Saturday, May 25, 2019

አአትብ ገጽየ ወኵለንታየ የቃል ትምህርት ክፍል 1

ወደ አማዞን በመሄድ የግእዝ መማርያ መጽሐፌንና ሌሎችንም መጻሕፍት ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ፡ 
ሌሎችንም መጻሕፍት ከአማዞን በነጻ ማንበብ ይችላሉ።

ይህ በአውደ ጥናት ዘግእዝ በግእዝ ቋንቋ እየተዘጋጀ የሚቀር የቃል ትምህርት ክፍል አንድ

የቃል ትምህር ክፍል አንድ
አአትብ ገጽየ ወኵለንታየ
በትእምርተ መስቀል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
 አሐዱ አምላክ
በቅድስት ሥላሴ
 እንዘ አአምን
ወእትመሐጸን
እክሕደከ ሰይጣን
በቅድመ ዛቲ እምየ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
እንተ ይእቲ ስምዕየ ማርያም ጽዮን
ለዓለመ አለም።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ
አዘጋጅና አቅራቢ መ/ር መላኩ አስማማው ቢሰጠኝ

Tuesday, May 21, 2019

ኢትብላዕ እምዕፅ ዘያርኢ ወያሌቡ እኵየ ወሠናየ/But of the tree of the knowledge of good &...

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ይጫኑ
https://amzn.to/2YLdJh5

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ ወቅታዊ ታሪክን መሠረት ያደረገ የግእዝ ቋንቋ ጥቅስ ትምህርታችን ክፍል 2 ይቀጥላል እንከታተል።
የዛሬውም ጥቅስ በቀዳማይ ምዕራፈ ታሪክ ውስጥ በሕገ ልቡና የተነገረ ነው።
“እምኵሉ ዕፅ ዘሀሎ ውስተ ገነት ብላዕ። ወእምዕፅሰ ዘያርኢ ወያሌቡ ሠናየ ወእኩየ ኢትብላዕ እምኔሁ፡ እስመ በዕለተ ትበልዕ እምኔሁ ሞተ ትመውት” ዘፍ. 2፡16-17
ትእዛዝ
ይህ ትእዛዝ  ለመጀመሪይዋ ሰው ለአዳም የተሰጠ ነው፤ ስለዚህ ትእዛዝ ሰጪው እግዚአብሔር ሲሆን ትእዛዝ ተቀባዩ አዳም ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ሰባክያን ስለ ዘመነ ሥጋዌ ሲያስተምሩ ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ። ምክንያቱም የሥጋዌን ታሪክ የፈጠረው የዚህ ትእዛዝ መሻር፤ የአዳም ይህንን ትእዛዝ አለመጠበቅ ስለሆነ የታሪኩን መነሻ በመሻት ለማስረዳት ስለሚፈልጉ ነው።
የጥቅሱ ወይም የትእዛዙ የአማርኛ ትርጉም
“እምኵሉ ዕፅ ዘሀሎ ውስተ ገነት ብላዕ። ወእምዕፅሰ ዘያርኢ ወያሌቡ ሠናየ ወእኩየ ኢትብላዕ እምኔሁ፡ እስመ በዕለተ ትበልዕ እምኔሁ ሞተ ትመውት”
·          በገነት ውስጥ ካለው ዛፍ ሁሉ ትበላለህ(ካለው ዛፍ የሚገኘውን ፍሬ ማለት ነው)
·          ክፉና ደጉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ ግን ከሱ አትብላ(ከሱ የሚገኘውን ፍሬ)
·          ከእሱ በበላህ ጊዜ ሞትን ትሞታለህና
በዚህ ትዕዛዝ ውስጥ 3 ነገሮችን እናያለን አንዱ በገነት ውስጥ ያለው ሁሉ ከአንድ ዛፍ በስተቀር ለአዳም እንደ ተፈቀደለት፤
ሁለት፡ በገነት ውስጥ ያለ ክፉን እና ደጉን የሚያሳይና የሚያስገነዝብ አንድ ዛፍ እንደ ነበረ ከዚያ ዛፍ እንዳይበላ የአዳም መከልከል
ሦስት፡ የተፈቀደለትን አልፎ ያልተፈቀደውን ዛፍ ከበላ ግን የሚጠብቀው ውጤት ሞት እንደ ሆነ ያለመታዘዝን ዋጋ ቀድሞ ማስታወቅ የሚሉት ናቸው።
አዳም ግን የወደደውን መረጠ የተነገረውንም አገኘ። ቀጣዩን ታሪክ በክፍል 3 እናየዋለን አሁን ግን
በጥቅሱ ውስጥ የሚገኙትን ቃላት ትርጉም፤ ዓይነት ሥራ እና ባሕርይ እናያለን።

በተጠቀሰው ጥቅስ ውስጥ ያሉትን 3 ዐረፍተ ነገራት፤ 31 ቃላትና አገባቦች ሲኖሩ ከ31ዱ ውስጥ 15ቱ አገባቦች ሲሆኑ 16ቱ ደግሞ ቃላት ናቸው። ከነዚህ ውስጥም ስሞች፤ ግሶች፤ አበይትና ንዑሳን አገባቦች ይገኛሉ አንድ በአንድ እናያቸዋለህ ትኩረት ሰጥታችሁ ተከታተሉ
ዐረፍተ ነገራት
·         “እምኵሉ ዕፅ ዘሀሎ ውስተ ገነት ብላዕ
·         ወእምዕፅሰ ዘያርኢ ወያሌቡ ሠናየ ወእኩየ ኢትብላዕ እምኔሁ
·          እስመ በዕለተ ትበልዕ እምኔሁ ሞተ ትመውት”
ቃላትና አገባቦች
1.   “እም
2.   ኵሉ
3.   ዕፅ
4.  
5.   ሀሎ
6.   ውስተ
7.   ገነት
8.   ብላዕ
9.  
10.  እም
11.  ዕፅ
12. 
13. 
14.  ያርኢ
15. 
16.  ያሌቡ
17.  ሠናየ
18. 
19.  እኩየ
20. 
21.  ትብላዕ
22.  እም
23.  ሁ፡
24.  እስመ
25. 
26.  ዕለተ
27.  ትበልዕ
28.  እም
29. 
30.  ሞተ
31.  ትመውት”

ልዑል አምላክ ለብዎቶ የሐበነ
እም አውደ ጥናት ዘግእዝ

Wednesday, May 15, 2019

ሕዝብ፡ ማለት ምን ማለት ነው? አማርኛ ነው? ወይስ ግእዝ?

ልሣነ ግእዝ የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ይጫኑ
https://amzn.to/2HlKMlO

ሕዝብ፡ ማለት ምን ማለት ነው? አማርኛ ነው? ወይስ ግእዝ?
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

ዛሬ “ሕዝብ” በሚለው የግእዝ ቃል ላይ ያተኮረ አጭር ትንታኔን ይዠላችሁ ቀርቤያለሁ ተከታተሉ። አስተያየት፤ ተጨማሪ፤ ወይም ጥያቄ ካላችሁ  Learngeez@outlook.com በሚለው የአውደ ጥናት ዘግእዝ ኢሜይል መላክ ትችላላችሁ። የግእዝና እና የአማርኛ ቋንቋን በተመለከተ ከአውደ ጥናት የሚተላለፉትን የትምህርት ዓይነቶች መከታተል ከፈለጋችሁ ሰብስክራይብ ማድረግንም አትርሱ።

ይህንን አጭር ማብራርያ የጻፍኩበት ምክንያት ባለፈው እንደ ዓለም አቀፉ አቆጣጠር ግንቦት 9 ቀን 2019 ዓ/ም “ዕለታዊ” በተሰኘው በኢሳት ESAT Satellite TV ፕሮግራም በተላለፈው ዝግጅት የዝግጅት አቅራቢዎቹ “ሕዝብ” በሚለው ቃል ላይ ከተለመደው ትንታኒያቸው ለየትና ረዘም ያለጊዜን ወስደው ያደረጉትን ውይይት መነሻ በማድረግ እኔም በበኩሌ በመጻሕፍት እና በሊቃውንቱ በጽሁፍ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን መረጃ ለነሱም እንደ ተጨማሪ ይሆናቸው ዘንድ ለማካፈል በማሰብ ነው።
በዚህ አጋጣሚ በበኩሌ በተጠቀሰው ቃል ላይ የሰጡት ትንታኔ በቋንቋው ይዘት ላይ ጠለቅ ያለ ችሎታ እንዳላቸው የሚያሳይ እንደሆነ ተረድቻለሁ፤ አድናቆቴንም ሳልገልጥ አላልፍም። ግሩም ነው።

“ሕዝብ” የሚለው ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን በአማርኛም እንዳለ በቁሙ “ሕዝብ” እየተባለ ይጠራል። ምክንያቱም በጣም ብዙ የግእዝ ቋንቋ ቃላት በአማርኛም እንዳሉ ሳይለወጡ አገልግሎት ይሰጣሉ።  ለምሳሌ እንደ ፍቅር፤ ሕግ፤ ፍትሕ፤ ሰላም፤ ሐገር፤ ብሔር፤ ቤተ መንግሥት፤ ቤተ ክህነት፤ ሕገ መንግሥት፤ ፍትሐ ብሔር ወዘ ተርፈ የመሳሰሉት ሁሉ የግእዝ ቃላትና ኃረጎች ናቸው። ሆኖም ግን ለ2ቱም ቋንቋዎች ያገለግላሉ፤ የግእዝን ቋንቋ የሚያውቁ ያውቋቸዋል የማያውቁ ደግሞ ፍፁም አማርኛ እንደሆኑ ይቆጥሯቸዋል።
“ሕዝብ” የሚለው ቃልም እንዲሁ በአማርኛም ተለምዶ ይልቁንም እንደ አማርኛ ተቆጥሮ ግእዝ መሆኑ ራሱ በአብዛኛው የቋንቋው ተጠቃሚ የሚታወቅ አይመስልም። በግእዝ ቋንቋነቱ ስንጠቀምበት በአማርኛ ከምንጠቀመው አጠቃቀም ብዙ ባይርቅም ለየት ያለ ባሕርይ አለው ልዩነቱ በመጠኑ እንመለከታለን።

·         የቃሉ ዓይነት “ነባር ስም” ይባላል። የግእዝ ቃላት በሁለት ይከፈላሉ ነባርና ዘር፤ ስለዚህ “ሕዝብ” ነባር ነው።
·        የቃሉ ይዘት “ውስጠ ብዙ” ይባላል። ማለትም ብዙ ሰዎች እንደማለት ነው።
ከዚህ ላይ አቶ ተወልደ የተናገረውን ታላቅና መሠረታዊ ነጥብ መጥቀስ ይገባል።

“በአንድ ብልቃጥ ወይም ብርጭቆ ውስጥ ያለ ስኳር ስኳሮች አትለውም ስኳር ነው የምትለው” በማለት ሕዝብ የሚለውን ቃል ውስጠ ብዙነት አሳይቷል።

እንደ ተባለው በአንድ አገር የሚኖሩ፤ በአንድ ባሕል፤ በአንድ ቋንቋ፤ በአንድ ሕገ መንግሥት አንድ ለሆኑ ብዙ ሰዎች የሚሰጥ ስያሜ ነው።
ማለትም በአንድነት አቅፎ በያዛቸው አንድ ጠርሙስ ውስጥ ተጠቃለዋል ማለት ነው። ስለዚህ የሚጠሩት በአንድነት ስያሜያቸው ነው። በሌላ አባባል ውሕደታቸው ወይም አንድነታቸው ነው እነሱን ተክቶ የሚጠራው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በዚሁ ቃል ላይ የሰጡትን ትንታኔ መጨረሻ ላይ እገልጸዋለሁ።

·        ሕዝብ የሚለው ቃል በግእዝ ቋንቋ አልፎ አልፎ  “አሕዛብ” በማለትም ሲበዛ ይገኛል።
ግን “ሕዝብ” ራሱ ብዙነትን የሚገልጽ ስለሆነ “አሕዛብ” የሚለውን ሊቃውንቱ “የብዙ ብዙ” ይሉታል። ከብዙም ያለፈ ለማለት ነው። ምክንያቱም ብዙውን ነገር እንደገና አሁንም ካበዛነው የብዙ ብዙ ሆነ ማለት ነው።

በግእዝ መዝገበ ቃላት መሠረት “ሕዝብ” = በቁሙ በአማርኛም ሕዝብ ይባላል። እንዲሁም ወገን ተብሎም ይተረጎማል።
ቃሉ እንደ ተነጋገርነው ውስጠ ብዙ ይባላል ወይም ነው። ስለዚህ፣ ለአንድ፤ ለብዙ፤ ለወንድ፤ ለሴት፤ ለሁሉም ይሆናል። ማለትም ለአንድም ለብዙም ለሴትም ለወንድም ያገለግላል።
ሌላው
ሕዝባዊ ሕዝባውያን፤ ሕዝባዊት ሕዝባውያት በመባልም ተገልጾ ይገኛል። በዚህ አገላለጽ ወገንነትን የሚገልጽ ቅጽል ሲሆን በቁሙ የሕዝብ ወይም የምእመናን ወገን፤አካል ወዘተ ማለት ነው።

 ሌላው ሥልጣነ ክህነት የሌለው ካህን ያልሆነ ምእመን ወይም ምእመናን ማለትም ነው። ይህንን አገላለጽ በተለይ በቅኔ ቤት አዘውትረን የምንጠቀምበት ሲሆን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ገልጸውታል። ሕዝብ አገር ማለትም ይሆናል።

“ሕዝብ” የሚለው ቃል በግእዝ ቋንቋ ጥቅም ላይ ሲውል፤
የብዙና የነጠላ የሁለቱንም ግስ ወይም አንቀጽ (ቨርብ) ይወስዳል። ማለትም በብዙ ቁጥርም በነጠላ ቁጥርም እንገለገልበታለን። በዚህ መሠረት ከአማርኛው አጠቃቀም ይለያል ማለት ነው።

ምሳሌ1. በነጠላ ሲያገለግል
1.  “ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃነ ዓቢየ” ኢሳ. 9፡2 = የአማርኛ ትርጉሙ በጨለማ ውስጥ የኖረ ወይም የሚኖር ሕዝብ ብርሃንን ዐየ ማለት ነው።
ከዚህ ላይ የአንድን ነጠላ ቃል አንቀጽ ይውሰድ እንጅ ነቢዩ የሚገልጸው በጥቅሉ የሰውን ዘር ወይም ሰብአዊ ፍጡርን ስለሆነ ውስጠ ብዙ የሚያሰኘው ይህ ነው። ምክንያቱም በአዳምና በሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት በጨለማ ይኖር የነበረውና በክርስቶስ ልደት ብርሃንን ያየ ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ነው።

ምሳሌ 2. በብዙ ቍጥር ሲያገለግል
2.   “እስመ አበሱ ሕዝብከ ዘአውጻእከ እምድረ ግብጽ” ዘፀ. 32፡7 በአማርኛ = ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህ (ወገኖችህ ሰዎችህ) በድለዋልና፤ ማለት ነው። “አበሱ” የሚለው ግስ ወይም ቨርብ ለብዙ የሚሆን ግስ ነው። በመሆኑም በግእዝ ያለው ልዩነት የብዙ ቝጥርን ግስ በመጠቀሙ ነው።

እኔ ለማስርጃ ያህል እነዚህን አቀረብኩ እንጅ  ቃሉ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በአንድም በብዙም ቍጥር በስፋት ተጠቅሶ ይገኛል። አሁን በአማርኛ ደግሞ እንይ።

“ሕዝብ” የሚለው ቃል በአማርኛ ቋንቋ ጥቅም ላይ ሲውል፤
እንደተነጋገርነው ቃሉ ሳይለወጥ በአማርኛ ቋንቋ ስንጠቀምበት ግን ከግእዙ የሚለይበት መለያ አለው። ይህም በአማርኛ ሕዝብ የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ግስን ወይም አንቀጽን (ቨርብን) አይወስድም።

በመሆኑም በአማርኛ “ሕዝብ መጣ” ይባላል እንጅ “ሕዝብ መጡ” አይባልም። ስለዚህ ከግእዙ አማርኛው ለየት ያለ አጠቃቀም አለው ማለት ነው። ሌላው ብዙ ሕዝብ መጣ ስንል ያለምንም የፆታ ልዩነት ብዙ ሴቶችን ወይም ብዙ ወንዶችንም ሁሉ የሚወክል አነጋገር ነው።
ቃሉ በአማርኛ የብዙ ቍጥር ግስን (ቨርብን) አይውሰድ እንጂ የብዙ ቍጥር ቅጽልን (አድጀክቲብን) ግን ይወስዳል ። እንደሚከተለው ማለት ነው ።

“ብዙ ሕዝብ” ይላል። ስለዚህ “ብዙ” ከአንድ በላይ የሆነ ነገርን የሚገልጽ ቅጽል ወይም ገላጭ(አድጀክቲብ) ነው። “ብዙ” የሚለው ቃል ከላይ እንደተገለጠው በጠርሙሱ ውስጥ ያሉትን ይገልጻል እንጅ ጠርሙሱን አይገልጽም። ስለዚህ አሁንም ውስጠ ብዙ፤ በጥቅል የሚነገር የወል ስም መሆኑን ነው የሚያሳየው። “ሰው” እንደሚለው ቃል ማለት ነው። “ሰው” ወይም “ብዙ ሰው ወይም ሰው መጣ” እንጂ “ብዙ ሰው ወይም “ሰው መጡ” አይባልም።

ቃሉ የሚያሳየው መሠረታዊ ነጥብ ግን በአንድ ሕብረት ውስጥ ያሉ አንድ ባደረጋቸው የሕብረት ትስሥር ውስጥ በአንድነት የተዋሐዱ ወይም የተጠቃለሉ ብዝኃነታቸውን አንድነታቸው ያጠቃለለው ብዙ ሰዎችን ነው።

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝበ ቃላት መጽሐፋቸው ገጽ 439 ላይ ሰፋ አድርገው እንደሚከተለው አብራርተውታል።
ሕዝብ፡ ብዙ ሕዝብ፤ ሕዝብ በቁሙ ወገን፤ ነገድ፤ የተሰበሰበ ብዙ ሰው፤ ጉባኤ፤ ሸንጎ ማለት ነው፡ ካሉ በኋላ
“የአንዲት አገር የአንዲት ከተማ ወይም የአንድ ብሔር የአንድ መንግሥት ሰው፤ ቋንቋውና ሕጉ አንድ የሆነ በአንድ ሕግ የሚኖር”  ማለት ነው ይላሉ።

በሕገ መንግሥቱ የተጠቀሰውን ትርጉም የሚይዘው ይህ ትንታኔ ሳይሆን አይቀርም ብየ አምናለሁ።
ይህንን ርእስ ወይም ቃል በተመለከተ የበለጠ ማብራርያ ከፈለጋችሁ
የሚከተሉትን የመጻሕፍት ጥቅሶችና መዝገበ ቃላት መመልከት ትችላላችሁ
·         ዘፀ. 32፡6
·         ኢሳ. 18፡2
·         ሚክ. 4፡7
·         ዘፍ. 12፡2
·         ዘዳ. 32፡6
·         መሳ. 21፡3
·         የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ439፤ እንዲሁም
·         የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ እና
·         “መጽሔተ አእምሮ ብሔራዊ ቋንቋ ዘኢትዮጵያ”ን በ “ሐ” ፊደል ስር የሳድስ ነባርን ተመልከቱ።

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

ሕዝብ፡ ማለት ምን ማለት ነው? አማርኛ ነው? ወይስ ግእዝ?

ሕዝብ፡ ማለት ምን ማለት ነው? አማርኛ ነው? ወይስ ግእዝ?

ሕዝብ፡ ማለት ምን ማለት ነው? አማርኛ ነው? ወይስ ግእዝ?
Watch video

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው
ዛሬ “ሕዝብ” በሚለው የግእዝ ቃል ላይ ያተኮረ አጭር ትንታኔን ይዠላችሁ ቀርቤያለሁ ተከታተሉ። አስተያየት፤ ተጨማሪ፤ ወይም ጥያቄ ካላችሁ  Learngeez@outlook.com በሚለው የአውደ ጥናት ዘግእዝ ኢሜይል መላክ ትችላላችሁ። የግእዝና እና የአማርኛ ቋንቋን በተመለከተ ከአውደ ጥናት የሚተላለፉትን የትምህርት ዓይነቶች መከታተል ከፈለጋችሁ ሰብስክራይብ 

ልሣነ ግእዝ የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ይጫኑ                                                                ማድረግንም አትርሱ።

ይህንን አጭር ማብራርያ የጻፍኩበት ምክንያት ባለፈው እንደ ዓለም አቀፉ አቆጣጠር ግንቦት 9 ቀን 2019 ዓ/ም “ዕለታዊ” በተሰኘው በኢሳት ESAT Satellite TV ፕሮግራም በተላለፈው ዝግጅት የዝግጅት አቅራቢዎቹ “ሕዝብ” በሚለው ቃል ላይ ከተለመደው ትንታኒያቸው ለየትና ረዘም ያለጊዜን ወስደው ያደረጉትን ውይይት መነሻ በማድረግ እኔም በበኩሌ በመጻሕፍት እና በሊቃውንቱ በጽሁፍ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን መረጃ ለነሱም እንደ ተጨማሪ ይሆናቸው ዘንድ ለማካፈል በማሰብ ነው።
በዚህ አጋጣሚ በበኩሌ በተጠቀሰው ቃል ላይ የሰጡት ትንታኔ በቋንቋው ይዘት ላይ ጠለቅ ያለ ችሎታ እንዳላቸው የሚያሳይ እንደሆነ ተረድቻለሁ፤ አድናቆቴንም ሳልገልጥ አላልፍም። ግሩም ነው።

“ሕዝብ” የሚለው ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን በአማርኛም እንዳለ በቁሙ “ሕዝብ” እየተባለ ይጠራል። ምክንያቱም በጣም ብዙ የግእዝ ቋንቋ ቃላት በአማርኛም እንዳሉ ሳይለወጡ አገልግሎት ይሰጣሉ።  ለምሳሌ እንደ ፍቅር፤ ሕግ፤ ፍትሕ፤ ሰላም፤ ሐገር፤ ብሔር፤ ቤተ መንግሥት፤ ቤተ ክህነት፤ ሕገ መንግሥት፤ ፍትሐ ብሔር ወዘ ተርፈ የመሳሰሉት ሁሉ የግእዝ ቃላትና ኃረጎች ናቸው። ሆኖም ግን ለ2ቱም ቋንቋዎች ያገለግላሉ፤ የግእዝን ቋንቋ የሚያውቁ ያውቋቸዋል የማያውቁ ደግሞ ፍፁም አማርኛ እንደሆኑ ይቆጥሯቸዋል።

“ሕዝብ” የሚለው ቃልም እንዲሁ በአማርኛም ተለምዶ ይልቁንም እንደ አማርኛ ተቆጥሮ ግእዝ መሆኑ ራሱ በአብዛኛው የቋንቋው ተጠቃሚ የሚታወቅ አይመስልም። በግእዝ ቋንቋነቱ ስንጠቀምበት በአማርኛ ከምንጠቀመው አጠቃቀም ብዙ ባይርቅም ለየት ያለ ባሕርይ አለው ልዩነቱ በመጠኑ እንመለከታለን።
·         የቃሉ ዓይነት “ነባር ስም” ይባላል። የግእዝ ቃላት በሁለት ይከፈላሉ ነባርና ዘር፤ ስለዚህ “ሕዝብ” ነባር ነው።
·        የቃሉ ይዘት “ውስጠ ብዙ” ይባላል። ማለትም ብዙ ሰዎች እንደማለት ነው።
ከዚህ ላይ አቶ ተወልደ የተናገረውን ታላቅና መሠረታዊ ነጥብ መጥቀስ ይገባል።
“በአንድ ብልቃጥ ወይም ብርጭቆ ውስጥ ያለ ስኳር ስኳሮች አትለውም ስኳር ነው የምትለው” በማለት ሕዝብ የሚለውን ቃል ውስጠ ብዙነት አሳይቷል።

እንደ ተባለው በአንድ አገር የሚኖሩ፤ በአንድ ባሕል፤ በአንድ ቋንቋ፤ በአንድ ሕገ መንግሥት አንድ ለሆኑ ብዙ ሰዎች የሚሰጥ ስያሜ ነው።
ማለትም በአንድነት አቅፎ በያዛቸው አንድ ጠርሙስ ውስጥ ተጠቃለዋል ማለት ነው። ስለዚህ የሚጠሩት በአንድነት ስያሜያቸው ነው። በሌላ አባባል ውሕደታቸው ወይም አንድነታቸው ነው እነሱን ተክቶ የሚጠራው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በዚሁ ቃል ላይ የሰጡትን ትንታኔ መጨረሻ ላይ እገልጸዋለሁ።

·        ሕዝብ የሚለው ቃል በግእዝ ቋንቋ አልፎ አልፎ  “አሕዛብ” በማለትም ሲበዛ ይገኛል።
ግን “ሕዝብ” ራሱ ብዙነትን የሚገልጽ ስለሆነ “አሕዛብ” የሚለውን ሊቃውንቱ “የብዙ ብዙ” ይሉታል። ከብዙም ያለፈ ለማለት ነው። ምክንያቱም ብዙውን ነገር እንደገና አሁንም ካበዛነው የብዙ ብዙ ሆነ ማለት ነው።

በግእዝ መዝገበ ቃላት መሠረት “ሕዝብ” = በቁሙ በአማርኛም ሕዝብ ይባላል። እንዲሁም ወገን ተብሎም ይተረጎማል።
ቃሉ እንደ ተነጋገርነው ውስጠ ብዙ ይባላል ወይም ነው። ስለዚህ፣ ለአንድ፤ ለብዙ፤ ለወንድ፤ ለሴት፤ ለሁሉም ይሆናል። ማለትም ለአንድም ለብዙም ለሴትም ለወንድም ያገለግላል።
ሌላው
ሕዝባዊ ሕዝባውያን፤ ሕዝባዊት ሕዝባውያት በመባልም ተገልጾ ይገኛል። በዚህ አገላለጽ ወገንነትን የሚገልጽ ቅጽል ሲሆን በቁሙ የሕዝብ ወይም የምእመናን ወገን፤አካል ወዘተ ማለት ነው።

 ሌላው ሥልጣነ ክህነት የሌለው ካህን ያልሆነ ምእመን ወይም ምእመናን ማለትም ነው። ይህንን አገላለጽ በተለይ በቅኔ ቤት አዘውትረን የምንጠቀምበት ሲሆን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ገልጸውታል። ሕዝብ አገር ማለትም ይሆናል።

“ሕዝብ” የሚለው ቃል በግእዝ ቋንቋ ጥቅም ላይ ሲውል፤
የብዙና የነጠላ የሁለቱንም ግስ ወይም አንቀጽ (ቨርብ) ይወስዳል። ማለትም በብዙ ቁጥርም በነጠላ ቁጥርም እንገለገልበታለን። በዚህ መሠረት ከአማርኛው አጠቃቀም ይለያል ማለት ነው።

ምሳሌ1. በነጠላ ሲያገለግል
1.  “ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃነ ዓቢየ” ኢሳ. 9፡2 = የአማርኛ ትርጉሙ በጨለማ ውስጥ የኖረ ወይም የሚኖር ሕዝብ ብርሃንን ዐየ ማለት ነው።
ከዚህ ላይ የአንድን ነጠላ ቃል አንቀጽ ይውሰድ እንጅ ነቢዩ የሚገልጸው በጥቅሉ የሰውን ዘር ወይም ሰብአዊ ፍጡርን ስለሆነ ውስጠ ብዙ የሚያሰኘው ይህ ነው። ምክንያቱም በአዳምና በሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት በጨለማ ይኖር የነበረውና በክርስቶስ ልደት ብርሃንን ያየ ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ነው።
ምሳሌ 2. በብዙ ቍጥር ሲያገለግል
2.   “እስመ አበሱ ሕዝብከ ዘአውጻእከ እምድረ ግብጽ” ዘፀ. 32፡7 በአማርኛ = ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህ (ወገኖችህ ሰዎችህ) በድለዋልና፤ ማለት ነው። “አበሱ” የሚለው ግስ ወይም ቨርብ ለብዙ የሚሆን ግስ ነው። በመሆኑም በግእዝ ያለው ልዩነት የብዙ ቝጥርን ግስ በመጠቀሙ ነው።

እኔ ለማስርጃ ያህል እነዚህን አቀረብኩ እንጅ  ቃሉ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በአንድም በብዙም ቍጥር በስፋት ተጠቅሶ ይገኛል። አሁን በአማርኛ ደግሞ እንይ።

“ሕዝብ” የሚለው ቃል በአማርኛ ቋንቋ ጥቅም ላይ ሲውል፤
እንደተነጋገርነው ቃሉ ሳይለወጥ በአማርኛ ቋንቋ ስንጠቀምበት ግን ከግእዙ የሚለይበት መለያ አለው። ይህም በአማርኛ ሕዝብ የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ግስን ወይም አንቀጽን (ቨርብን) አይወስድም።

በመሆኑም በአማርኛ “ሕዝብ መጣ” ይባላል እንጅ “ሕዝብ መጡ” አይባልም። ስለዚህ ከግእዙ አማርኛው ለየት ያለ አጠቃቀም አለው ማለት ነው። ሌላው ብዙ ሕዝብ መጣ ስንል ያለምንም የፆታ ልዩነት ብዙ ሴቶችን ወይም ብዙ ወንዶችንም ሁሉ የሚወክል አነጋገር ነው።
ቃሉ በአማርኛ የብዙ ቍጥር ግስን (ቨርብን) አይውሰድ እንጂ የብዙ ቍጥር ቅጽልን (አድጀክቲብን) ግን ይወስዳል ። እንደሚከተለው ማለት ነው ።

“ብዙ ሕዝብ” ይላል። ስለዚህ “ብዙ” ከአንድ በላይ የሆነ ነገርን የሚገልጽ ቅጽል ወይም ገላጭ(አድጀክቲብ) ነው። “ብዙ” የሚለው ቃል ከላይ እንደተገለጠው በጠርሙሱ ውስጥ ያሉትን ይገልጻል እንጅ ጠርሙሱን አይገልጽም። ስለዚህ አሁንም ውስጠ ብዙ፤ በጥቅል የሚነገር የወል ስም መሆኑን ነው የሚያሳየው። “ሰው” እንደሚለው ቃል ማለት ነው። “ሰው” ወይም “ብዙ ሰው ወይም ሰው መጣ” እንጂ “ብዙ ሰው ወይም “ሰው መጡ” አይባልም።

ቃሉ የሚያሳየው መሠረታዊ ነጥብ ግን በአንድ ሕብረት ውስጥ ያሉ አንድ ባደረጋቸው የሕብረት ትስሥር ውስጥ በአንድነት የተዋሐዱ ወይም የተጠቃለሉ ብዝኃነታቸውን አንድነታቸው ያጠቃለለው ብዙ ሰዎችን ነው።

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝበ ቃላት መጽሐፋቸው ገጽ 439 ላይ ሰፋ አድርገው እንደሚከተለው አብራርተውታል።
ሕዝብ፡ ብዙ ሕዝብ፤ ሕዝብ በቁሙ ወገን፤ ነገድ፤ የተሰበሰበ ብዙ ሰው፤ ጉባኤ፤ ሸንጎ ማለት ነው፡ ካሉ በኋላ
“የአንዲት አገር የአንዲት ከተማ ወይም የአንድ ብሔር የአንድ መንግሥት ሰው፤ ቋንቋውና ሕጉ አንድ የሆነ በአንድ ሕግ የሚኖር”  ማለት ነው ይላሉ።
በሕገ መንግሥቱ የተጠቀሰውን ትርጉም የሚይዘው ይህ ትንታኔ ሳይሆን አይቀርም ብየ አምናለሁ።
ይህንን ርእስ ወይም ቃል በተመለከተ የበለጠ ማብራርያ ከፈለጋችሁ
የሚከተሉትን የመጻሕፍት ጥቅሶችና መዝገበ ቃላት መመልከት ትችላላችሁ
·         ዘፀ. 32፡6
·         ኢሳ. 18፡2
·         ሚክ. 4፡7
·         ዘፍ. 12፡2
·         ዘዳ. 32፡6
·         መሳ. 21፡3
·         የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ439፤ እንዲሁም
·         የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ እና
·         “መጽሔተ አእምሮ ብሔራዊ ቋንቋ ዘኢትዮጵያ”ን በ “ሐ” ፊደል ስር የሳድስ ነባርን ተመልከቱ።

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

Saturday, May 11, 2019

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን /Review on Lisane Geez Yegara Quanquachin part 1

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘው የግእዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፍ ጠቅላላ ማብራርያና ለአንባቢዎች የሚጠቅሙ መሠረታውያን የአጠናን ስልቶችን ጨምሮ ስለመጽሐፉ ጠቃሚነት ግምገማ ክፍል አንድ::

“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የተሰኘውን የግእዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፍ ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

“ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” ይህ መጽሐፍ በአማርኛ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከተጻፉ መጻሕፍት ብቸኛውና የመጀመሪያው ነው፤ 81ዱን እና በዓለም ዙሪያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሁሉ የሚቀበሏቸውን፤ የማይቀበሏቸውን ሁሉ በአንድ ላይ አካቶ እስከ ምክንያቱ ቀላልና ልዩ አጭርም በሆነ መንገድ የሚያስተምር ልዩ መጽሐፍ ነው። ይህንን የመጀመሪያና ብቸኛ መጽሐፍ ለመግዛት ይህንን ይጫኑ። https://amzn.to/2LEyp8A 

Another important self help book in English
Atomic Habit
The instant New York Times bestseller
No matter your goals, Atomic Habits offers a proven framework for improving--every day. James Clear, 
to buy click this link https://amzn.to/2vUCkmZ 

Friday, May 10, 2019

ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበ አምሳሊነ/”Let us make man in our image, after our likeness”

“ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ”
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው ዛሬ ወቅታዊ ታሪክን መሠረት ያደረገ የግእዝ ቋንቋ ትምህርትን አዘጋጅቸላችኋለሁ ።
 በመሠረታዊነት በአውደ ጥናት ዘግእዝ ተመዝግበው ለሚማሩ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደ ልምምድ ይሆን ዘንድ የሚዘጋጅ ነው።

ሆኖም ግን ቋንቋውን መማር ለምንፈልግ ሁሉ በጣም ጠቃሚ ግንዛቤን የሚሰጥ ትምህርት ነው።
በዚህ ዝግጅት የምናየው ስለ አምላክ ሰው መሆን እና ስለ ዓለም ድኅነት  ሲነገር ወይም ሲተረክ በሊቃውንቱ አንደበት ተዘውትረው በግእዝ ቋንቋ ስለሚነገሩ  ጠለቅ ያለ ምሥጢርን ስለያዙ ልዩ ልዩ ጥቅሶች ነው።

·         ታሪኩ በሕገልቡና
·         በሕገ ኦሪት እና
·         በሕገ ወንጌል በሦስቱ ሕግጋት የተከፈለ ነው።

በመሆኑም ከዚህ በላይ ባሉት 3 ሕግጋት ወይም የታሪክ ምዕራፎች ውስጥ የሚከተሉትን ባጭሩ የምናይበት ዝግጅት ነው።
·          እግዚአብሔር ሰውን እንዴት እንደ ወደደውና ፍቅሩም ምክንያት አልባ እንደሆነ፤
·         ሰው እንዴት እንደ ተፈጠረና የአምላኩን ሕግ እንዴት እንደተላለፈ፤
·         ሰው ከክብሩ ከተዋረደ በኋላ ከእግዚአብሔር ስለተሰጠው ተስፋ
·         ስለ አምላክ ሰው መሆን የነቢያት ትንቢት
·         ሰለ አምላክ ሰው መሆንና የትንቢቱ ፍጻሜ እንዴት እንደነበር
ጠቅለል ባለ አገላለጽ ከሰው ልጅ በአምላክ መወደድ ጀምሮ እስከ ዘመነ ትንሣኤ ድረስ ያለውን ታሪክ ለመናገር ከሚጠቀሱ ብዙ ጥቅሶች መካከል ጥቂቶቹን እና ተዘውትረው በግእዝ ቋንቋ የሚጠቀሱትን ጥቅሶች በግእዝ እየጠቀስን ወደ አማርኛ እየተረጎምን ይዘታቸውን የሥራ ድርሻቸውን እያብራራን እንማራለን። እንከታተል።

ለዛሬው የምናየው የመጀመሪያውን አንድ ጥቅስ ብቻ ይሆናል ይህም በመጀመሪያው የሰውልጅ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ስለ ሰው አፈጣጠር የሚናገር የመጀመሪያ ጥቅስ ነው

ቀዳማይ ምዕራፈ ታሪክ
 “ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ” ዘፍ.1፡26
በዚህ ጥቅስ
1.    እግዚአብሔር በአንድነትና በሦስትነት የሚመለክ አምላክ መሆኑን፤
2.    የሰው ልጅ ከሥነ ፍጥረት ሁሉ የበለጠ ክብርን እንዳገኘ
3.    እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሳይፈጥረው አስቀድሞ እንደወደደው የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው

1.    ንግበር
2.    ሰብእ
3.   
4.    አርአያ
5.   
6.   
7.    አምሳል
8.   
·         ፍቅር እንበለ ምክንያት ወፈጢር በአምሳሊሁ
 ልዑል አምላክ ለብዎቶ የሐበነ
እም አውደ ጥናት ዘግእዝ

ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን እና “ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” የሚባሉትን መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
https://amzn.to/2VWunwn 
 https://amzn.to/2Yix4Wt
Another important book to build life changing habit, The instant New York Times bestseller
https://amzn.to/2LxyL0K
No matter your goals, Atomic Habits offers a proven framework for improving--every day. James Clear, 

Sunday, May 5, 2019

“አባታችን ሆይ” እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ”

ዛሬ በዚህ ዝግጅቴ “አባታችን ሆይ” የሚለውን እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ” የሚባሉትን ሁለት የጸሎት ክፍሎች በውጭ አገር ተወልዳችሁም ሆነ ወይም በሌላ ምክንያት አማርኛና ግእዝ ለማታነቡና ለማትናገሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን አማርኛውንና ግእዙን በምታውቁት የእንግሊዘኛ ፊደል አዘጋጅቼ አቅርቤላችኋለሁ ተከታተሉ፤ 

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው፡
ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ እና ሌሎቹንም መጻሕፍቶቼን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ

 https://amzn.to/2V2fMLl         ( ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የሚለውን መጽሐፍ)
https://amzn.to/2DPUStg    (ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ)
ዛሬ በዚህ ዝግጅቴ “አባታችን ሆይ” የሚለውን እና “እመቤታችን ማርያም ሆይ” የሚባሉትን ሁለት የጸሎት ክፍሎች በውጭ አገር ተወልዳችሁም ሆነ ወይም በሌላ ምክንያት አማርኛና ግእዝ ለማታነቡና ለማትናገሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን አማርኛውንና ግእዙን በምታውቁት የእንግሊዘኛ ፊደል አዘጋጅቼ አቅርቤላችኋለሁ ተከታተሉ፤ ምን ያህል የሚጠቅማችሁ መሆኑን፤ ወይም የበለጠ የተሻለ መንገድ አለ የምትሉትም የአቀራረብ ዘዴ ካለ ተናገሩ፤ አስተያየታችሁን ለመስጠት ወደኋላ አትበሉ።
እንደምታዩት የተዘጋጀው አማርኛውና ግእዙን በእንግሊዘኛ ፊደል በመጻፍ ስለሆነ አማርኛውንም ሆነ ግእዙን የማንበብ ችሎታ ይኖራችኋል፤ የእንግሊዘኛ ትርጉሙንም አብሬ አስቀምጨዋለሁ፤ የአነባበብ ስልቱን ደግሞ በድምጽ ትሰማላችሁ ማለት ነው።

በነዚህ ሁለት ጸሎታት በግእዝም ሆነ በአማርኛ መጻሕፍት ተጽፎ ከሚገኘው ኃይለ ቃል ሌላ በቃል ስንጸልይ የምንጨምራቸው ተጨማሪ ቃላት አሉ፤ እኔ የጻፍኩት በመጻሕፍቶቻችን የተጻፈውን ነው። በቃል የሚጨመሩት እነዚህ ቃላት ችግር የማያመጡና ከይዘቱ አንጻር ተገቢ ቢሆኑም፤ ሁሉም ምእመናን በአንድ ዐይነት መንገድ ስለማያነቡት ልዩነት የተፈጠረ ስሕተት መስሎ እንዳይታያችሁ፤ ከወዲሁ አሳስባለሁ ።
ከሚጨመሩትም ቃላት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
1.  “እመቤቴ ማርያም ሆይ” ይህ ከመጽሐፉ በግእዝም በአማርኛም የሚገኘው ኃይለቃል ነው። በቃል በአማርኛ ስንል “እመቤታችን ቅድስት፤ ድንግል፤ ማርያም ሆይ” እንላለን፤ እመቤታችን ቅድስ ናት ድንግልም ናት፤ ትክክለኛ አባባል ነው፤ በዚህ የጸሎት ክፍል ከመጽሐፉ ውስጥ ስለማይገኝ፤ ለምን ቀረ ወይም ለምን ተጨመረ ብለን ግራ እንዳንጋባ ነው።
2.  “ወቡሩክ ፍሬ ከርስኪ” ወይም “የማሕጸንሽ ፍሬ” የተባረከ ነው። ይህ ከመጽሐፉ የሚገኘው ሲሆን፤ በቃል “የማሕጸንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ ነው” እንላለን። በዚህ ላይ ምምህራን የሚያስተምሩት፤ አንድ ነጥብ አለ እመቤታችን በድንግልና ጸንሣ በድንግልና የወለደቺው የእግዚአብሔር ቃሉና ልጁ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው። ስለዚህ የማሕጸንሽ ፍሬ ከተባለ ሌላ የማሕጸኗ ፍሬ ስለሌለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ መጥቀስ አይጠበቅብንም ምክንያቱ በስም የሚጠቀሰው ከብዙዎች መካከል ለመለየት እንጅ አሻሚ የለለውን ነገር መጥቀስ አያስፈልግም ይላሉ። ያም ሆነ ይህ የእኔ አላማ ግን ልዩነቱን እንድታውቁ ብቻ ነው።
ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን

ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

Thursday, May 2, 2019

አቡነ ዘበሰማያት እና በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ በግእዝ ቋንቋ /Prayers in Ge'ez Language

ግእዝ/ in Ge’ez Language
አቡነ ዘበሰማያት፣
Abune Zebesemayat

ይትቀደስ ስምከ
Yitkedes Smike

ትምጻእ መንግሥትከ
Timtsa-e Mengistike

ወይኩን ፈቃድከ
Weyikun Fekadike

በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር
Be Keme Be Semay Kemahu Bemidr

ሲሳየነ፣ ዘለለ ዕለትነ፣ ሀበነ ዮም
Sisayene Zelele Eletine Habene Yom

ኅድግ ለነ አበሳነ፡ ወጌጋየነ፡
Hidig Lene Abesane Wegegayene

ከመ ንሕነኒ፣ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ፤
Keme Nhineni Nhidig Leze Abese Lene

ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት፤
Etabi- Ane Egzio wiste Mensut

አላ አድኅነነ፡ ወባልሐነ ፡
Ala Adhinene Webalihane

እምኵሉ እኩይ፤
Emkulu  Ekuy

እስመ ዚአከ፡
Esme Ziake

ይእቲ፡ መንግሥት፡
Yi- Eti Mengist

ኀይል ወስብሐት
Hail Wesbihat

ለዓለመ ዓለም። ኣሜን
Le Alem Alem Amen

============================================================

በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ
Beselame Kidus Gebriel Mel-Ak

ኦ፡ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣
O Egzi-Etiye Mariam Selam Leki

ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ
Dingil Behilinaki Wedingil Besigaki

እመ እግዚአብሔር ጸባኦት ሰላም ለኪ
Eme Egiziabiher Tseba-Ot Selam Leki

ቡርክት አንቲ እምአንስት ፡ ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ
Burikt Anti Em- Anist Weburikt Frie Kersiki

ተፈሥሒ ፡ ፍሥሕት፡ ኦ፡ ምልእተ ጸጋ
Tefesihi Fsiht O Mliete Tsega

እግዚአብሔር ምስሌኪ
Egzia Biher Misleki

ሰአሊ ፡ ወጸልዪ ለነ 
Se-Ali wetseliy Lene

ኀበ ፍቁር ወልድኪ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ
Habe Fikur Weldiki Eyesus Kirstos

ከመ ይስረይ ለነ ፡ ኀጣውኢነ (ተማሕጸነ ብኪ)
Keme Yisrey Lene HaTawi- Ene