰት?
49.   “እግዚአብሔር የሀሉ ምስለ ኵልክሙ” ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲተረጎም  “እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን” ማለት ነው።
50.   በሰላም ያስተራክበነ ብሂል  ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲቀየር “በሰላም ያገናኘን ማለት” ማለት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም ውጤት

No comments:

Post a Comment