Sunday, May 5, 2019

“አባታችን ሆይ” እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ”

ዛሬ በዚህ ዝግጅቴ “አባታችን ሆይ” የሚለውን እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ” የሚባሉትን ሁለት የጸሎት ክፍሎች በውጭ አገር ተወልዳችሁም ሆነ ወይም በሌላ ምክንያት አማርኛና ግእዝ ለማታነቡና ለማትናገሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን አማርኛውንና ግእዙን በምታውቁት የእንግሊዘኛ ፊደል አዘጋጅቼ አቅርቤላችኋለሁ ተከታተሉ፤ 
















ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው፡
ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ እና ሌሎቹንም መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

 https://amzn.to/2V2fMLl         ( ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ)
https://amzn.to/2DPUStg    (ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ)
ዛሬ በዚህ ዝግጅቴ “አባታችን ሆይ” የሚለውን እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ” የሚባሉትን ሁለት የጸሎት ክፍሎች በውጭ አገር ተወልዳችሁም ሆነ ወይም በሌላ ምክንያት አማርኛና ግእዝ ለማታነቡና ለማትናገሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን አማርኛውንና ግእዙን በምታውቁት የእንግሊዘኛ ፊደል አዘጋጅቼ አቅርቤላችኋለሁ ተከታተሉ፤ ምን ያህል የሚጠቅማችሁ መሆኑን፤ ወይም የበለጠ የተሻለ መንገድ አለ የምትሉትም የአቀራረብ ዘዴ ካለ ተናገሩ፤ አስተያየታችሁን ለመስጠት ወደኋላ አትበሉ።
እንደምታዩት የተዘጋጀው አማርኛውና ግእዙን በእንግሊዘኛ ፊደል በመጻፍ ስለሆነ አማርኛውንም ሆነ ግእዙን የማንበብ ችሎታ ይኖራችኋል፤ የእንግሊዘኛ ትርጉሙንም አብሬ አስቀምጨዋለሁ፤ የአነባበብ ስልቱን ደግሞ በድምጽ ትሰማላችሁ ማለት ነው።

በነዚህ ሁለት ጸሎታት በግእዝም ሆነ በአማርኛ መጻሕፍት ተጽፎ ከሚገኘው ኃይለ ቃል ሌላ በቃል ስንጸልይ የምንጨምራቸው ተጨማሪ ቃላት አሉ፤ እኔ የጻፍኩት በመጻሕፍቶቻችን የተጻፈውን ነው። በቃል የሚጨመሩት እነዚህ ቃላት ችግር የማያመጡና ከይዘቱ አንጻር ተገቢ ቢሆኑም፤ ሁሉም ምእመናን በአንድ ዐይነት መንገድ ስለማያነቡት ልዩነት የተፈጠረ ስሕተት መስሎ እንዳይታያችሁ፤ ከወዲሁ አሳስባለሁ ።
ከሚጨመሩትም ቃላት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
1.  “እመቤቴ ማርያም ሆይ” ይህ ከመጽሐፉ በግእዝም በአማርኛም የሚገኘው ኃይለቃል ነው። በቃል በአማርኛ ስንል “እመቤታችን ቅድስት፤ ድንግል፤ ማርያም ሆይ” እንላለን፤ እመቤታችን ቅድስ ናት ድንግልም ናት፤ ትክክለኛ አባባል ነው፤ በዚህ የጸሎት ክፍል ከመጽሐፉ ውስጥ ስለማይገኝ፤ ለምን ቀረ ወይም ለምን ተጨመረ ብለን ግራ እንዳንጋባ ነው።
2.  “ወቡሩክ ፍሬ ከርስኪ” ወይም “የማሕጸንሽ ፍሬ” የተባረከ ነው። ይህ ከመጽሐፉ የሚገኘው ሲሆን፤ በቃል “የማሕጸንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ ነው” እንላለን። በዚህ ላይ ምምህራን የሚያስተምሩት፤ አንድ ነጥብ አለ እመቤታችን በድንግልና ጸንሣ በድንግልና የወለደቺው የእግዚአብሔር ቃሉና ልጁ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው። ስለዚህ የማሕጸንሽ ፍሬ ከተባለ ሌላ የማሕጸኗ ፍሬ ስለሌለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ መጥቀስ አይጠበቅብንም ምክንያቱ በስም የሚጠቀሰው ከብዙዎች መካከል ለመለየት እንጅ አሻሚ የለለውን ነገር መጥቀስ አያስፈልግም ይላሉ። ያም ሆነ ይህ የእኔ አላማ ግን ልዩነቱን እንድታውቁ ብቻ ነው።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

No comments:

Post a Comment