50 የመመዘኛ ጥያቄዎች
የልሣነ ግእዝ ትምህርት የመግቢያው ፤ የክፍል አንድ ምዕራፍ አንድ 50 የመመዘኛ ጥያቄዎች
ለሚከተሉት 50 ጥያቄዎች “ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” በተሰኘው 1ኛ የግእዝ ትምህርት የመማርያ መጽሐፍ በተማሩት መሠረት ትክክለኛውን መልስ ይስጡ።
ጥ፡1-14 የቃላት ትርጉም፦የሚከተሉትን ቃላት
ወደ አማርኛ ቋንቋ ቀይሩ።
1.
“ስባሔ” ማለት ምን ማለት ነው?
2.
“እመ” ማለት ምን ማለት ነው?
3.
“ኅየንተ” ማለት ምን ማለት
ነው?
4.
“ቦ” ማለት ምን ማለት ነው?
5.
“ቢጽ” ማለት ምን ማለት ነው?
6.
“ዮም” ማለት ምን ማለት ነው?
7.
“ሙባእ” ማለት ምን ማለት
ነው?
8.
“መጽሔተ አእምሮ” ማለት ምን
ማለት ነው?
9.
“ልሣን” ማለት ምን ማለት
ነው?
10.
“ሣልስ” ማለት ምን ማለት
ነው?
11.
“ፊደል” ማለት ምን ማለት
ነው?
12.
“እፎ” ማለት ምን ማለት ነው?
13.
“ራብዕ” ማለት ምን ማለት
ነው?
14.
በፊደላት የደረጃ ስም መሠረት “ሣብዕ” ማለት ምን ማለት ነው?
ጥ፡15-25 የዐረፍተ ነገር ትርጉም፦የሚከተሉትን አባባሎች ወደ አማርኛ ተርጉሙ
15.
“አውሥኡ ጥያቄያተ” ማለት
ምን ማለት ነው?
16.
“አድንኑ አርእስቲክሙ” ማለት
ምን ማለት ነው?
17.
“ምክር ሠናይት ለዘይገብራ” ማለት ምን ማለት ነው?
18.
“ከመ ይቤሉ አበዊነ ጠይቆት
ይገብር ሊቀ” ማለት ምን ማለት ነው?
19. “ባኡ በሰላም ኀበ ጽርሐ አውደ ጥናት ከመ ታእምሩ ፈሪሐ እግዚአብሔር ቅድመ ወልሣነ ግእዝ ድኅረ” ማለት ምን ማለት
ነው?
20.
“ተናገራ ስመ አበ አቡክን”
ማለት ምን ማለት ነው?
21.
“መኑ አንተ ወምንት ግብርከ”
ማለት ምን ማለት ነው?
22.
አነ ኢኮንኩ ዐይኑ “ዐ” አላ
አልፋው “አ” ማለት ምን ማለት ነው?
23.
“ብየ ምክንያት ለዘእገብር
ኵሉ” ማለት ምን ማለት ነው?
24.
“ፌስቡክ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።
25.
“መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።
ጥ፡26-37 ተጨማሪ ማብራርያን የሚሹ፦ተጨማሪ ማብራርያ በመስጠት ጥያቄዎቹን መልሱ
26. መስተዋድድ እና መስተጻምር ለሚባሉት ቃላት የአማርኛ ትርጉማቸውን ተናገሩ፤ ከያንዳንዱ
አንድ ምሳሌንም ስጡ።
27.
አይቴ ውእቱ ብሔሩ ለአቡነ
ሰላማ ማለት ምን ማለት ነው? (ጥያቄውን ወደ አማርኛ ከተረጎማችሁ በኋላ መልሱን መልሱ)
28.
“እምነ አስተጋባኢ” ማለት እና “እምነ ጽዮን
ይብል ሰብእ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉማቸውን እና ልዩነታቸውን ጻፉ።
29. 22 (ሃያ ሁለት) ቍጥርን በግእዝ አኃዝ (ቍጥር) እና በፊደልም ጭምር ጻፉ።
30.
“መምህራን ኮኑ በበ ደወሉ
ፊደላተ ዘኆለቍ ኵሉ” የሚለው አባባል ምን ለማለት ነው? ትርጉሙን
እና ምሥጢሩን ተናገሩ።
31.
ስለ ሞክሼ ሆሄያት ስንማር
“ፊደላት በስማችን ጥሩን ይላሉ” በሚለው ርእስ ሥር በተማርነው መሠረት “ይቤ “ጸ”(ጸልሎቱ ጸ) ጸውአኒ እንዘ ትጼሊ” የሚለው
ዐ/ነገርን ተርጉሙ ምን ዓይነት ምሥጢር እንዳለውም አስረዱ።
32.
“ይቤ “ሠ”(ንጉሡ ሠ) ሴመኒ
ብሂሎ ንጉሡ “ሠ” ዘወለደኒ” ይህን ዐ/ነገር እስከ ማብራርያው ተርጉሙና አስረዱ።
33.
ስም የሚለው ቃል ግእዝ ነው
ብለናል ስለዚህ ወደ ብዙ ቍጥር ቀይሩት ማለትም “ስሞች” ለማለት
በግእዝ እንዴት ነው? በአገራችን የሚሰጠውን ከቋንቋ ትርጉም ወይም ይዘት የተለየ ትርጉምስ ምንድነው?
34.
“ተንሥኡ ለጸሎት” ይህንን ወደ አማርኛ ተርጉሙ፤የተናጋሪውንና የሰሚውን የስም
ተለዋጭም በግእዝ ጻፉ።
35.
ሆረ ማለት ምን ማለት ነው?
ግሡስ ምን ዓይነት ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፣ ወይስ ትእዛዝ)?
36. “አርኅዉ” ማለት ምን ማለት ነው? አንቀጹስ ወይም ግሡስ ምን ዓይነት ግሥ ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፤
ወይስ ትእዛዝ)?
37.
“መድኃኒ” የሚለውን ቃልና
“ዓለም” የሚለውን ቃል 2ቱን ቃላት አያይዞ ለመጻፍ ምን ማድረግ አለብን? አያይዛችሁም ጻፉ።
ጥ፡ 38-47 ትርጉምን የማይሹ ጥያቄዎች፦ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ
38. በከርሰ ምድር ውስጥ በፍለጋ የተገኙትና ሙሉ ይዘታቸው በግእዝ ቋንቋ ብቻ ተጽፎ የተገኘውን የ2ቱን ቅዱሳት መጻሕፍት
ስሞች ጥቀሱ።
39. የግእዝ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
40.
የአማርኛ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን
ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
41.
ከአረብኛ የተደቀሉ የሚባሉት
ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
42.
የአረብኛ ዲቃላዎች ከሚባሉት
ሆሄያት ውስጥ የማይገኙት ሆሄያት--እና---ናቸው።
43.
በጉሮሮ የሚነበቡ ሆሄያት ስንትና
የትኞቹ ናቸው?
44.
መኵሸ ሆሄያት የሚባሉት ስንት
ናቸው?
45.
እያንዳንዳቸው ሞክሼ ሆሄያት
ስንት ስንት ስሞች አሏቸው?
46. ከሞክሼ ፊደላት የሁለት ፊደላትን ሁለት ሁለት ስሞች ብቻ ጥቀስ
47.
በክፍል 10 ትምህርት መሠረት
የሆሄያትን የጋራ መጠሪያ ስም ተናገሩ?
ጥ፡ 48-50 እውነት፤ ሐሰት፦ እውነት ሐሰት በማለት
መልሱ
48.
“ግ” ሳድስ ወይም የ”ገ”
6ኛ ሆሄ ነው “ሳድስ” ሆሄ ስንል ግን በጠቅላላ የሆሄያትን ሁሉ 6ኛ ፊደል መጥራታችን ነው። ይህ ዐ/ነገር እውነት ነው ወይስ
ሐሰት?
49. “እግዚአብሔር የሀሉ ምስለ
ኵልክሙ” ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲተረጎም “እግዚአብሔር ከናንተ
ጋር ይሁን” ማለት ነው።
50.
በሰላም ያስተራክበነ ብሂል
ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲቀየር “በሰላም ያገናኘን ማለት” ማለት
ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም ውጤት
ጠቅላላ ፈተና 1
የግእዝ ቋንቋ ፈተና አንድ
መጽሐፉን ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ
No comments:
Post a Comment