Wednesday, August 9, 2017

8ቱ የንግግር ክፍሎች በአንድ ዐ/ነገር/The 8 Parts of speech in One Sentences


8ቱ የንግግር ክፍሎች በአንድ ዐ/ነገር/The 8 Parts of speech in One Sentences




ሰላም ለክሙ አርድእተ ልሣነ ግእዝ፣ ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው። ክፍል 14 የግእዝ ትምህርታችንን እንቀጥላለን  ወደ ትምህርቱ ከመግባቴ በፊት የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች እነግራችኋለሁ።

1.      “ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የተሰኘውን የግእዝ መማርያ መጽሐፍና “ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” የሚባለውን የ8ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት ማጥኛ መጽሐፍ ወደ ኢትዮጵያ እንዲላክላችሁ የምትፈልጉ ሰዎች ተመዝገቡ። በዚህ ስልክ በመደወል ስምና ስልክ ቁጥር ስጡ። 703 254 6601

2.     ከአማዞን ላይ መግዛት የምትፈልጉ ቶሎ ግዙ ምክንያቱም 1ኛ ትምህርቱ እያለፋችሁ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ዋጋው ይጨምራል አሁን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከ20 ዶላር ወደ 25 ስለሚወጣ በዝህ ሳምንት የምትገዙ ብቻ በዋጋው ታገኛላችሁ።
3.     በዚህ የሚሰጠው ትምህርት ከበድ የሚላችሁ ሰዎች በቫይበር፤በዋትስአፕና በኢሞ ለጀማሪዎች የሚሆን ትምህርት እየሰጠሁ ነው መከታተል ትችላላችሁ።

4.     ከአማዞን መጻሕፍቴን የምትገዙና የገዛችሁ ሰዎች ስለመጻሕፍቱና ስለአላላኩ ፍጥነትም ሆነ ስለጥራቱ አስተያየት ብትሰጡ መልካም ነው ምክንያቱም ለአውደ ጥናት ታላቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። በተረፈ ሽር፤ላይክና ሰብስክራይብ ማድረግን አትርሱ።

በዛሬው ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን ክፍል 14 ትምህርታችን ስለ 8ቱ የንግግር ክፍሎች ነው የምንቀጥለው። ባለፈው በክፍል 13 8ቱ የንግግር ክፍሎች የሚባሉት የትኞቹ እንደሆኑ ስማቸውን እና የስማቸውን ትርጉም ባጭሩ ተመልክተን ነበር።

ዛሬም በመቀጠል ስምንቱን(8ቱን) የንግግር ክፍሎች በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ በማስገባት ማለትም በአጠቃቀም እንዴት እንደሚገቡ እናያለን ማለት ነው።  ስለዚህ የምታዩትን ምሣሌ በሚገባ ደጋግማችሁ መስማትና መመልከት ልምምድም ማድረግ ይጠበቅማችኋል።

ባለፈው ትምህርታችን እርማት አድርጌ ነበረ ማለትም 1ኛው እርማት (ዝርዝር ቅጽሎችና አገባብ የሚባሉትን ከስምንቱ የንግግር ክፍሎች ውስጥ አስገብቸ ቆጥሬ ነበረ ግን ራሳቸውን ችለው ሳይሆን “ዝርዝር ቅጽሎች” “ከተውላጠ ስሞች” ጋር የሚቆጠሩ ሲሆን “አገባብ” ደግሞ “ከመስተጻምርና ከመስተዋድድ” ውስጥ የሚቆጠሩ ናቸው። ሌላው 2ኛው እርማት ደግሞ  ከ8ቱ የንግግር ክፍሎች የሚቆጠሩት “መስተዋድድ” እና “መስተጻምር” የሚባሉት ተቆርጠው  ከቪዲዮው ውስጥ ሳይገቡ ስለቀሩ ነበር።

እንደገና ለማስታዎስ ያህል 8ት የንግግር ክፍሎች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው።
ስምንቱ የንግግር ክፍሎች/The Eight Parts of Speech

1.      ስም= ስም/Noun
2.     ተውላጠ = የስም ተለዋጭ/Pronoun
3.     አንቀጽ/ግሥ=ማሠሪያ አንቀጽ/Verb
4.     ተውሳከ ግሥ =የግሥ ረዳት/Adverb
5.     ቅጽል=ገላጭ/Adjective
6.     መስተዋድድ= አዛማጅ/Prepositions
7.     መስተጻምር=አያያዥ/Conjunctions
8.     ቃለ አጋኖ= የሚያጋንን/የሚያጎላ ቃል/Interjections













የዛሬው የክፍል አሥራ አራት ትምህርት 8ቱን የንግግር ክፍሎች በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ በማስገባት አጠቃቀማቸውን እና ስያሜያቸውን መመልከት ነው። በዚህ ትምህርታችን በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በቁመቱ ረጅሙ ሰው የሆነውን አቶ አሥራትን ለ8ቱ የንግግር ክፍሎች ማብራርያ ባዘጋጀሁት ዐረፍተ ነገር ውስጥ አስገብቸዋለሁ። አቶ አሥራትን ለምሣሌየ የተጠቀምኩበት ዋናው ምክንያት “ነዊኅ” የሚለውን ቅጽል ለማስረዳት ስል ነው። ነዊ ረጅም ማለት ነው። ትምህርትን ትኩረት በሚሰጥና አስደናቂ፤ አስገራሚ፤ ከተለመደው ነገር ልዩ የሆነ ነገርን ወይም ሁኔታን እንደ ምሣሌ በማቅረብ ስንማረው የማይረሳና በአእምሮ ተቀርጾ የሚቀር እንዲሆን ያደርጋል ስለዚህም ነው ታዋቂውን አሥራት ለግእዝ ትምህርታችን እንደምሳሌ የተጠቀምኩት።

“አሥራት ነዊኅ ሆረ ግብተ ኀበ አሜሪካ፤ ወውእቱ ይነብር ውስተ ትእይንተ ሲያትል” ወይም እንደ ሚከተለውም ማለት እንችላለን።= ረጅም አስራት ወደ አሜሪካ በድንገት ሄደ፤ እሱም በሲያትል ከተማ ይኖራል።
“ነዊኃ ነዊኃን አሥራት ሆረ ግብተ ኀበ አሜሪካ፤ ወውእቱ ይነብር በውስተ ትእይንተ ሲያትል” = ከረጅሞች ሁሉ የሚረዝም አሥራት በድንገት ወደ አሜሪካ ሄደ፤ በሲያትል ከተማም እየኖረ ነው /ይኖራል።

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን አሜን

ከአውደ ጥናት


በመ/ር መላኩ አስማማው ቢሰጠኝ

No comments:

Post a Comment