Monday, June 29, 2020

#EnglishLesson1

English  lesson one/የአንግሊዘኛ ትምህርት ኣንድ ለጀማሪዎች

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ ነው፣ ወደ አውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ እንኳን በሰላም መጣችሁ፤ በዚህ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርታችን ስለ እንግሊዘኛ ቋንቋ መሠረታዊ ነገሮችን እናያለን፤ በመጀመሪያ ግን የሚከተሉትን ምክራዊ መመሪያዎች ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ።

አንድ የማናውቀውንና በጣም በጉጉት ማወቅ የምንፈልገውን ነገር በምንመኘው ልክ ለማወቅ ለየት ያሉ ባሕርያትን በውስጣችን መፍጠር ይኖርብናል፤ ከነዚህም የስኬት ባሕርያት መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህም

·         በጸጥታና በተረጋጋ ስሜት ለሚተላለፈው ትምህርት ልዩ ትኩረትን መስጠትና መልእክቱን ማስተዋል
·        የሚተላለፈውን ትምህርት ሳያቋርጡ እስከ መጨረሻው በጥንቃቄ መመልከት
·        ወሳኝ የሆኑ ነጥቦችን በልዩ ማስታዎሻ ጽፎ መያዝና እየተመለሱ ማየት
·        ቃሉን ወይም ዐረፍተ ነገሩን እየደጋገሙ መስማት፤ማየት፣ እና መናገር
·         የማናውቀው ቃል ወይም ኃረግ ካጋጠመን ከመዝገበ ቃላት ወይም ዲክሺነሪ ውስጥ ፈልገን ትርጉሙን ማግኘት
·        ትምህርቱ ቢከብደንም እንኳን የበለጠ መደጋገም እንጅ ተስፋ አለመቁረጥ የሚሉት እነዚህ ስድስት ነጥቦች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፤ እነዚህን መተግበር ከቻልን ያለምንም ጥርጥር ምኞታችን ይሳካል።

የዛሬው ትምህርታችን ስለፊደላት ነው በልዩ ትኩረት እንከታተል
 በዚህ በክፍል አንድ ስለ ፊደላት የምናየው የፍደላቱን ብዛት፣ ቅርጻቸውን ወይም መልካቸውን፤ ስማቸውን፤ ድምጻቸውን፣ እና የሚተኳቸውን የአማርኛ ወይም የግእዝ ፊደላት፤ እንዲሁም አናባቢ ፊደላትን እና ተናባቢ ፊደላትን ይሆናል።

በእንግሊዘኛ አልፋቤት ወይም የፊደል ገበታ 26 ፊደላት ይገኛሉ። ከነዚህ 26 ፊደላት ውስጥ 5ቱ መደበኛ አናባቢዎች ናቸው፤ አንዱ ልዩ ፊደል እና ቀሪዎቹ 20 ፊደላት ደግሞ ተናባቢዎች ናቸው። ሃያ ስድስቱም(26ቱም) ስሞል እና ካፒታል ወይም አፐር ኬዝ እና ለወር ኬዝ ወይም በአማርኛ ትንሺና ትልቅ የሚባሉ ሁለት ዓይነት መልክን የያዙ ናቸው፤ አንዳንዶቹ  በመጠን እንጅ በቅርጽ ልዩነት የላቸውም  (upper and lowercase letters (Capital and small letters)

ከዚህ በታች የምናየው የእንግሊዘኛ የፊደል ገበታ ነው፤ ፊደላቱ በትልቁና በትንሹ ፊደል ተጽፈው በሰንጠረዥ ውስጥ ይታያሉ።
በዚህ ሰንጠረዥ 26ቱም ፊደላት ይገኛሉ፤ ስለዚህ ይህ ሰንጠረጅ አንድ በአንድ ከ1 እስከ 26 ድረስ ያሉትን ፊደላት ቅርጻቸውን ስማቸውን፣ ድምጻቸውን እና የሚተካቸውን የግእዝ ወይም የአማርኛ ፊደል አጠቃሎ ይዟል። ማለትም በ1ኛው መስመር ፊደላቱ፣ በ2ኛው የፊደላቱ ስም፣ በ3ኛው የፊደላቱ ድምጽ፣ በ4ኛው ደግሞ የሚተካቸው የግእዝ ፊደል ይገኛል። መጨረሻ ላይ ደግሞ “መፍቻ” በሚለው ሥር ከአንድ በላይ ድምጽ ያላቸው ፊደላትና ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ፊደላት ሲቀናጁ የሚፈጥሩት የአማርኛ ሆሄ ተገልጿል። ሌላው ለማስታዎስ እንዲያመች በማሰብ በልዩ ልዩ ቀለማት የተጻፉ ፊደላት አሉ። አናባቢዎች በቀይ፣ ተናባቢዎች በወይን ጠጅ፣ እና ስሞል ሌተሮች(ወይም ትንንሾቹ ፊደላት) በሰማያዊ ተጽፈው ይገኛሉ አስተውሉ።
ክፍል ሁለት



ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘእንግሊዘኛ ነው ዛሬ በዚህ በክፍል 2 ትምህርታችን ስለ አናባቢዎችና ተናባቢዎች እንማራለን ተከታተሉ።


አሁን በሥዕሉ ላይ ወዳሉት ፊደላት ተመልከቱ እያንዳንዳቸውን እየለያየን እንመለከታቸዋለን
በሥዕሉ ላይ እንደምታዩት አናባቢዎች ወይም ቫውልስ በቀይ ባግራውንድ ላይ ተጽፈዋል፤ ተናባቢዎች በጥቁር ተጽፈዋል፤ አንድ ፊደል ደግሞ በሁለት አይነት ቀለም ተከፍሏል። ስለሱ በኋላ ሰፋ አድርገን እናያለን።

A the first main Vowel
B consonant
C consonant
D consonant
E vowel
F consonant
G consonant
H consonant
I vowel
J consonant
K consonant
L consonant
M consonant
N consonant
O vowel
P consonant
Q consonant
R consonant


የግአዝ ቋንቋ መማርያ መጽሐፌን ለመግዛት የሚከተለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በ +1 703 254 6601 ይደውሉ

#LisaneGeez~ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን ክፍል ሁለት

ልሣነ ግአዝ የጋራ ቋንቋችን ስለተሰኘው ምጽሐፍ ክፍል ሁለት1:30ፒኤም የቀጥታ ስርጭት

Sunday, June 14, 2020

መጽሐፈ ነገሥት 2ኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 11



የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍለ አሥራ አንድ መጽሐፈ ነገሥት ሁለተኛ እንማራለን መጽሐፈ ነገሥት 2ኛ
ታሪኩን ከ1ኛ ነገሥት ይቀጥላል


ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ዛሬ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2ፒም ላይ ይጀምራል እንዳይረሱ፤ ሰብስክራይብ፣
ሼርና ላይክ ያድርጉ፤ ካልወደዱት ምክንያቱን ጠቅሰው አልወደድኩትም የሚለውን መጫን ይችላሉ፤  አስተያየትም ይጻፉ::

“ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቁ” የሚለውን የምንማርበትን  መጽሐፍ ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ (ራሱ መጽሐፉን)
 
ተጭነው ከአማዞን ይግዙ ወይም በዚህ ስልክ ይደውሉ፡    +1 703 254 6601

Thursday, June 11, 2020

የዐረፍተ ነገር አመሠራረት እና ዕድገት በልሣነ ግእዝ ለ2ኛ እና ለ3ኛ ክፍል ተማሪዎች



“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የሚለውን መጽሐፍ ለመግዛት የሚከተለውን ይጫኑ ወይም ይደውሉ. ልሣነ ግእዝ የሚለውን መጽሐፍ ይግዙ+1 703 254 6601https://amzn.to/30A7Nvd

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው፡ ዛሬ ስለ ዐረፍተ ነገር ዕድገት የተሰጠውን  ልምምድ መሠረት በማድረግ ተጨማሪ መልስና ማብራርያ እሰጣችኋለሁ ተከታተሉ።

ይህ ትምህርት የበለጠ ትኩረት ሰጥታችሁ ልታጠኑት የሚገባ ነው። ብዙ ቃላት ማወቅ ብቻ ጥቅም የለውም ዋናው ነገር ግን በተወሰኑ ቃላት አስተካክሎ መጻፍ፣ መናገር ወዘተ መቻል ነው፤ ስለዚህ ለመግባባት ወሳኙ የቃላትን ዓይነትና ሥራ ለይቶ ማወቅ ነው። (ስምንቱን(8)፤፰ቱን የንግግር ክፍሎች)

አንድ የተሟላ ትርጉምን የሚሰጥ ዐረፍተ ነገር ለመሥራት 2 ነገሮችን ማወቅና በቦታቸው ማስቀመጥ መቻል አለብን፡፡ ይህ መሠረታዊው ነው፡ ማለትም ዝቅተኛው ነው። ከዚያ በኋላ ግን ዐረፍተ ነገሩ ዕያደገ በመሄድ ሙሉ ታሪክን ሊፈጥር ይችላል ማለት ነው። እንዴት ነው የምናሳድገው? ለሚለው ጥያቄ የቃላትን ሥራ ለይቶ ማወቅ ነው። (ሙያን እና ባለሙያን ማወቅ ማለት ነው)

መሠረታዊ ለሆነ ዐረፍተ ነገር ሁለት ነገሮች መኖር አለባቸው ያልናቸው የሚከተሉት ናቸው
·        “የዐረፍተ ነገር ባለቤት” እና
·        “የዐረፍተ ነገር ማሠሪያ” ወይም “አንቀጽ፤ግሥ” እነዚህ ግዴታ መኖር አለባቸው።

መስፍን ሰትየ
1. ማን? ገብረ ማርያም
2. ምን ሠራ? ጠጣ
ይህ መሠረታዊ ዐረፍተ ነገር ሁለት ጥያቄዎችን መለሰልን ማለት ነው።

ዐረፍተ ነገሩን ለማሳደግ ልዩ ልዩ ትርጉም የሚሰጡ ጥያቄዎችን በመጠየቅና መልስ በማግኘት የሚከናወን ነው፡ (በሌላ አባባል በዚህ ውስጥ እንጨት ሚስማርና ስሚንቶ መኖር አለባቸው)

እንጨቱ = ባለቤት፤ ሚስማሩ= ማሠሪያ አንቀጽ፤ ስሚንቶው= መስተጻምር እና መስተዋድድ እንዲሁም ቃለ አልዕሎ የሚባሉትን ሊወክሉ ይችላሉ።
3. ምን ጠጣ?  ወይን፤ አሁን “ወይን” የሚለውን ቃል በምን ዓይነት መልኩ ነው በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ መቀመጥ ያለበት የሚለውን ጥያቄ መመለስ መቻል አለብን (ይቀየራል ወይስ እንዳለ ነው የሚቀመጠው?)

መስፍን ሰትየ ወይነ።
4. በምን ጠጣ? በመጠጫ ወይም በጽዋ፤  “ምስታይ” ወይም “ጽዋዕ” የሚባሉት ቃላትስ ምን ዓይነት ናችው? ይቀየራሉ? ወይምስ አይቀየሩም? ሌላ ተጨማሪ ቃል ወይም አገባብን ይፈልጋሉ? ወይም አይፈልጉም?
መስፍን ሰትየ ወይነ ምስታይ (በምስታየ ወይን)

5. እንዴት ጠጣ? ነቢሮ (እንዘ ይነብር)።
መስፍን ሰትየ ወይነ ምስታይ ነቢሮ።

6. የት ወይም በምን ላይ ተቀምጦ ጠጣ? ወንበር ላይ(ውንበሩ ላይ)፤
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር (መንበሩ)

7. መቼ ነው የጠጣው? ከምግብ ወይም ከበላ በኋላ፤
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ።

8. ምንን ከበላ በኋላ ነበር የጠጣው? ምግብን ወይም ዳቦን፡
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ ምሳሐ

9. ከማን ጋር ነበር የበላው? ከሚስቱ ጋር፤
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ ምሳሐ ምስለ ብእሲቱ

10.   ሚስቱ ማን ትባላለች? ራሄል
መስፍን ሰትየ ወይነ በምስታይ ነቢሮ ላዕለ መንበር ድኅረ በልአ ምሳሐ ምስለ ብእሲቱ እንተ ትሰመይ ራሄል

እንደምታዩት ከለፈው በበለጠ ዐረፍተ ነገሩን ከ7 ወደ 10 ደረጃ አሳድጌዋለሁ፤ ስለዚህ በዚህ ዓይነት መልኩ የሚከተሉትን 4 ቃላት ትሠራላችሁ ። ማለትም ሁለቱ የዐረፍተ ነገራት ባለቤቶች ናቸው፤ ሁለቱ ደግሞ የዐረፍተ ነገሩ ማሠሪያ ናቸው። ስለዚህ በሁለቱ 10 መሥመሮችን፤ በሁለቱ እንደዚሁ 10 መሥመሮችን ትጽፋላችሁ። (ሁለት የቤት ሥራዎች ማለት ነው አንድ በሴት ፆታ ሌላው በወንድ ፆታ)


ስሞቹ፡
“ራሄል” እና “መንክር”
ግሶቹ ደግሞ
“ሰትየ” እና “በልአ” ናቸው

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት ዘግእዝ

Saturday, June 6, 2020

የቃላት ባሕርይና ትርጉም በመጽሐፍ ቅዱስ



የቃላት ባሕርይና ትርጉም በመጽሐፍ ቅዱስ


ቃላት ያድጋሉ፣ ይበዛሉ፣ ይሻሻላሉ፣ ትርጉማቸውን ይቀይራሉ፣ ተጨማሪ ትርጉምን ይፈጥራሉ፣ ወዘተ. በመሆኑም አንድ ቃል አንድ ትርጉምን ብቻ ይዞ አይገኝም አይኖርም፣ ነገር ግን አስተማሪዎች በየዘመናቱ የቃላትን ልዩ ልዩ ትርጉም ማስተማር ይኖርባቸዋል። ይህ ሁኔታ በተለይ በመጽሐፍ ቅዱስ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፤ ዛሬ የምንማረው የተወሰኑ ቃልትን ነገር ግን በብዙኃኑ ዘንድ ተዘውትረው አጠያያቂ በሆኑት ላይ እንነጋገራለን።

“አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ
እስከ ዛሬ ድረስ በየዕለቱ እየማለድኩ ባርያዎቼ ነቢያትን
ሁሉ ልኬላችሁ ነበር” ኤር.7፡25

“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ራሱ በማይነገር
መቃተት ይማልድልናል” ሮሜ 8፡ 26

“ስለ እኛ የሚማልደው
ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ሮሜ፡ 8፡34

·        “ባርክዎሙ ለእለ ይረግሙክሙ” ማቴ 5፡44
·        “ባረከ ኢዮብ ዕለተ ልደቱ” ኢዮ. 3፡
·        “ኢታምልክ ባዕደ አምላከ ዘእንበሌየ” ዘጸ.20
  •   አምለከ
  •  ተዋቅሶ(ይትዋቀስ)
  • ባረከ

ይህንን በዘመናዊ መልኩ በእንግሊዘኛም ጭምር የግእዝን ቋንቋ መማሪያ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀውን መጽሐፍ ለመግዛት ከዚህ በታች ያለውን ራሱ መጽሐፉን ይጫኑ ወይም በዚህ ስልክ ይደውሉ፡ +1 703 254 6601



እነዚህን ሁለት መጻሕፍት ማግኘት አለበዎ! ይረኩባቸዋል