Monday, June 26, 2017

Library/መጻሕፍት ቤት

መጻሕፍት መደብር ስለ እያንዳንዱ መጽሐፍ ይዘት ያንቡ


 ልሣነ-ግእዝ-የጋራ ቋንቋችን







ይህ መጽሐፍ በመሠረታዊነት የተዘጋጀው ቋንቋውን ምንም ለማያውቁ ጀማሪዎችና መጠነኛ ግንዛቤ ኖሯቸው ሰዋስዋዊ አካሄዱን ግን ለማያውቁ ሲሆን ከዚያም በላይ የእውቀት ደረጃ ላሉም ቢሆን በተለይ የአገባብ መዋቅሮችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤን እንዲሰጥ ታስቦ ነው።  



ይህንን መጽሐፍ ለመግዛት መጽሐፉን ይጫኑ




መጽሐፉን ካህናት፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፤ በየአብያተ ክርስቲያናት ሕጻናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ የእምነትንና የሥነ ምግባርን ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ለማስተማሪያነትም ሆነ የግል እውቀትን ለማዳበር እንዲሁም በማነኛውም የቋንቋ ጥናት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የቋንቋን አካሄድ፤ የቃላትን ቅንብርና አገባብ ለመገንዘብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። 
 መጽሐፉ ቀላልና ግልጽ በሆነ የአጻጻፍ ስልት ቢጻፍም “ያለ መምህር መማሪያ” ለመሆን ከበድ ሊል ይችላል ብየ አምናለሁ። በመሆኑም “አውደ ጥናትን መጎብኘት አይዘንጉ። 

ከዚህ መጽሐፍ ላቅ ያለ ዕውቀት ያላችሁ አንባብያን ለወጣንያንና ለማዕከላውያን1 የተዘጋጀ 1ኛ መጽሐፍ እንደ መሆኑ መጠንም በውስጡ የሚገኘው እያንዳንዱ ርእስ የተሰጠው ትርጉም፤ አገልግሎትና ትንታኔ ያለቀለት ሳይሆን ለክፍል አንድ የተመጠነ ብቻ ነው። ማለትም በክፍል ሁለትና በቀጣዮቹም ክፍሎች ትምህርቱ እየሰፋና እያደገ ወይም እየጨመረ የሚሄድ ነው። ስለዚህ አንድ ቃል ወይም አገባብ እናንተ የምታውቁትን ሁሉ አካቶ ባለመገኘቱ የተረሣ ወይም ሳይታወቅ የታለፈ እንዳይመስላችሁ፤ ለክፍል አንድ ተመጥኖ የቀረበ ስለሆነ ብቻ ነው።  
ሌላው ተማሪዎች ለጥናት የበለጠ እንዲተጉ በማሰብ በመጽሐፉ ውስጥ የቀረቡት ጥያቄዎች እየተመለስን መጽሐፉን እያነበብን የምንመልሳቸው ናቸው እንጅ መልሳቸው አልተሰጠም።

  ሌላው የአማርኛን ቋንቋ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የማይችሉ ወይም የማይናገሩ በውጭው ዓለማት የተወለዱ በትውልድ ኢትዮጵያውያን ለሆኑ፤ ከዚያም አልፎ ሌሎች የውጭ ዜጎችም የግእዝን ቋንቋ መማር ይችሉ ዘንድ የተወሰኑትን ክፍሎች በእንግሊዘኛም ጭምር ያዘጋጀሁት ስለሆነ መጽሐፉ የሚያበረክተውን ጥቅሙ የበለጠ ጉልህ ያደርገዋል ብየ አምናለሁ። በእውነትም የሚረኩበት መጽሐፍ ነው።በመሆኑም ከዚህ መጽሐፍ የሚከተሉትን ቋንቋዎች በሚገባ ይማራሉ1.      የግእዝን ቋንቋ እስከ ሰዋስው(አገባቡ)
2.     የአማርኛን ቋንቋ እስከ ሰዋስዉ(አገባቡ)
እንዲሁም መሠረታዊ የሆኑ የእንግሊዘኛ ቃላትን፤ ዐ/ነገራትን/ እንዲሁም የእንግሊዘኛን ቋንቋ አገባብ(ግራመር) ከጀማሪ በላይ የሆነ እውቀትን ያገኙበታል። ለመግዛት ይህንን ይጫኑ/To buy the booksgo to Amazon




“ሕያው ታሪክ በሕያዋን ምስክርነት” 

የተሰኘው ይህ መጽሐፍ 300 ገጾች ያሉት በ31 ምዕራፎች 
የተከፈለና ከ140 በላይ ንኡሳን አርእስት ያሉት ነው ።
 መጠኑን ለመቀነስ ሲባል ሁሉም አርእስት በማውጫው
ስላልተጠቃለሉ መጽሐፉን በመገላለጥ ይምረጡ ።

የመጽሐፉ አብዛኛው ክፍል በቀጥታ የብፁዕ ወቅዱስ
 ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊን የሕይወት ታሪክ
ከልደት እስከ ሕልፈት ድረስ ይዟል ።

ቀሪውና አናሳው ክፍል ደግሞ ከዚሁ ከ5ኛው ፓትርያርክ ጋር ተያያዥ የሆኑ ታሪኮችን ለማጠቃለል በማሰብ 
ከኢትዮጵያ መንበረ ጵጵስና አመሠራረት በመነሣት የ4ቱን ፓትርያርኮች ታሪክ ባጭሩ በመተረክ የ4ኛውን ፓትርያርክ
 ከሥልጣን መውረድ በተመለከተም በቋሚ ምስክሮች የተደገፈ እውነትን ለኢትዮጵያውያን ይፋ ያደርጋል ።

ይህ መጽሐፍ ባጭሩ ሲገለጽ ለ20 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን የመሩት 5ኛው ፓትርያርክ ማን እንደ ነበሩና በተጨባጭ
 ማስረጃና በቋሚ የዐይን ምስክሮች በመደገፍ በሥራቸው አስደናቂና ልዩ መሪ እንደ ነበሩ ይናገራል።

5ኛው ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በተለዩ ጊዜ የ20 ዓመታት ሥራቸውን በጥንቃቄ ሲመለከቱ የነበሩ :: 
በአገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ታዋቂ የሃይማኖትና የሕዝብ መሪዎች የሰጡትን እጅግ አስደናቂና ያልተለመደ 
ምስክርነትንም በከፊል ይዟል ።


የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ሦስት ምዕራፎችንና አሥር አበይት 
ክፍሎችን የያዘ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ በአማርኛ ቋንቋ
 ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ባቀራረቡና በይዘቱ ፍፁም 
የመጀመሪያው ነው ።
ስለመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው ሁሉ 
በዚህ መጽሐፍ ተካቶ ይገኛል ። በቂ ግንዛቤ ከሌላቸው
 ጀማሪዎች እስከ መጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ድረስ ከዚህ 
መጽሐፍ የማይለካ ዘርፈ-ብዙ እውቀትን ያገኛሉ ፤ 
ይማሩበታል ያስተምሩበታልም ።

 ስለዚህ ስለእምነትዎ በሚገባ በማወቅም ሆነ በማሳወቅ ራሰዎን ፤ ቤተሰበዎንና ሕብረተሰቡን ሕያው
 በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ቃል ማነጽ ከፈለጉ ፤ ስለ እያንዳንዱ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ፤
የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የሚቀበሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሰዎ ከያዙት ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚለያይ መሆኑን 
ማወቅየሚሹ ከሆነ ፤ ስለመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማርና የመስበክ ሃላፊነት ካለብዎ ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪ ፤ 
ዲያቆን ፤ ቄስ ፤መነኩሴ ፤ ጳጳስ ፤ ኤጲስ ቆጶስ ወዘተ ከሆኑ፤ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂዱ ከሆነ ፤ 
በአጠቃላይ ፍፁም የሆነውን ሃይማኖታዊውንና ማኅበራዊውን ሕገ-መንግሥት ሊመሩበት ከወደዱ ፤
 ከዘፍጥረት እስከ ራእየ-ዮሐንስ እንዲሁም  2ኛ የቀኖና መጻሕፍትን ጨምሮ በ81ዱ ፤ በ76ቱ ፤ በ73ቱ ፤በ66ቱና በ24ቱ  የዕብራውያን ብሉይ ኪዳን የሚገኙ መጻሕፍት ሁሉ በቀላልና ልዩ በሆነ ዘመናዊ አቀራረብ የመጽሐፉ ጸሐፊ ፤ የተጻፈበት ዘመንና ቦታ ፤ የመጽሐፉ ፍሬ-ሐሣብ ባጭሩ ፤
 የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት ባጭር ትንታኔ ምርጥ ጥቅሶች ፤ ልዩና ያልተለመዱ ፤ እንዲሁም የመጽሐፉ መልዕክት 
በሚሉ መሠረታውያን አርእስት የያንዳንዱመጽሐፍ ይዘት ማራኪ በሆነ መንገድ የመጽሐፉን ጠቅላላ ሐሣብ ባጭሩ 
ተምሮ በሰፊው  መረዳት በሚያስችል ዘዴ ቀርቧል ።በእኔ እይታ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከልጅ እስካዋቂ
 ይህንን መጽሐፍ ሊይዝ ይገባልእላለሁ ። በመሆኑም እርሰዎም ከመጽሐፍ ቅዱሰዎ ጋር ተዋውቀው ያስተዋውቁት እላለሁ ።



የዘመኑ ታሪክ

ስለዘመናት አቆጣጠር ቤዓለም ዙሪያ፤ ስለክርስቶስ የልደት ቀን፤ ስለ ዓመተ
 ምሕረት መጀመሪያ ወር ወዘተርፈ ከአሁን በሁዋላ ጥያቄ አይኖርም።
ሁሉንም ከዚህ መጽሐፍ በማያሻማ ሁኔታ እስከ ማስረጃው ያገኙታል፡
የዚህ መጽሐፍ ዋና አላማ በታሪካዊ እውነት ላይ በመመርኮዝ ለብዙኃኑ ጥያቄ
በተቻለ መጠን ምክንያት ወይም ማስረጃ ያለው መልስ መስጠት ነው፡፡
በዓለማችን የሚገኙ ቢያንስ ክ40 በላይ የሚሆኑ የዘመን ቆጠራ ስልቶች
በጣም የተለያየና የተራራቀ ወይም የማይገናኘ የዘመን ቁጥርን ያሳዩናል
 ምክንያቱን ከዚሁ መጽሐፍ ያገኙታል። እንዲሁም የ10 ዓመታት የበ ዓላትና
 የአጽዋማት ማውጫ ካላንደር አብሮ ተካቶ ይገኛል። ከሁሉም በላይ ጊዜ ወርቅ
 ነው በማለት እግዚአብሔር የለገሰለዎን ጊዜ ወርቅነቱን አውቀው እንዴት
ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አበክሮ ይመክረዎታል። መጽሐፉ ለስጦታ አመች
ሆኖ ስለተዘጋጀ ይህንን ወርቅ የሆነ ስጦታ ለሚወዱዋቸው ገዝተው መስጠት
 ይችላሉ::

የቋንቋ ውበት፡

ይህ የቋንቋ ውበት የተባለው መጽሐፍ የዕውቅ ግጥሞች ስብስብ ነው፡፡
በዚህ የዕውቅ ግጥሞች ስብስብ መጽሐፌ ውስጥ ያካተትኳቸው ሥነ ጽሁፎች 
ከ1979 እስከ 2000 (የኢትዮጵያ ሚሊኒየም) ዓ/ም ድረስ ከጻፍኳቸውና 
በምሁራን ዘንድ ተወዳጅነትን ከተቀዳጁት ከብዙዎቹ ግጥሞቼ መካከል 
በውበታቸውና በስሜት ኮልኳይ ባሕርያቸው ጉድና ድንቅ የተባለላቸውን፤
ልባዊ የሆነ የአድናቆት ሳቅ የተሳቀላቸውን የደስታ ዕንባ የተነባላቸውን፤
ዓለም ከመቀመጫው ብድግ ብሎ አዳራሾች እስከ ሚነዋወጡ ያጨበጨበላ
 ቸውን፤የክብር መዛግብት ብሎ በሰየማቸው ዓለም አቀፍ የግጥምና ቅኔ 
መዛግብቱ (መጻሕፍቱ) የመዘገባቸውንና ውድና ድንቅ ሽልማቶችን
 ለውበታቸውና ለጥዑም አንደበታቸው ያበረከተላቸውን በቁጥር ውሱን፤
በደረጃ ግን አንደኛ የሆኑትን ብቻ በማሰባሰብ ነው፡፡

በዚች መጽሐፍ የሚገኙት ግጥሞች አብዛኛዎቹ አዳዲሶች ሲሆኑ 
‹‹የጸጋ ግምጃ ቤት›› ከተሰኘው መጽሐፌ የተወሰዱም ብዙ ግጥሞች ይገኛሉ፡፡
 ይህ የግጥም መጽሐፍ ሃይማኖታዊ፤ማኅበራዊና ፖለቲካዊ በሚሉ ሦስት አበይት
 ሐሣቦች ዙሪያ በማተኮር ጠቅላላ የሕይወት ክስተቶችን ያጠቃለለ ሲሆን የቅኔን 
አነጋገርና የቋንቋን ሁለንተናዊ ውበት ቁልጭ ጥርት አድርጎ ያሳያል፡፡
 መጽሐፉ የቋንቋን ኅብርና ሰምና ወርቃዊ ውበት ማስተማርያ እንዲሆን ስለታሰበ በጥያቄና በመልስ መልክ
ጭምር የቀረበ ናነው፡፡ከዚህ መጽሐፍ ሰምና ወርቅን፤ኅብርንና ታሪክን መሠረት ያደረጉ ከሰው ልጅ ውስጣዊ ስሜት ጋር በቅጽበት ለመዋሐድ ጊዜን 
የማይወስድባቸው ሕይወት አቀፍ ድርሰቶችን ያገኛሉ፡፡

ግራኛዊው አዋጅ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከግራኝ መሐመድና
ከጉዲት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተክርስቲያናችንን ያዋረደና ሰብአዊና
 ሃይማኖታዊ ክብራችንን ያለገደብ የነካውን ካህንና ዶክተር ነኝ ባይ ከሁሉም
 በላይ በቀጥታ እግዚአብሔር ጠራኝ የሚለውን ተመጻዳቂውን ሰው የደ/ር
ፓስተር ቶሎሳ ጉዲናን የክህደትና የድፍረት ትምህርት (አዋጅ ብለው ይቀላል)
በመቃወም ተጨባጭና አጥጋቢ መልስ የሚሰጥ፤ የቤተ ክርስቲያንን   አኩሪ
ታሪክና፤ለመላው ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያ ያበረከተቺውን እንዲሁም ያለማቋረጥ
 የምታበረክተውን የማይለካ ማሕበራዊ፤ ሐይማኖታዊና መንግሥታዊ ጥበብ
ቁልጭ አድርጎ የሚያስረዳ ኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆኑ ማነኛውም ኢትዮጵያዊ
ሁሉ ይልቁንም እርስ በርስ ተከባብረው የሌላውን ሰብአዊ ክብርና ሃይማኖታዊ
ነጻነት ሳይጋፉ፤የራሳቸውን ክብርና ነጻነት ሳይቀሙ መኖርን የሚሹና የሚወዱ
 ሰላማውያን ሁሉ፤ከሁሉም በላይ‹‹በአንተ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን
 በሌላው ላይ አታድርግ፤ ለአንተ እንዲደረግልህ የምትሻውን ለሌላው ደግሞ
አድርግ››የሚለውን ቅዱስ መርሕ ያልዘነጉ ሊያነቡትና እንደታሪክ ሊያስቀምጡት
የሚገባ ታሪካዊ መጽሐፍ ነው፡፡ይሀ መጽሐፍ በመላዋ ኢትዮጵያና በሰሜን
አሜሪካ የሕዝብም ሆነ የሐይማኖት ቤተመጻሕፍት እንዲሁም መዝሙር ቤቶችና
የቤተክህነት ማዕከላት ይገኛል፡፡

ሀብታችንና ሥርዓቱ

‹‹ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዓት ይሁን›› 1ኛ ቆሮ.14፣40
በዚህ መጽሐፍ በምሳሌነት ከህገ-ልቡና ጀምሮ እስከ ሕገ-ሐዲስ ወይም እስከ
 አማናዊቷ ቤተክርስቲያን ድረስ ያለው የታሪክ ትስስር፤ የእውነተኛዋ
ቤተክርስቲያን አካላዊና መንፈሳዊ አመሠራረት፤ አሠራር፤ አከፋፈልና
 ስያሜ፤ ክልሏን ከሚጠብቁ አጸውተ-ኆኅት ወይም የጥበቃ ክፍሎች ጀምሮ
መሠረቷና ጉልላቷ ወይም የክርስቶስ ምድራዊ ወኪል እስከ ሆነው እስከ
ፓትርያርክ ድረስ ያለው የመንፈሳዊ ሥልጣን አመዛዘንና አሰያየም፣ (አሿሿም፤)
 መዋቅርና ሕልውና በአጠቃላይ የጾታ ምዕመናን ልዩ ልዩ አከፋፈልና የሥራ
ድርሻ ሌሎችም የእምነታችን ቁልፍ ትምህርቶች ተካተው ይገኙበታል፡፡
መጽሐፉ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው የጥናት ጽሁፍ ስለሆነ በከፍተኛ ትምህርት
ለሚገኙ ወይም በጥናት ሥራ ለተሰማሩ ሁሉ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡በመላዋ
ኢትዮጵያ የመጻህፍት ሱቆችና በሰሜን አሜሪካ በተለይ በዲሲና አካባቢዋ
በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትና እንዲሁም
በኢትዮጵያውያን የገበያ ማዕከላት ያገኙታል፡፡ (በቅርብ ጊዜ በሲዲ ይዘጋጃል)

የጸጋ ግምጃ ቤት

የጸጋ ግምጃ ቤት የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በብዙዎቹ የታወቁና
በሊቃውንቱም ዘንድ ታላቅ አድናቆትን ያተረፉ ማሕበራዊውን፤
 ሐይማኖታዊውን፤ እንዲሁም ፖለቲካዊውን የሕይወት መስመር
ሁሉ የሚቃኙ ልዩ ልዩ የአማርኛ ሰምና ወርቅ የግጥም
ድርሰቶችን በዘመናዊ ስልት ሰብስቦ የያዘ ሲሆን በውስጡ
 ከተካተቱት ሥነ-ጽሁፎች መካከል በሰው ልጅ ምድራዊና
ሰማያዊ ሕይወት ውስጥ የሚታዩና ሊታዩ የሚችሉ ልዩ ልዩ
ክስተቶችና መፍትሔዎቻቸው ጭምር፤ ከ1979 ዓ/ም ጀምሮ
 እስከ 1989 ዓ/ም ድረስ በወቅቱ በአበይት ታሪክነታቸው
የታወቁ አሰቃቂም ሆኑ አስደሳች አንኳር ድርጊቶች ስሜት
 ኮልኳይ በሆኑ የግጥም ስንኞች በድርሰት መልክ ተካተው
ይገኙበታል፡፡የምስጋና፤የጸሎት፤ የደስታና የኀዘን ቅኔዎችንም ቀላልና ግልጽ በሆኑ ቃላት አቀነባብሮ ይዟል፡፡ 
በተጠቀሱት የአማርኛ ሰምና ወርቅ የግጥም ድርሰቶች • ራስዎን ያዝናናሉ፤ • ከኀዘንዎ ይጽናናሉ • ደስታዎንም ከልኩ
 እንዳያልፍ ይቆጣጠራሉ፡፡ መጽሐፉ የሚገኘው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የቤተክህነት የመጻሕፍት ሱቆች ብቻ ነው፡
video

የፍቅር ምሥጢር 1ኛ


‹‹መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር
መኝታውም ንጹሕ ይሁን›› ዕብ.13፣4
 ይህም መጽሐፍ የፍቅር
ምሥጢርና ትንሿ ወይም
አዲሷ ቤተክርስቲያን የተባለቺውን
 ማንነት፣በጋብቻ የሚዋሐዱ
 የሁለት ተቃራኒ
ጾታዎች ፍቅር ከሥነ-ተፈጥሮ
 ጋር የተመሠረተ፤ልዩና
 ጥልቅ ምሥጢር
 እንዳለው፤ምሥጢሩም እንዴት እንደሆነ ምንና እንዴት
እንደሆነ እስከ ማስረጃው፤በሁለት የጋብቻ ምርጦች መካከል
የሚጣለው የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማዕቀብ በትዳር ላይ የሚፈጥረው ችግርና ችግሩ ምን እንደሆነ፤ ኤድስ 
መከላከያም ሆነ መድኃኒት በትክክል እንዳለው፤ አራቱ የጋብቻ ዓይነቶች የትኞቹ እንደሆኑ፤የሚሉና ሌሎችም በትዳራችን መካከል አዘውትረው የሚከሰቱ
ችግሮችን ከመፍትሔዎቻቸው ጋር አካቶ የያዘ ሲሆን ፍቅርና ሰላም የሰፈነበት የተሳካ ጋብቻን መገንባት የሚያስችል
መንፈሳዊጥበብን ይጋብዘናል፡፡በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን የጋብቻ መፍትሔዎችና ትክክለኛ ሐሳቦች በሌላ 
በማንም ሃይማኖታዊ የጋብቻመጻህፍት ውስጥ በፍፁም አያገኟቸውም፡በአጠቃላይ መልኩ ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች
 ከጋብቻ በፊት፤ በጋብቻ ጊዜ፤ከጋብቻምበኋላ ሊፈጽሟቸው የሚገባቸውን የያንዳንዳቸውን ፆታዊና ጋብቻዊ 
ድርሻዎችን አንድ በአንድ በመተንተን የጋብቻን ትርጉምናጠቅላላ ይዘት ያስተምራል፡፡ይህም በመጽሐፍና በካሴት
መልክ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡በቪዲዮ በድራማ መልክም ለማዘጋጀት ታቅዷል፡፡


Sunday, June 25, 2017

50 የመመዘኛ ጥያቄዎች


50 የመመዘኛ ጥያቄዎች


የልሣነ ግእዝ ትምህርት የመግቢያው ፤ የክፍል አንድ ምዕራፍ አንድ 50 የመመዘኛ ጥያቄዎች


ለሚከተሉት 50 ጥያቄዎች “ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” በተሰኘው 1ኛ የግእዝ ትምህርት የመማርያ መጽሐፍ በተማሩት መሠረት ትክክለኛውን መልስ ይስጡ።


ጥ፡1-14 የቃላት ትርጉም፦የሚከተሉትን ቃላት ወደ አማርኛ ቋንቋ ቀይሩ።
1.      “ስባሔ”  ማለት ምን ማለት ነው?
2.      “እመ” ማለት ምን ማለት ነው?
3.     “ኅየንተ” ማለት ምን ማለት ነው?
4.     “ቦ” ማለት ምን ማለት ነው?
5.     “ቢጽ” ማለት ምን ማለት ነው?
6.     “ዮም” ማለት ምን ማለት ነው?
7.     “ሙባእ” ማለት ምን ማለት ነው?
8.     “መጽሔተ አእምሮ” ማለት ምን ማለት ነው?
9.     “ልሣን” ማለት ምን ማለት ነው?
10.    “ሣልስ” ማለት ምን ማለት ነው?
11.     “ፊደል” ማለት ምን ማለት ነው?
12.    “እፎ” ማለት ምን ማለት ነው?
13.    “ራብዕ” ማለት ምን ማለት ነው?
14.    በፊደላት የደረጃ ስም መሠረት  “ሣብዕ” ማለት ምን ማለት ነው?
ጥ፡15-25 የዐረፍተ ነገር ትርጉም፦የሚከተሉትን አባባሎች ወደ አማርኛ ተርጉሙ
15.    “አውሥኡ ጥያቄያተ” ማለት ምን ማለት ነው?
16.   “አድንኑ አርእስቲክሙ” ማለት ምን ማለት ነው?
17.     “ምክር ሠናይት ለዘይገብራ” ማለት ምን ማለት ነው?
18.    “ከመ ይቤሉ አበዊነ ጠይቆት ይገብር ሊቀ” ማለት ምን ማለት ነው?
19.    “ባኡ በሰላም ኀበ ጽርሐ አውደ ጥናት ከመ ታእምሩ ፈሪሐ እግዚአብሔር ቅድመ ወልሣነ ግእዝ ድኅረ” ማለት ምን ማለት ነው?
20.   “ተናገራ ስመ አበ አቡክን” ማለት ምን ማለት ነው?
21.    “መኑ አንተ ወምንት ግብርከ” ማለት ምን ማለት ነው?
22.   አነ ኢኮንኩ ዐይኑ “ዐ” አላ አልፋው “አ” ማለት ምን ማለት ነው?
23.   “ብየ ምክንያት ለዘእገብር ኵሉ” ማለት ምን ማለት ነው?
24.   “ፌስቡክ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።
25.   “መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።

ጥ፡26-37 ተጨማሪ ማብራርያን የሚሹ፦ተጨማሪ ማብራርያ በመስጠት ጥያቄዎቹን መልሱ
26.  መስተዋድድ እና መስተጻምር ለሚባሉት ቃላት የአማርኛ ትርጉማቸውን ተናገሩ፤ ከያንዳንዱ አንድ ምሳሌንም ስጡ።
27.   አይቴ ውእቱ ብሔሩ ለአቡነ ሰላማ ማለት ምን ማለት ነው? (ጥያቄውን ወደ አማርኛ ከተረጎማችሁ በኋላ መልሱን መልሱ)
28.   “እምነ አስተጋባኢ” ማለት እና “እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉማቸውን እና ልዩነታቸውን ጻፉ።
29.  22 (ሃያ ሁለት) ቍጥርን በግእዝ አኃዝ (ቍጥር) እና በፊደልም ጭምር ጻፉ።
30.   “መምህራን ኮኑ በበ ደወሉ ፊደላተ ዘኆለቍ ኵሉ” የሚለው አባባል  ምን ለማለት ነው? ትርጉሙን እና ምሥጢሩን ተናገሩ።
31.    ስለ ሞክሼ ሆሄያት ስንማር “ፊደላት በስማችን ጥሩን ይላሉ” በሚለው ርእስ ሥር በተማርነው መሠረት “ይቤ “ጸ”(ጸልሎቱ ጸ) ጸውአኒ እንዘ ትጼሊ” የሚለው ዐ/ነገርን ተርጉሙ  ምን ዓይነት ምሥጢር እንዳለውም አስረዱ።
32.   “ይቤ “ሠ”(ንጉሡ ሠ) ሴመኒ ብሂሎ ንጉሡ “ሠ” ዘወለደኒ” ይህን ዐ/ነገር እስከ ማብራርያው ተርጉሙና አስረዱ።
33.   ስም የሚለው ቃል ግእዝ ነው ብለናል  ስለዚህ ወደ ብዙ ቍጥር ቀይሩት ማለትም “ስሞች” ለማለት በግእዝ እንዴት ነው? በአገራችን የሚሰጠውን ከቋንቋ ትርጉም ወይም ይዘት የተለየ ትርጉምስ ምንድነው?
34.    “ተንሥኡ ለጸሎት” ይህንን ወደ አማርኛ ተርጉሙ፤የተናጋሪውንና የሰሚውን የስም ተለዋጭም በግእዝ ጻፉ።
35.   ሆረ ማለት ምን ማለት ነው? ግሡስ ምን ዓይነት ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፣ ወይስ ትእዛዝ)?
36.  “አርኅዉ” ማለት ምን ማለት ነው? አንቀጹስ ወይም ግሡስ ምን ዓይነት ግሥ ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፤ ወይስ ትእዛዝ)?
37.   “መድኃኒ” የሚለውን ቃልና “ዓለም” የሚለውን ቃል 2ቱን ቃላት አያይዞ ለመጻፍ ምን ማድረግ አለብን? አያይዛችሁም ጻፉ።
ጥ፡ 38-47 ትርጉምን የማይሹ ጥያቄዎች፦ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ
38.    በከርሰ ምድር ውስጥ በፍለጋ የተገኙትና ሙሉ ይዘታቸው በግእዝ ቋንቋ ብቻ ተጽፎ የተገኘውን የ2ቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ስሞች ጥቀሱ።
39.  የግእዝ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
40.   የአማርኛ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
41.    ከአረብኛ የተደቀሉ የሚባሉት ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
42.   የአረብኛ ዲቃላዎች ከሚባሉት ሆሄያት ውስጥ የማይገኙት ሆሄያት--እና---ናቸው።
43.   በጉሮሮ የሚነበቡ ሆሄያት ስንትና የትኞቹ ናቸው?
44.   መኵሸ ሆሄያት የሚባሉት ስንት ናቸው?
45.   እያንዳንዳቸው ሞክሼ ሆሄያት ስንት ስንት ስሞች አሏቸው?
46.  ከሞክሼ ፊደላት የሁለት ፊደላትን ሁለት ሁለት ስሞች ብቻ ጥቀስ
47.   በክፍል 10 ትምህርት መሠረት የሆሄያትን የጋራ መጠሪያ ስም ተናገሩ?
ጥ፡ 48-50 እውነት፤ ሐሰት፦ እውነት ሐሰት በማለት መልሱ
48.   “ግ” ሳድስ ወይም የ”ገ” 6ኛ ሆሄ ነው “ሳድስ” ሆሄ ስንል ግን በጠቅላላ የሆሄያትን ሁሉ 6ኛ ፊደል መጥራታችን ነው። ይህ ዐ/ነገር እውነት ነው ወይስ ሐሰት?
49.   “እግዚአብሔር የሀሉ ምስለ ኵልክሙ” ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲተረጎም  “እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን” ማለት ነው።
50.   በሰላም ያስተራክበነ ብሂል  ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲቀየር “በሰላም ያገናኘን ማለት” ማለት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መልካም ውጤት
ጠቅላላ ፈተና 1
የግእዝ ቋንቋ ፈተና አንድ

መጽሐፉን ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ

About Geez/ስለ ግእዝ ቋንቋ

About Geez Language/ስለ ግእዝ ቋንቋ


Friday, June 23, 2017

About Me/ ስለ እኔ!

የዚህ ድረ-ገጽ ባለቤት


Melaku Besetegn

Welcome to "Awde Tinat" and thank you for visiting my page.


I am Melaku Asmamaw Besetegn;an Ethiopian orthodox Tewahedo church Preacher,Theologian, Religious and Secular Poet. 

I became Poet of the years in 2003 & 2004 in Orlando,FL and Reno,NV through the International Famous Poets society;I received Poet of the year Medallion and the Shakespeare Trophy of Excellence in the above mentioned years.

I have written and published 9 religious & secular books. I enjoy writing and reading; I teach online an Ancient Ethiopian language called "Ge'ez" which is one of the oldest historical and biblical languages.If you are interested in learning this amazing language, please come and join me on WhatsApp Group. Thank you again!





























መምህር መላኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ዲያቆን፤ ሰባኬ ወንጌልና የቲኦሎጅ
 ምሩቅ;እንዲሁም የሃይማኖትና የሕዝብ ገጣሚም ።

 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2003 እና በ2004 ዓ/ም
በሰሜን አሜሪካ ውስጥ በኔባዳና በፍሎሪዳ ስቴቶች
በዓለም አቀፉ የእውቅ ገጣሚዎች ወይም ባለቅኔዎች
ድርጅት በተዘጋጀው ዓመታዊ ውድድር የዓመታቱ
ዝነኛ ገጣሚ በመባል ሜዳልያና የዊሊያም ሸክስፒርን
የክብር ሽልማቶችን
ተሸልሟል።

 ግጥሞቹን ለመስማት ይህንን ይጫኑ/Click here
ሁለት የግጥም፤ ሁለት የታሪክ፤ ሦስት የሃይማኖት ሕግጋትና ሥርዓታት እንዲሁም አንድ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በድምሩ 8መጻሕፍትን ጽፎ በማሳተም ለአንባብያን አበርክቷል
አሁንም የተጠቀሱትን ሥራዎቹንና ሌሎችንም በእርሱና በልዩ ልዩ ምሁራን የሚዘጋጁ
ትምህርታዊ መረጃዎችን ፍላጎት ያላቸው ሁሉ በነጻ መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ
ይህንን ድረ-ገጽ አዘጋጅቷል ። በመሆኑም እርሰዎም ከዚህ ድረ-ገጽ የቀሰሙትን
ዕውቀት ለሌሎች ያዳርሱ ዘንድ ፈቃደዎ ይሁን እንላለን ።
 click here/መጻሕፍቱን ለማየት ይህንን ይጫኑ




"The Land Of Collections" 

/የስብስብ መሬት


Ethiopian orthodox Tewahido church Deacon, Preacher, 
and Theologian, as well as Religious and Secular Poet.
 he became Poet of the years in 2003 
& 2004 in Orlando, FL and Reno, NV
 through the International Famous 
Poets society and got Poet of the year Medallion 
as well as the ShakespeareTrophy of Excellence.He 
has written and published 8 religion and secular books.
From American Red Cross Employees' Spotlight page
more/ ተጨማሪ






















በፎቶ፣ በጋዜጣ አና በመጽሔቶች ከተዘጋጁ ታሪኮችን በከፊል በሚከተለው ቪዲዮ ይመልከቱ



መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ፥








Wednesday, June 21, 2017

ልሣነ ግእዝ ፈተና 1


የክፍል አንድ ማጠቃለያ የመመዘኛ ፈተና 1


ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው። “ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” በሚለው የግእዝ ቋንቋ ትምህርታችን ይህ የዛሬው ክፍል አሥራ አንድ ነው። በክፍል 11 ደግሞ ምዕራፍ ሁለት “የንግግር ክፍሎች” የሚለውን ምዕራፍ እንጀምራለን ብየ ነበር ግን በያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ የመመዘኛ ጥያቄዎችን ማዘጋጀቱ የሚሰጠው ትምህርት ምን ያህል እንደገባችሁ ራሳችሁን ለመመርመር ይረዳችኋል ብየ ስላመንኩ ይህንን ክፍል አሥራ አንድ ትምህርታችንን የመመዘኛ ጥያቄዎችን እንድንሠራ 50 ጥያቄዎችን አዘጋጀሁላችሁ ማለት ነው።
በዚህ ምክንያት፤ ክፍል 12ም ለክፍል 11 ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበት ነው የሚሆነው።  በመሆኑም የምዕራፍ 2 መጀመሪያ የሚሆነው ክፍል 13 ነው።
ጥያቄዎቹ 50 ናቸው፤ እያንዳንዱ ጥያቄ ሁለት፤ሁለት ነጥብ ወይም ማርክ ስላለው ከመቶ የሚወሰድ ነው። አንድ ተማሪ ከመቶ 70ውን/70% ከመለሰ ትምህርቱን እንዳለፈ ይቆጠራል።
ጥያቄዎቹን ለመመለስ ሁለት ሣምንታትን እሰጣችኋለሁ ከዚያ በኋላ ቪዲዮውን አንድ ሺ ሰዎች ካዩት በኋላ የጥያቄዎቹ ሙሉ መልስ በክፍል 12 ዝግጅት ይሰጣል።
የጥያቄዎቹን መልሶች በሦስት መንገዶች መመለስ ትችላላችሁ
1.      ከዚሁ ቪዲዮ ስር በኮሜንት ወይም በአስተያየት መስጫ ቦታ መልሶቹን መጻፍ
2.     learngeez@outlook.com በሚለው ኢሜይል በኩል ወይም
3.     በቪዲዮ አዘጋጅታችሁም መልሳችሁን መላክ ትችላላችሁ መልካም ፈተና!
ሌላው፡
የግእዝ መማሪያ መጽሐፉን ግዙ ምክንያቱም መጽሐፉ የታተመው ለናንተ ነው። 1ኛ እናንተ ትምህርቱን የምትማሩበት ነው፤ ግእዝን ከአውደ ጥናት ለማወቅ ሙሉ ፍላጎት ካላችሁ መጽሐፉን መግዛት ግድ ነው።
የመጽሐፉ መሸጥ ለኔም ትምህርቱን በተሻለ መንገድ ለማስተማር፤ በተሻለ የድምጽ መቅረጫ፤ በተሻለ የቪዲዮ ካሜራ ትምህርቱን ለማዘጋጀት ይረዳኛል።
እኔ ትምህርቱን የማስተምራችሁ በበጎ ፈቃድ በነጻ ነው ስለዚህ ቢያንስ ትምህርቱ የምትማሩበትን መጽሐፍ ሳዘጋጅላችሁ ሁላችሁም መጽሐፉን መግዛት ይጠበቅባችኋል ብየ አምናለሁ።
ስለዚህ በዚህ እኔ በምኖርበት በሰሜን አሜሪካ ለምትኖሩ ሰዎች መጽሐፉን ለማግኘት በጣም ቀላል ነው፤ ምክንያቱም ከአማዞን ብትገዙ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ መጽሐፉ በፖስታ ይደርሳችኋል። ወይም ከእኔ በአካል መግዛትም ትችላላችሁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የምትኖሩና በአውሮፓ በእስያ፤ በሌሎችም አገሮች እየኖራችሁ በኢትዮጵያ በኩል መጽሐፉን ማግኘት ለምትፈልጉ መጽሐፉን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ዝግጁ ነኝ። ከዚህ በፊት ወደ አዲስ አበባ ተልኮ የነበረው  ትሽጦ ስላለቀ አሁን ወደ አዲስ አበባ እንዲላክላችሁ የምትፈልጉ ሁሉ በሚከተሉት መንገዶች ስማችሁን፤ የስልክ ቁጥራችሁን(የአዲስ አበባ)፤ እና የምትፈልጉትን የመጻሕፍት ብዛት በመናገር ከአሁኑ ተመዝገቡ ከዚያ በኋላ በሚፈልገው ሰው ልክ መላክ ይቻላል።
0911 866346
703 254 6601 ወይም
 learngeez@outlook.com 

መጽሐፉን ከአማዞን ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ

Lisane Geez Yegara Quanquachin


ሌላው ጥያቄን በተመለከተ ነው ፤
ካለኘ የጊዜ እጥረት የተነሣ የምቀበለው ጥያቄ ግእዝን የሚመለከትና በማስተምራችሁ ትምህርት መሠረት ላይ የተመሠረተ ብቻ ሲሆን ነው። ከሌላ ቦታ በማምጣት ከቃላት፤ከዐረፍተ ነገራትም አልፎ በገጽ የሚለካ ጽሁፍ ተርጉምልን የምትሉ ወይም የተለያዩ የእምነት ጥያቄዎችን የምትጠይቁም አላችሁ። እውነቱን ለመናገር ለኔ የማስተምራችሁ የግእዝ ትምህርት በቂ ነው። ሌላውን ደግሞ በአካባቢያችሁ የሚገኙ መምህራንን ብትጠይቁ ለናንተም በአካል መረዳቱ መልካም ነው። ወይም እምነትን በተመለከተ በአውደ ጥናት ያስተላለፍኳቸው ልዩ፤ ልዩ ዝግጅቶች አሉ እነሱን በመመልከት ጥያቄዎቻችሁ ሊመለሱ ይችላሉ ብየ አምናለሁ ። በአውደ ጥናት ውስጥ ከሚገኙት አርእስት መካከል
·         ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ
·         የዘመን አቋጣጠር ታሪክና ልዩነት በዓለም ዙሪያ
·         ይህንን ያውቃሉ
·         ምን ማለት ነው
·         ፍትሐ ነገሥት
የሚሉትና ሌሎችም ናቸው እና እነዚህን ተመልከቱ ጥያቄዎቻችሁን በነዚሁ አርእስት ውስጥ ልታገኙ ትችላላችሁ።
ጥ፡1-14 የቃላት ትርጉም፦የሚከተሉትን ቃላት ወደ አማርኛ ቋንቋ ቀይሩ።
1.      “ስባሔ”  ማለት ምን ማለት ነው?
2.      “እመ” ማለት ምን ማለት ነው?
3.     “ኅየንተ” ማለት ምን ማለት ነው?
4.     “ቦ” ማለት ምን ማለት ነው?
5.     “ቢጽ” ማለት ምን ማለት ነው?
6.     “ዮም” ማለት ምን ማለት ነው?
7.     “ሙባእ” ማለት ምን ማለት ነው?
8.     “መጽሔተ አእምሮ” ማለት ምን ማለት ነው?
9.     “ልሣን” ማለት ምን ማለት ነው?
10.    “ሣልስ” ማለት ምን ማለት ነው?
11.     “ፊደል” ማለት ምን ማለት ነው?
12.    “እፎ” ማለት ምን ማለት ነው?
13.    “ራብዕ” ማለት ምን ማለት ነው?
14.    በፊደላት የደረጃ ስም መሠረት  “ሣብዕ” ማለት ምን ማለት ነው?
ጥ፡15-25 የዐረፍተ ነገር ትርጉም፦የሚከተሉትን አባባሎች ወደ አማርኛ ተርጉሙ
15.    “አውሥኡ ጥያቄያተ” ማለት ምን ማለት ነው?
16.   “አድንኑ አርእስቲክሙ” ማለት ምን ማለት ነው?
17.     “ምክር ሠናይት ለዘይገብራ” ማለት ምን ማለት ነው?
18.    “ከመ ይቤሉ አበዊነ ጠይቆት ይገብር ሊቀ” ማለት ምን ማለት ነው?
19.    “ባኡ በሰላም ኀበ ጽርሐ አውደ ጥናት ከመ ታእምሩ ፈሪሐ እግዚአብሔር ቅድመ ወልሣነ ግእዝ ድኅረ” ማለት ምን ማለት ነው?
20.   “ተናገራ ስመ አበ አቡክን” ማለት ምን ማለት ነው?
21.    “መኑ አንተ ወምንት ግብርከ” ማለት ምን ማለት ነው?
22.   አነ ኢኮንኩ ዐይኑ “ዐ” አላ አልፋው “አ” ማለት ምን ማለት ነው?
23.   “ብየ ምክንያት ለዘእገብር ኵሉ” ማለት ምን ማለት ነው?
24.   “ፌስቡክ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።
25.   “መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉሙን በግእዝ ጻፉ።
ጥ፡26-37 ተጨማሪ ማብራርያን የሚሹ፦ተጨማሪ ማብራርያ በመስጠት ጥያቄዎቹን መልሱ
26.  መስተዋድድ እና መስተጻምር ለሚባሉት ቃላት የአማርኛ ትርጉማቸውን ተናገሩ፤ ከያንዳንዱ አንድ ምሳሌንም ስጡ።
27.   አይቴ ውእቱ ብሔሩ ለአቡነ ሰላማ ማለት ምን ማለት ነው? (ጥያቄውን ወደ አማርኛ ከተረጎማችሁ በኋላ መልሱን መልሱ)
28.   “እምነ አስተጋባኢ” ማለት እና “እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ” ማለት ምን ማለት ነው? ትርጉማቸውን እና ልዩነታቸውን ጻፉ።
29.  22 (ሃያ ሁለት) ቍጥርን በግእዝ አኃዝ (ቍጥር) እና በፊደልም ጭምር ጻፉ።
30.   “መምህራን ኮኑ በበ ደወሉ ፊደላተ ዘኆለቍ ኵሉ” የሚለው አባባል  ምን ለማለት ነው? ትርጉሙን እና ምሥጢሩን ተናገሩ።
31.    ስለ ሞክሼ ሆሄያት ስንማር “ፊደላት በስማችን ጥሩን ይላሉ” በሚለው ርእስ ሥር በተማርነው መሠረት “ይቤ “ጸ”(ጸልሎቱ ጸ) ጸውአኒ እንዘ ትጼሊ” የሚለው ዐ/ነገርን ተርጉሙ  ምን ዓይነት ምሥጢር እንዳለውም አስረዱ።
32.   “ይቤ “ሠ”(ንጉሡ ሠ) ሴመኒ ብሂሎ ንጉሡ “ሠ” ዘወለደኒ” ይህን ዐ/ነገር እስከ ማብራርያው ተርጉሙና አስረዱ።
33.   ስም የሚለው ቃል ግእዝ ነው ብለናል  ስለዚህ ወደ ብዙ ቍጥር ቀይሩት ማለትም “ስሞች” ለማለት በግእዝ እንዴት ነው? በአገራችን የሚሰጠውን ከቋንቋ ትርጉም ወይም ይዘት የተለየ ትርጉምስ ምንድነው?
34.    “ተንሥኡ ለጸሎት” ይህንን ወደ አማርኛ ተርጉሙ፤የተናጋሪውንና የሰሚውን የስም ተለዋጭም በግእዝ ጻፉ።
35.   ሆረ ማለት ምን ማለት ነው? ግሡስ ምን ዓይነት ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፣ ወይስ ትእዛዝ)?
36.  “አርኅዉ” ማለት ምን ማለት ነው? አንቀጹስ ወይም ግሡስ ምን ዓይነት ግሥ ነው(ሐላፊ፤ትንቢት፤ ወይስ ትእዛዝ)?
37.   “መድኃኒ” የሚለውን ቃልና “ዓለም” የሚለውን ቃል 2ቱን ቃላት አያይዞ ለመጻፍ ምን ማድረግ አለብን? አያይዛችሁም ጻፉ።
ጥ፡ 38-47 ትርጉምን የማይሹ ጥያቄዎች፦ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ
38.    በከርሰ ምድር ውስጥ በፍለጋ የተገኙትና ሙሉ ይዘታቸው በግእዝ ቋንቋ ብቻ ተጽፎ የተገኘውን የ2ቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ስሞች ጥቀሱ።
39.  የግእዝ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
40.   የአማርኛ ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
41.    ከአረብኛ የተደቀሉ የሚባሉት ፊደላት ግእዝ ግእዛቸውን ብቻ በመቍጠር ስንት ናቸው?
42.   የአረብኛ ዲቃላዎች ከሚባሉት ሆሄያት ውስጥ የማይገኙት ሆሄያት--እና---ናቸው።
43.   በጉሮሮ የሚነበቡ ሆሄያት ስንትና የትኞቹ ናቸው?
44.   መኵሸ ሆሄያት የሚባሉት ስንት ናቸው?
45.   እያንዳንዳቸው ሞክሼ ሆሄያት ስንት ስንት ስሞች አሏቸው?
46.  ከሞክሼ ፊደላት የሁለት ፊደላትን ሁለት ሁለት ስሞች ብቻ ጥቀስ
47.   በክፍል 10 ትምህርት መሠረት የሆሄያትን የጋራ መጠሪያ ስም ተናገሩ?
ጥ፡ 48-50 እውነት፤ ሐሰት፦ እውነት ሐሰት በማለት መልሱ
48.   “ግ” ሳድስ ወይም የ”ገ” 6ኛ ሆሄ ነው “ሳድስ” ሆሄ ስንል ግን በጠቅላላ የሆሄያትን ሁሉ 6ኛ ፊደል መጥራታችን ነው። ይህ ዐ/ነገር እውነት ነው ወይስ ሐሰት?
49.   “እግዚአብሔር የሀሉ ምስለ ኵልክሙ” ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲተረጎም  “እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን” ማለት ነው።
50.   በሰላም ያስተራክበነ ብሂል  ይህ ዐ/ነገር ወደ አማርኛ ሲቀየር “በሰላም ያገናኘን ማለት” ማለት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም ውጤት

አጠቃላይ የመመዘኛ ፈተና አንድ





ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን #1 የመመዘኛ አጠቃላይ
ፈተና