Tuesday, May 21, 2019

ኢትብላዕ እምዕፅ ዘያርኢ ወያሌቡ እኵየ ወሠናየ/But of the tree of the knowledge of good &...


ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ይጫኑ
https://amzn.to/2YLdJh5

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ ወቅታዊ ታሪክን መሠረት ያደረገ የግእዝ ቋንቋ ጥቅስ ትምህርታችን ክፍል 2 ይቀጥላል እንከታተል።
የዛሬውም ጥቅስ በቀዳማይ ምዕራፈ ታሪክ ውስጥ በሕገ ልቡና የተነገረ ነው።
“እምኵሉ ዕፅ ዘሀሎ ውስተ ገነት ብላዕ። ወእምዕፅሰ ዘያርኢ ወያሌቡ ሠናየ ወእኩየ ኢትብላዕ እምኔሁ፡ እስመ በዕለተ ትበልዕ እምኔሁ ሞተ ትመውት” ዘፍ. 2፡16-17
ትእዛዝ
ይህ ትእዛዝ  ለመጀመሪይዋ ሰው ለአዳም የተሰጠ ነው፤ ስለዚህ ትእዛዝ ሰጪው እግዚአብሔር ሲሆን ትእዛዝ ተቀባዩ አዳም ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ሰባክያን ስለ ዘመነ ሥጋዌ ሲያስተምሩ ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ። ምክንያቱም የሥጋዌን ታሪክ የፈጠረው የዚህ ትእዛዝ መሻር፤ የአዳም ይህንን ትእዛዝ አለመጠበቅ ስለሆነ የታሪኩን መነሻ በመሻት ለማስረዳት ስለሚፈልጉ ነው።
የጥቅሱ ወይም የትእዛዙ የአማርኛ ትርጉም
“እምኵሉ ዕፅ ዘሀሎ ውስተ ገነት ብላዕ። ወእምዕፅሰ ዘያርኢ ወያሌቡ ሠናየ ወእኩየ ኢትብላዕ እምኔሁ፡ እስመ በዕለተ ትበልዕ እምኔሁ ሞተ ትመውት”
·          በገነት ውስጥ ካለው ዛፍ ሁሉ ትበላለህ(ካለው ዛፍ የሚገኘውን ፍሬ ማለት ነው)
·          ክፉና ደጉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ ግን ከሱ አትብላ(ከሱ የሚገኘውን ፍሬ)
·          ከእሱ በበላህ ጊዜ ሞትን ትሞታለህና
በዚህ ትዕዛዝ ውስጥ 3 ነገሮችን እናያለን አንዱ በገነት ውስጥ ያለው ሁሉ ከአንድ ዛፍ በስተቀር ለአዳም እንደ ተፈቀደለት፤
ሁለት፡ በገነት ውስጥ ያለ ክፉን እና ደጉን የሚያሳይና የሚያስገነዝብ አንድ ዛፍ እንደ ነበረ ከዚያ ዛፍ እንዳይበላ የአዳም መከልከል
ሦስት፡ የተፈቀደለትን አልፎ ያልተፈቀደውን ዛፍ ከበላ ግን የሚጠብቀው ውጤት ሞት እንደ ሆነ ያለመታዘዝን ዋጋ ቀድሞ ማስታወቅ የሚሉት ናቸው።
አዳም ግን የወደደውን መረጠ የተነገረውንም አገኘ። ቀጣዩን ታሪክ በክፍል 3 እናየዋለን አሁን ግን
በጥቅሱ ውስጥ የሚገኙትን ቃላት ትርጉም፤ ዓይነት ሥራ እና ባሕርይ እናያለን።

በተጠቀሰው ጥቅስ ውስጥ ያሉትን 3 ዐረፍተ ነገራት፤ 31 ቃላትና አገባቦች ሲኖሩ ከ31ዱ ውስጥ 15ቱ አገባቦች ሲሆኑ 16ቱ ደግሞ ቃላት ናቸው። ከነዚህ ውስጥም ስሞች፤ ግሶች፤ አበይትና ንዑሳን አገባቦች ይገኛሉ አንድ በአንድ እናያቸዋለህ ትኩረት ሰጥታችሁ ተከታተሉ
ዐረፍተ ነገራት
·         “እምኵሉ ዕፅ ዘሀሎ ውስተ ገነት ብላዕ
·         ወእምዕፅሰ ዘያርኢ ወያሌቡ ሠናየ ወእኩየ ኢትብላዕ እምኔሁ
·          እስመ በዕለተ ትበልዕ እምኔሁ ሞተ ትመውት”
ቃላትና አገባቦች
1.   “እም
2.   ኵሉ
3.   ዕፅ
4.  
5.   ሀሎ
6.   ውስተ
7.   ገነት
8.   ብላዕ
9.  
10.  እም
11.  ዕፅ
12. 
13. 
14.  ያርኢ
15. 
16.  ያሌቡ
17.  ሠናየ
18. 
19.  እኩየ
20. 
21.  ትብላዕ
22.  እም
23.  ሁ፡
24.  እስመ
25. 
26.  ዕለተ
27.  ትበልዕ
28.  እም
29. 
30.  ሞተ
31.  ትመውት”







ልዑል አምላክ ለብዎቶ የሐበነ
እም አውደ ጥናት ዘግእዝ

No comments:

Post a Comment