Saturday, June 30, 2018

ለ2019/2011 ዓ/ም የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ምዝገባ ዛሬ ተጀመረ/Registration for Ge'ez Langua...


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ የአውደ ጥናት ዘግእዝን የቀጣይ የትምህርት ዘመን የምዝገባና የአከፋፈል እንዲሁም የትምህርት ሁኔታ አንድ በአንድ አስረዳችኋለሁ ቪዲዮውን በትኩረት በመስማት በተሰጠው መመሪያ መሠረት ምዝገባችሁን ከወዲሁ ታጠናቅቃልችሁ ማለት ነው።  መልካም የምዝገባ ጊዜ።
በ2019 ወይም 2011 በአውደ ጥናት ዘግእዝ ለሚስጠው የልሣነ ግእዝ ትምህርት የወጣ ማስታዎቂያ
አውደ ጥናት ዘግእዝ በመጭው ዓመት 500 አምስት መቶ ተማሪዎችን ለማስተማር በዝግጅት ላይ እንገኛለን።
ለጀማሪዎችና ለመካከለኞች የሚሰጡ ሁለት ዓይነት የትምህርት ደረጃዎች ብቻ ይኖራሉ. በያንዳንዳቸው 250 ተማሪዎችን ብቻ እንቀበላለን።
በዚሁ ዓመት በአውደ ጥናት ዘግእዝ የብዙኃኑን የመማር ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ቅናሽ አድርገናል።
ከአሁን በፊት ከነበረው የአከፋፈል መንገድ የተደረገ ለውጥም አለ ይህም ለውጥ የሚከተለዉን ይመስላል።
1.  ባለፈው ዓመት እንደምታውቁት የአከፋፈል አማራጭ ከሙሉ ክፍያ ጀምሮ እስከ ወርሃዊ ክፍያ ድረስ የመክፈል አማራጭ ነበረ፤ ሁኖም ግን እስካሁን ከልምድ እንዳየነው ተማሪዎች በወቅቱ ባለመክፈል፤ከከፈሉ በኋላም የተሟላ መረጃ ባለመላክ አሠራሩን አመች እንዳይሆን አድርገውታል።
 ማለትም በተለያየ መንገድ የሚላከውን ክፍያ ለመቀበል ከአንድ ጊዜ በላይ በመመላለስ፤ በመደዋወል ጊዜን የሚያባክን በመሆኑ ይህንን ሁኔታ የተሻለ ለማድረግ ሲባል በ2019 ሁለት  የአከፋፈል አማራጮች  ብቻ ይኖራሉ፤ እነዚህም በየ ዓመቱና በየ 6 ወር  የሚፈጸሙ ናቸው።
2.  የክፍያ መጠንን በተመለከተ አዲስ የወጣ የክፍያ ቅናሽ አለ ይህንን ቅናሽ ማግኘት የሚችሉት ግን የዓመቱን በአንድ ጊዜ የሚከፍሉ ተማሪዎች ብቻ ናቸው፤ በየ6 ወራት የሚከፍሉ ቅናሽ አያገኙም ማለት ነው። አንድ ጊዜ የሚከፍሉ ብቻ ናቸው የቅናሹ ተጠቃሚዎች ማለት ነው።
የተማሪዎች ብዛትና የወጣው ልዩ ቅናሽ፡ እንዲሁም ቅናሹን ለማግኘት ወይም ሙሉውን ለመክፈል የሚቻልባቸው ቀናት
በሁለቱም ደረጃዎች(ለጀማሪና ለመካከለኛ) 500 ተማሪዎች ብቻ ይመዘገባሉ።እነዚህም በጀማሪ 250 በመካከለኛ 250 ድምር 500 ተማሪዎች ማለት ነው።
ይህ ማስታዎቂያ ከወጣበት ከዛሬ ከ ከሰኔ 28/ 2018/ ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 1 ቀን 2018/ መስከረም 2 ቀን 2011 ዓ/ም ድረስ ክፍያቸውን አጠናቀው የተመዘገቡ የመጀመሪያ 300 ተማሪዎች እንደየ አገሩ ከተመደበው ዓመታዊ ክፍያ ላይ ጀማሪዎች የግማሽ ዋጋ ቅናሽ፤ መካከለኞች ደግሞ የ 50 ብር ወይም ዶላር ቅናሽ ያገኛሉ።
ማለትም እንደየ አገሩ
·        በአፍሪካ የሚኖሩ በጀማሪዎች የመጀመሪያ 150 ተማሪዎች 1000 (አንድ ሺህ ብር)፤
·        በዐረብ አገራት የሚኖሩ $63 (63 ዶላር)፤
·         በአሜሪካና በአውሮፓ በሌሎችም አገራት (ከአፍሪካና ከዐረብ አገሮች ውጭ)ያሉ $100 (አንድ መቶ ዶላር) ይሆንላቸዋል።
በመካከለኞች ክፍል፡ የመጀመሪያ 150 ተማሪዎች 50 ብር ወይም ዶላር ተቀንሶላቸው ማለትም
በአሜሪካና በአውሮፓ በሌሎችም አገራት (ከአፍሪካና ከዐረብ አገሮች ውጭ)ያሉ
·        $125 ዶላር፤
በዐረብ አገራት የሚኖሩ
·        $75 ዶላር
በአፍሪካ የሚኖሩ
·        1950 ብር በመክፈል ለአንድ ዓመት መማር ይችላሉ
ከዚህ ላይ ግልጽ ለማድረግ ከተወሰነው ቀን ወይም ከ 300 ተማሪዎች በኋላ የሚገቡ ተማሪዎች ግን በተመደበው ክፍያ መሠረት ሙሉውን ክፍያ በመክፈል መማር ይችላሉ ማለትም ቅናሹ ለ300 ተማሪዎች(150 ከጀማሪ፤ 150 ከመካከለኛ) ብቻ ነው የሚሰጠው፤ ስለዚህ ቀኑን መጠበቅ የለባችሁም፤ ምክንያቱም ቀኑ ከመድረሱ በፊት 150 ሰው ከያንዳንዱ ደረጃ ከተመዘገበ ቅናሹ ይቆማል ማለት ነው።
·        ነባር ተማሪዎች ማለትም በአሁኑ ጊዜ በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ መካከለኛ ስለሚሸጋገሩ በግማሽ ዋጋ መቀጠል ይችላሉ። ነገር ግን  ነባር ተማሪዎችም ቢሆኑ ቅናሹን ለማግኘት በተመደበው ጊዜ ቀድመው መመዝገብና መክፈል ይኖርባቸዋል።
·        ትምህርቱ የሚጀመረው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር አንድ ቀን ሲሆን በአገራችን አቆጣጠር ታሕሳስ 23 ቀን ነው የሚሆነው ከዚያ በፊት ቢያንስ ጥር ከመግባቱ በፊት ማለትም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከታህሳስ 23 በፊት ምዝገባውን መጨረስ ግድ ነው ።
በ2019 የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ባጭሩ የሚከተሉት ናቸው የተጠቀሱት መሠረታውያኑ ናቸው እንጂ በውስጣቸው ስፋ ብለው የሚሰጡ ናቸው።
ለጀማሪዎች ከሚሰቱት ዋና ዋናዎቹ
ስለ ፊደላት ታሪክ፤ ስያሜ፤ብዛት፤ አይነት፤ ስምጽና አከፋፈል
ስለ ሆሄያት ተናባቢና አናባቢ
ስለ መኩሸ ሆሄያትና አጠቃቀማቸው
ስለ ቍጥሮች መሠረታዊ ትምህርት የሚሉት ሲሆኑ በምእራፍ አንድ የሚጠቃለሉ ናቸው።
በምዕራፍ ሁለት የሚሰጠው ስምንቱን የንግግር ክፍሎች የሚያጠቃልል ሲሆን ስምንቱ የንግግር ክፍሎች ደግሞ በተለያዩ ምዕራፎች ይከፈላሉ።
ማለትም
3.  ስም
4.  ተውላጠ ስም
5.  ግሥ
6.  ረዳት ግሥ
7.  ቅጽል
8.  መስተዋድድ
9.  መስተጻምር
10.         ቃለ አጋኖ የሚባሉት ሲሆኑ ለጀማሪዎች በሚመጥን መልኩ ይሰጣሉ።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና አርእስትና ሌሎችንም ከነዚሁ ጋር የሚያያዙትን ስንማር በሦስት ዓይነት መልኩ በጥልቀት እንማራለን፤ መጀመሪያ ትምህርቱ በድምጽና በጽሁፍ ይተላለፋል፤ ቀጥሎ ከ3 ቀናት በኋላ ከትምህርቱ የተውጣጡ አሥር ጥያቄዎች ይሰጣሉ፤ ተማሪዎች በተማሩት መሠረት በጥያቄዎቹ አማካኝነት ራሳቸውን ወይም ችሎታቸውን ይፈትሻሉ፤ በመጨረሻም ለተሰጡ አሥር የመመዘኛ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስና ሙሉ ማብራርያ ጭሙር በድምጽና በጽሁፍ ይለቀቃል ተማሪዎችሁ መልሳቸውን በማስተያየት ስህተታቸውን ያርማሉ።
ለመካከለኞች የሚሰጠው ትምህርት በመሠረታዊነት በስምንቱ የንግግር ክፍሎች ዙሪያ ሲሆን ልዩነቱ ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ይሄዳል፤ ለምሳሌ ግሥነ ብንወስድ በጀማሪዎች የሚሰጡት አበይት ግሦች ብቻ ሲሆኑ በመካከለኞች ሙሉ ትንታኔውን ጭምር እንማራለን ማለትም ከግሥ የሚወጡ ዘሮችን ጭምር በሰፊው እናረባለን፤ ውስብስብ የሆኑ ዐረፍተ ነገራትን እንሠራለን፤
የትምህርት አሠጣጡን በተመለከት በሁለቱም ክፍሎች አንድ አይነት ነው ትምህርት፤ጥያቄ፤መልስ በየሳምንቱ ይሰጣል ማለት ነው።
በተጨማሪም ተማሪዎች እርስ በርሳቸው በግእዝ ቋንቅው የሚወያዩበት የተለየ ግሩፕ ይኖራቸዋል።
በጭሩ ይህንን ይመስላል፡ የመማር ፍላጎቱ ያላችሁ ቀደም ብላችሁ በመመዝገብ መጀመር ትችላላችሁ።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

1 comment:

  1. የምኖረው ኢትዮጵያ ነው መማር እፈልጋለሁ ገንዘቡን እንዴት ነው መክፈል የምችለው

    ReplyDelete