Tuesday, July 11, 2017

Answer/መልሶች

የ50ው የመመዘኛ ፈተናዎች መልሶ

ለሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የመመዘኛ ፈተና አንድ መልሶች


ጥ፡1-14 የቃላት ትርጉም፦የሚከተሉትን ቃላት ወደ አማርኛ ቋንቋ ቀይሩ።
1.      ምስጋና
2.     ቢ፤ባ፤ብ/እናት
3.     ስለ
4.     አለ(ለ ይጠብቃል) አለኝ፤አለን --- እና በአሥሩም መራሕያን ይረባል)
5.     ጓደኛ
6.     ዛሬ
7.     መግቢያ
8.     የእውቀት መስተዋት
9.     ቋንቋ(ምላስ)
10.    3ኛ
11.     ጽሁፍ(ሆሄ)
12.    እንዴት
13.    4ኛ
14.    7ኛ
ጥ፡15-25 የዐረፍተ ነገር ትርጉም፦የሚከተሉትን አባባሎች ወደ አማርኛ ተርጉሙ
15.    ጥያቄዎችን መልሱ
16.   ራሶቻችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ(ወንዶች ብዙ ሴቶች ቢኖሩም አንድ ወንድ ካለ በወንዶች ይጠራል)
17.    ምክር ለሚያደርጋት (ለሚቀበላት፤ለሚሰማት፤ ለሚፈጽማት)መልካም ናት
18.    አባቶቻችን እንደሚሉት(እንዳሉት) መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ
19.     (እናንተ ሆይ) በመጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራትን፤ ከዚያ በኋላም የግእዝን ቋንቋ ታውቁ ዘንድ ወደ አውደ ጥናት አዳራሽ(ቤት) በሰላም ግቡ።
20.   የአባታችሁን አባት ስም(የአያታችሁን ስም) ተናገሩ (ለብዙ ሴቶች)
21.    አንተ ማነህ? ሥራህስ ምንድነው?
22.   እኔ ዐይነኡ “ዐ” አይደለሁም ነገር ግን አልፋው “አ” ነኝ
23.   ለማደርገው ነገር ሁሉ ምክንያት አለኝ
24.   ገጸ መጽሐፍ
25.   ጠይቆት ይገብር ሊቀ
ጥ፡26-37 ተጨማሪ ማብራርያን የሚሹ፦ተጨማሪ ማብራርያ በመስጠት ጥያቄዎቹን መልሱ
26.   “መስተዋድድ/ Prepositions” የሚያፈቃቅር (ማለትም የሚያጣጥም) ማለት ሲሆን “ንኡሳን ወይም ትንንሽ አበባቦች ናቸው) ምሳሌ ለመስተዋድድ “ኀበ” “ምስለ”  ለመስተጻምር“/Conjunctions)አያያዥ ማለት ሲሆን ለምሳሌ፦ “ወ” “አላ” ወዘተ
27.   የአቡነ ሰላማ አገሩ የት ነው? ግሪክ
28.   ከአዘጋጅው ፤ ሰው እናታችን ጽዮን ይላል የመጀመሪያው “እምነ” “ከ” ማለት ሲሆን ንኡስ አገባብ ነው “ም” አይጠብቅም። ሁለተኛው “እምነ” “እናታችን” ማለት ሲሆን ስም ነው “ም” ይጠብቃል
29.  ፳፪/፳፪ቱ(እሥራ ወክልኤቱ) እሥራ ወሰንዩም ይባላል
30.    “ፊደልን የቆጠሩ ሁሉ በየቦታው አስተማሪዎች ሆኑ” የማስተማር ችሎታ ሳይኖራቸው በድፍረት ለሚያስተምሩ ሰዎች የሚነገር ትችታዊ አባባል ነው።
31.     “ጸሎቱ” ጸ ስትጸልይ ጥራኝ አለ” ማለት ለሰሙ ለመጸለይ ስትፈልግ ወይም ስትዘጋጅ ጥራኝ ይባላል፤ ለወርቁ ግን ጸሎቱ ጸ ስትጸልይ ጥራኝ አለ ማለት ስለጸሎትና ስለ መጸለይ ለመጻፍ መጠቀም ያለብህ እኔን ነው (ፀሐዩን ፀ አይደለም ማለት ነው)
32.   ንጉሡ ሠ “የወለደኝ ንጉሡ ሠ ብሎ ስም አወጣልኝ” ማለት የፈለሰፈኝ ሰው ንጉሡ ሠ ብሎ ሰየመኝ ማለት ነው
33.   አስማት/መተት የጥንቆላ
34.   ለጸሎት ተነሡ/አነ/ ተናጋሪ አነ/ንሕነ፤ ሰሚዎች አንትሙ 
35.   ሄደ/ሐላፊ
36.  ክፈቱ/ትእዛዝ 
37.   “ኒ” ወደ “ኔ” መቀየር/ መድኃኔ ዓለም
ጥ፡ 38-47 ትርጉምን የማይሹ ጥያቄዎች፦ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ
38.   መጽሐፈ ሄኖክና መጽሐፈ ኵፋሌ  
39.  21
40.   7
41.    5
42.   ካዕብና ሣብዕ
43.   5/ ሀ፤ሐ፤ኀ፤አ፤ዐ
44.   9
45.   ሁለት፤ሁለት
46.  ሠ፤ንጉሡ ሠ፤/ ሰ፤እሳቱ ሰ
47.   የደረጃ/የተራቍጥር ስማቸው
48.   እውነት
49.  እውነት

No comments:

Post a Comment