Friday, July 24, 2015

ግእዝ ጽሁፍ ክፍል 28 ዘንድ አንቀጽ

Ge'ez Lessons for Beginners part 28 text (ዘንድ አንቀጽ = in order to)


መሀረ = አስተማረ (ያለፈ ድርጊት) past
ህር= ያስተምራል (ወደፊት የሚደረግ ትንቢት) futur
ይምሀር= ያስተምር ዘንድ (ምክንያታዊ ) in order to


እርማት፡ መሀረ = አስተማረህር 
ይምሀር
ይምሀር
መሐረ = ይቅር አለ የሚለው ግስ ሲሆን ነው ህር በማለት የሚረባው። መሀረ = አስተማረ የሚለው ግን መሀረ (ሐላፊ) ይህር (ትንቢት) ማለትም በትንቢት (በሁለተኛው ግስ) የሚገኘው ሆሄ "ም" ሳይሆኝ "" (ይህር) ይሆናል።



ተንሥአ ይምሀር መምህረ ግእዝ =የግእዝ መምህር ያስተምር ዘንድ ተነሣ
ዘንድ አንቀጽ = In order to
ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች በክፍል 25 ስለ አራቱ አበይት አናቅጽ ስለ
1.      ሃላፊ፤
2.     ትንቢት፤
3.     ዘንድ  እና
4.     ትዕዛዝ (ዘንድ እና ትዕዛዝ ሳልሳይ ወይም 3ኛ ይባላሉ) ጠቅለል ባለ መልኩ ተምረን ነበር።
በድጋሚ ለማስታዎስ ያህል ግሦቹ የሚከተሉት ናቸው።
ሖረ=  ሄደ  ሃላፊ አንቀጽ
ይሐውር= ይሄዳል  ትንቢት አንቀጽ
ይሑር= ይሄድ ዘንድ  ዘንድ አንቀጽ
ይሑር= ይሂድ  ትእዛዝ አንቀጽ
በመሆኑም እነዚህን ግሦች መሠረት አድርገን እንደ መግቢያ ከተማርን በኋላ በመቀጠልም አንድ በአንድ  በክፍል 26 ስለ ሃላፊ ግሥ ወይ አንቀጽ፤ በክፍል 27 ስለ ትንቢት ግሥ ወይም አናቅጽ ተምረናል።
በዛሬው በክፍል 28 ትምህርታችን ደግሞ
ስለ ዘንድ አንቀጽ እንማራለን። ዘንድ አንቀጽ ሳልሳይ ተብሎም ይጠራል ።ሦስተኛ ማለት ነው። ምክንያቱም በሦስተኛ ተራቁጥር ስለሚገኝ ነው። ዘንድ አንቀጽ የሚባለውም ዘንድ ተብሎ ስለሚተረጎም ነው። (ይሄድ ዘንድ)
ዘንድ አንቀጽ ከአበይት ግሦች ሦስተኛው አንቀጽ ሲሆን በቀጥታ ማሠሪያ አንቀጽ አይሆንም ማለትም አያሥርም። (ውእቱን መርምሮ ካልሆነ በስተቀር)፤
 ስለዚህ ሌላ ተጨማሪ አንቀጽን ይፈልጋል። ውእቱ (ገብረ ሥላሴ) ተንሥአ ይሁር = እሱ ይሄድ ዘንድ ተነሣ፤ ብንል የዚህ ዐረፍተ ነገር ማሠርያ የሆነው “ተንሥአ” የሚለው ግሥ ሲሆን ይሁር የሚለው ምክንያቱን ይገልጻል እንጂ አያሥርም። ስለዚህ በዚህ ዐረፍተ ነገር ሁለት አበይት ግሦች ሲኖሩ አንዱ ብቻ ማሠሪያ ሆነ። ለዚህም ነው ዘንድ አንቀጽ በቀጥታ ስለማያሥር ሌላ ሁለተኛ አንቀጽን ይሻል ያልነው።
ዘንድ አንቀጽ አገባባዊ ባሕርይ አለው፤ (ከመ ከሚለው አገባብ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም እና ሥራ አለው። ሁለቱ ማለትም ከመ እና ዘንድ አንቀጽ በአንድ ላይ ይነገራሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ዘንድ አንቀጹ የተለመደውን ትርጉሙን ሲይዝ “ከመ” የሚለው አገባብ የዘንድ አንቀጹ ሞገሥ ወይም አጃቢ ይባላል።
ለምሳሌ
መርድእ ሖረ ከመ ይትመሀር ልሣነ ግእዝ = ተማሪ የግእዝን ቋንቋ ይማር ዘንድ ሄደ። በዚህ ዐ/ነገር ላይ ከመ የይትመሀር አዳማቂ ሆነ እንጂ ሌላ አገልግሎት አልሰጠም። ምክንያቱም “ይትምሀር” የሚለው ግሥ ራሱ ትርጉሙ “ይማር ዘንድ” የሚል ነው። ልዩነታቸው ዘንድ አንቀጽ  አንቀጽም ነው እንደ አገባብም ይተረጎማል፤ “ከመ” ግን “እንደ” የሚል ትርጉም ነው ያለው። ስሙም አገባብ ይባላል። ለሁለቱም ማለትም ለዘንድ አንቀጽና “ከመ” ለሚለው አገባብ ምሳሌዎቹን ተመልከቱ
መነኮስ ቆመ ከመ ይጼሊ= መነኩሴ ይጸልይ ዘንድ ቆመ።
መነኮስ ቆመ ይጸሊ = መነኩሴ ይጸልይ ዘንድ ቆመ።
 በነዚህ በሁለቱ ዐረፍተ ነገራት መሠረት ዘንድ አንቀጽና “ከመ” የሚለው አገባብ ተመሳሳይ አገልግሎት አላቸው። ነገር ግን “ከመ” ከአንቀጽ ጋር በመሆን አንቀጹ እንዳያሥር ለመከላከል ነው የሚያገለግለው፤ ዘንድ አንቀጽ ግን   ብቻውን በመሆን ነው የሚነገረው የራሱ የሆነ አገባባዊ ባሕርይ አለው ማለት ነው።
ዘንድ አንቀጽ ከሁሉም ግሦች (ከሐላፊ፤ከትንቢት፤ እና ከትእዛዝ አናቅጽ ) ጋር አብሮ ይሠራል።
ምሳሌ፡
·         ይብላእ ሆረ = ይበላ ዘንድ ሄደ (ሃላፊ)
·         የሐውር ይብላእ= ይበላ ዘንድ ይሄዳል (ትንቢት)
·         ይሁር ይብላእ= ይበላ ዘንድ ይህድ(ትእዛዝ)
ዘንድ አንቀጽ በዓረፍተ ነገር ሲገባ ለሌላ ድርጊት ወይም አንቀጽ እንደ ምክንያት በመሆን ይገባል።
ለምሳሌ “ መርድእ ሖረ ይትምሀር” ቢል የዓረፍተ ነገሩን ባለቤት የጎዞ ምክንያት ይገልጽለታል። ማለትም ተማሪው የሄደበት ምክንያት “ይማር ዘንድ” ወይም ለመማር ነው። በማለት ምክንያቱን ገለጸለት ማለት ነው።
ከግሡ መጀመሪያ ላይ ባእድ ሆሄን ይጨምራል ሆሄያቱም አሥራውይባላሉ
ምሳሌ
መሀረ መሠረታዊ ግሥ ሲሆን
ይትመሀር እና ባእድ ሆሄ ይባላሉ ። ምክንያቱም ከመሠረታዊው ግሥ ያልነበሩ የመሠረታዊው ግሥ ወገን ስላልሆኑ ነው። ከግሡ መጀመሪያ ላይ ስለሚገኙ ደግሞ “አሥራው” ይባላሉ በአማርኛ ሥሮች ማለት ነው፤፡
ስለዚህ ለማጠቃለል ያህል የዘንድ አንቀጽ መሠረታዊ ወይም አበይት መለያዎችን  ባጭሩ እንደሚከተለው ይመልከቱ።
·         ዘንድ አንቀጽ ከአበይ አናቅጽ መካከል ሦስተኛው አንቀጽ ነው በዚህም ሳልሳይሦስተኛይባላል
·         ዘንድ ተብሎ ስለሚተረጎምዘንድ አንቀጽእየተባለ ይጠራል። ስለዚህ ስሙ ከትርጉም ጋር የተያያዘ ነው።
·         ብቻውን ስለማያሥር ሌላ ግሥ (ሃላፊ፤ ትንቢት፤ ወይም ትእዛዝአናቅጽ) ያስፈልገዋል።
·         ከሁሉም አበይ አናቅጽ ማለትም ከሃላፊ፤ከትንቢት፤ እና ከትእዛዝ አናቅጽ ጋር እየተቀናጀ ያገለግላል
·         አገባባዊ ትርጉምና ሥራ አለው። ለምሳሌከመከሚለው አገባብና ከመሰሎቹ ጋር በትርጉምና በአገልግሎት ይመሳሰላል
·         ሁለት ነገሮችን በአንድ ላይ ይዟል፡ ዘንድ የሚል አገባብ() እና አንቀጽያእምር”= ያውቅ ዘንድ= ያውቅ(አንቀጽ) ዘንድ=አገብባብ() ስለዚህ አገባብና አንቀጽ በአንድ ላይ ይበኙበታል።
·         የዐረፍተ ነገርን ምክንያታዊ ተግባር ይገልጻል
·         ከግሡ መጀመሪያ ላይአሥራው የሚባሉትን ሆሄያት ይጨምራል።