Thursday, June 11, 2020

የዐረፍተ ነገር አመሠራረት እና ዕድገት በልሣነ ግእዝ ለ2ኛ እና ለ3ኛ ክፍል ተማሪዎች



“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ ወይም ይደውሉ. ልሣነ ግእዝ የሚለውን መጽሐፍ ይግዙ+1 703 254 6601https://amzn.to/30A7Nvd

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው፡ ዛሬ ስለ ዐረፍተ ነገር ዕድገት የተሰጠውን  ልምምድ መሠረት በማድረግ ተጨማሪ መልስና ማብራርያ እሰጣችኋለሁ ተከታተሉ።

ይህ ትምህርት የበለጠ ትኩረት ሰጥታችሁ ልታጠኑት የሚገባ ነው። ብዙ ቃላት ማወቅ ብቻ ጥቅም የለውም ዋናው ነገር ግን በተወሰኑ ቃላት አስተካክሎ መጻፍ፣ መናገር ወዘተ መቻል ነው፤ ስለዚህ ለመግባባት ወሳኙ የቃላትን ዓይነትና ሥራ ለይቶ ማወቅ ነው። (ስምንቱን(8)፤፰ቱን የንግግር ክፍሎች)

አንድ የተሟላ ትርጉምን የሚሰጥ ዐረፍተ ነገር ለመሥራት 2 ነገሮችን ማወቅና በቦታቸው ማስቀመጥ መቻል አለብን፡፡ ይህ መሠረታዊው ነው፡ ማለትም ዝቅተኛው ነው። ከዚያ በኋላ ግን ዐረፍተ ነገሩ ዕያደገ በመሄድ ሙሉ ታሪክን ሊፈጥር ይችላል ማለት ነው። እንዴት ነው የምናሳድገው? ለሚለው ጥያቄ የቃላትን ሥራ ለይቶ ማወቅ ነው። (ሙያን እና ባለሙያን ማወቅ ማለት ነው)

መሠረታዊ ለሆነ ዐረፍተ ነገር ሁለት ነገሮች መኖር አለባቸው ያልናቸው የሚከተሉት ናቸው
·        “የዐረፍተ ነገር ባለቤት” እና
·        “የዐረፍተ ነገር ማሠሪያ” ወይም “አንቀጽ፤ግሥ” እነዚህ ግዴታ መኖር አለባቸው።

መስፍን ሰትየ
1. ማን? ገብረ ማርያም
2. ምን ሠራ? ጠጣ
ይህ መሠረታዊ ዐረፍተ ነገር ሁለት ጥያቄዎችን መለሰልን ማለት ነው።

ዐረፍተ ነገሩን ለማሳደግ ልዩ ልዩ ትርጉም የሚሰጡ ጥያቄዎችን በመጠየቅና መልስ በማግኘት የሚከናወን ነው፡ (በሌላ አባባል በዚህ ውስጥ እንጨት ሚስማርና ስሚንቶ መኖር አለባቸው)

እንጨቱ = ባለቤት፤ ሚስማሩ= ማሠሪያ አንቀጽ፤ ስሚንቶው= መስተጻምር እና መስተዋድድ እንዲሁም ቃለ አልዕሎ የሚባሉትን ሊወክሉ ይችላሉ።
3. ምን ጠጣ?  ወይን፤ አሁን “ወይን” የሚለውን ቃል በምን ዓይነት መልኩ ነው በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ መቀመጥ ያለበት የሚለውን ጥያቄ መመለስ መቻል አለብን (ይቀየራል ወይስ እንዳለ ነው የሚቀመጠው?)

መስፍን ሰትየ ወይነ።
4. በምን ጠጣ? በመጠጫ ወይም በጽዋ፤  “ምስታይ” ወይም “ጽዋዕ” የሚባሉት ቃላትስ ምን ዓይነት ናችው? ይቀየራሉ? ወይምስ አይቀየሩም? ሌላ ተጨማሪ ቃል ወይም አገባብን ይፈልጋሉ? ወይም አይፈልጉም?
መስፍን ሰትየ ወይነ ምስታይ (በምስታየ ወይን)

5. እንዴት ጠጣ? ነቢሮ (እንዘ ይነብር)።
መስፍን ሰትየ ወይነ ምስታይ ነቢሮ።

6. የት ወይም በምን ላይ ተቀምጦ ጠጣ? ወንበር ላይ(ውንበሩ ላይ)፤
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር (መንበሩ)

7. መቼ ነው የጠጣው? ከምግብ ወይም ከበላ በኋላ፤
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ።

8. ምንን ከበላ በኋላ ነበር የጠጣው? ምግብን ወይም ዳቦን፡
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ ምሳሐ

9. ከማን ጋር ነበር የበላው? ከሚስቱ ጋር፤
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ ምሳሐ ምስለ ብእሲቱ

10.   ሚስቱ ማን ትባላለች? ራሄል
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ ምሳሐ ምስለ ብእሲቱ እንተ ትሰመይ ራሄል

እንደምታዩት ከለፈው በበለጠ ዐረፍተ ነገሩን ከ7 ወደ 10 ደረጃ አሳድጌዋለሁ፤ ስለዚህ በዚህ ዓይነት መልኩ የሚከተሉትን 4 ቃላት ትሠራላችሁ ። ማለትም ሁለቱ የዐረፍተ ነገራት ባለቤቶች ናቸው፤ ሁለቱ ደግሞ የዐረፍተ ነገሩ ማሠሪያ ናቸው። ስለዚህ በሁለቱ 10 መሥመሮችን፤ በሁለቱ እንደዚሁ 10 መሥመሮችን ትጽፋላችሁ። (ሁለት የቤት ሥራዎች ማለት ነው አንድ በሴት ፆታ ሌላው በወንድ ፆታ)


ስሞቹ፡
“ራሄል” እና “መንክር”
ግሶቹ ደግሞ
“ሰትየ” እና “በልአ” ናቸው

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

No comments:

Post a Comment