English for Amharic Speakers part 10 Objective Pronouns
Objective Pronouns
ባለፈው ትምህርታችን ስለ Subject Pronouns ተምረን ነበር፤ ለማስታዎስ ያህልም ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስ የሚባሉት በአንድ ዐረፍተ ነገር
ውስጥ የሚገኘውን የዐረፍተ ነገር ባለቤት የሚተኩ የስም ተለዋጮች ወይም “ፕሮናውንስ” በእንግሊዘኛ፣ ተውላጠ ስም በግእዝ፤ በአማርኛ ደግሞ የስም ተለዋጮች የምንላቸው
ናቸው። ብዙ ጊዜ እነዚህ ለሰብአዊ አካል የሚሆኑ ናቸው። ምሳሌያቸውንም አይተናል።
Subject
Pronouns
are pronouns
that replace the subject in the sentence. ማለትም “ሰብጀክት”ወይም
ሰብጀክት የሚባለው የአንድ ዐረፍተ ነገር ባለቤት ወይም ድርጊት ፈጻሚ/ድርጊቱ የሚነገርለት ወዘተ ማለት ነው። ስለዚህ ባጭሩ ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስ የሚባሉት የዐረፍተ ነገር ባለቤት የነበረውን አካል
ተክተው የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት የሚሆኑ ቃላት ናቸው።
ወደ ዛሬው ትምህርታችን እንሸጋገርና የዛሬው ትምህርት ስለ “ኦብጀክቲቭ ፕሮናውንስ” ስለሚባሉት ነው።
Objective Pronouns
Objective Pronouns /ኦብጀክት
ማለት ደግሞ ተደራጊ /ወይም የሚፈጸመው ድርጊት ወይም ነገር ነው።
The object is the part of the sentence that is being done to, from
or with the action.
የሚከተሉት “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስን” እና ኦብጀክቲቭ ፕሮናውንስን” ለማነጻጸር የሚጠቅሙን ዐረፍተ ነገሮች ናቸው
እንከታተል። “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውንስ” በቀይ፣ “ኦብጀክቲቭ ፕሮናውንስ” ደግሞ በሰማያዊ ቀለም ተጽፈዋል።
The following are subjective and Objective
pronouns together. subjective pronouns are written in red and objective
pronouns are written in blue.
1.
I will call you
tomorrow or (you can) call me
ዐይ ዊል ኮል ዩ ትሞሮ ወይም ደውልልኝ/ልትደውልልኝ ትችላለህ
ነገ እደውልልሃለሁ(እደውልልሻለሁ) ወይም ደውልልኝ(ልትደውልልኝ ትችላለህ)
2.
We will tell you before
you leave the country but, let us know before you
go.
ዊ ዊል ቴል ዩ ቢፎር ዩ ሊቭ ዘ ካንትሪ፣ ባት ሌት አስ ነው ቢፎር ዩ ገው፤
ከአገር ከመውጣትህ በፊት እንነግርሃለን፤ ነገር ግን ከመሄድህ በፊት አስታውቀን
3.
You will see me
tomorrow or I will email you
ዩ ዊል ሲ ሚ ትሞሮ ኦር ዐይ ዊል ኢሜይል ዩ
ነገ ታገኘኛለህ/ታየኛለህ ወይም እሜይል አደርግልሃለሁ.
4.
He gave me the book
to read it.
ሒ ጌቭ ሂም ዘ ቡክ ቱ ሪድ እት
(እሱ) መጽሐፉን እንዳነበው ሰጠኝ።
5.
She went with her boyfriend
yesterday before I told her
about the class.
ሺ ዌንት ዊዝ ኸር ቦይፍሬንድ የስተርደይ ቢፎር ዐይ ቶልድ ኸር አባውት
ዘ ችላስ
(እሷ) ስለ ትምህርቱ ሳልነግራት በፊት ትናንት ከወንድ ጓደኛዋ ጋር ሄደች።
6.
It is my book just leave it there.
እት ኢዝ ማይ ቡክ! ጀስት ሊቭ እት ዜር.
(እሱ) የኔ መጽሐፍ ነው እዛው ተወው።
7.
They left me a message
last sundy before I called them.
ዘይ ሌፍት ሚ ኤ መሴጅ ላስት ሰንደይ ቢፎር ዐይ ኮልድ ዘም.
ሳልደውልላቸው በፊት የለፈው እሁድ መልክት ትተውልኝ ነበር።
The following are
the Objective pronouns by
theirself /ኦብጀቲቭ ፕሮናውንስ
የሚባሉት ራሳቸውን ችለው ሲጻፉ የሚከተሉት ናቸው፤
- Me -ሚ
- You - ዩ
- Him -ሒም
- Her- ኸር
- It -እት
- Us - አዝ
- Them -ዘም
የስም ተለዋጮች ወደ ተሳቢ ወይም ፕሮናውንስ ቱ ኦብጀክት(from Subjective pronouns to
Objective pronouns)
·
I = Me (ዐይ ይሆናል ሚ) ማለትም የዐረፍተ
ነገር ባለቤት ሲሆን I
ይሆናል
·
We = Us ማለትም የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን We ይሆናል
·
You = You ማለትም የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን You ይሆናል
·
He = Him ማለትም የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን He ይሆናል
·
She = Her ማለትም የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን She ይሆናል
·
It = It ማለትም የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን It ይሆናል
·
They =Them ማለትም የዐረፍተ ነገር ባለቤት ሲሆን They ይሆናል
No comments:
Post a Comment