Sunday, February 28, 2021

ለወደፊቱ በሰው የማይሰሩ ሥራዎች/Jobs jobs will disappear in the future: እነዚህ ሥራዎች ...


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው፣ አምላካችን እግዚአብሔር ለዚች ሰዓት ስላደረሰን የተመሰገነ ነው።

 መጻሕፍት ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ

ዛሬ የማቀርብላችሁ በጣም ወሳኝና ወቅታዊ እስካሁን ከማዘጋጃቸው መልእክቶችና ትምህርቶ ለየት ያለ ርእስ ነው፣ እያንዳንዳችን ቢያንስ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተን ሰዎች፡ ልዩ ትኩረት ልንሰጠውና መረጃውን ተገንዝበን ከመረጃው ተጠቃሚ ልንሆን ይገባል ብየ አምናለሁ፣ እንከታተል።

 

ይህ ዝግጅት ለመረጃ ለአጠቃላይ ግንዛቤ ብቻ የሚሆን ነው። እኔ የዚህ ጉዳይ ባለሙያ አይደለሁም ይህንን የምነግራችሁ ከባለሙያዎቹ በመስማት የጻፉትን የጥናት ጽሁፍ በመመልከት፤ ራሴም ጥናት በማድረግ ነው፤ ስለዚህ ለመረጃነት የሚሆን ነው፤ ውሳኔ ለመወሰን ግን ምንም ነገር ከማድረጋችሁ በፊት ባለሙያዎችን ማነጋገር፤ ራሳችሁም ተከታትላችሁ መረጃዎችን በመሰብሰብ ሙሉ በሙሉ ሲገባችሁና ስታምኑበት መሆን አለበት።

 

 

ሁላችንም እንደምናውቀው አሁን ያለንበት 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አሉታ ወይም መጥፎ ጉኑ እንዳለ ሆኖ በሥልጣኔ እጅግ የመጠቀና አስደናቂ አዲስና ሕይወታችንን በተለይ ሥጋዊ ሕይወታችንን ቀላልና አመች ሊያደርጉ የሚችሉ ወይም የቻሉ የጥበብ ውጤቶች የሚታዩበት ጊዜ ነው።

 

ለምሳሌ

ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ቀላልና አመች በመሆኑ ዓለም ጠባብ መንደር ሆናለች፤ የትም ዓለም ሆነን በሰባቱም ዓለማት የሚገኙ ወገኖቻችንን ጓደኞቻችንን ሁሉ በየቅጽበቱ በእጃችን መዳፍ ባለ ዘመናዊ ስልክ በጽሁፍ በድምጽ እናነጋግራቸዋለን ከዚያም አልፎ በቪድዮ በአካላዊ ዓይን እየተያየን መወያየት እንችላለን፤ ያውም አብዛኛውን ጊዜ በነጻ ነው።

 

ከቤታችን ሳንወጣ ከአልጋችንም ቢሆን ሳንነሣ ያለምንም ገደብ በመላው ዓለም ተሰራጭቶ ጥቅም ሊያስገኝልን የሚችል ሥራን እየሠራን ገቢ እናገኝበታለን፤ አንድ ጊዜ ያዘጋጀነው ቪድዮ፣ የጻፍነው ጽሁፍ የለቀቅነው ድምጽ እኛ ተኝተን እያንቀላፋን ሥራችን በቀንም በሌሊትም በየትም ዓለም በማነኛውም ሰዓት ገንዘብ እየሰበሰበ ወደ ኪሳችን ያስገባል።

 

አሁን አሁን የሥራ ልብስ ለብሶ ቢሮ መግባት ከሰዎች ጋር በአካለ ሥጋ የተገናኙ አብሮ መሥራት፤ ወደ ምግብ ቤት ገብቶ በአስተናጋጆች መገልገል እየቀረ ነው።  በቴክኖሎጅ ወይም ዘመኑ ባመጣው የሥልጣኔ ውጤት ተጽእኖ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፉ ገዳይ ቫይረስ ምክንያት ተጨማምሮ ሰዎች በያሉበት ሆነው ዘመን ባፈራቸው የጥበብ ውጤቶች በመታገዝ መሥራት እንደ ግዴታ ሆኗል።

 

ሌላው ቀርቶ ሥርዓተ አምልኮቱም ቭርቹዋል የርቀት ከሆነ ውሎ አድሯል።

·        ኦንላይ

·        ድጅታል

·         ቭርቹዋል ወዘተ የሚባሉት ቃላትም የሚነግሩን የርቀት ወይም በአካለ ሥጋ በአንድ ውሱን ቦታ ሳንገናኝ በጽሁፍ፤በቃል በቪድዮ በመግባባት ስለሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ነው።

ታዲያ ይህ ሁኔታ ለብዙዎች አመችና የበለጠ ምርታማ ቢሆንም ለተወሰነው ምርታማ ላይሆን ይችላል በመሆኑም ዛሬ የምንነጋገረው በነዚህ ከዚህ በላይ በጠቀስኳቸው ነገሮች ወይም ክስተቶች እድገቶችም ልንላቸው እንችላለን ምክንያት ጥቅም ብቻ ሳይሆን ጉዳቱንም በተለያየ መልኩ እየተጋራን ነው።

ከዚያም አለፍ ባለ ሁኔታ ለተወሰነው ልዩ ዝግጅት ማድረግ ግዴታ የሚሆንበት ወቅት እንደሚመጣ ባለሙያዎች ደጋግመው እየተናገሩ ነው።

ስለዚህ የተለያዩ ምሁራን የሚተነብዩትን ማለትም በጥናትና በተጨባጩ እይታ ላይ በመመሥረት ወደፊት በሰብአዊ ፍጡር መሠራታቸው ይቀራል ከሚሏቸው ሥራዎች መካከል የሚከተሉት 14ቱ ተቀዳሚዎቹ እንደሆኑ ይናገራሉ፤ በመሆኑም በነዚህ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ሰዎች ከአሁኑ ሙያቸውን ሊቀይሩ ወይም ተጨማሪ ሙያ ሊቀስሙ ይገባል በማለት ይመክራሉ። ስለዚህ የትኞቹ የሥራ ዓይነቶች እንደሆኑ እናያለን።

1.  Drivers/ (ሹፌሮች ወይም ሹፌርነት)

2.  Farmers (ገበሬዎች ወይም የግብርና ሥራ)

3.  Printing and publishing (ፕሪንቲንግ ወይም የሕትመት ሥራዎች)

4.  Cashers (ካሸርስ የገንዘብ መቀበያ ማሽን ላይ የሚሠሩ)

5.  Travel agencies (የጉዞ ወኪሎች)

6.  Manufacturing workers (የፋብሪካ ሠራተኞች)

7.   Dispatchers (ዲስፓቸርስ በታክሲ፣ በእሳት አደጋ፣ በፖሊስ ወዘተ መሥሪያ ቤቶች የስልክ ጥሪ የሚያደርጉና የሚቀበሉ)

8.  Waiters and waitress (የሆቴሎችና የምግብ ቤት ሠራተኞች)

9.  Bank Tellers(የባንክ ገንዘብ ተቀባዮች ወይም ከፋዮች)

10. Airforce pilots (የአየር ሃይል አብራሪዎች ወይም ፓይለቶች)

11. Tele marketing (በስልክ የሚያስተዋውቁ የሚሸጡና የሚገዙ ወዘተ)

12. Accounting and Tax Preparers (የሂሳብና የግብር አሰባሰብ ሥራ ወይም  ሠራተኞች)

13. Stock market Traders (የስታክ ማርኬት ወይም አክሲዮን አሻሻጮችና አጋዥዎች)

14. Constriction workers (የሕንጻና የመንገድ ሥራዎች ሠራተኞች)

አሁን እያንዳንዳቸውን ባጭሩ እንመልከት

በ1ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰው የሹፌርነት ሥራ ነው፤ የሹፌርነት ሥራ የግል መኪናን  የጭነት መኪናን  ታክሲን፣ ለምሳሌ እንደ ኡቨር፣ ሊፍት ሌሎችም ልዩ ልዩ የታክሲ ድርጅቶች አሉ፡ በአጠቃላይ የሹፌርነት ሥራ በሰብአዊ ፍጡር ወይም በሰው መነዳቱ ይቀራል፤ ራሳቸው የሚሽከረከሩ (ሰልፍ ድራይቪንግ ቪክልስ) እየተሰሩ ነው አሁንም በልዩ ልዩ ቦታዎች ልዩ ልዩ ካምፓኒዎች እየተገለገሉባቸው ነው፤

በ2ኛ ደረጃ የተጠቀሰው የግብርና ሥራ ነው፤ (Farmers) እንደምታውቁት በሠለጠነው ዓለም ብግብርና ሥራ በበሬና በገበሬ መጠቀም ከቆመ ሰነባብቷል ባላደጉ አገሮች ግን እስካሁንም  በልዩ ልዩ እንስሳት ይታረሳል፤ አሁንም በአገራችን በበሬ ማረስ የተለመደ ነው፤ ዓለም በሥልጣኔ እየመጠቀ ሲመጣ ግን በመኪና በልዩ ልዩ ትራክተሮች ማረስ ተጀመረ

 በአሁኑ ጊዜ የሚያርሱ የሚዘሩ አዝመራውን የሚሰበስቡ ማሽኖች ተፈጥረዋል እስካሁን ማሽኖቹ “ፋርም ዩቲሊቲ” ቪክልስ” የሚባሉ የሚሰሩት በሰዎች ነጅነት ማለትም በሹፌር ነው የሚነዱት፤ አሁን ግን በሮባት የሚሠሩ ወይም ራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ሆነው የተሰሩ ናቸው፡ ስለዚህ በሬንም ሆነ ሰብአዊ ገበሬን ወይም ሹፌርን አይፈልጉም። ስለዚህ በግብርና ሥራ የተሰማራን ሰዎች ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን፤

የግብርና ሥራ ገበሬን ብቻ ሳይሆን መሬት ከማረስ ጀምሮ እህል ወይም ሌላ የመሬት ወይም የግብርና ውጤቶችን አምርቶ እስከ መሰብሰብ ድረስ ባለው የሥራ መስክ የተሰማራውን ኅብረተሰብ ሁሉ ያጠቃልላል።

በ3ኛ ደረጃ የተጠቀሰው “ፕሪንቲንግ እና ፐብሊሺንግ”(Printing and Publishing) ወይም ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ወይም የሕትመት ሥራ ነው። ይህም የጋዜጣ የመጽሔት የመጻሕፍት የሌሎችንም የሕትመት ሥራዎችን ይመለከታል። ወደፊት ጋዜታ መጽሔት መጻሕፍት ገዝቶ መአካል እያገላበጡ ማንበብ ይቀራል፤ ሁሉንም ኦን ላይን በኢንተርኔት እናሳትማለን በዚያ በኢቡክ ለምሳሌ እንደ ኪንድል ኑክ በተባሉት ድጅታል መሳሪያዎች እናነባለን ወይም ጉግል ፕሌይ፣ በአፕል ቡክ ወዘተ ፕላት ፎርሞች እናነባለን። እኔ ራሴ አብዛኛዎቹን መጻሕፍቶችን በጉግል ፕሌይ ስቶር ነው የምሸጠው፤ ጉግል ፕሌይ የሚባለው መጻሕፍቱን ስካን በማድረግ በፒዲኤፍ እና በሌሎችም ሴብ በማድረግ በጉግል ድጅታል ስቶር በማስቀመጥ ሰዎች በስልካቸውና በተለያዩ መሣሪያዎች እንዲያነቡ የሚያስችል ነው።

 

4ኛው የካሸርነት ሥራ ነው፤(Cashers) የካሸርነት ሥራ አሁንም እንደምታውቁት በታላላቅ ሱፐር ማርኬቶች የካሸርነት ሥራ የሚከናወነው በአውቶ ማቲክ ማሽኖች ነው፤ ምን አልባት የምታዩት የማሽኖቹን አጠቃቀም የማያውቁ ሰዎችን የሚረዱ አልፎ አልፎ የቆሙ ሰዎችን ነው። ስለዚህ የካሸርነት ሥራ ለወደፊቱ ሙሉ በሙሉ የሚሰራው በሚናገሩ ማሽኖች ብቻ ይሆናል ይባላል።

5ኛ የጉዞ ዎኪልነት ሥራ ነው፤(Travel agencies) ማለትም የአገር አቋራጭ የመኪና የአይሮፕላን የትሬይን ወዘተ ጉዞ ወኪሎች ወይም ባለ ንብረቶች ትኬት የሚቆርጡ ወይም የሚሸጡ ሥራተኞችን መቅጠር አያስፈልጋቸውም ሁሉም ነገር በኢንተርኔእት በሥልካችን በየቤታችን ሆነን ትኬት መቁረጥ በክሬዲት ካርድ መክፈል እንችላለን ትኬት ብቻ ሳይሆን ሆቴል ታክሲ ሁሉንም በአንድ ላይ በሥልካችን እንጨርሳለን።

6ኛ ፋብሪካዎች ናቸው(Manufactures) የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ሰዎች በሚያንቀሳቅሷቸው ማሽኖት መሥራታቸው ቀርቶ በሮባት የሚሠሩ ይሆናሉ ሮባት ፕሮግራም የሚደረግ ማሺን ስለሆነ ይናገራል ይንቀሳቀሳል ያዛል ይሠራል። ስለዚህ ሰብአዊ ፍጡርን ተክቶ መሥራት ይችላል ማለት ነው።

7ኛው ዲስፓቸርነት ነው። (dispatchers) ዲስፓቸር ማለት ልዩ ልዩ መልእክትን ትዕዛዝን እየተቀበለ አገልግሎት የሚያስፈጽም (sender) ማለት ነው ለምሳሌ በታክሲ ካምባኒዎች የሚሰሩ ዲስፓቸሮች ታክሲ የሚፈልግ ሰው ሲደውል ስልክ ያነሱና ምን አይነት ታክሲ እንደሚፈልግ፣ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሚሄድ በመጠየቅ በአቅራቢያው ያሉ ታክሲ ነጅዎችን በማናገር ወደ ተጠቃሚው ይልካሉ፤

በእሳት አደጋ መከላከያ በሥሪያ ቤት፤ በፖሊስ ጣቢያ ወዘተ በስልክ ተቀባይነት የሚሠሩ ሠራተኞችም “ዲስፓቸሮች “ ይባላሉ የእሳት አደጋ ሲከሰት በምንደውል ጊዜ የሚያነሱት ዲስፓቸሮች ናቸው። ችግሩን ጠይቀው በአፋጣን ፖሊስ ወይም የእሳት ማጥፊያ መኪና እንዲላክ ያደርጋሉ። አሁን የተለያዩ ሶፍት ዌሮች አፕሊኬሽኖች በስልካችን አሉ እነሱን ክሊክ ማድረግ ነው፤ ወይም ጉግል አሲስታንት፤ ሲሪ ወዘተ የሚባሉትን ማነጋገርና ሎኬሽናችንን ኦን ማድረግ ነው።

8ኛው የአስተናጋጅነት ሥራ ነው፤(waiters and waitress) ለምሳሌ የሆቴል የምግብ ቤት ፋስት ፉድ ወዘተ በነዚህ የሚያስተናግዱ ሰዎች ወደፊት አይኖሩም እንደሰው የሚታዘዙ ሮባቶች አርቲፊሻል ሰዎች ይታዘዛሉ የሚፈለገውን ያቀርባሉ።  እንዲያውም ቲፕ መስጠት አይጠበቅብንም።

9ኛው የባንክ ሥራ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ እንደ ድሮውም ባይሆን አልፎ አልፎ ወደ ባንክ እየሄድን በሰዎች እንገለገላለን፤ ገንዘብ እናስገባለን፤ እናወጣለን።

ለወደፊቱ ይህ ሁሉ ይቀራል ገንዘባችንን በሚከተሉት መንገዶች ማስገባት ማስወጣትም ወይም ማዘዋወር ወይም መጠቀም እንችላለን፡

·        ከምንሠራበት መሥሪያ ቤት ደሞዛችን ወደ አካውንታችን ይገባል

·        ቸክ የምንቀበል ከሆነ የባንኮችን አፕሊኬሽኖች በስልካችን በማውረድ ቸኩን በስልካችን ወደ አካውንታችን ዲፖሲት ማድረግ እንችላለን

·         ካሽ የምንፈልግ ከሆነ ከአውቶ ማቲክ ማሽን ወይም ኤይቲኤም  ማሽን ራሳችን ማውጣት እንችላለን

·        ማነኛውንም ነገር መግዛት ስንፈልግ ክሬዲት ካር እንጠቀማለን ወደ ባንክ ቤቶች መሄድ አያስፈልገንም፤ ይህም ከሆነ ባንኮች ገንዘብ የሚቀበልና የሚሰጥ ሰው መቅጠር አያሻቸውም

10ኛ ፓይለቶች፤ የግል፤ የድርጅት የወታደር አየር ሃይል አብራሪዎች ወዘት፡ አሁን ራሳቸው የሚበሩ ወይም ሰው አልባ ተዋጊ አይሮ ፕላኖች ተፈጥረዋል አሁን በተወሰነ መልኩ ቢሆንም ለወደ ፊቱ ሙሉ በሙሉ አይሮፕላኖች ሰው አልባ ይሆናሉ ፤ እንደ ጥንቱ በፈረስ በእግር ወዘተ እየዘመተ አገርን ከጠላት የሚጠብቅ ወታደር፣ ወታደሮችን የሚሸከም ፈረስ ወይም መኪና አይሮፕላን ወዘተ ሳያስፈልግ ሰው አልባ አይሮፕላኖችን መሳሪያ አስታጥቆ መላክ ወይም በርቀት በሪሞት ኮንትሮል ማሽከርከር ብቻ ነው።

11ኛ ቴሌ ማርኬቲንግ ( በስልክ የሚያስተዋውቁ የሚያሻሽጡ ወዘተ) ሠራተኞች እስከሁን አሁንም ጭምር ብዙ ጊዜ አጋጥሟችሁ ይሆናል በስልክ እየደወሉ የመኪና ኢንሹራንስ የጤና ኢንሹራንስ ወይም የተለያዩ ነገሮችን በቅናሽ ግዙ ተበደሩ ወዘተ እያሉ የሚደውሉ ሰዎች ተሌ ማርኬተር ይባላሉ። አሁን በድጅታል ማርኬቲንግ በነፌስ ቡክ በነጉግል ወዘተ በደቂቃ ውስጥ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲያነቡትና እንዲሰሙት በማድረግ ማስተዋወቅ ተችሏል፤ ስለዚህ በስልክ መሥራት ማስተዋወቅ የሚባለው ሥራ ቦታ አይኖረውም ይላሉ።

12ኛው አካውንታንት እና ታክስ አዘጋፎች ናቸው፤ እንደምታውቁት በተለይ በየ አመቱ ባለሙያ ወችን  እየከፈልን አመታዊ ግብር የከፈልነውን በማነጻጸር ወይም ይመለስልና አልያም እኛ ተጨማሪ እንከፍላለን፤ እና ታክስ ረተርን የሚያዘጋጁ ሰዎች ወደፊት ተጠቃሚዎችን ማግኘት ከባድ ይሆንባቸዋል፤ ምክንያቱም በጣም ቀላል እና ፈጣን ነጻም የሆኑ በኢንተርኔት የምናገኛቸው ሶፍት ዌሮች ተዘጋጅተው ቀርበዋል፤ መንግስትም የሚያበረታታን በነዚህ ሶፍት ዌሮች ተጠቅመን ራሳችን መሥራት እንድንችል ነው። ስለዚህ ለወደፊቱ ሰው ሙሉ በሙሉ የነዚሁ የኦንላየን አገልግሎቶች ተጠቃሚ ይሆናል።

13ኛው የሕንጻና የመንገድ ሥራዎች ናቸው እነዚህም ሥራዎች ወደ ፊት በሮባት ወይም በአርቲፍሻል ሰዎች  ሊሠሩ እንደሚችሉ ይተነበያል

14ኛው ስታክ ማርኬት ሠራተኞች ናቸው። (Stock market treders) ስታክ ማርኬት የሚባለው በአገራችን የአክሲሆን አገልግሎት ወይም የአክሲዮን ገበያ ማለት ነው። ይህ የስታክ ማርኬት ሥራ የአለምን ኢኮኖሚ የሚያነሳ እና የሚጥል ከፍተኛ ሃይል ያለው የኢንቨስትመንት(investment) ሥራ ነው። ለወደፊቱ አንድ ስለስታክ ማርኬት መረጃዎችን እሰጣችኋለሁ።

እስካሁን ወይም ትንሽ ቀድም ብሎ የስታክ ማርኬት ሥራ የሚሰራው በባለሙያዎች ብቻ ነበር ተጠቃሚው ስታክ ማርኬት ውስጥ invest ማድረግ ሲፈልግ ባለሙያውን ያነጋግራል፤ የአገልግሎት ዋጋ እየከፈለ “ሸር” ወይም አክሲሆን የሚባለውን ይገዛለታል ይሸጥለታል። በዚህ ዓይነት መልኩ ነበር የሚሰራው።

አሁን ግን ቴክኖሎጅ እያደገ ተጠቃሚው እየበዛ፤ ሲሄድ ነጻ, ለአጠቃቀምም ቀላል የሆኑ  (Apps) አፕሊኬሽኖች ተፈጠሩ፤ ስለዚህ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግ አፕሊኬሽኖቹን ወደ ስልኩ ኢንስቶል (instale) ያደርጋል፤ አካውንት ይከፍታል ራሱ በነጻ ከተለያዩ ካምፓኒዎች “ሼር” እየገዛ መሸጥና መለዋወጥ ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ የስታክ ማርኬት ባለሙያዎች ከተጠቃሚው የማግኘቱ ሁኔታ ስለሚቀር ሥራ ሊያጡ ይችላሉ፤ ሆኖም ግን ራሳቸው ባለሙያዎች ስለሆኑ ለራሳቸው ከሠሩ ከበቂበላይ ማግኘታቸው አይቀርም።

እነዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሁሉ በፍጥነት በአንድ ጊዜ የሚጠፉ ወይም የሚወገዱ ሳይሆኑ ሙሉ በሙሉ ለመጥፋት ዓመታት ይፈጃል እስከዚያውም ሠራተኛ ይቀንሳሉ እንጅ ሙሉ በሙሉ ሰው አልባ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ማሽኖቹ ወይም ሮባቶቹ አልፎ አልፎ ሰው ሊያስፈልጋቸው ይችላ

No comments:

Post a Comment