Friday, August 21, 2020

ቢፅ ሐሳዊ/Deceiver Friend

 ቢፅ ሐሳዊ/Deceiver Friend

















ቢፅ ሐሳዊ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው ዛሬ ቃላትን እና ኃረጋትን ወይም ዐረፍተ ነገራትን በምናብራራበት ዝግጅት የምናየው “ቢፅ ሐሣዊ” የሚለውን ኃረግ ነው። ኃረግ የሚባለው እንደምታውቁት ከአንድ በላይ ቃላትን የያዘ ነው። በመሆኑም “ቢፅ ሐሳዊ” የሚለው ሐረግ ሁለት ቃላትን ይዟል፤ ሁለቱም ቃላት ቅጽሎች ናቸው። በትርጉም ግን ሁለቱ የተለያዩ ናቸው። ቢፅ ሐሳዊ የሚለው ኀረግ


·         ምን ማለት ነው?

·         በዚህ ስም የሚጠራው ማነው ወይም እነማናቸው?

·         ይህ ስም በብዛት የሚነገረው በየት ነው?

·         ለምንና በምን ምክንያትስ ይነገራል? የሚሉትን 4

ጥያቄዎችን እናያለን እንከታተል።

 መን ማለት ነው፡ ሁለቱንም ቃላት ለያይተን እናያለን።

ቢፅ = ማለት ጓደኛ፤ ወዳጅ፣ አብሮ አደግ ወዘተ ማለት ነው። የቃሉ ዓይነት ወይም ሥራ ደግሞ “ቅጽል” ወይም “ገላጭ” ይባላል።

ሐሳዊ = ማለት ውሸታም ፣ ሐሰተኛ ወይም በተቃራኒው የእውነተኛ ተቃራኒ ነው። የቃሉ ዓይነት ወይም ሥራ ደግሞ

“ቅጽል” ወይም “ገላጭ” ንው። ስለዚህ በአንድ ላይ “ቢፅ ሐሳዊ” ማለት ሐሰተኛ ጓደኛ፤ ሐሰተኛ ወዳጅ፣ ማለት ሲሆን  “ቢፅ” የተባለበት ምክንያት “ወዳጅ ወይም ጓደኛ መስሎ” ስለሚቀርብ ሲሆን “ ሐሳዊ” የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጓደኝነቱ የውሽትና በማስመሰል ላይ የተመሠረተ ስለሆነ ነው።

·         በዚህ ስም የሚጠራው ማነው ወይም እነማናቸው? ሐገርን፣ ቤተ ክርስቲያንንና ግለሰብንም ሊሆን ይችላል በድብቅ አሳልፈው የሚሰጡ፤ ወይም በሐገር፤ በቤተ ክርስቲያንና በያንዳንዱ ግለሰብ ሕይወት ላይ የውስጥ ለውስጥ ጥፋትን  የሚያዘጋጁ ክፉ ሰዎች ናቸው። ለምሳሌ “ይሁዳ” አምላኩን

እና መምህሩን ወዳጅ ናፋቂ አክባሪም መስሎ በመሳም ነበር አሳልፎ ለሮማ ጨካኝ ወታደሮች በ30 ብር የሸጠው።

·         ይህ ስም በብዛት የሚነገረው በየት ነው?

ይህ ኀረገ ቃል የሚነገረው በብዛት በቤተ ክርስቲያን እና በሐገር ታሪክ ጋር ተያይዞ ነው።

 

ለምንና በምን ምክንያትስ ይነገራል?

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ  አማኝ ወይም ኦርቶዶክሳዊ መስለው

·         በቤተ ክርስቲያን ስም እየኖሩ፤

·         ቤተክርስቲያን አገልጋይ አድርጋ

·         ሹማቸው ውስጥ ውስጡን ግን

·         ከመናፍቃን ጋር ተስማምተው

·         የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ለማፍረስ የሚጥሩ፤

·         ተከታዮቿን ወደ መናፍቃን የሚወስዱ ናቸው።

በሐገር ታሪክም እንደዚሁ ለአገራቸው ታማኝ መስለው በሥልጣን ላይ ለመቆየት ወይም ሥልጣን ለማግኘት ሲሉ

·         የሐገራቸውን ምሥጢር በማውጣት ለጠላት በመስጠት፤

·         የሐገሪቱ የጦር ኃይል እንዲዳከም ብሎም

·         በጠላት እንዲማረክ ውስጥ ውስጡን የሚሠሩ ናቸው። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ወይም ቢፅ ሐሳዊ 

አብያፅ ሐሳውያን ብንላቸውም እንችላለን ባማርኛ “ሐሰተኛ ወዳጆች” በጣም አደገኛ የቤተ ክርስቲያን እና የሐገር ጠላቶች ናቸው።

 ምክንያቱም እውነተኛ ወዳጅ ለሐገርም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን የታመኑ መስለው በድብቅ ስለሚሰሩ ነው።


መጻሕፍት ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ


 

 


 

No comments:

Post a Comment