የግእዝ ትምህርት ክፍል 24
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ
ባለፈው በክፍል 23 ትምህርታችን “አውደ ጥናት”
ስለምትባል አንዲት እናት በግእዝ ቋንቋ አጭር ታሪክን ጽፌላችሁ ነበር። ይህ ክፍል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በግእዝ ቋንቋ ብቻ
የተዘጋጀ ነበር። ይህንንም ያደረግሁት ልምምድ እንድታደርጉ እንደ መመሪያ እንዲሆናችሁ በማሰብ ነው።
ዛሬ በክፍል 24 ትምህርታችን ደግሞ ትርጉሙንና
ተጨማሪ ማብራርያን እነግራችኋለሁ(የክፍል 23ን ማለት ነው)። እያንዳንዳችሁም
የራሳችሁን ታሪክ ለመጻፍ ሞክሩ።
አንድ ታሪክ ለመጻፍ እንደሚታወቀው ሦስት ነገሮች
ወይም ክፍሎች መኖር አለባቸው። እነዚህም
1.
መግቢያ
2.
ዋና ታሪክ
እና
3.
መዝጊያ ወይም ማጠቃለያ ያስፈልገዋል። ይህ
ማለት ስለ ምን መናገር እንደ ፈለግን ለአድማጮቻችን እንናገራለን (ይህ መግቢያ ይባላል)
መናገር
የምንፈልገውን ፍሬ ሐሣብ በዝርዝር እንናገራለን (ይህ ዋና ታሪክ
ወይም የጽሁፉ ዋና ክፍል ይባላል)
እንደ
ገና የተናገርነውን ታሪክ ባጭሩ ፍሬ ሐሳቦችን ብቻ ለአድማጮቻችን
እንነግራቸዋለን (ይህ ማጠቃለያ ይባላል)
በሌላ አገላለጽ መግቢያው ቀድመው ስለሚሰጠው ታሪክ እንዲያስቡና ምን ዓይነት መልእክትና ፍሬ ሐሳብ እንደሚኖረው
ለመገመትና በተገቢው መልኩ ለመከታተል እንዲችሉ ይረዳቸዋል።
ዋናው ንግግር ታሪኩን
በልዩ ልዩ ማስረጃና ድጋፍ ማስተማር ማለት ነው ስለዚህ አድማጮቹ ፍሬ ሐሣቡን እስከ ማስረጃው አዳመጡ።
ማጠቃለያው ደግሞ ከሰሙት
ታሪክ መካከል ባጭሩ ፍሬ ሐሳቦችን ብቻ ጨምቆ ወይም አጣርቶ በማውጣት ስለሚነገር ከረጅሙ ንግግር ውስጥ ፍሬ ሐሳቦችን ቶሎ ማስታዎስ
እንዲችሉ ይረዳቸዋል።
እነዚህ ሦስት ነገሮች
የአንድ ታሪክ አካላት ናቸው። የአጻጻፍ ስልታቸው ግን ሊለያይ ወይም ሊያጥርና ሊረዝም ይችላል።
በዛሬው ትምህርታችን
ግን ባጭር አጠቃቀም ብቻ እናያለን።
ከዚህ በላይ ያለው
አገላለጽ ብዙጊዜ ለመጻሕፍት (መጽሐፍ ስንጽፍ) ለሌሎችን ጥናታዊ
ጽሁፎችን ስናዘጋጅ ለመሳሰሉት የምንጠቀምበት ነው። ከተቻለ ለማነኛውም ንግግር በዚህ ዓይነት ምልኩ ማቅረቡ ይመረጣል ። ካልሆነ
ግን
በመልካም ምኞት ወይም
በሰላምታ መጀመርና መደምደም እንችላለን / ለምሳሌ እንደምን አደራችሁ በማለት የንግግራችንን ርእስ ብቻ በመጥቀስ እንጀምራለን;
ስንጨርስም ለሰሚወቻችን መልካም ምኞትን በመመኝት መልካም አዳር በማለት በመሳሰሉት የእምነት ጉባኤ ከሆነ (እግዚአብሔር ለመስማት
የተዘጋጀን ያድርገን፤ የሰማነውን በልቡናችን ይጻፍልን በማለት መጀመርና መጨረስ እንችላለን ።
አሁን የክፍል 23ን
መግቢያ፤ ዋና ፍሬ ሐሣብና ፤ ማጠቃለያ እንመልከት
መግቢያ
ሰላም ለክሙ አኃውየ ወአኃትየ አርድእተ ልሳነ ግእዝ ኩልክሙ። (ይህ ሰላምታ ነው)
ዮምሰ ፈቀድኩ
ከመ
እምሀርክሙ ልሳነ ግእዝ በልሳነ ግእዝ ባህቲቱ። ወእስእለክሙ ከመ ትስምኡ ወታጽምኡ በእዝነ ልቡናክሙ፤ ወትነጽሩ በዐይነ ልቡናክሙ።
ኅበ ዜና አሐቲ ብእሲት ዘእዜንወክሙ ድኅረ ሰለስቱ ቅጽበታት።
ዮም በእሥራ ወሰለስቱ ክፍለ
ትምህርትነ እዜንወክሙ በይነ አሐቲ ብእሲት ዘስማ አውደ ጥናት። (መመሪያ)
(ሰላም ለክሙ/ለክን/ለኪ/ለከ (አንድ ወንድ ካለ ብዙ ሴቶች ቢኖሩም በወንዶች አንቀጽ ነው
የሚጠራው)
(ዮም፤ ናሁ
እነግረክሙ፤
እዜንወክሙ፤
እዜንወክሙ በይነ አሐቲ
ብእሲት ዘስማ አውደ ጥናት።
(ዮም እነግረክሙ፤እዜንወክሙ፤
እዜንወክሙ በይነ አሐቲ
ብእሲት።
ዋናው ታሪክ
ቅድመ ሰለስቱ ዓመታት
እንዘ አሀውር በፍንወት ረከብኩ
እቤርተ ዕድሜ ብእሲተ ዘስማ አውደ ጥናት፤ ወስመ ጥምቀታ ወለተ ማርያም። ወይእቲሰ እምነ ነገደ ኢትዮጵያ። ወብእሲት ነበበተኒ ከመ
ወለደት ብዙኃነ ደቂቀ እለ ይነብሩ ዝርዋነ በውስተ ኵሉ ዓለም ወሰአለተኒ ከመ እምሀር ላቲ ደቂቃ ልሳነ ግእዝ ወቅኔ ወአነኒ እቤላ
ኦሆ።
ማጠቃለያ/መዝጊያ
ተፈጸመ ዜና ሕይወታ ለብእሲት
ናሁ እጤይቀክሙ ሐምስተ ጥያቄያተ እለ ወጽኡ እምነ ዜናሃ ለብእሲት ዘዜነውኩክሙ በዛቲ ዕለት
(ይህ ክፍል ሊረዝም ይችል ነበር። ማጠቃለያ ሲባል በዋናው ታሪክ ውስጥ የተጻፉትን በአጭሩ
እንደ ገና መግለጽ ነው። ከዚህ ላይ ግን ታሪኩ ማለቁን በመናገር እና ከታሪኩ ውስጥ ጥያቄዎችን በማውጣትና በመጠየቅ ይጨርሳል።
በመሆኑም በተዛዋሪ መንገድ ማጠቃለያ ተሰጠ ማለት ነው።