Friday, May 10, 2019

ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበ አምሳሊነ/”Let us make man in our image, after our likeness”


“ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ”
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ ወቅታዊ ታሪክን መሠረት ያደረገ የግእዝ ቋንቋ ትምህርትን አዘጋጅቸላችኋለሁ ።
 በመሠረታዊነት በአውደ ጥናት ዘግእዝ ተመዝግበው ለሚማሩ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደ ልምምድ ይሆን ዘንድ የሚዘጋጅ ነው።

ሆኖም ግን ቋንቋውን መማር ለምንፈልግ ሁሉ በጣም ጠቃሚ ግንዛቤን የሚሰጥ ትምህርት ነው።
በዚህ ዝግጅት የምናየው ስለ አምላክ ሰው መሆን እና ስለ ዓለም ድኅነት  ሲነገር ወይም ሲተረክ በሊቃውንቱ አንደበት ተዘውትረው በግእዝ ቋንቋ ስለሚነገሩ  ጠለቅ ያለ ምሥጢርን ስለያዙ ልዩ ልዩ ጥቅሶች ነው።

·         ታሪኩ በሕገልቡና
·         በሕገ ኦሪት እና
·         በሕገ ወንጌል በሦስቱ ሕግጋት የተከፈለ ነው።

በመሆኑም ከዚህ በላይ ባሉት 3 ሕግጋት ወይም የታሪክ ምዕራፎች ውስጥ የሚከተሉትን ባጭሩ የምናይበት ዝግጅት ነው።
·          እግዚአብሔር ሰውን እንዴት እንደ ወደደውና ፍቅሩም ምክንያት አልባ እንደሆነ፤
·         ሰው እንዴት እንደ ተፈጠረና የአምላኩን ሕግ እንዴት እንደተላለፈ፤
·         ሰው ከክብሩ ከተዋረደ በኋላ ከእግዚአብሔር ስለተሰጠው ተስፋ
·         ስለ አምላክ ሰው መሆን የነቢያት ትንቢት
·         ሰለ አምላክ ሰው መሆንና የትንቢቱ ፍጻሜ እንዴት እንደነበር
ጠቅለል ባለ አገላለጽ ከሰው ልጅ በአምላክ መወደድ ጀምሮ እስከ ዘመነ ትንሣኤ ድረስ ያለውን ታሪክ ለመናገር ከሚጠቀሱ ብዙ ጥቅሶች መካከል ጥቂቶቹን እና ተዘውትረው በግእዝ ቋንቋ የሚጠቀሱትን ጥቅሶች በግእዝ እየጠቀስን ወደ አማርኛ እየተረጎምን ይዘታቸውን የሥራ ድርሻቸውን እያብራራን እንማራለን። እንከታተል።

ለዛሬው የምናየው የመጀመሪያውን አንድ ጥቅስ ብቻ ይሆናል ይህም በመጀመሪያው የሰውልጅ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ስለ ሰው አፈጣጠር የሚናገር የመጀመሪያ ጥቅስ ነው

ቀዳማይ ምዕራፈ ታሪክ
 “ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ” ዘፍ.1፡26
በዚህ ጥቅስ
1.    እግዚአብሔር በአንድነትና በሦስትነት የሚመለክ አምላክ መሆኑን፤
2.    የሰው ልጅ ከሥነ ፍጥረት ሁሉ የበለጠ ክብርን እንዳገኘ
3.    እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሳይፈጥረው አስቀድሞ እንደወደደው የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው

1.    ንግበር
2.    ሰብእ
3.   
4.    አርአያ
5.   
6.   
7.    አምሳል
8.   
·         ፍቅር እንበለ ምክንያት ወፈጢር በአምሳሊሁ
 ልዑል አምላክ ለብዎቶ የሐበነ
እም አውደ ጥናት ዘግእዝ


ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን እና “ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” የሚባሉትን መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
https://amzn.to/2VWunwn 
 https://amzn.to/2Yix4Wt
Another important book to build life changing habit, The instant New York Times bestseller
https://amzn.to/2LxyL0K
No matter your goals, Atomic Habits offers a proven framework for improving--every day. James Clear, 

No comments:

Post a Comment