Sunday, December 27, 2020
ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ በግእዝ ቋንቋ
በአውደ ጥናት የአማርኛ ትምህርትን በተመለከተ ማብራርያ
Wednesday, December 23, 2020
Monday, December 21, 2020
What do you know About Awde Tinat/ ስለ አውደ ጥናት ምን ያውቃሉ?
Thursday, December 17, 2020
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በአውደ ጥናት
Wednesday, December 16, 2020
Daily Prayers in Amharic Language/የዘወትር ጸሎት በአማርኛ ቋንቋ መጽሐፍ ለማንበብ የምትቸገሩ ...
Saturday, December 12, 2020
Wednesday, December 2, 2020
Monday, November 30, 2020
ፊደሎቻችንን በዜማ፡ ሁሉም የግአዝና የአማርኛ ሆሄያት በዜማ ቀርበዋል ራሰዎንም ሆነ ልጆቸዎን በቀላሉ ሊታወስ በሚ...
Wednesday, November 18, 2020
በአውደ ጥናት በኩል በአማዞን የሚገኙ/የሚሽጡ መጻሕፍት
Tuesday, November 3, 2020
ውዳሴ ማርያም ዘሰሉስ ከአንቲ ውእቱ ዕፅ አስከ መጨረሻው ክልፍ 3
Monday, October 12, 2020
የግእዝ ትምህርት ምዝገባ
ሰላም ለክሙ
ለ2021/2013 ዓ/ም የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ተመዝጋቢዎች ሁሉ
1ኛ የቅድመ ዝግጀት ትምህርት ስላለን ቶሎ በመመዝገብ ዝግጅት አድርጉ
2ኛ. በዌስተርን ዩኒየን እና በመኒግራም የምትከፍሉ ሁሉ መጀመሪያ እኔን በዋትስአብ ደውላችሁ ፣ በድምጽ፣ ወይም በጽሁፍ መልእት አነጋግሩኝ። በባንክ፣ በ"Zelle" እና በሌሎች ተመሳሳ መንገዶች የምትከፍሉ ግን የአካውንት ቊጥሬ ካላችሁ መካክና ደረሰኙን ወደ እኔ መላክ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ
3ኛ. ሌላ የተሻለ መንገድ እየፈለግሁ ስለሆነ ለመጻሕፍት የተተመነውን ተጨማሪ ክፍያ እንዳትከፍሉ (ትምህርቱን ለመማር መጽሐፉን መግዛት አሁን ግዴታ አይደለም)
ሠናይ ለክሙ
ወእግዚአብሔር ምስሌክሙ
እም አውደ ጥናት ዘግእዝ
Monday, September 14, 2020
Friday, September 11, 2020
የዘመኑ ታሪክ
የዘመኑ ታሪክ
Thursday, September 10, 2020
Tuesday, September 1, 2020
Thursday, August 27, 2020
Personal pronouns part 8
Personal pronouns part 8
Personal pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውን/
ሰብአዊ ወይም አካላዊ የስም ተለዋጮች
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው፤ በዛሬው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ስለ personal
pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ ነው የምንማረው። ባለፈው እንደመግቢያ እንዳየነው pronounse/ፕሮናውንስ ብዙ ዓይነት እንደሆኑ፤
ከብዙዎቹ መካከልም አንድዱ “ፐርሰናል ፕሮናውን/personal pronoun” የሚባለው እንደሆነና “ፐርሰናል ፕሮናውንስ” ራሳቸው
በ3 እንደሚከፈሉ። ተነጋግረን ነበር።
ስለዚህ ዛሬ ስለ ሦስቱ የስም ተለዋጭ/personal
pronouns ዓይነቶች በምሳሌ እናያለን እንከታተል። ሰብስክራይብ እና ሽር ማድረግን አትርሱ።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ
መጻሕፍት ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ በአድራሻዎ ይላክለዎታል።
ባለፈው ባጭሩ እንደጠቀስኩት Personal Pronouns/ፐርሰናል ፕሮናውንስ በ3 ዐበይት
ክፍሎች ይከፈላሉ፤ እነሱም
1. Subjective/ስብጀክቲብ (ባለቤት የሚሆኑ)
2. Objective/ኦብጀክቲቭ(ተሳቢ የሚሆኑ) እና
3.
Possessive
pronouns/ፖሰሲብ (ባለቤትነትን አመልካች) ፕሮናውንስ የሚባሉት
ሲሆኑ Subjective/ሰብጀክቲቭ የዐ/ነገር ባለቤት፣ Objective/ኦብጀክቲቭ ተሳቢ፣ Possessive/ፖሰሲብ ደግሞ ባለቤትነትን
የሚጠቁም ወይም የሚያመለክቱ ተውላጠ ስሞች ናቸው።
ከዚህ በታች ባሉት 4 የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ዐረፍተ ነገራት ሦስቱን የስም ተለዋጮችና እንዴት ዓይነት አገልግሎትን
እንደሚሰቱ እንመለከታለን ተከታተሉ። በተጓዳኝም ስለ ዐረፍተ ነገራቱ መዋቅር እና ስለ እያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ
ባጭሩ እንዳስሳለን።
በመጀመሪያ በአማርኛችን ግልጽ እንዲሆንልን የአማርኛውን
ዐ/ነገራት አንድ በአንድ አስረዳና ወደ እንግሊዘኛው አልፋለሁ። በቀይ በተጻፉት ወይም ቀስቱ የተመለከተባቸውን ቃላት ላይ የበለጠ
አትኩሮት ስጡ።
ምሳሌዎቹ የሚናገሩት ስላለፈ ጊዜ ነው፤ ትምህርታችን
ግን የሚያተኩረው ስለ ጊዜው ሳይሆን ስለ ዐረፍተ ነገር ባለቤቶች እና ተሳቢዎች ነው።
ማለትም “ፐርሰናል ፕሮናውንስ” ስለሚባሉት አርእስት ነው።
በተሰጡት 4 ዐ/ነገራት ውስጥ ሰብጀክቲብ/Subjective፤ኦብጀክቲብ/
Objective እና ፖሰሲቭ/Possessive ፕሮናውንስ/Pronouns የሚባሉት አገባቦች ይገኛሉ። ይህ ማለት ሦስቱም የስም ተለዋጭ
ዓይነቶች ወይም ፕሮናውንስ ይገኙበታል ማለት ነው።
በመጀመሪያው ዐ/ነገር “እኔ” እና “አቤል” የሚባሉት ሁለት ቃላት ናቸው የሚፈለጉት። “እኔ” የሚለው የስም ተለዋጭ ሲሆን በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም
ሥራውን የሠራው አካል ነው። በእንግሊዘኛው “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን/Subjective
Pronoun” ይባላል። ባለቤታዊ የስም ተለዋጭ ማለት ነው። ወይም በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ በባለቤትነት የተጠቀሰውን ሰው
ወይም አካል ተክቶ የሚሠራ የስም ተለዋጭ ነው።
“አቤል” የሚለው ቃል ግን የስም ተለዋጭ ሳይሆን ራሱ የሰው ስም ነው። የሥራ ድርሻውም ተሳቢ “ኦብጀክት” መሆን ነው። ስለዚህ በስም ተለዋጭ ሲተካ “እሱን” ማለት ይሆናል፤ በሁለተኛው ዐ/ነገር ላይ ተጠቅሷል። “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን” “who/ማን”? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ የስም ተለዋጭ ነው።
በሁለተኛው ዐ/ነገር “እኔ” እና “እሱን” የሚባሉት ሁለት ቃላት ናቸው የሚፈለጉት። “እኔ” የሚለው የስም ተለዋጭ ሲሆን በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት ወይም
ሥራውን የሠራው አካል ነው። በእንግሊዘኛው “ሰብጀክቲቭ ፕሮናውን/Subjective
pronoun” ይባላል ባለቤታዊ የስም ተለዋጭ ማለት ነው።
“እሱ” የሚለው ቃል ከላይ “አቤል” ብለን የጠቀስነው “ኦብጀክቲቭ
ናውን/Objective” “እሱን” በሚለው የስም ተለዋጭ ተተክቷል።
ይህም “ኦብጀክቲቭ ፕሮናውን/Objective” የሚባለው ነው። ኦብጀክቲብ ፕሮናውንስ
“ምንን whom”? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው።
በሦስተኛው ዐ/ነገር “የእኔ” የሚለው ቃል ብቻ ነው በዚህ
ትምህርታችን የሚፈለገው። ይህ ባለቤትነትን የሚያመለክት የስም ተለዋጭ ወይም ፖሰሲብ ፕሮናውን ይባላል። ምክንያቱም መጽሐፉ የእኔ
መሆኑን የሚገልጽ ወይም የሚናገር ስለሆነ ነው። ይህም “የማን/whose” ? የሚለውን
ጥያቄ የሚመልስ አመልካች ነው።
በአራተኛው ዐ/ነገር “የእኔ” የሚለው ቃል ብቻ ነው በዚህ
ትምህርታችን የሚፈለገው። ይህ የስም ተለዋጭ እንደ ሦስተኛው የስም ተለዋጭ ባለቤትነትን የሚያመለክት ሲሆን ሁለቱ የሚለዩት
የሚመለከተውን ወይም በዚህ ዐረፍተ ነገር “መጽሐፍ” የሚለውን ንብረት ከፊት ለፊታቸው
ወይም ከኋላቸው በማስቀመጥ ነው።
ስለዚህ 3ኛው የስም ተለዋጭ “ፖሰሲብ አድጀክቲቭ/Possessive
Adjective” ይባላል (ቅጽላዊ አመልካች ማለት ነው)
በ4ኛው ዐ/ነገር የሚገኘው የስም ተለዋጭ ደግሞ
“ፖሰሲብ ፕሮናውን/Possessive
Pronoun”(ባለቤታዊ አመልካች) ይባላል። ወደፊት የሁለቱን ልዩነት በሰፊው እንማራለን።
ዐረፍተ ነገራቱን እናንብ ።
1.
እኔ ትላንት አቤልን ዐየሁት
2.
እኔ ትላንት እሱን ዐየሁት
3.
ይህ የእኔ መጽሐፍ ነው
4.
ይህ መጽሐፍ የእኔ ነው
·
I saw Abel yesterday
አይ ሳው(ሳ) አቤል የስተርደይ
እኔ አቤልን ትናንት አየሁት
·
I saw him yesterday
አይ ሳው ሒም የስተርደይ
እኔ እሱን ትላንት አየሁት
·
This is my book
ዚስ ኢዝ ምይ ቡክ
ይህ የእኔ መጽሐፍ ነው
·
This book is mine
ዚስ ቡክ ኢዝ ማይን
ይህ መጽሐፍ የእኔ ነው
Read on you phone this English E book
መጽሐፉ አካላዊ ሳይሆን በስልክ ወይም
በሌላ ኤሌክትሮኒስ መሳሪያ የሚነበብ (ኪንድል ቡክ ነው) በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንደኝነት አልፈው ሽልማትን ያስገኙ የእንግሊዘኛ
ግጥሞቼ ናቸው
ቃላት/wors
Subject/Subjective = ርዕስ፣ ርዕሰ ጉዳይ (በዚህ ትምህርታችን የዐረፍተ ነገር ባለቤት)
Object/Objective = ነገር፣ አካል፣ (በዚህ ትምህርታችን ተሳቢ)
Possessive = የባለቤት አመልካች (ንብረትን እና ባለ ንብረትን የሚያመለክት)
To see – saw = ማየት፣ ሃላፊ ጊዜ(አየሁ)
1ኛ መደብ/አካል = First person(s)
2ኛ መደብ/አካል = second person(s)
3ኛ መደቦች/አካል = Third Person(s)
ለዛሬው
ከዚህ ላይ ይበቃናል
ልዑል
አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ
ምዝገባ
ሰላም ለክሙ አርድእተ የ2021/2013 ዓ/ም የልሣነ ግእዝ ትምህርት ዓመታዊ ምዝገባ ተጀመረ!
ሰላም ለክሙ አርድእተ የ2021/2013
ዓ/ም የልሣነ ግእዝ ትምህርት ዓመታዊ ምዝገባ ተጀመረ!
ከአፍሪካ ተማሪዎች በስተቀር ከያንዳንዱ ተማሪ $15፤ ከአፍሪካ ተማሪዎች 250 ብር በኦረሚያ ክልል በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያ ቤተሰዎችና ንበረታቸው ለወደመ ወገኖች በርዳታ ይሰጣል።
መጻሕፍት ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን
ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ በአድራሻዎ ይላክለዎታል።
Friday, August 21, 2020
ቢፅ ሐሳዊ/Deceiver Friend
ቢፅ ሐሳዊ/Deceiver Friend
ቢፅ
ሐሳዊ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው ዛሬ ቃላትን እና ኃረጋትን ወይም ዐረፍተ ነገራትን በምናብራራበት ዝግጅት የምናየው “ቢፅ ሐሣዊ” የሚለውን ኃረግ ነው። ኃረግ የሚባለው እንደምታውቁት ከአንድ በላይ ቃላትን የያዘ ነው። በመሆኑም “ቢፅ ሐሳዊ” የሚለው ሐረግ ሁለት ቃላትን ይዟል፤ ሁለቱም ቃላት ቅጽሎች ናቸው። በትርጉም ግን ሁለቱ የተለያዩ ናቸው። ቢፅ ሐሳዊ የሚለው ኀረግ
·
ምን ማለት ነው?
·
በዚህ ስም የሚጠራው ማነው ወይም እነማናቸው?
·
ይህ ስም በብዛት የሚነገረው በየት ነው?
·
ለምንና በምን ምክንያትስ ይነገራል? የሚሉትን 4
ጥያቄዎችን እናያለን እንከታተል።
መን ማለት ነው፡ ሁለቱንም ቃላት ለያይተን እናያለን።
ቢፅ = ማለት ጓደኛ፤ ወዳጅ፣ አብሮ አደግ ወዘተ ማለት ነው። የቃሉ ዓይነት ወይም ሥራ ደግሞ “ቅጽል” ወይም “ገላጭ” ይባላል።
ሐሳዊ = ማለት ውሸታም ፣ ሐሰተኛ ወይም በተቃራኒው የእውነተኛ ተቃራኒ ነው። የቃሉ ዓይነት ወይም ሥራ ደግሞ
“ቅጽል” ወይም “ገላጭ” ንው። ስለዚህ በአንድ ላይ “ቢፅ ሐሳዊ” ማለት ሐሰተኛ ጓደኛ፤ ሐሰተኛ ወዳጅ፣ ማለት ሲሆን “ቢፅ” የተባለበት ምክንያት “ወዳጅ ወይም ጓደኛ መስሎ” ስለሚቀርብ ሲሆን “ ሐሳዊ” የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጓደኝነቱ የውሽትና በማስመሰል ላይ የተመሠረተ ስለሆነ ነው።
· በዚህ ስም የሚጠራው ማነው ወይም እነማናቸው? ሐገርን፣ ቤተ ክርስቲያንንና ግለሰብንም ሊሆን ይችላል በድብቅ አሳልፈው የሚሰጡ፤ ወይም በሐገር፤ በቤተ ክርስቲያንና በያንዳንዱ ግለሰብ ሕይወት ላይ የውስጥ ለውስጥ ጥፋትን የሚያዘጋጁ ክፉ ሰዎች ናቸው። ለምሳሌ “ይሁዳ” አምላኩን
እና መምህሩን ወዳጅ ናፋቂ አክባሪም መስሎ በመሳም ነበር አሳልፎ ለሮማ ጨካኝ ወታደሮች በ30 ብር የሸጠው።
·
ይህ ስም በብዛት የሚነገረው በየት ነው?
ይህ ኀረገ ቃል የሚነገረው በብዛት በቤተ ክርስቲያን እና በሐገር ታሪክ ጋር ተያይዞ ነው።
ለምንና በምን ምክንያትስ ይነገራል?
በቤተ
ክርስቲያን ታሪክ አማኝ ወይም ኦርቶዶክሳዊ መስለው
·
በቤተ ክርስቲያን ስም እየኖሩ፤
·
ቤተክርስቲያን አገልጋይ አድርጋ
·
ሹማቸው ውስጥ ውስጡን ግን
·
ከመናፍቃን ጋር ተስማምተው
·
የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ለማፍረስ የሚጥሩ፤
·
ተከታዮቿን ወደ መናፍቃን የሚወስዱ ናቸው።
በሐገር ታሪክም እንደዚሁ ለአገራቸው ታማኝ መስለው በሥልጣን ላይ ለመቆየት ወይም ሥልጣን ለማግኘት ሲሉ
·
የሐገራቸውን ምሥጢር በማውጣት ለጠላት በመስጠት፤
·
የሐገሪቱ የጦር ኃይል እንዲዳከም ብሎም
· በጠላት እንዲማረክ ውስጥ ውስጡን የሚሠሩ ናቸው። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ወይም ቢፅ ሐሳዊ
አብያፅ ሐሳውያን ብንላቸውም እንችላለን ባማርኛ “ሐሰተኛ ወዳጆች” በጣም አደገኛ የቤተ ክርስቲያን እና የሐገር ጠላቶች ናቸው።
ምክንያቱም እውነተኛ ወዳጅ ለሐገርም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን የታመኑ መስለው በድብቅ ስለሚሰሩ ነው።
መጻሕፍት ለመግዛት የሚከተለውን
ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ+1 703 254 6601 ይደውሉ
Tuesday, August 18, 2020
የአውደ ጥናት ዘግእዝ ልዩ አባል ይሁኑ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው
መጻሕፍት ለመግዛት ይህንን ይጫኑ
ወይም በ +1 703 254 6601 ይደውሉ
ምን አልባት “አውደ ጥናትን እና አውደ ጥናት ዘግእዝን ” የማታውቁ ካላችሁ ትንሽ ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ። ከስያሜው ለመነሳት ያህል “አውደ ጥናት” ማለት የጥናት፣ የትምህርት ወይም ባጭሩ የምርምር ማዕከል ማለት ነው።
“አውደ ጥናት ዘግእዝ ማለት” ደግሞ የግእዝ
ቋንቋ ትምህርትና ጠቅላላ ይዘት የሚጠናበት ማለት ሲሆን አውደ ጥናትም ሆነ አውደ ጥናት ዘግእዝ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ሁሉ ቦታና ጊዜ የማይወስናቸው በመላው ዓለም የሚገኙ፤ በመላው ዓለም የሚገኙትን
ማስተናገድ የሚችሉ “የዩቱብ ቻናሎች ወይም ድረገጾች” ሲሆኑ የትምህርትና የጥናት ማዕከላት ናቸው።
በአውደ ጥናትና በአውደ ጥናት ዘግእዝ
· የአማርኛ
· የግእዝ
· የእንግሊዘኛ እንዲሁም ወደፊት
· የግሪከኛ ቋንቋ ትምህርት በሰፊው ይሰጣል።
ባጠቃላይ በአውደ ጥናት እና
በአውደ ጥናት ዘግእዝ በመንፈሳዊና በማሕበራዊም ሕይወት ዙሪያ ልዩ ልዩ መረጃዎችን እና የጥናት ጽሁፎችን ያገኛሉ።
በተለይ ለኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ተከታዮች
ወሳኝ የሆኑ ድረ-ገጾች ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ የዘወትር ጸሎት፤ የውዳሴ ማርያም፤ የመልክአ ማርያም እና መልክአ ኢየሱስ፤
የዶግማና የቀኖና የዘመናት አቆጣጠር ሌሎችም ልዩ ልዩ ትምህርቶችን ቀላል፣ ግልጽና ዘመናዊ በሆነ የማስተማር ዘዴ ከቤታችሁ ሳትወጡ፤
ከቤተሰባችሁ ሳትለዩ በያላችሁበት ቦታ፤ በምትኖሩበት ዓለም ሁሉ በስልካችሁም ሆነ በኮምፕዩተራቸሁ ማለትም በማነኛውም ድጅታል መሣሪያ
ጊዜና ቦታ ሳይወስናችሁ ጊዜያችሁን መርጣችሁ ልትማሩባቸው፤ ልጆቻችሁንም ልታስተምሩባቸው የምትችሉባቸው ድረገጾች ናቸው።
በአውደ ጥናት እና በአውደ ጥናት ዘግእዝ በሚተላለፉት ሁለ ገብ
የእምነትና የሥነ ምግባር ትምህርቶች ራሳችሁን እና ልጆቻችሁን ማስተማርና ማነጽ ትችላላችሁ። በመሆኑም ዛሬውኑ ሰብስክራይብ በማድረግ
የአውደ ጥናትና የአውደ ጥናት ዘግእዝ ተጠቃሚዎች መሆን ትችላላችሁ።
በተጨማሪም በአውደ ጥናት ዘግእዝና
በአውደ ጥናት የሚሰጠው አገልግሎት ከማረካችሁና በተሻለ መልኩ አገልግሎቱን እንድያሳድግ የምትፈልጉ ከሆነም በበጎ ፈቃድ ልዩ አባል
በመሆን መርዳት የምትፈልጉ ከሆነ መርዳት የምትችሉበት ዕድል በሚከተለው ዓይነት የሚገኝ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።
በአውደ ጥናት ዘግእዝ የሚከተሉት
4 የልዩ አባልነት ደረጃዎች ይገኛሉ፤ ክፍያቸውና ያላቸው ልዩ አገልግሎትም አብሮ ተጠቅሶ ይገኛል፤ የምትችሉትንና የምትፈልጉትን
ደረጃ መምረጥ ትችላላችሁ።
1ኛ ደረጃ አባልነት በየወሩ
$1፡99
2ኛ ደረጃ አባልነት በየወሩ
$4፡99
3ኛ ደረጃ አባልነት በየወሩ
$9፡99 እና
4ኛ ደረጃ አባልነት $19፡99
ይከፈላል ወይም ያስከፍላሉ።
በልዩ አባልነት የሚያገኙት
ጥቅም ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል።
1. አንደኛ ደረጃ አባላት በወር አንድ ጊዜ በመረጡት ርእስ የቀጥታ ስርጭት ትምህርት ወይም
ውይይት ይደረግላቸዋል፤
2. ሁለተኛ ደረጃ አባላት በወር አንድ ጊዜ በመረጡ ርእስ የቀጥታ ስርጭት ትምህርት ወይም ውይይት
ይደረግላቸዋል። በተጨማሪም ከአውደ ጥናት ከሚገዧቸው ነገሮች (ብዙ ጊዜ መጻሕፍት) 25% ቅናሽ ያገኛሉ።
3. ሦስተኛ ደረጃ አባላት በወር ሁለት ጊዜ የግእዝ ቋንቋ ተከታታይ ትምህርት በቀጥታ ስርጭት
ይሰጣቸዋል። 25% ቅናሽም ያገኛሉ።
4. አራተኛ ደረጃ አባላት በክፍያ በተከታታይ በዋትስአፕ ከሚሰጠው ተከታታይ የአንድ ዓመት የግእዝ
ቋንቋ ትምህርት ገብተው መማር ይችላሉ። እንዲሁም 25% ቅናሺም ያገኛሉ።
ከዚህ ሌላ ሁሉም አባላት የተለየ
መታወቂያ ይኖራቸዋል። ማለትም አስተያየት በሚሰጡ ጊዜ የተለየ እና ከሌላው አባል ካልሆነው ሰው ይልቅ በዩቱብ ቻናል ተሳትፏቸው
ጎልተው እንዲታዩ የሚያደርግ ድጅታል አርማ ወይም መታወቂያ ይኖራቸዋል። ልዩነታቸው የሚታወቀው ማለትም አርማቸው የሚታየው አስተያየት
ሲሰጡ ወይም ጥያቄ ሲያቅርቡ ነው።
በመሆኑም የአውደ ጥናት ዘግእዝ
ልዩ አባል ለመሆን ሲወስኑ ቀጥታ ወደ አውደ ጥናት ዘግእዝ ቻናል ሲገቡ “Join” የሚል ምልክት ያገኛሉ እሱ ይጫኑ፤ ከገቡ በኋላ
ማብራርያውን ወይም መመሪያውን ይከታተሉ። አመሰግናለሁ።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ