Thursday, February 26, 2015

ግእዝ ክፍል 22


የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል 22

ሰላም ለክሙ
አኃውየ ወአኃትየ
እለ ትነብሩ በውስተ ሐገሪትነ ኢትዮጵያ ወበውስተ ኵሉ ዓለም እፎ ኀለውክሙ? ወእፎ ኃለዉ አዝማዲክሙ? ወደቂቅክሙ?
ሰላመ እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ ወምስለ ኵልነ።
በአገራቺን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የምትኖሩ ወንድሞቼና እኅቶቼ ሁላችሁ ሰላም ለናንተ ይሁን።
 ልጆቻችሁና ዘመዶቻችሁስ እንዴት ናቸው?
የእግዚአብሔር ሰላም ከእናንተና ከእኛ ጋርም ይሁን ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን

የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል 22
የሰላምታ ቃላት በግእዝ ቋንቋ
በዛሬው በክፍል 22 የግእዝ ትምህርታችን  ስለ ሰላምታ ልውውጥ እንማራለን።
ሰላምታ ሲባል
ሰዎች ሲገናኙ የሚለዋወጡት ሰላምታ፤ የሚሰጣጡት መልካም ምኞት ማለት ነው?
የሚከተሉት ቃላት በግእዝ ቋንቋ ለሰላምታ ከምንጠቀምባቸው ቃላት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
እነዚህም ሰላም፤ እፎ፤ ዳኅን  የሚሉት ሦቱ ቃላት ናቸው።
·         ሰላም= ማለት ጸጥታ/ የኅሊና ነጻነት፤ መረጋጋት/ ከረብሻና ከብጥብጥ ነጻ የሆነ ሕይወት ወዘተ ማለት ነው። ይህም የደስታ ምንጭ ነው ። ስለዚህ ሰላም ስንል ወይም ይህንን ቃል ለሌሎች ስናስተላልፍ
 = ሰላም ለአንተ ይሁን/ ለአንተ ሰላምታ ይገባል። ወይም  እንደ ምን አደርክ? እንደምን ዋልክ? እንደምን አረፈድክ? እንደምን አመሸህ? ማለታችን ነው።
·         እፎ= እንዴት/ እንደምን ማለት ሲሆን ለጥያቄ የሚያገለግል ነው።
·         ዳኅን= ደህና/ ጤና፤ሰላም ወዘተ ማለት ነው። “ኑ” የሚለውን ሆሄ በመጨመር እንደ መጠየቂያ ቃላት ያገለግላል።
ሰላም! ስንል = ወይም “ሰላም” በምንል ጊዜ  የሚከተሉትን ማለታችን ነው
·         ሰላም ለአንተ ይሁን/ለአንተ ሰላምታ ይገባል
·         እንደ ምን አደርክ/አረፈድክ/ዋልክ/አመሸህ? ለማለት ነው።

·       አሁን በግእዝ አጠቃቀማቸውን እንመልከት

ሰላም፡
ሰላም! = ሰላም ለአንተ ይሁን/ለአንተ ሰላምታ ይገባል (በአሥሩም መራህያን ሁሉ አስገባ)
ሰላም ለከ!= ሰላም ላንተ ይሁን

ሰላም እኁየ!= ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ!
ሰላም ለከ እኁየ= ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ

እፎ
         እፎ ሐደርከ? እኁየ?= እንዴት/ እንደምን አደርክ ወንድሜ ?
·         ሐደርከ
·         ጸናሕከ
·         ወአልከ
·         መሰይከ
·         ሀሎከ

ዳኅን፡ (በአሥሩ መራኅያን ተውላጠ ስሞች ሲገባ)

1.      ዳኅንኑ  አነ ? = እኔ ደኅና ነኝን? (ደኅና ነኝን?)

2.     ዳኅንኑ ንኅነ ? = እኛ ደኅና ነን? (ደኅና ነንን?)

3.     ዳኅንኑ ውእቱ ?= እሱ ደኅና ነውን? (ደኅና ነውን)

4.     ዳኅንኑ ውእቶሙ ?=እነሱ ደኅና ናቸውን(ደኅና ናቸውን?) ለወንዶች

5.     ዳኅንኑ ይእቲ ?= እሷ ደኅና ናትን?

6.     ዳኅንኑ ውእቶን ?= እነሱ ደኅና ናቸውን? (ለሴቶች)

7.     ዳኅንኑ አንተ ?= አንተ ደኅና ነኅን?(ደኅና ነኅን?)

8.     ዳኅንኑ አንትሙ ?= እናንተ ደኅና ናችሁን? (ደኅና ናችሁን?)

9.     ዳኅንኑ አንቲ ?= አንቺ ደኅና ነሽን? (ደኅና ነሺን?)

10.    ዳኅንኑ አንትን ?= እናንተ ደኅና ናችሁን? (ደኅና ናችሁን)



ሰላምታ ክፍል 2(ክፍል 23)


1.      ለከ= ለአንተ
2.     ለክሙ= ለናንተ
3.     ለኪ= ለአንቺ
4.     ለክን= ለናንተ
5.     ለሊሁ= ለእርሱ
6.      ለሊሆሙ= ለነሱ
7.     ለሊሃ= ለርሷ
8.     ለሊሆን= ለነሱ
9.     ለልየ= ለእኔ
10.    ለሊነ= ለእኛ

ይህ ሲተረጎም ከቀጥታ ቃላቱ ለየት ያለ አባባል አለዉ።
ይህም ሰላም የሚለው ቃል  +ለ+ የተውላጠ ስም (ስም) አመልካች  (ዝርዝር) + ይኩን(ይሁን) በማለት ይጨመራል ወይም ይገባል ማለት ነው።

ሰላም+ ለ+ የተውላጠስም ወይም ስም አመልካች (ሊሃ)+ ይሁን (ሰላም ለ-ሊሃ= ሰላም ወይም ሰላምታ ለእርሷ ይገባል) ይገባል የሚለው ማሠሪያ ለሊሃ ከሚለው ቃል ውስጥ የሚፈጠር ሲሆን የቋንቋው ባሕርይ ነው።
ለምሳሌ ሙሉ ዐረፍተ ነገር በመሥራት እንመልከት።

“ሰላም ለኪ አውደ ጥናት” ማላት አውደ ጥናት፣ (አውደ ጥናት ሆይ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ለአንቺ ይሁን፤ ወይም እንደ ምን አደርሽ? ወልሽ? አረፈድሽ? አመሸሽ? ተብሎ ይፈታል። በመሆኑም ለከ= ላንተ፤ ለኪ=ላንቺ፤ ለክሙ=ለናንተ(ወንዶች)፤ ለክን= ለናንተ (ሴቶች)፤ ወዘተ እያልን በአሥሩ መራህያን ሁሉ በማስገባት መጠቀም እንችላለን። ቀጥለን በ10 መራህያን ትንታኔውን እንመልከት።

በአሥሩ መራህያን ሁሉ እያስገባን የሰላምታ አይነቶችንና አተረጓጎማቸውን እንመልከት።
1.      አንተ = አንተ  በሚለው ተውላጠ ስም፡

ሰላም - ለከ= ሰላምታ ለአንተ ይገባል ( እንደ ምን ዋልክ? እንደምን አደርክ? አመሸህ/አረፈድክ ወዘተ ይሆናል)
2.     አንት= እናንተ

ሰላም - ለክሙ= ሰላም (ሰላምታ) ለናንተ ይገባል፤ ለናንተ ይሁን፤ (እንደ ምን አደራችሁ?)
3.     አንቲ= አንቺ

ሰላም - ለኪ= ሰላምታ ለአንቺ ይሁን (እንደ ምን አደርሽ)
4.     ንትን= እናንተ (ሴቶች)

ሰላም - ለክን= ሰላምታ ለእናንተ ይሁን (እንደ ምን አደራችሁ?)
5.     እቱ= እሱ

ሰላም - ለሊሁ= ሰላምታ ለሱ(ለእሱ)ይገባዋል ይገባል( እንዴት አድሯል? (በመልእክት)
6.     እቶሙ= እነሱ (ወንዶች)

ሰላም - ለሊሆሙ= ሰላምታ ለነሱ ይገባል ( እንደምን አሉ፤ ናቸው፤ አድረዋል፤ሰንብተዋል) ሰላም በሉልኝ
7.     እቲ= እሷ

ሰላም ለሊሃ= ሰላምታ ለ እርሷ ይገባል፤ ለ እርሷ ይሁን፤ (እንደ ምን አድራለች?)
8.     እቶን= እነሱ (ለሴቶች)

ሰላም ለሊሆን= ሰላምታ ለእነርሱ ይገባል፤ይሁን፤ እንደ ምን አሉ፤ ናቸው?
9.     አነ= እኔ (ለሴትም፤ ለወንድም)

ሰላም - ለልየ= ሰላምታ ለእኔ ይገባል(ይገባኛል)
10.    ንሕነ== እኛ (ለሴቶችም፤ ለወንዶችም)

ሰላም - ለሊነ= ሰላምታ ለ እኛ ይገባል።

No comments:

Post a Comment