Wednesday, August 9, 2017

የግእዝ ቃላት ለቅማችሁ አውጡ/Find the Ge'ez words


የግእዝ ቃላትን  ለቅማችሁ አውጡ/Find the Ge'ez words 


“ፍልሰታ ለማርያም” በሚለው እና “የግል ጸሎት” በሚለው ቪድዮዎች ውስጥ የሚገኙትን የግእዝ ቃላት ለቅማችሁ አውጡ፤ ለሚለው ጥያቄ መልስ እንደሚከተለው ይሆናል። ምን አልባት ያልተጠቀሱ ተጠማሪ ቃላት ካሉ ንገሩኝ።





“የግል ጸሎት” በሚለው ቪዲዮ ውስጥ የሚገኙት የግእዝ ቃላት የሚከተሉት ናቸው። (የአማርኛ ትርጉማቸውን በስተቀኝ ባለው ሰንጠርጅ ተመልከቱ።

የግእዝ ቃላት
አማርኛ ትርጉማቸው
ማብራርያ
ስም
በቁሙ ስም(መጠሪያ)
በግእዝም በአማርኛም ስም ይባላል (በቁሙ ማለት አይቀየርም ማለት ነው)
ደቂቀ ሰላም
የሰላም ልጆች
ሰላም በቁሙ ሰላም ይባላል ትክክለኛው ግን መረጋጋት፤የመንፈስ ጸጥታ ማግኘት ወዘተ ማለት ነው
ሰላም
የመንፈስ/የውስጥ ጸጥታና መረጋጋት ተቃራኒው ብጥብጥ/ጸብ ወዘተ ነው

ፍቅር


አርድእተ ክርስቶስ
የክርስቶስ ደቀመዛሙርት/ተማሪዎች

አንትሙ
እናንተ ለወንዶች

ትግሁ
ትጉ (ለብዙ ወንዶች ለቅርቦቹ)

እስከ ይትፌጸም ተስፋሁ
ተስፋው እስከ ሚፈጸም

ሰላም ለክሙ
ሰላም ለናንተ ይሁን

በስመ አብ
በአብ ስም

እም አውደ ጥናት ዘግእዝ
ከግእዝ መማሪያ ከሆነችው ከአውደ ጥናት
አውድ አደባባይ/ መሰብሰቢያ ቦታ፤ ትምህርት መማርያ ወዘተ ይሆናል፤ ጥናት አማርኛ ነው
አብ
አባት
ከሦስቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር አብ
ወወልድ
በወልድም ስም

ወልድ
ልጅ
ከሦስት አካላት አንዱ እግዚአብሔር ወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ
በመንፈስ ቅዱስም ስም

መንፈስ
ረቂቅ የማይጨበጥ የማይዳሰስ(የቃሉ ትርጉም ብቻ)
ከሦስቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
ም (ደቂቅ አገባብ)

ቅድመ ዓለም
ከዓለም በፊት

ማዕከለ ዓለም
በዓለም መካከል

ቅድም
መጀመሪያ/በፊት

ዓለም
ፍጥረት

ቅዱስ
ንጹህ፤ልዩ

ቅዱሳን
ቅዱስ የሚለው ሲበዛ ቅዱሳን ይሆናል (ለወንዶች)

ቅድስተ ቅዱሳን
ንጹህ፤ልዩ፤ ከሆኑት ይልቅ የነጻች፤የተለየች፤የከበረች

ቅድስት
ቅዱስ ለወንድ ሲሆን ቅድስት ለሴት ነው

ጸጋ
ሥጦታ (ነጻ የሆነ ከአምላክ የሚሰጥ ስጦታ)

ፍቅር
መውደድ
በአማርኛም ፍቅር ይባላል ትክክለኛው አማርኛ ግን መውደድ ነው
ትእግሥት
መቻል
በአማርኛም ትእግሥት ይባላል ትክክለኛው አማርኛ ግን መቻል ነው
ሞተ ነፍስ
የነፍስ ሞት

ዘልዓለማዊ
የሁል ጊዜ/የዘላለም(የማያልፍ)

ኃጢአት
በደል/ወንጀል
በአማርኛም ኃጢአት ይባላል ግን ትክክለኛው አማርኛ ወንጀል ነው
ንስሐ
ጸጸት
በአማርኛም በቁሙ ንስሐ ይባላል ግን ትክክለኛው አማርኛ ጸጸት ነው





“ፍልሰታ ለማርያም ወላዲተ አምላክ” በሚለው ቪዲዮ ውስጥ የሚገኙ የግእዝ ቃላት
የግል ጸሎት በሚለው ውስጥ የተጠቀሱትን ቃላት ድጋሚ ትርጉማቸውን ማስቀመጥ ስለማያስፈልግ አልፋቸዋለሁ።

የግእዝ ቃላት
አማርኛ ትርጉማቸው
ማብራርያ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ


እግዚአብሔር (እግዚእ፤ አብ፤ ብሔር) ወይም “እግዚእ ብሔር
እግዚእ ጌታ፤ አብ አባት፤ብሔር አገር፤ ወይም ፍጥረት

ፈጣሪ
በቁሙ መፍጠር ከዜሮ ተነስቶ መፍጠር
ፈጣሪ የሚባለው እግዚአብሔር ብቻ ነው
ፍጡር
የተፈጠረ የተሰራ
በእግዚአብሔር የተፈጠረው ሁሉ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሁሉም ፍጡር ይባላል
እምነት
በቁሙ ማመን

ጾም
በታቀብ፤ዝም ማለት፤ ከምግብ መከልከል

ትንሣኤ
መነሣት

እርገት
ወደላይ መውጣት

ትንሣኤሃ
መነሣቷ

እርገታ
ማረጓ ወይም ወደላይ መውጣቷ

ፍልሰታ
መፍለሷ/ከቦታ ቦታ መዘዋወሯ

ፍልሰት
መሰደድ/ከቦታ ቦታ መዘዋወር

ፈለሰ
ተሰደደ (ግሥ)

ፍልሰታ ለማርያም
የማርያም ከቦታ ቦታ መሰደድ (የቅዱስ ሥጋዋ ዝውውር)

ቅድስት


ቅድመ ክርስቶስ
ከክርስቶስ በፊት(ዘመነ ፍዳ)

ዓመተ ምሕረት
የምሕረት ዘመን/ዓመት(ዘመነ ይቅርታ)

ብሔረ ሕያዋን
የሕያዋን(ያልሞቱ ፍጡራን ወይም ሰዎች) አገር

ብሔር
ሐገር/ቦታ

ሕያዋን
ያልሞቱ (በሞተ ሥጋ ያልተለዩ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይገባል

ስብሐት
ምስጋና

ተግሣጽ
ምክር

ቅድስና
ከፍ ከፍ ማለት/ልዩ ንፁህ መሆን

ራብዕ
አራተኛ

ድንግል
ጥብቅ/እንደ ተፈጠረች ወይም እንደ ተፈጠረ ያለ

ወላዲተ አምላክ
የአምላክ እናት/ወላጅ/የወለደች

ወላዲት
የወለደች

አምላክ
እግዚአብሔር/ፈጣሪ

ቅድስተ ቅዱሳን



ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

በመም/ር መላኩ አስማማው

1 comment:

  1. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete