English lesson one/የአንግሊዘኛ ትምህርት ኣንድ ለጀማሪዎች
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ ነው፣ ወደ አውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ እንኳን በሰላም መጣችሁ፤ በዚህ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ስለ እንግሊዘኛ ቋንቋ መሠረታዊ ነገሮችን እናያለን፤ በመጀመሪያ ግን የሚከተሉትን ምክራዊ መመሪያዎች ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ።
አንድ የማናውቀውንና በጣም በጉጉት ማወቅ የምንፈልገውን ነገር
በምንመኘው ልክ ለማወቅ ለየት ያሉ ባሕርያትን በውስጣችን መፍጠር ይኖርብናል፤ ከነዚህም የስኬት ባሕርያት መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ
ናቸው። እነዚህም
·
በጸጥታና
በተረጋጋ ስሜት ለሚተላለፈው ትምህርት ልዩ ትኩረትን መስጠትና መልእክቱን ማስተዋል
·
የሚተላለፈውን ትምህርት ሳያቋርጡ እስከ መጨረሻው በጥንቃቄ መመልከት
·
ወሳኝ የሆኑ ነጥቦችን በልዩ ማስታዎሻ ጽፎ መያዝና እየተመለሱ ማየት
·
ቃሉን ወይም ዐረፍተ ነገሩን እየደጋገሙ መስማት፤ማየት፣ እና መናገር
·
የማናውቀው ቃል ወይም ኃረግ ካጋጠመን ከመዝገበ ቃላት ወይም ዲክሺነሪ ውስጥ ፈልገን ትርጉሙን
ማግኘት
·
ትምህርቱ ቢከብደንም እንኳን የበለጠ መደጋገም እንጅ ተስፋ አለመቁረጥ የሚሉት
እነዚህ ስድስት
ነጥቦች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፤ እነዚህን መተግበር ከቻልን ያለምንም ጥርጥር ምኞታችን ይሳካል።
የዛሬው ትምህርታችን ስለፊደላት ነው በልዩ ትኩረት እንከታተል
በዚህ በክፍል አንድ ስለ ፊደላት የምናየው
የፍደላቱን ብዛት፣ ቅርጻቸውን ወይም መልካቸውን፤ ስማቸውን፤ ድምጻቸውን፣ እና የሚተኳቸውን የአማርኛ ወይም የግእዝ ፊደላት፤ እንዲሁም
አናባቢ ፊደላትን እና ተናባቢ ፊደላትን ይሆናል።
በእንግሊዘኛ አልፋቤት ወይም የፊደል ገበታ 26 ፊደላት
ይገኛሉ። ከነዚህ 26 ፊደላት ውስጥ 5ቱ መደበኛ አናባቢዎች ናቸው፤ አንዱ ልዩ ፊደል እና ቀሪዎቹ 20 ፊደላት ደግሞ ተናባቢዎች
ናቸው። ሃያ ስድስቱም(26ቱም) ስሞል እና ካፒታል ወይም አፐር ኬዝ እና ለወር ኬዝ ወይም በአማርኛ ትንሺና ትልቅ የሚባሉ
ሁለት ዓይነት መልክን የያዙ ናቸው፤ አንዳንዶቹ በመጠን እንጅ በቅርጽ ልዩነት የላቸውም (upper
and lowercase letters (Capital and small letters)
ከዚህ በታች የምናየው የእንግሊዘኛ የፊደል ገበታ ነው፤ ፊደላቱ በትልቁና በትንሹ
ፊደል ተጽፈው በሰንጠረዥ ውስጥ ይታያሉ።
በዚህ ሰንጠረዥ 26ቱም ፊደላት ይገኛሉ፤ ስለዚህ ይህ ሰንጠረጅ አንድ በአንድ ከ1 እስከ 26 ድረስ ያሉትን ፊደላት
ቅርጻቸውን ስማቸውን፣ ድምጻቸውን እና የሚተካቸውን የግእዝ ወይም የአማርኛ ፊደል አጠቃሎ ይዟል። ማለትም በ1ኛው መስመር ፊደላቱ፣
በ2ኛው የፊደላቱ ስም፣ በ3ኛው የፊደላቱ ድምጽ፣ በ4ኛው ደግሞ የሚተካቸው የግእዝ ፊደል ይገኛል። መጨረሻ ላይ ደግሞ “መፍቻ”
በሚለው ሥር ከአንድ በላይ ድምጽ ያላቸው ፊደላትና ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ፊደላት ሲቀናጁ የሚፈጥሩት የአማርኛ ሆሄ ተገልጿል።
ሌላው ለማስታዎስ እንዲያመች በማሰብ በልዩ ልዩ ቀለማት የተጻፉ ፊደላት አሉ። አናባቢዎች በቀይ፣ ተናባቢዎች በወይን ጠጅ፣ እና
ስሞል ሌተሮች(ወይም ትንንሾቹ ፊደላት) በሰማያዊ
ተጽፈው ይገኛሉ አስተውሉ።
ክፍል ሁለት
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ ነው ዛሬ በዚህ
በክፍል 2 ትምህርታችን ስለ አናባቢዎችና ተናባቢዎች እንማራለን ተከታተሉ።
አሁን በሥዕሉ ላይ ወዳሉት ፊደላት ተመልከቱ እያንዳንዳቸውን እየለያየን
እንመለከታቸዋለን።
በሥዕሉ ላይ እንደምታዩት አናባቢዎች ወይም ቫውልስ በቀይ ባግራውንድ
ላይ ተጽፈዋል፤ ተናባቢዎች በጥቁር ተጽፈዋል፤ አንድ ፊደል ደግሞ በሁለት አይነት ቀለም ተከፍሏል። ስለሱ በኋላ ሰፋ አድርገን እናያለን።
A the first main Vowel
B consonant
C consonant
D consonant
E vowel
F consonant
G consonant
H consonant
I vowel
J consonant
K consonant
L consonant
M consonant
N consonant
O vowel
P consonant
Q consonant
R consonant
የግአዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፌን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ +1 703 254 6601 ይደውሉ
No comments:
Post a Comment