Sunday, July 30, 2017

8ቱ የንግግር ክፍሎች/The Eight Parts of Speech

ይበሉ መምህራን እንዘ ይበዉኡ ኀበ ቤተ ትምህርት ቅድመ ይውጥኑ ከመይምሀሩ ትምህርተ

ሰ     ላም ለኵልክሙ አርድእተ ልሣነ ግእዝ
·         እንቋዕ አብጽሐክሙ እግዚአብሔር በሰላም ለዛቲ ሰዓት
·         ዮም ንትሜሀር በይነ ክፍላተ ነገር
·         ስምኡ ወአጽምኡ በአርምሞ ልሣን
·         ጠይቁ ወአውሥኡ ጥያቄያተ
















ስምንቱ የንግግር ክፍሎች/The Eight Parts of Speech

1.      ስም= ስም/Noun
2.     ተውላጠ = የስም ተለዋጭ/Pronoun
3.     አንቀጽ/ግሥ=ማሠሪያ አንቀጽ/Verb
4.     ተውሳከ ግሥ =የግሥ ረዳት/Adverb
5.     ቅጽል=ገላጭ/Adjective
6.     መስተዋድድ= አዛማጅ/Prepositions
7.     መስተጻምር=አያያዥ/Conjunctions
8.     ቃለ አጋኖ= የሚያጋንን/የሚያጎላ ቃል/Interjections


በመጽሐፉ ውስጥ ከስምንቱ የንግግር ክፍሎች ጋር ተዘርዝረው የሚገኙት በቪዲዮውም ውስጥ ከስምንቱ ጋር ያብራራኋቸው “ዝርዝር ቅጽል” እና “ሰዋስው” የሚባሉት ተዳብለው ወይም ከሌሎች ጋር ተጨምረው ይቆጠራሉ ።

ስለዚህ፤
“ዝርዝር ቅጽል”(Possessive Pronouns) ከ “ተውላጠ ስም”(Pronouns) ፤ “ሰዋስው” (Grammar) ደግሞ ከ “መስተዋድድ”(Prepositions) እና ከ “መስተጻምር” (Conjunctions)ጋር ይመደባሉ።

መስተ ዋድድና መስተጻምር ተቆርጠው ስለቀሩ ይቅርታ የያንዳንዱን ትንታኔ ስንማር እንማራቸዋለን


ይህ ትምህርት የሚገኘው “ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” ከተሰኘው የግእዝ ቋንቋ መማርያ 1ኛ መጽሐፍ ክፍል/ምእራፍ 2 ገጽ 31 ላይ ነው መጽሐፉን ማግኘት ይኖርባችኋል።



ለግእዝ ተማሪዎች ሕግና ሥርዓት/ Law and Rules for Geez student


“ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን” የግእዝን ቋንቋ ለመማር በተለያዩ ግሩፖች ለታቀፉ ተማሪዎች የወጣ ሕግና መመሪያ

 



የትምህርት አሰጣጥን ስልት በተመለከተ


በቫይበር፤በዋትስአፕ እና በኢሞ አንድነት (Viber, WhatsApp, & Imo) በሚሰጠው የልሣነ ግእዝ ትምህርት ውስጥ የተደነገገ የመማር ማስተማር ሕግና መመሪያ
በዚህ ግሩፕ ውስጥ የሚሰጠው የግእዝ ትምህርት ብቻ ይሆናል፤ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና የሚሰጡት መልሶችም በአውደ ጥናት በሚሰጠው የግእዝ ትምህርት ዙሪያ እና በሚሰጠው የትምህርትና የተማሪዎች የዕውቀት ደረጃ ብቻ ያተኮረ ነው፤

በዚህ ግሩፕ መማር የሚችሉ፡

ግእዝ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋነቱና ከመንፈሳዊነቱ ባሻገር እንደ ማነኛውም ቋንቋ መግባቢያ እንደመሆኑ መጠን ፍላጎት ያለው ሁሉ ያለምንም የብሔር፤ የእምነትም ሆነ የፆታ ልዩነት ሳይደረግ መማር ይችላሉ።

በዚህ ግሩፕ ውስጥ በጥብቅ የሚከለከሉ ወይም የማይፈቀዱ

1.     ፖለቲካና ፖለቲካ ነክ የሆኑ ጥያቄዎች፤መልሶች፤ እንዲሁም ማነኛውም ጽሁፍ ወይም የቃል ውይይት
2.     አከራካሪ እና ልዩነትንና ጥላቻን የሚፈጥሩ የሃይማኖት ወሬዎች (መናፍቅ፤ ተሐድሶ ወዘተ--)
3.     ከግእዝ ትምህርትና መማርያ፤ እንዲሁም በአውደ ጥናት ከሚተላለፉት የመማርያ መጻሕፍት በስተቀር ማነኛውም የሽያጭ ማስታወቂያ ማስተላለፍ አይፈቀድም ይህንን የሚያደርግ ያለምንም ጥያቄ ከግሩፑ ይወገዳል

 

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግሩፑ ሐላፊዎች ፈቃድ ሊተላለፉ የሚችሉ ነገሮች፤ሁኔታዎች፤ ወይም ማስታዎቂያዎች

1.     ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በአላት
2.     ለብዙሃኑ ጥቅም ነው ተብሎ የታመነበት የስብሰባ ጥሪ
3.     በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ሥር የሚገኝ የበጎ አድራጎት የስብሰባ ጥሪ እና የመሣሰሉት ሲሆኑ
መጀመሪያ ከእኔ ጋር መነጋገር ግድ ነው። እንዲሁ ይህንን ህግ በመጣስ የሚያስተላልፍ ሰው ከአንድ ጊዜ ምክር በኋላ ከግሩፑ ይወገዳል።

ሸር (share)ማድረግ ወይም ማነኛውንም ትምህርት ወደዚህ ግሩፑ መልቀቅን(post) በተመለከተ


1. ወደዚህ ግሩፕ ማነኛውንም ትምህርት፤መረጃ፤ የግእዝ ትምህርትን ቪዲዮን ከአውደ ጥናትም ቢሆን ወደዚህ ግሩፕ ሽር ማድረግና መልቀቅ የሚችለው አስተማሪ/እኔ ብቻ ነኝ ።ምክንያቱም እኔ እንደ ተማሪዎቹ አቅምና ችሎታ ለክቼ ነው የማስተምረው ከአቅማችሁ በላይ ወይም በታች ከሆነ ውጤት ያለው ትምህርት አይሆንም ትርፉ ድካም ነው።
2. ከዚህ ግሩፕ ውስጥ ወደ ሌላ ሽር ማድረግ የሚችለውስ ማነው? ሁላችሁም ከዚህ ግሩፕ የምትማሩትንም ሆነ ከአውደ ጥናት (በዩቱብ) ወደ ሌላ ግሩፕ፤ግለሰብ ወዘተ ሸር ማድረግ ትችላላችሁ። ግን “ኢምቤድ አታድርጉ” Embedding? no, no,no.
3. ከአውደ ጥናትም ሆነ (ከዚህ ግሩፕ ፤ ከዩቱብ ወዘተ) ወይም ከሌላ አንድን ነገር ሸር ስታደርጉ ማድረግ የሌለባችሁ ነገር “ኢምቤድ) (Embed/Embedding)ማድረግ ነው። ኢምቤድ ማድረግ የለባችሁም፤ ኢምቤድ ማድረግ “ከመስረቅ የተለየ አይደለም”

የናንተ የተማሪዎች መብት

•   መማር
•   በተማርነው መሠረት መጠየቅ
•   መልስ ማግኘት
•   በጣም አንገብጋቢና ለብዙኃኑ ጥቅም
የሚሆን መረጃ ካላችሁ ከእኔ ጋር  በግል
መስመር መነጋገር የሚሉት ናቸው


















ለሕግ መገዛትና የብዙኃኑን ክብርና መብት መጠበቅ እግዚአብሔርን መፍራት ሰውንም ማክበር ነው::

Tuesday, July 11, 2017

Answer/መልሶች

የ50ው የመመዘኛ ፈተናዎች መልሶ

ለሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የመመዘኛ ፈተና አንድ መልሶች


ጥ፡1-14 የቃላት ትርጉም፦የሚከተሉትን ቃላት ወደ አማርኛ ቋንቋ ቀይሩ።
1.      ምስጋና
2.     ቢ፤ባ፤ብ/እናት
3.     ስለ
4.     አለ(ለ ይጠብቃል) አለኝ፤አለን --- እና በአሥሩም መራሕያን ይረባል)
5.     ጓደኛ
6.     ዛሬ
7.     መግቢያ
8.     የእውቀት መስተዋት
9.     ቋንቋ(ምላስ)
10.    3ኛ
11.     ጽሁፍ(ሆሄ)
12.    እንዴት
13.    4ኛ
14.    7ኛ
ጥ፡15-25 የዐረፍተ ነገር ትርጉም፦የሚከተሉትን አባባሎች ወደ አማርኛ ተርጉሙ
15.    ጥያቄዎችን መልሱ
16.   ራሶቻችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ(ወንዶች ብዙ ሴቶች ቢኖሩም አንድ ወንድ ካለ በወንዶች ይጠራል)
17.    ምክር ለሚያደርጋት (ለሚቀበላት፤ለሚሰማት፤ ለሚፈጽማት)መልካም ናት
18.    አባቶቻችን እንደሚሉት(እንዳሉት) መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ
19.     (እናንተ ሆይ) በመጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራትን፤ ከዚያ በኋላም የግእዝን ቋንቋ ታውቁ ዘንድ ወደ አውደ ጥናት አዳራሽ(ቤት) በሰላም ግቡ።
20.   የአባታችሁን አባት ስም(የአያታችሁን ስም) ተናገሩ (ለብዙ ሴቶች)
21.    አንተ ማነህ? ሥራህስ ምንድነው?
22.   እኔ ዐይነኡ “ዐ” አይደለሁም ነገር ግን አልፋው “አ” ነኝ
23.   ለማደርገው ነገር ሁሉ ምክንያት አለኝ
24.   ገጸ መጽሐፍ
25.   ጠይቆት ይገብር ሊቀ
ጥ፡26-37 ተጨማሪ ማብራርያን የሚሹ፦ተጨማሪ ማብራርያ በመስጠት ጥያቄዎቹን መልሱ
26.   “መስተዋድድ/ Prepositions” የሚያፈቃቅር (ማለትም የሚያጣጥም) ማለት ሲሆን “ንኡሳን ወይም ትንንሽ አበባቦች ናቸው) ምሳሌ ለመስተዋድድ “ኀበ” “ምስለ”  ለመስተጻምር“/Conjunctions)አያያዥ ማለት ሲሆን ለምሳሌ፦ “ወ” “አላ” ወዘተ
27.   የአቡነ ሰላማ አገሩ የት ነው? ግሪክ
28.   ከአዘጋጅው ፤ ሰው እናታችን ጽዮን ይላል የመጀመሪያው “እምነ” “ከ” ማለት ሲሆን ንኡስ አገባብ ነው “ም” አይጠብቅም። ሁለተኛው “እምነ” “እናታችን” ማለት ሲሆን ስም ነው “ም” ይጠብቃል
29.  ፳፪/፳፪ቱ(እሥራ ወክልኤቱ) እሥራ ወሰንዩም ይባላል
30.    “ፊደልን የቆጠሩ ሁሉ በየቦታው አስተማሪዎች ሆኑ” የማስተማር ችሎታ ሳይኖራቸው በድፍረት ለሚያስተምሩ ሰዎች የሚነገር ትችታዊ አባባል ነው።
31.     “ጸሎቱ” ጸ ስትጸልይ ጥራኝ አለ” ማለት ለሰሙ ለመጸለይ ስትፈልግ ወይም ስትዘጋጅ ጥራኝ ይባላል፤ ለወርቁ ግን ጸሎቱ ጸ ስትጸልይ ጥራኝ አለ ማለት ስለጸሎትና ስለ መጸለይ ለመጻፍ መጠቀም ያለብህ እኔን ነው (ፀሐዩን ፀ አይደለም ማለት ነው)
32.   ንጉሡ ሠ “የወለደኝ ንጉሡ ሠ ብሎ ስም አወጣልኝ” ማለት የፈለሰፈኝ ሰው ንጉሡ ሠ ብሎ ሰየመኝ ማለት ነው
33.   አስማት/መተት የጥንቆላ
34.   ለጸሎት ተነሡ/አነ/ ተናጋሪ አነ/ንሕነ፤ ሰሚዎች አንትሙ 
35.   ሄደ/ሐላፊ
36.  ክፈቱ/ትእዛዝ 
37.   “ኒ” ወደ “ኔ” መቀየር/ መድኃኔ ዓለም
ጥ፡ 38-47 ትርጉምን የማይሹ ጥያቄዎች፦ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ
38.   መጽሐፈ ሄኖክና መጽሐፈ ኵፋሌ  
39.  21
40.   7
41.    5
42.   ካዕብና ሣብዕ
43.   5/ ሀ፤ሐ፤ኀ፤አ፤ዐ
44.   9
45.   ሁለት፤ሁለት
46.  ሠ፤ንጉሡ ሠ፤/ ሰ፤እሳቱ ሰ
47.   የደረጃ/የተራቍጥር ስማቸው
48.   እውነት
49.  እውነት

Wednesday, July 5, 2017

የግእዝ ቃል ትንታኔ/Analyzing Ge'ez Word

Analyzing Ge'ez word "Tewnet" (Play)

ኢትዮጵያዊ ቋንቋችሁን ተማሩ/Learn Your  Ethiopic: 
Vocabulary the meaning and usage of Action, Actor, Actress


የግእዝን ቃላት በተግባራዊ ወይም በሥዕላዊ መግለኛ እያስደገፉ ማስተማሩ

በዚህ ክፍል “ተውኔት” በሚለው ቃል ግሦችን፤ ስሞችን፤ እንዲሁም ቅጽሎች እንመለከታለን::

ቃላት በተናጠል ሳይሆን በቤተሰብ ወይም በክፍል ማለትም በአንድ ቃል ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ክፍሎችን ወይም አካላትን እየለያዩ በማውጣት ሥራቸውን እና ስያሜያቸውን በመለየት በሥልዕላዊ መግለጫ በመመልከት ማጥናት እጅግ ይጠቅማል። 
ምክንያቱም አይረሳም፤ በአንድ ጊዜ ብዙ ቃላትን ማወቅ ያስችላል፤ ከሁሉም በላይ አንድ ቃል ብዙ አካላት እንዳሉት ለያይቶ ማወቅ በቋንቋ ላይ የሚኖረንን ግንዛቤ ፍ ያደርገዋል። በተለይ ለሥነ ጽሁፍ  ሙያ መሠረት ነው።


የግእዝ መማሪያ መጽሐፉን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ/To buy this Book Click this link
https://amzn.to/2Q8POov
https://amzn.to/30m8VQN

ተዋንዮ ተዋንዮት = መጫወት


  • ተዋነየ =ተጫወተ= He acts
  • ይትዋነይ= ይጫወታል = He will act
  • ይትዋነይ= ይጫወት ዘንድ = in order to act
  • ይትዋነይ=ይጫወት=  act (command verb)        
እነዚህ አራቱ ቃላት ግሦች ማሠሪያ አንቀጽ የሚሆኑ ናቸው።= Verbs


ለሴት ደግሞ እንደሚከተለው ይረባል (ፆታ መቀየር ብቻ ነው ትርጉሙ አይለያይም)

  • ተዋነየት
  • ትትዋነይ
  • ትትዋነይ
  • ትትዋነይ
  • ተዋናዪት


ተዋንዮ ተዋንዮት=መጫወት     acting       
ግሥም ይሆናል ስምም ይሆናል
ተዋናዪ ተዋናያን = ተጫዋች፤ ትጫዋቾች (ወንዶ) =Actor/Actors
ተዋናዪት-ተዋናያት=ተጫዋት/ተጫዋቾች(ሴቶ) =Actress/Actresses       
 እነዚህ ደግሞ ቅጽል (ገላጭ) የሚሆኑ ናቸው።=Adjectives


ተዋንዮ ተዋንዮት=acting/playing
ተውኔት=ጨዋታ/= play
ትዋኔ= አጨዋወት/ጨዋታ  =the method of play
 እነዚህ ስሞች ሲሆኑ ባለቤት የሚሆኑ ናቸው። Nouns/ Subjects

Saturday, July 1, 2017

The Land of Collections


The Land Of Collections

You are wise and beautiful
So pretty and attractive
Everybody in your love has been fallen.
The Land of Collection
Has loved you all the nation
Black, White, and Hispanic
Japhet, Ham, and Semitic
From four sides of the earth
East, West, North, and South
Every Season without limit
Every time day and night
Unexceptional all human being
Is flowing to you more and more
Refusing his homeland to come here
Point at you the world’s eyes
All believe you as the land of the promises
A special land full of hopes
As Jerusalem the land of our Jesus
Your name, your flag, and your dollars
Have been worshiped by the others
All mankind female and males.


Poem of the year 2003 by the Famous Poet Sociaty
This poem was published on Anthology of the year 2003 on “Today’s Famous Poems on the Wings of Pegasus” written by M/r Melaku Asmamaw Besetegn who became Poet of the year 2003 and honored recepient of the Shakespeare Trophy of Excellent also Poet of the year Medalion by The famous Poets society
ይህንን እና ሌሎችንም እውቅ ግጥምች ለመግዛት ሊንኩን ይጫኑ/buy this famous poem of the year