Sunday, May 31, 2020

መጽሐፈ ነገሥት 1ኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 11/the book of 1st Kings bible study part...



“ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ”

 የሚባለው ይህ መጽሐፍ በአማርኛ ከተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መማርያ መጻሕፍት ብቸኛውና የመጀመሪያው መጽሐፍ ሲሆን 81ዱን ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ አጠቃሉ ይዧል፤ በመላው ዓለም በልዩ ልዩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ያለውን ልዩነት እና አንድነትም ግልጽና በማስረጃ የተደገፈ መሠረታዊ እውቀትን ያስጨብጠዎታል፤ እያንዳንዱን መጽሐፍ ከዘፍጥረት ጀምሮ ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍትን ጨምሮ
  የመጽሐፉ ጸሐፊ የተጻፈበት ዘመንና ቦታ
2     የመጽሐፉ ፍሬ ሐሳብ ባጭሩ
3     የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት ባጭር ትንታኔ
4          ምርጥ ጥቅሶ
5          ልዩና ያልተለመዱ
6         የመጽሐፉ መልእክት


በሚሉ ቁልፍ ነጥቦች መጻሕፍቱን በመከፋፈል ቀላል፤ግልጽ፤ አቋራጭና ዘመናዊ በሆነ ልዩ መንገድ ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። እንዲሁም ከ75 በላይ የክለሳ ጥያቄዎች እስከመልሶቻቸው አጠቃሎ ይዟል፤ ይህ መጽሐፍ  ሊኖረዎ ይገባል። ከዚህ በላይ ያለውን ቪዲዮም አዳምጡ በሳምንት አንድ ጊዜ በዚሁ መጽሐፍ መሠረት በአውደ ጥናት ቻናሌ (በዩቱብ) ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት ይሰጣል፤ ሰብስክራይብ በማድረግ ትምህርቱንም ይከታተሉ። መጽሐፉን ይዘው ቢከታተሉ ደግሞ የበለጠ ውጤት ይኖረዋል።

 ከመግዛት ከወሰኑ ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ፤ ወይም በ ይደውሉ +1 703 254 6601
ሠናይ ለክሙ

ከአውደ ጥናት
Click on the book

Saturday, May 30, 2020

ስም -አስማት - የመጠሪያ ስም እና የክርስትና ስም



የስመዎ ትርጉም ምን ማለት ነው? የልጆቸዎም ሆነ የእርሰዎ ስሞች ከአባት ስም ጋር ተያይዘው ሲነገሩ ስሕተት ይፈጥራሉ ወይምስ የተስማሙ ናቸው? ለወደፊቱ ስም ማውጣት ሲፈልጉ አውደ ጥናትን ይጎብኙ ቀድመውም ከአውደ ጥናት ይማሩ።
ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ
https://amzn.to/3ciLDAb   ወይም ይደውሉ +1 703 254 6601

ማን ይባላሉ? የስመዎ ትርጉምስ ምን ማለት ነው?
አስማት ምን ማለት ነው?
“አስማተ መለኮት” ይባላል?
አመተ ማርያም? ወይስ ዓመተ ማርያም?
በአውደ ጥናት ነገ በቀጥታ ስርጭት መልሶቹን ያገኛሉ
ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ፤ ወይም በ ይደውሉ +1 703 254 6601 















የክርስትና ስም  እና ትርጉሙ

ኀይለ ሥላሴ
ኀይለ መስቀል
ኀይለ ማርያም
ኀይለ ሚካኤ

ገብረ እግዚአብሔር
ገብረ ሥላሴ
ገብረ ማርያም

አመተ ማርያም
አመተ ኢየሱስ
አመተ ሥላሴ

ወልደ ኢየሱስ
ወልደ ማርያም
ወልደ ገብርኤል

ወለተ ኢየሱስ
ወለተ ማርያም

ፅጌ ማርያም
ፅጌ ድንግል
መዐዛ ማርያም
መዐዛ ድንግል
መዐዛ ሥላሴ
ሥርጉተ ሥላሴ
ሠርጸ ድንግል
ጽርሐ ጽሆን
ወልደ ሰንበት
ሥርጉተ ማርያም
ፀዳለ ማርያም
 እኅተ ማርያም

የመጠሪያ ስም
የመጠሪያ ስም እና የክርስትና ስም
·        በግእዝ
·        በሐምስ
·        በራብዕና
·        በሣብዕ
የሚጨርሱ ስሞች ከአባት ስም ጋር ለመያያዝ አመች ይሆናሉ።
·        በሳድስ
·        በካዕብ
·        በሣልስ
የሚጨርሱ ስሞች ከአባት ጋር አብረው መያያዝ ይኖርባቸዋል ብቻቸውን ስንጠራቸው ግን ሰዋስዋዊ ስሕተትን ይፈጥራሉ።

ለምሳሌ፡
በግእዝ የሚጨርስ ስም ብዙ ጊዜ ግስ ወይም ቨርብ ነው። ለምሳሌ
“አበበ” ግስ ነው ራሱን ችሎም ሊጠራ ይችላል ግን የቃሉ ባሕርይ ስም አይደለም “ግስ” ይባላል፤ “ግስ”ደግሞ የዐረፍተ ነገር ማሠሪያ ነው የሚሆነው፡

“ፍቅሩ” ይህ ቃል “ቅጽል” ነው ስምም ይሆናል፤ ግን ከአባት ስም ጋር ለማያያዝ ሲፈለግ ከሰዋስዋዊ ሕግ ውጭ በሆነ መልኩ ነው የሚያያዘው


“አለሚቱ” አለም የሚለው ቃል “ይህች ዓለም” ማለት ነው። ይህ ቃል ከ አባት ስም ጋር ሲያያዝ ወንድ እና ሴት የሚባል የዐረፍተ ነገር ወይም የግግር መዋቅርን ስለሚያፈርስ “ወንድ እና ሴት” የሚባል የአገባብ ስህተትን ይፈጥራል

Thursday, May 28, 2020

መጽሐፈ ሳሙኤል 2ኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 10/The Book of 2nd Samuel



ሰላም ለክሙ ዛሬ 12፡50ፒም ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 10 መጽሐፈ ሳሙኤል 2ኛን በቀጥታ
ሥርጭት እንማራለን በአውደ ጥናት እንገናኝ፤ ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን ከአውደ ጥናት

Tuesday, May 26, 2020

የእንግሊዘኛ ታሪክ መግቢያ


ሰላም ጤና ይስጥልኝ፡ ከአውደ ጥናት ነው።



ዛሬ አዲስ ዜናን ይዠላችሁ ቀርቤያለሁ፤ ይህ ዜና አዲስና መልካም ዜና ነው። ይኸውም አውደ ጥናት የእንግሊዘኛ ቋንቋን ለጀማሪዎች ለማስተማር መወሰኗን የሚያበሥር  ዜና ነው። 

እንደሚታወቀው የእንግሊዘኛ ቋንቋ የውዴታ ትምህርት ሳይሆን የግዴታ ነው። ምክንያቱም የዓለማችን ሁሉ አንደበትና የዕድገት መሣሪያ በመሆኑ በተለይ ለሥጋዊው ሕይወት መሳካት አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው።

አውደ ጥናትም ይህንን ተፈላጊነቱን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥቅሙን ተረድተው መማር የሚፈልጉትን ለመርዳት የግእዝን ቋንቋ በምታስተምርበት ዘዴ ቀላልና ግልጽ በሆነው የማስተማር ንድፋ እቅድ አውጥታ ለማስተማር በበጎፈቃድ መነሣቷን አበሥራችኋለሁ። 




ስለዚህ ከአሁኑ ሰብስክራይብ በማድረግ ትምህርቱ ሲጀመር ለመከታተል ተዘጋጅታችሁ ትጠብቁ ዘንድ አሳስባችኋለሁ። ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።

መጽሐፍ ቅዱስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን “የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው” ይላሉ፤ ይህም የማይታበል ሐቅ ነው። በአንጻሩም የትምህርትና የሥነ ጽሁፍ ምሁራን ደግሞ በበኩላቸው “የትምህርት መጀመሪያው ስለሚማሩት ትምህርት ስያሜና ይዘት፤ ታሪክና ጥቅም ጠንቅቆ ማወቅ ነው” ይላሉ።

እኛም ይህንኑ አባባል መሠረት በማድረግ ለመጀመር ስላሰብነው የእንግሊዘኛ ቋንቋ በመጠኑም ቢሆን እንደ መግቢያ ይሆነን ዘድን “እንግሊዘኛ” ምን ማለት ነው? የማን ቋንቋ ነው? እንዴትስ አሁን ከደረሰበት ከፍተኛ ደረጃ ደረስ? ለምንስ የግዴታ ትምህርት ሊሆን ቻለ? ወዘተርፈ የሚሉትን ነጥቦች መሠረት አድርገን እንነጋገራለን፤ መልካም ቆይታ።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት ከዚህ በታች ያለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ
 


እንግሊዘኛን አለመማር አይቻልም!You can not avoid learning English!

Brief History of English Language/የእንግሊዘኛ ቋንቋ አጭር ታሪክ
English language/የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት አጠቃላይ መግቢያ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ቅድመ ታሪክ ባጭሩ

Name:ስያሜ፡
እንግሊዘኛ/ኢንግሊዥ፡/English የኢንግላንድ ቋንቋ ነው፤ “ኢንግላንድ”/England ማለት ደግሞ “አንግለስ” እና “ላንድ” ከተባሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ሲሆን “አንግለስ” የሰው ስም ሲሆን “ላንድ” ማለት ደግሞ በእንግሊዘኛ ቋንቋ “መሬት ወይም ቦታ ማለት ነው። ስለዚህ “ኢንግላንድ”(Engla-Land) ማለት የአንግልስ ቦታ ወይም አገር ማለት ነው።
አንግልስ/Angles ማነው?
አንግልስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ (ከዌስተርን ጀርመን) ተነሥተው በመምጣት አሁን ኢንግላንድ የሚባለውን አገር በመያዝ ነዋሪዎቹን አስለቅቀው አገሩን ከተቆጣጠሩት ሦስት ሰዎች(Angles, Saxson, and Jules) መካከል አንዱ ነው። ስለዚህ ስያሜው የተመሠረተው ወይም የተወሰደው ከእርሱ ስም መሆኑ ነው። በመሆኑም ኢንግላንድ ማለት ዘላንድ ኦፍ አንግለስ ወይም በእንግሊዘኛው The Land of Angles ማለት ነው።

እንግሊዘኛ የኢንዶ ኤብሮፒያን ቋንቋዎች ቤተሰብ (Indo-Europian Family) ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ቋንቋ ሲሆን ምንጩ የምዕራባዊ ጀርመን ቋንቋ (West Germanic Language) እንደነበር ይነገራል። ይህ የቋንቋ ቤተሰብ የአውሮፓን፤የሕንድን፣ እና የኢራንን ቋንቋዎች የሚያቅፍ ግሩፕ ነው። ኢንዶ-ኤብሮፒያን(Indo-European Family)ፋሚሊ በዓለም ላይ “ከአፍሮአስያቲክ”(Afroasiatic”) ከሚባለው የቋንቋዎች ቤተሰብ ቀጥሎ ሁለተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል።

ስለ እንግሊዘኛ ቋንቋ ግኝትና እድገት ወይም ባጭሩ ቅድመ ታሪኩን እና አሁን የደረሰበትንም ደረጃ ለመረዳት የሚከተሉትን የዘመናት ክፍሎች ወይም ጊዜያት ባጭሩም ቢሆን ማየት አለብን።

እነዚህም
·        ከ55 ቅድመ ክርስቶስ(BC) - 600 ዓ/ም (AD) Ano domain
·        ከ600 -1100 ዓ/ም
·        ከ1100 -1500 ዓ/ም
·        ከ1500 -1700 ዓ/ም
·        ከ1700 - አሁን ያሉት ጊዜያት ናቸው።

1.  ከኢንግላንድ እና ከእንግሊዘኛ በፊት የነበረው ጊዜ/The Name “Englanድ” befor the language “English” 55BC to 600 AD
ቅድመ ብሪታንያ/ኢንግላንድ ይህ ጊዜ የመጀመሪያዎቹ ኢንዶ ኤብሮፒያውያን ወይም የአውሮፓ ቋንቋን የሚናገሩ አሁን ኢንግላንድ ወደምንለው አገር መጡ(ቀኑ በትክክል ባይታወቅም ከ55 ቅድመ ክርስቶስ(BC) እስከ 600 ዓ/ም(AD) ድረስ ነበር)።
ይህ ዘመን የጁልዮስ ቄስር ዘመን ሲሆን በ50 ዓ/ዓ (BC) አካባቢ ኢንግላንድ በሮማ ግዛት ስር ነበረች። ከ410 እስከ 600 (AD) ባለው ጊዜ ሮማውያን ከኢንግላንድ ወጡ። እስከዚህ ያለው ቅድመ ኢንግላንድ ነው።

2.   ጥንታዊው እንግሊዘኛ/“Old English” ከ600 to 1100 AD (Angles, SAxson, and Jules)
ከዚያም በ600 ዓ/ም(AD) (በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን/Cencury) Angles, Saxson, and Jules/እንግሌስ፣ ሳክሶንስ፣ እና ጁሌስ የሚባሉ 3 የጀርመን ጎሳዎች ወደ ኢንግላንድ ገብተው አገሪቱን በመቆጣጠር ኗሪዎቹን አስወጥተው እነሱ የበላይነትን ያዙ። “ኢንግላንድ” እና “እንግሊዘ”/England and English የሚባለው ስያሜ ለአገሩ እና ለቋንቋው የተሰጠበት ምክንያትም ከተጠቀሱት 3 ጉሳዎች መካከል በአንዱ ኢንግለስ ከተባለው ሰው ስም በመነሳት ነበር። በዚህ ግዜ የነበረው ቋንቋም ጥንታዊው (ኦልድ ኢንግሊዥ) የሚባለው ሲሆን፤ “አንግሎ-ሳክሶን ኢንግሊዥ”(Anglo-Saxson)  በመባልም ይታዎቃል።

ይህ ቋንቋ አሁን ካለው እንግሊዘኛ በጣም የተራራቀ ሲሆን የተስተካከለ የቋንቋ ይዘት አልነበረውም። “Engla” “Land”  = the land of Angles / “ኢንግላንድ” ማለትም “ኢንግላ” እና “ላንድ” አንድ ላይ በመናበብ የተፈጠረ ቃል ሲሆን ትርጉሙ  የአንግለስ መሬት ማለት ነው።

3.  መካከለኛው እንግሊዘኛ/Middle Englis 1100 to 1500
የሚድል ወይም መካከለኛው እንግሊዘኛ ዘመን የሚባለው ከ1100 – 1500 ዓ/ም የነበረው ዘመን ሲሆን በዚህ ዘመን የነበረው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ከጥንቱ እንግሊዘኛ በጣም የተሻለ እና አሁን ካለው ጋር በመጠኑም ቢሆን የሚቀራረብ ሲሆን ቋንቋው ለሥነ ጽሁፍ የበለጠ ብቁ ሆኖ የተዋቀረበት ልዩ ልዩ ሥነ ጽሁፎችና ግጥሞችም የተጻፉበት ነው። ሚድል እንግሊዘኛ የጀርመን ጎሳዎች ቋንቋ ስለሆነ ጀርመንኛ ተብሎ ነበር የሚታወቀው፤ ይህ መካከለኛው እንግሊዘኛ የሚባለው የቋንቋ አይነትም በጣም ብዙ የላቲን ቃላትን ይጠቀም ነበረ።

ይህ ዘመን ብሪትሽ ዓለምን በቅኝ ግዛት (Colonized/Colonizatio) መያዝ የጀመረችበት እና Christopher Columbos/ክርስቶፈር ኮሎምቦስ የተባለው አውሮፓዊ ሰው አሜሪካን ያገኘበት(1492) ዘመን ስለሆነ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዓለም አቀፋዊ ዕድገቱን የጀመረበት ወቅት ነበር።

4.   ከዘመናዊው ወይም አሁን ካለው እንግሊዘኛ ቀደም ብሎ የነበረው እንግሊዘኛ/Early modern English 1500 to 1700 AD
17ኛው ምዕት ዓመት (Early Modern English)  ወይም የእንግሊዘኛ ቋንቋ በጣም የተሻሻለበት እና የስነጽሁፍ እና የሳይንስ እድገት የተስፋፋበት ዘመን ሲሆን ታላቁ የዓለም የሥነ ጽሁፍ አባት የሚባለው ዊልያም ሸክስፒር(William Shakespeare) የተነሳበት ዘመን ስለ ነበረ በዚህ ዘመን የነበረው እንግሊዘኛ “Shakespearian English”/“ሸክስፒርያን” እንግሊዝ እየተባለም ይጠራ ነበር።

 በዚህ ጊዜ ብዙ የሥነጽሁፍ ሊቃውንት የሳይንስ ተመራማሪዎች የበዙበት ዘመን ስለነበረ ለሥነ ጽሁፋቸው መሳርያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ቃላትን ከተለያዩ አገሮች ቋንቋዎች እየወሰዱ ይጠቀሙ ነበር፤ ለምሳሌ ከላቲን፤ ከግሪክ ከሌሎችም ቋንቋዎች በመውሰድ ይጠቀሙ ስለነበር አሁን ወደፊት እንደምናየው እንግሊዘኛ ብዙ የተውሶ ቃላትን ሰብስቦ ይገኛል።

5.  አሁን ያለው እንግሊዘኛ/Present Day English 1700 up to today
በአሁኑ ጊዜ ያለው እንግሊዘኛ/Present day English/ አሁን እንግሊዘኛ ከአካባቢ ቋንቋነት ወደ ዓለም አቀፋዊነት ተሸጋግሯል. ይህ ዘመን ከ17ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ ሲሆን እንግሊዘኛ የቋንቋ መዋቅሩን በከፍተኛ ደረጃ አስተካክሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን እያገኘ የመጣበት ጊዜ ነው።

እንግሊዘኛ እንዴት አለም አቀፍ ሊሆን ቻለ?
የእንግሊዘኛን ቋንቋ የዓለም ቋንቋ ወይም ቍጥር አንድ በዓለም ዙሪያ ተፈላጊ እንዲሆን ካስቻሉት ምክንያቶች የሚከተሉት ሁለቱ አበይት ነጥቦች ናቸው።

1.  ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (in the 16th century) ጀምሮ የብሪታንያ አንድ አራተኛ የሚሆነውን የአለም ክፍል በቅኝ ግዛት ይዛ ስለ ተቆጣጠረቺው የእንግሊዘኛን ቋንቋ በዓለም ዙሪያ ሰዎች እንዲማሩት ግድ ሆኗባቸዋል።

2.  በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (in the 20th century) እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆነቺው አሜሪካ በኢኮኖሚ፤ በተክኖሎጂ እና በጦርኃይልም ወዘተርፈ ዓለምን በበላይነት መምራት በመቻሏ እነዚህ ሁለት ኀያላን የቋንቋው ባለቤቶች ቋንቋቸውን የአለማት አንደበት እንዲሆን አድርገውታል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንግሊዘኛ በአለም ሕዝብ አእምሮ እንዲቀረጽና ለመማርም በቋንቋው ላይ ፍላጎቱ እንዲኖረውና ያለው ፍላጎትም እያደገ እንዲሄድ ካደረጉት ዘመን አመጣሽ ምክንያቶ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው።

የአሜሪካ ልዩ ልዩ ሥጋዊ ሥሜትን የሚያጠናክሩ ወይም የሚያነሳሱ ሙቪዎች(Movies) ወይም ትዕይንቶች፤ የቴሌቪዥን ድራማዎች፤(TV Shows/Dramas) ልዩ ልዩ ሙቃዎች(Musics) ዘዘተ በሕዝቡ በተለይም በወጣቱ አእምሮ እንዲገባና የሚያየውንና የሚሰማውን ለመገንዘብ የሚተላለፍበትን ቋንቋ ለማወቅ ጽኑ ፍላጎት እንዲያድርበት አድርገውታል።

እንግሊዘኛ ከሌሎች ቋንቋዎች የተወሰዱ ቃላት ስብስብ ነው
እንግሊዘኛ ከተወለደ ወደ ሦስት ሺህ ዓመታትን አሳልፏል፤ አሁን ካለበት ለመድረስም ከላይ እንዳየነው ብዙ የመሻሻልና የእድገት ጉዞዎችን አድርጓል፤  እንግሊዘኛ ከብዙ የዓለማችን በተለይ ታላላቅ ከሚባሉት ከላቲን፤ ከግሪክ፤ ከፈረንሳይ ወዘተ ቋንቋዎች ብዙ ቃላትን የተዋሰ እንደሆነ የታሪክ መዛግብትና በተለይም በቋንቋው ውስጥ የማናገኛቸው ቃላት ይናገራል(ይመሰክራሉ)፤ የሚከተለው ከያንዳንዱ ቋንቋ ምን ያህሉን በእንግሊዘኛ ውስት እንደምናገኘው የሚያሳይ ስሌት ነው።

·         በእንግሊዘኛ ቋንቋ ውስጥ የሚገኙትን የባዕድ ቋላት በፐርሰንት ሲያስቀምጡት
·         ከላቲን 29%
·         ከፈረንሳይኛ 29%
·         ከጀርመንኛ 26%
·         ከግረክኛ 6%
·         ከሌሎች(የማይታወቁ) 6% እና
·         ከተለያዩ የመጠሪያ ስሞች 4% የሚሆኑ ቃላትን ይጠቀማል።

እንግሊዘኛ በዓለማች እንግሊዘኛ በአለም አንደኛና ብቸኛው አለም አቀፍ መግባቢያ ነው።
·        ከ380 ሚሊየን በላይ ለሚሆን ሕዝብ የአፍ መፍቻ/Native speakers ቋንቋ ነው
·        ከ300 ሚሊየን በላይ ለሚሆን ሕዝብ 2ኛ ቋንቋቸው ነው/As Second language speakers
·        ከ1.5 ቢሊየን በላይ የሚሆን ሕዝብ እየተማረው ይገኛል
·        ባለ ሙያዎች እንደሚተነብዩት በ2050ዓ/ም ላይ የዓለማችን ግማሽ የሚሆነው ሕዝብ የእንግሊዘኛን ቋንቋ አቀላጥፎ መናገር እንደሚችል ይተነብያሉ።

 “ማንዳሪን”(Mandarin)የተባለው የቻይና ቋንቋ ብቻ በነቲብ ተናጋሪዎች(Native Speakers)ብቻ እንግሊዘኛን ይበልጠዋል (አፍ መፍቻቸው በሆኑ ሰዎች ብቻ ማለት ነው እንጂ በዓለም ላይ ብዙ ሕዝብ የሚናገረው ማለት አይደለም)
እንግሊዘኛ በዓለም አገሮችና መንግሥታት እንዲሁም ታዋቂ ድርጅቶች፤ የሥራ መስኮች
እንግሊዘኛ፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የሥራ፤ የዓለም አቀፍ ግንኙነት፤ የኮምፕዩተር፤ የኢንተርኔት ወዘተርፈ ቋንቋ ነው፤

እንግሊዘኛ ብሔራዊ ቋንቋቸው ከሆኑት አገሮች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው

እንግሊዘኛ፡
·        የታላቋ ብሪታንያ/Great Britine
·        አየር ላንድ/Irland
·        ኒውዘር ላንድ/New zearland
·        የተባበሩት አሜሪካ/United states
·        የካናዳ/Canada
·        የአውስትራሊያ/Australia
·        /Careavian  ብሔራዊ ቋንቋ ነው

እንግሊዘኛን የሥራ ቋንቋቸው አድርገው ከሚጠቀሙ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

·        የተባበሩት መንግሥታት(United Nations)
·        የአውሮፓ ሕብረት(Europian Union)
·        የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት(NATO)
·        የዓለም የጠና ድርጅት የሥራ ቋንቋ ነው(WHO)

እንግሊዘኛ ግዴታ እንጅ አማራጭ የማይኖንባቸው ሥራዎች
·        በአለም አቀፍ የጎብኝዎች ወይም የጉብኝት ሥራ/Traveling
·        በጋዜጠኝነት ሥራ/Jornalism
·        በኮምፕ ዩተር ሥራ/Computers
·        በአይሮፕላን በረራ መቆጣጠሪያ ሥራ/Airtrafic controling ወዘተ መሥራት ከፈለጉ እንግሊዘኛን አለመማር አይችሉም

የእንግሊዘኛ ቃላት የልዩ ልዩ ሳይንሳዊ ስያሜዎች የተጻፉባቸው ናቸው
ለምሳሌ
·        የቴክኖሎጅ/Technologe
·        የሕክምና/Medical
·        የመድኃኒቶች/Medicine ወዘተ ስሞች የእንግሊዘኛናቸው(ከላቲን እና ከግሪክ የተዋቀሩ)
·        የቴኦሎጅTheology)
ለምሳሌ የሚከተሉትን ቃላት መጥቀስ ይቻላል
·        ፔዲያትሪክ/Pediatric
·        ኦርሶፐዲክ/Orthopedic
·        ኦፍሳልሞሎጊስት/Ophthalmologist
·        ቴኦሎጊ/ጂያን/Theology

በዓለማችን በአሁኑ ጊዜ ከ96% በላይ የሚሆኑት የሳይንሳዊ ጥናት ጽሁፎች ተጽፈው የሚገኙት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው። ይህ ማለት ከመቶ 4 ብቻ ነው በሌሎች የአለም ቋንቋዎች ተጽፈው የምናገኘው።

የእንግሊዘኛ ቃላት ብዛትና እንግሊዘኛ የአፍ መፍቻው የሆነ ግለስብ ሊያውቃቸው ይችላል ተብሎ የሚገመቱ የቃላት ብዛት።
ቃላትን ለመቁጠር አስቸጋሪ እንደሆነ ቢናገሩም በተቀራረበ ወይም በአማካኝ ከ1 ሚሊየን በላይ ቃላት እንዳሉት ምሁራኑ (የሊንጉስቲክ ወይም የቋንቋ ጥናት ምሁራን) ይናገራሉ።

እንግሊዘኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋው የሆነ አንድ ሰው
ከ20 ሺህ እስከ 35 ሺህ ቃላትን ሊናገር ይችላል። ስለዚህ አንድ ሰው ከአንድ ሚሊየን ቃላት ውስጥ 20 ሺህ የሚሆኑትን ካወቀ አቀላጥፎ መናገር መጻፍና ማንበብ ይችላል ማለት ነው።

በመሆኑም እንግሊዘኛን አለመማር አይቻልም/You can not avoid learning it. ለምን?
·        የአለማችን መናገሪያ አንደበት ነው
·        ከ380 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው
·        ከ300 ሚሊየን በላይ ለሚሆነው ሕዝብ 2ኛ ቋንቋ ነው
·        ከ28 በላይ ለሚሆኑ አገሮች ብሔራዊ ቋንቋቸው ነው
·        ከ1.5 ቢሊየን በላይ የሚሆነው የአለም ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ እየተማረው ይገኛል
·        ታላላቅ ለሆኑ አለም አቀፍ ድርጅቶች የሥራ ቋንቋ ነው
·        የኮምፕዩተር፤ የኢንተርኔት፤ የቴክኖሎጅም ብቸኛው ቋንቋ ነው
·        96% (ዘጠና ስድስት ከመቶ) የሚሆነው የምርምር ጽሁፍ) የተጻፈው በእንግሊዘኛ ነው
·         በ2050 ዓ/ም ከግማሽ በላይ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ የእንግሊዘኛ ተጠቃሚ እንደሚሆን ይተነበያል
እነዚህ ባጭሩ እና ጥቂቶቹ ናቸው!

ስለዚህ እንግሊዘኛን አለመማር አይቻልም/Therefore, You can not avoid learnig English!


ቁልፍ የሆኑ ቃላት
·         BC(before Christ or before the current area) - ቅድመ ክርስቶስ
·         AD(Ano Domain) - ዓመተ ምሕረት (ዓመተ እግዚእ)
·         Native speakers (የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ሰዎች ነቲብ ስፒከርስ ይባላሉ)
·         Century = ምዕተ ዐመት

የእንግሊዘኛ ታሪክ



ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት ከዚህ በታች ያለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ



ሰላም ጤና ይስጥልኝ፡ ከአውደ ጥናት ነው።


ዛሬ አዲስና ለየት ያለ ዜናን ይዠላችሁ ቀርቤያለሁ፤ ይህ ዜና ለብዙዎቻችሁ በተለይም አውደ ጥናትን ለምታውቁና የአውደ ጥናትን የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ለተገነዘባችሁ ሁሉ መልካምና አስደሳች ዜና ነው ብየ አምናለሁ ።

ይኸውም አውደ ጥናት የእንግሊዘኛ ቋንቋን ለጀማሪዎች ለማስተማር መወሰኗን የሚያበሥር  ዜና ነው። እንደሚታወቀው የእንግሊዘኛ ቋንቋ የውዴታ ትምህርት ሳይሆን የግዴታ ትምህርት ነው። ምክንያቱም የዓለማችን ሁሉ አንደበትና የዕድገት መሣሪያ በመሆኑ በተለይ ለሥጋዊው ሕይወት መሳካት አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው። ስለዚህ ቢያንስ የውዴታ ግዴታ ነው ማለት ነው።

አውደ ጥናትም ይህንን የእንግሊዘኛን ቋንቋ ተፈላጊነት ግምት ውስጥ በማስገባት ጥቅሙን ተረድተው ይልቁንም በቋንቋቸው እንግሊዘኛን መማር የሚፈልጉትን ለመርዳት የግእዝን ቋንቋ በምታስተምርበት ዘዴ ቀላልና ግልጽ በሆነው የማስተማር ንድፋ እቅድ አውጥታ ለማስተማር በበጎ ፈቃድ መነሣቷን በደስታ አበሥራችኋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ አውደ ጥናትን ሰብስክራይብ በማድረግ ትምህርቱ ሲጀመር ለመከታተል ተዘጋጅታችሁ መጠበቅ ይኖርባችኋል። ከዚህ ቀጥየ ስለ እንግሊዘኛ ቋንቋ ታሪካዊ አመጣጥ አጭር ማብራርያን እሰጣችኋለሁ እንከታተል።

መጽሐፍ ቅዱስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን “የጥበብ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው” ይላሉ፤ ይህም የማይታበል ሐቅ ነው። በአንጻሩም የትምህርትና የሥነ ጽሁፍ ምሁራን ደግሞ በበኩላቸው “የትምህርት መጀመሪያው ስለሚማሩት ትምህርት ስያሜና ይዘት፤ ታሪክና ጥቅም ጠንቅቆ ማወቅ ነው” ይላሉ። ይህም አባባል በበኩሉ ተግባራዊ እውነት አለው።

እኛም ይህንኑ አባባል መሠረት በማድረግ ለመጀመር ስላሰብነው የእንግሊዘኛ ቋንቋ በመጠኑም ቢሆን እንደ መግቢያ ይሆነን ዘድን “እንግሊዘኛ” ምን ማለት ነው? የማን ቋንቋ ነው? እንዴትስ አሁን ከደረሰበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረስ? ለምንስ የግዴታ ትምህርት ወይም የውዴታ ግዴታ ሊሆን ቻለ? ወዘተርፈ የሚሉትን ነጥቦች በመዳሰስ እንነጋገራለን፤ እንከታተል መልካም ቆይታ።

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስያሜና ምድብ
አብዛኛዎቻችን እንደምናውቀው እንግሊዘኛ የኢንግላንድ ቋንቋ ነው፤ “ኢንግላንድ” ደግሞ የታላቋ ብሪታንያ ሌላው ስሟ ነው፤ “ኢንግላንድ” የሚለው የቃሉ ትርጉም ግን  “ኤንግልስ” እና “ላንድ” ከተባሉ ሁለት የተለያዩ ቃላት የተመሠረተ ሲሆን “ኤንግለስ” የአንድ ጥንታዊ ሰው መጠሪያ ስም ።  “ላንድ” የሚለው ሁለተኛው ቃል ደግሞ በእንግሊዘኛ ቋንቋ “መሬት ወይም ቦታ ማለት ነው። ስለዚህ “ኢንግላንድ” ማለት የኤንግለስ ቦታ ወይም አገር ማለት ነው። ይህም በእንግሊዘኛው (The Land of Angles) እንደ ማለት ሲሆን የኤንግለስ መሬት ወይም አገር ተብሎ ይተረጎማል።

ኤንግልስ ማነው?
ኤንግለስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ወይም ከምዕራባዊው ጀርመን ተነሥተው አሁን ኢንግላንድ ወደ ሚባለው ቦታ መጥተው አካባቢውን በመያዝ ነዋሪዎቹን አስለቅቀው አገሩን ከተቆጣጠሩት ኤንግልስ፣ ሳክስንስ፣ እና ጁለስ ከተባሉት ሦስት ሰዎች(Angles, Saxson, and Jules) መካከል አንዱ ነው። ስለዚህ ኢንግላንድ የሚለው ስያሜ የተወሰደው ከዚሁ ኤንግልስ ከተባለው አውሮፓዊ ወይም ጀርመናዊ ሰው ስም በመነሣት ነው። በመሆኑም የእርሱ አገርና ቋንቋ መሆኑን ለመግለጽ በስሙ አገሩን ኢንግላንድ፤ ቋንቋውን ደግሞ “ኢንግሊዥ” ብለውታል።

እንግሊዘኛ የኢንዶ ኤብሮፒያን ቋንቋዎች ቤተሰብ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ቋንቋ ሲሆን ምንጩ የምዕራባዊ ጀርመን ቋንቋ እንደነበር ይነገራል። ይህ የቋንቋ ቤተ ሰብ የአውሮፓን፤ የሕንድን፣ እና የኢራንን ቋንቋዎች የሚያቅፍ የቋንቋ ቤተሰብ ነው። ይህ ኢንዶ-ኤብሮፒያን ቤተሰብ የሚባለው የቋንቋ ስብስብ በዓለም ላይ “አፍሮ-አስያቲክ” ከሚባለው የቋንቋዎች ቤተሰብ ቀጥሎ ሁለተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። አፍሮ-አስያቲክ የሚባለው የቋንቋ ቤተሰብ ግን ከዓለም አንደኛው ሲሆን የሰመቲክ ወይም የእኛ ቋንቋዎች ሁሉ የሚጠቃለሉት በአፍሮ-አስያቲክ ቤተሰብ ቋንቋዎች ሥር ነው።

እንግሊዘኛ ከ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ወደ ሦስት ሺህ ለሚጠጉ ዓመታት ራሱን እያሻሻለ እያደገ አሁን ከደረሰበት አለም አቀፍ ቋንቋነት ደርሷል።
 እንግሊዘኛ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ሲነጻጸር በዕድሜ በጣም ጥንታዊ ባይሆንም ከ 1 ሚሊየን በላይ ቃላት ያሉትና ከልዩ ልዩ ጥንታውያን ቋንቋዎች የተወሰዱ ብዙ ቃላትንም ሰብስቦ የያዘ ቋንቋ ነው። በነዚህ ልዩ ልዩ ጉዞዎቹም ከእድገቱ ጋር አብረው የተጓዙ ልዩ ልዩ ስያሜዎችም ነበሩት ለምሳሌ፤ ጀርመኒክ ላንጉች(የጀርመን ቋንቋ)፤ አንግሎ-ሳክሰንስ ኢንግሊዥ ወይም የአንግሎ ሳክሰን እንግሊዘኛ፤  ሸክስፒሪያን ኢንግልዥ፤ ወይም የሸክስፒር እንግሊዘኛ እየተባለ ይጠራ ነበር።

በአሁኑ ጊዜ እንግሊዘኛ በዓለማችን አንደኛና ብቸኛው አለም አቀፍ መግባቢያ ነው። የአለም አቀፍ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ግንኙነት፤ የሥራ ቋንቅው ነው፤ የኮምፕዩተር፤ የኢንተርኔት የሌሎችም ቁልፍ የሆኑ ሥልጣኔ ወለድ ሥራዎችና መሣሪያዎች ቋንቋ ነው።

ለምሳሌ፡
·        የተባበሩት መንግሥታት ወይም (United Nations)
·        የአውሮፓ ሕብረት ወይም (Europian Union)
·        የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ወይም (NATO)
·        የዓለም የጠና ድርጅት ወይም (WHO) የሥራ ቋንቋ ነው።
የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያዎች እንግሊዘኛን አለመማር እንደማይቻል ሲናገሩ

ምክንያቱም ይላሉ
·        የአለማችን መግባብያ አንደበት ነው
·        ከ380 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው
·        ከ300 ሚሊየን በላይ ለሚሆነው ሕዝብ 2ኛ ቋንቋ ነው
·        ከ28 በላይ ለሚሆኑ አገሮች ብሔራዊ ቋንቋቸው ነው
·        በዓለም አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መማሪያ ቋንቋ ነው
·        ከ1.5 ቢሊየን በላይ የሚሆነው የአለም ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ እየተማረው ይገኛል
·        ታላላቅና ቁልፍ ለሆኑ አለም አቀፍ ድርጅቶች የሥራ ቋንቋ ነው
·         የኮምፕዩተር፤ የኢንተርኔት፤ የሌሎችም ልዩ ልዩ ቴክኖሎጅ-ነክ ለሆኑ የሥራ መስኮች ብቸኛው ቋንቋ ነው
·         በዓለም ላይ 96% ወይም ዘጠና ስድስት ከመቶ የሚሆነው የምርምር ሥነ ጽሁፍ የተጻፈው በእንግሊዘኛ ነው
·          ከ50 ዓመታት በኋላ በዓለማችን ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የእንግሊዘኛ ተጠቃሚ እንደሚሆን ይተነበያል። ይላሉ

ታዲያ ከዚህ በላይ ባየናቸው አጭር የእንግሊዘኛ ዓለም አቀፍ ድርሻዎች መሠረት እንግሊዘኛን አለመማር ጉዳት አለው? ወይስ የለውም? መልሱን ከናንተ።


ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
መልካም ትምህርት
ከአውደ ጥናት



ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት ከዚህ በታች ያለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ