የግእዝ ቋንቋ ግሦች እና የባለቤት አመልካች ሆሄያት/the Geez verbs and their suffixes

የግእዝ ቋንቋ ግሦች እና የባለቤት አመልካች ሆሄያት/the Geez verbs and their suffixes




በክፍል 9 የሚጠቃለሉ ትምህርቶች
1.   የግሥ ርባታ ከሃላፊ እስከ ትእዛዝ
2.   የአሥሩ መራሕያን ግሶች የሚጨርሱባቸው ፊደላት
3.   አሥሩ መራሕያን እንደ ነባር ግሥ ወይም አንቀጽ ሲያገለግሉ  
1.የግሥ ርባታ ከሃላፊ እስከ ትእዛዝ አንቀጽ (እነዚህ አበይት አናቅጽ ይባላሉ በቁጥራቸው 4 ናቸው)
1.      አእመረ  = ዐወቀ (ሃላፊ አንቀጽ)
2.     የአምር = ያውቃል(ትንቢት አንቀጽ)
3.     ያእምር- = ያውቅ ዘንድ (ዘንድ አንቀጽ)
4.    ያእምር = ይወቅ(ትእዛዝ አንቀጽ)
ለምሳሌ በቀደሰ ግሥ አራቱን አበይት አናቅጽ እንደ ሚከተለው እናረባለን
1.      ቀደሰ፤
2.     ይቄድስ፤
3.     ይቀድስ፤
4.    ይቀድስ
ምሳሌ ሦስቱን አበይት አናቅጽ በዐረፍተ ነገር እያስገባን እንመልከት
 ለሃላፊ አንቀጽ፦     መርድእ አእመረ ልሳነ-ግእዝ ተምሂሮ እምነ አቡሁ፡= ተማሪ የግእዝን ቋንቋ ከአባቱ ተምሮ አወቀ።
ለትንቢት አንቀጽ፦   መርድእ የአምር ልሳነ-ግእዝ ድኅረ ክልኤቱ ዓመታት፡= ተማሪ ከ2 ዓመታት በኋላ የግእዝን ቋንቋ ያውቃል።
ለዘንድ አንቀጽ፦     ወራዙት አፍቀሩ ልሳነ-ግእዝ ይትመሀሩ፡= ወጣቶች የግእዝን ቋንቋ ይማሩ ዘንድ ወደዱ።
ለትእዛዝ አንቀጽ፦   መርድአ-ቅኔ ያእምር ሰዋስወ ግእዝ  በቃሉ፡= የቅኔ ተማሪ የግእዝን አገባብ በቃሉ ይወቅ።




2.የአሥሩ መራሕያን ግሶች የሚጨርሱባቸው ፊደላት
አሥሩ መራህያን እና አንቀጾቻቸው (የግሡን የመጨረሻ ፊደል በማየት ብቻ ባለቤቱን ወይም ከመራሕያን መካከል ዐረፍተ ነገሩ ለማን እንደ ሚነገር ማወቅ ይቻላል።(የባለቤት ዝርዝር ይባላል)

መደብ
መራሕያን
መሠረታዊው ግሥ
የባለቤት ዝርዝር
የሆሄያቱ ስም ቁጥር


ቀደሰ


3ኛ መድብ ነጠላ ለወንድ
ውእቱ
ቀደ-
-ሰ
-ከ

-ነ
ግእዝ (1ኛ ሆሄ)
2ኛ መደብ ነጠላ ለወንድ
አንተ
ቀደ-ስከ

1ኛ መደብ ለብዙ ወንዶችም ሴቶችም
ንህነ
ቀደ-ስነ





1ኛመደብ ነጠላ ወንዶችም ሴቶችም
አነ
ቀደ-ስኩ
-ኩ
-ሱ
-ክሙ
ካእብ (2ኛ ሆሄ)
3ኛ መደብ ለብዙ ወንዶች
ውእቶሙ
ቀደ-ሱ
2ኛ መደብ ለብዙ ወንዶች
አንትሙ
ቀደ-ስክሙ





2ኛ መደብ ለአንዲት ሴት
አንቲ
ቀደ-ስኪ
-ኪ
ሳልስ (3ኛ ሆሄ)
3ኛ መደብ ለብዙ ሴቶች
ውእቶን
ቀደ-
-ሳ
ራብእ (4ኛ ሆሄ)
3ኛ መደብ ለአንዲት ሴት
ይእቲ
ቀደ-ሰት
-ት
ሳድስ (6ኛ ሆሄ)
2ኛ መደብ ለብዙ ሴቶች
አንትን
ቀደ-ስክን



 
10ቱ መራሕያን እንደ ነባር ግሥ ወይም አንቀጽ (ማሠሪያ ግሥ ሲያገለግሉ)
ውእቱ የሚለው መራሂ እንደ አንቀጽ ሆኖ ለ3ኛ መደብ አንስታይ ጾታ ሲያገለግል

መኑ ውእቱ ዝንቱ = ይህ ማነው?
መኑ ይእቲ ዛቲይህቺ ማናት?
መኑ ውእቱ አንተ = አንተ ማነህ?
መኑ ውእቱ አንቲ = አንቺ ማነሽ?
(አንቲ ውእቱ ተስፋሁ  ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት) ቅዳሴ ማርያም
ትርጉም፦ ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ፡
መኑ ውእቱ አነ = እኔ ማነኝ?
እለ መኑ ውእቶሙ እሙንቱ= እነሱ እነ ማን ናቸው?( ብዙ ወንዶች የሩቅ)
እለ መኑ ውእቶን እማንቱ= እነሱ እነ ማን ናቸው?(ብዙ ሴቶ)
እለ መኑ ውእቱ አንትሙእናንተ እነ ማን ናችሁ?( ብዙ ወንዶች የቅርብ )
እለ መኑ ውእቱ አንትንእናንተ እነ ማን ናችሁ” (ብዙ ሴቶች ቅርብ)
እለ መኑ ውእቱ ንሕነ= እኛ እነ ማነን? (ወንዶችም ሴቶችም)

የአጠናን ዘዴ

ምክሮችና ማሳሰቢያዎች፤

1.      መድከማችን ካልቀረ ብዙ ወገኖች እንዲማሩና እንዲጠቀሙ ለምናውቃቸው ሁሉ በኢሜይልም ሆነ በተክስት በስልካችን በመጠቀም ሼር በማድረግ ማዳረስ ይጠበቅብናል።
2.     በአካልም ሆነ በስልክ ወይም በኢሜይል መገናኘት የምትችሉ የዚህ ትምህርት ተከታታዮች እርስ በርሳችሁ መጠያየቅና ማጥናት በተለይ እንደ ስካይፕ ወይም ቪዲዮ ኮል የመሳሰሉ ሌሎችንም መሣሪያዎች መጠቀም ከቻላችሁ የበለጠ መረዳዳትና ርስ በርስ ማጥናቱ እጅግ ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ ስለዚህ አስቡበት።
3.     ወደ ቤተ ክርስቲያን የምትሄዱ በግእዝ የሚባሉትን የጸሎት ክፍሎች በማስተዋል ወደ አማርኛ ወይም ወደሌላ ወደ ምታውቁት ቋንቋ ለመተርጎም መሞከር፤ ቢያንሰ እያንዳንዱን ቃል ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ መሞከር፤
ለምሳሌ፦ “ተንሥኡ ለጸሎት” ሲል ምን ማለት እንደ ሆነ ማስተዋል ማለት “ለጸሎት ወይም ለልመና ተነሡ” ማለት መሆኑን መገንዘብ ብቻ አይደለም። ምክንያቱም ለጸሎት ተነሡ የሚለው በአማርኛ ተጽፎ በየቦታው አለ። ሁሉ ለጸሎት ተነሱ ማለትን ለምዷል። ማስተዋል ያለብን ግን ተንሥኡ ምን ዓይነት ግሥ ነው? ከ 10 መራሕያን የትኛውን ይመለከታል ?
1ኛ መደብ ነጠላ፤ብዙ፤ሴት፤ወንድ፤ ሩቅ፤ ቅርብ፤
2ኛ መደብ፤ 3ኛ መደብ==== ወዘት
የ “ለ” ትርጉም በተንሥኡ ለጸሎት ላይ ምን ማለት ነው?
ጸሎት በአማርኛ ወይስ በግእዝ
ጸሎት ግሥ ነው ወይስ ስም? ወይስ ቅጽል?
የዐረፍተ ነገሩ ማሠሪያና ባለቤት የትኛው ቃል ነው? ወዘተ በሚሉት መንገዶች መመራመር ነው ጥናት የሚባለው፡
watch video for this part




4 comments:

  1. እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥልኝ
    በቪዲዮ ማብራሪያ ከሌለ ለመረዳት ይከብዳል እና አድካሚ ቢሆንም አጠናክረህ ቀጥልበት፡፡ ተባረክልኝ

    ReplyDelete
  2. እናመሰግለን ግን በመፅሐፍ መልክ ገበያ ለይ የት ይገኛል

    ReplyDelete
    Replies
    1. የሚከተለውን ሊንክ ተጭነው ያገኙታል አመሰናለሁ
      https://amzn.to/2HlKMlO

      Delete
  3. በጣም ጥሩ ነው።

    ReplyDelete