መጻሕፍት መደብር ስለ እያንዳንዱ መጽሐፍ ይዘት ያንቡ
ልሣነ-ግእዝ-የጋራ ቋንቋችን
ይህ መጽሐፍ በመሠረታዊነት የተዘጋጀው ቋንቋውን ምንም ለማያውቁ ጀማሪዎችና መጠነኛ ግንዛቤ ኖሯቸው ሰዋስዋዊ አካሄዱን ግን ለማያውቁ ሲሆን ከዚያም በላይ የእውቀት ደረጃ ላሉም ቢሆን በተለይ የአገባብ መዋቅሮችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤን እንዲሰጥ ታስቦ ነው።
ይህንን መጽሐፍ ለመግዛት መጽሐፉን ይጫኑ
መጽሐፉን ካህናት፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፤ በየአብያተ ክርስቲያናት ሕጻናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ የእምነትንና የሥነ ምግባርን ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ለማስተማሪያነትም ሆነ የግል እውቀትን ለማዳበር እንዲሁም በማነኛውም የቋንቋ ጥናት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የቋንቋን አካሄድ፤ የቃላትን ቅንብርና አገባብ ለመገንዘብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
መጽሐፉ ቀላልና ግልጽ በሆነ የአጻጻፍ ስልት ቢጻፍም “ያለ መምህር መማሪያ” ለመሆን ከበድ ሊል ይችላል ብየ አምናለሁ። በመሆኑም “አውደ ጥናትን መጎብኘት አይዘንጉ።
ከዚህ መጽሐፍ ላቅ ያለ ዕውቀት ያላችሁ አንባብያን ለወጣንያንና ለማዕከላውያን1 የተዘጋጀ 1ኛ መጽሐፍ እንደ መሆኑ መጠንም በውስጡ የሚገኘው እያንዳንዱ ርእስ የተሰጠው ትርጉም፤ አገልግሎትና ትንታኔ ያለቀለት ሳይሆን ለክፍል አንድ የተመጠነ ብቻ ነው። ማለትም በክፍል ሁለትና በቀጣዮቹም ክፍሎች ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ወይም እየጨመረ የሚሄድ ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ወይም አገባብ እናንተ የምታውቁትን ሁሉ አካቶ ባለመገኘቱ የተረሣ ወይም ሳይታወቅ የታለፈ እንዳይመስላችሁ፤ ለክፍል አንድ ተመጥኖ የቀረበ ስለሆነ ብቻ ነው።
ሌላው ተማሪዎች ለጥናት የበለጠ እንዲተጉ በማሰብ በመጽሐፉ ውስጥ የቀረቡት ጥያቄዎች እየተመለስን መጽሐፉን እያነበብን የምንመልሳቸው ናቸው እንጅ መልሳቸው አልተሰጠም።
ሌላው የአማርኛን ቋንቋ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል
የማይችሉ ወይም የማይናገሩ በውጭው ዓለማት የተወለዱ በትውልድ ኢትዮጵያውያን ለሆኑ፤ ከዚያም አልፎ ሌሎች የውጭ ዜጎችም የግእዝን
ቋንቋ መማር ይችሉ ዘንድ የተወሰኑትን ክፍሎች በእንግሊዘኛም ጭምር ያዘጋጀሁት ስለሆነ መጽሐፉ የሚያበረክተውን ጥቅሙ የበለጠ ጉልህ
ያደርገዋል ብየ አምናለሁ። በእውነትም የሚረኩበት መጽሐፍ ነው።በመሆኑም ከዚህ መጽሐፍ የሚከተሉትን ቋንቋዎች
በሚገባ ይማራሉ1.
የግእዝን ቋንቋ እስከ ሰዋስው(አገባቡ)
ሌላው የአማርኛን ቋንቋ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል
የማይችሉ ወይም የማይናገሩ በውጭው ዓለማት የተወለዱ በትውልድ ኢትዮጵያውያን ለሆኑ፤ ከዚያም አልፎ ሌሎች የውጭ ዜጎችም የግእዝን
ቋንቋ መማር ይችሉ ዘንድ የተወሰኑትን ክፍሎች በእንግሊዘኛም ጭምር ያዘጋጀሁት ስለሆነ መጽሐፉ የሚያበረክተውን ጥቅሙ የበለጠ ጉልህ
ያደርገዋል ብየ አምናለሁ። በእውነትም የሚረኩበት መጽሐፍ ነው።በመሆኑም ከዚህ መጽሐፍ የሚከተሉትን ቋንቋዎች
በሚገባ ይማራሉ1.
የግእዝን ቋንቋ እስከ ሰዋስው(አገባቡ)
2.
የአማርኛን ቋንቋ እስከ ሰዋስዉ(አገባቡ)
እንዲሁም መሠረታዊ የሆኑ
የእንግሊዘኛ ቃላትን፤ ዐ/ነገራትን/ እንዲሁም የእንግሊዘኛን ቋንቋ አገባብ(ግራመር) ከጀማሪ በላይ የሆነ እውቀትን ያገኙበታል። ለመግዛት ይህንን ይጫኑ/To buy the booksgo to Amazon
“ሕያው ታሪክ በሕያዋን ምስክርነት”
የተሰኘው ይህ መጽሐፍ 300 ገጾች ያሉት በ31 ምዕራፎች
የተከፈለና ከ140 በላይ ንኡሳን አርእስት ያሉት ነው ።
መጠኑን ለመቀነስ ሲባል ሁሉም አርእስት በማውጫው
ስላልተጠቃለሉ መጽሐፉን በመገላለጥ ይምረጡ ።
የመጽሐፉ አብዛኛው ክፍል በቀጥታ የብፁዕ ወቅዱስ
ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊን የሕይወት ታሪክ
ከልደት እስከ ሕልፈት ድረስ ይዟል ።
ቀሪውና አናሳው ክፍል ደግሞ ከዚሁ ከ5ኛው ፓትርያርክ ጋር ተያያዥ የሆኑ ታሪኮችን ለማጠቃለል በማሰብ
ከኢትዮጵያ መንበረ ጵጵስና አመሠራረት በመነሣት የ4ቱን ፓትርያርኮች ታሪክ ባጭሩ በመተረክ የ4ኛውን ፓትርያርክ
ከሥልጣን መውረድ በተመለከተም በቋሚ ምስክሮች የተደገፈ እውነትን ለኢትዮጵያውያን ይፋ ያደርጋል ።
ይህ መጽሐፍ ባጭሩ ሲገለጽ ለ20 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን የመሩት 5ኛው ፓትርያርክ ማን እንደ ነበሩና በተጨባጭ
ማስረጃና በቋሚ የዐይን ምስክሮች በመደገፍ በሥራቸው አስደናቂና ልዩ መሪ እንደ ነበሩ ይናገራል።
5ኛው ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በተለዩ ጊዜ የ20 ዓመታት ሥራቸውን በጥንቃቄ ሲመለከቱ የነበሩ ::
በአገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ታዋቂ የሃይማኖትና የሕዝብ መሪዎች የሰጡትን እጅግ አስደናቂና ያልተለመደ
ምስክርነትንም በከፊል ይዟል ።
የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ሦስት ምዕራፎችንና አሥር አበይት
ክፍሎችን የያዘ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ በአማርኛ ቋንቋ
ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ባቀራረቡና በይዘቱ ፍፁም
የመጀመሪያው ነው ።
ስለመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው ሁሉ
በዚህ መጽሐፍ ተካቶ ይገኛል ። በቂ ግንዛቤ ከሌላቸው
ጀማሪዎች እስከ መጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ድረስ ከዚህ
መጽሐፍ የማይለካ ዘርፈ-ብዙ እውቀትን ያገኛሉ ፤
ይማሩበታል ያስተምሩበታልም ።
ስለዚህ ስለእምነትዎ በሚገባ በማወቅም ሆነ በማሳወቅ ራሰዎን ፤ ቤተሰበዎንና ሕብረተሰቡን ሕያው
በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ቃል ማነጽ ከፈለጉ ፤ ስለ እያንዳንዱ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ፤
የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የሚቀበሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሰዎ ከያዙት ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚለያይ መሆኑን
ማወቅየሚሹ ከሆነ ፤ ስለመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማርና የመስበክ ሃላፊነት ካለብዎ ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪ ፤
ዲያቆን ፤ ቄስ ፤መነኩሴ ፤ ጳጳስ ፤ ኤጲስ ቆጶስ ወዘተ ከሆኑ፤ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂዱ ከሆነ ፤
በአጠቃላይ ፍፁም የሆነውን ሃይማኖታዊውንና ማኅበራዊውን ሕገ-መንግሥት ሊመሩበት ከወደዱ ፤
ከዘፍጥረት እስከ ራእየ-ዮሐንስ እንዲሁም 2ኛ የቀኖና መጻሕፍትን ጨምሮ በ81ዱ ፤ በ76ቱ ፤ በ73ቱ ፤በ66ቱና በ24ቱ የዕብራውያን ብሉይ ኪዳን የሚገኙ መጻሕፍት ሁሉ በቀላልና ልዩ በሆነ ዘመናዊ አቀራረብ የመጽሐፉ ጸሐፊ ፤ የተጻፈበት ዘመንና ቦታ ፤ የመጽሐፉ ፍሬ-ሐሣብ ባጭሩ ፤
የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት ባጭር ትንታኔ ምርጥ ጥቅሶች ፤ ልዩና ያልተለመዱ ፤ እንዲሁም የመጽሐፉ መልዕክት
በሚሉ መሠረታውያን አርእስት የያንዳንዱመጽሐፍ ይዘት ማራኪ በሆነ መንገድ የመጽሐፉን ጠቅላላ ሐሣብ ባጭሩ
ተምሮ በሰፊው መረዳት በሚያስችል ዘዴ ቀርቧል ።በእኔ እይታ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከልጅ እስካዋቂ
ይህንን መጽሐፍ ሊይዝ ይገባልእላለሁ ። በመሆኑም እርሰዎም ከመጽሐፍ ቅዱሰዎ ጋር ተዋውቀው ያስተዋውቁት እላለሁ ።
|
No comments:
Post a Comment