Sunday, July 30, 2017

ለግእዝ ተማሪዎች ሕግና ሥርዓት/ Law and Rules for Geez student


“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የግእዝን ቋንቋ ለመማር በተለያዩ ግሩፖች ለታቀፉ ተማሪዎች የወጣ ሕግና መመሪያ

 



የትምህርት አሰጣጥን ስልት በተመለከተ


በቫይበር፤በዋትስአፕ እና በኢሞ አንድነት (Viber, WhatsApp, & Imo) በሚሰጠው የልሣነ ግእዝ ትምህርት ውስጥ የተደነገገ የመማር ማስተማር ሕግና መመሪያ
በዚህ ግሩፕ ውስጥ የሚሰጠው የግእዝ ትምህርት ብቻ ይሆናል፤ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና የሚሰጡት መልሶችም በአውደ ጥናት በሚሰጠው የግእዝ ትምህርት ዙሪያ እና በሚሰጠው የትምህርትና የተማሪዎች የዕውቀት ደረጃ ብቻ ያተኮረ ነው፤

በዚህ ግሩፕ መማር የሚችሉ፡

ግእዝ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋነቱና ከመንፈሳዊነቱ ባሻገር እንደ ማነኛውም ቋንቋ መግባቢያ እንደመሆኑ መጠን ፍላጎት ያለው ሁሉ ያለምንም የብሔር፤ የእምነትም ሆነ የፆታ ልዩነት ሳይደረግ መማር ይችላሉ።

በዚህ ግሩፕ ውስጥ በጥብቅ የሚከለከሉ ወይም የማይፈቀዱ

1.     ፖለቲካና ፖለቲካ ነክ የሆኑ ጥያቄዎች፤መልሶች፤ እንዲሁም ማነኛውም ጽሁፍ ወይም የቃል ውይይት
2.     አከራካሪ እና ልዩነትንና ጥላቻን የሚፈጥሩ የሃይማኖት ወሬዎች (መናፍቅ፤ ተሐድሶ ወዘተ--)
3.     ከግእዝ ትምህርትና መማርያ፤ እንዲሁም በአውደ ጥናት ከሚተላለፉት የመማርያ መጻሕፍት በስተቀር ማነኛውም የሽያጭ ማስታወቂያ ማስተላለፍ አይፈቀድም ይህንን የሚያደርግ ያለምንም ጥያቄ ከግሩፑ ይወገዳል

 

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግሩፑ ሐላፊዎች ፈቃድ ሊተላለፉ የሚችሉ ነገሮች፤ሁኔታዎች፤ ወይም ማስታዎቂያዎች

1.     ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በአላት
2.     ለብዙሃኑ ጥቅም ነው ተብሎ የታመነበት የስብሰባ ጥሪ
3.     በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ሥር የሚገኝ የበጎ አድራጎት የስብሰባ ጥሪ እና የመሣሰሉት ሲሆኑ
መጀመሪያ ከእኔ ጋር መነጋገር ግድ ነው። እንዲሁ ይህንን ህግ በመጣስ የሚያስተላልፍ ሰው ከአንድ ጊዜ ምክር በኋላ ከግሩፑ ይወገዳል።

ሸር (share)ማድረግ ወይም ማነኛውንም ትምህርት ወደዚህ ግሩፑ መልቀቅን(post) በተመለከተ


1. ወደዚህ ግሩፕ ማነኛውንም ትምህርት፤መረጃ፤ የግእዝ ትምህርትን ቪዲዮን ከአውደ ጥናትም ቢሆን ወደዚህ ግሩፕ ሽር ማድረግና መልቀቅ የሚችለው አስተማሪ/እኔ ብቻ ነኝ ።ምክንያቱም እኔ እንደ ተማሪዎቹ አቅምና ችሎታ ለክቼ ነው የማስተምረው ከአቅማችሁ በላይ ወይም በታች ከሆነ ውጤት ያለው ትምህርት አይሆንም ትርፉ ድካም ነው።
2. ከዚህ ግሩፕ ውስጥ ወደ ሌላ ሽር ማድረግ የሚችለውስ ማነው? ሁላችሁም ከዚህ ግሩፕ የምትማሩትንም ሆነ ከአውደ ጥናት (በዩቱብ) ወደ ሌላ ግሩፕ፤ግለሰብ ወዘተ ሸር ማድረግ ትችላላችሁ። ግን “ኢምቤድ አታድርጉ” Embedding? no, no,no.
3. ከአውደ ጥናትም ሆነ (ከዚህ ግሩፕ ፤ ከዩቱብ ወዘተ) ወይም ከሌላ አንድን ነገር ሸር ስታደርጉ ማድረግ የሌለባችሁ ነገር “ኢምቤድ) (Embed/Embedding)ማድረግ ነው። ኢምቤድ ማድረግ የለባችሁም፤ ኢምቤድ ማድረግ “ከመስረቅ የተለየ አይደለም”

የናንተ የተማሪዎች መብት

•   መማር
•   በተማርነው መሠረት መጠየቅ
•   መልስ ማግኘት
•   በጣም አንገብጋቢና ለብዙኃኑ ጥቅም
የሚሆን መረጃ ካላችሁ ከእኔ ጋር  በግል
መስመር መነጋገር የሚሉት ናቸው


















ለሕግ መገዛትና የብዙኃኑን ክብርና መብት መጠበቅ እግዚአብሔርን መፍራት ሰውንም ማክበር ነው::

No comments:

Post a Comment