የግእዝ ትምህርት መግቢያ አንድ/Geez Part 1


የግእዝ ትምህርት መግቢያ አንድ


Lisane Geez Yegara Quanquachin/ ልሣነ ግእዝ የጋራ ቋንቋችን የተሰኘውን ይህንን የግእዝ ቋንቋ መማርያ ክፍል አንድ መጽሐፍ ከአማዞን ለመግዛት ይህንን ይጫኑ.

ባለፈው መግቢያ ክፍል አንድ ብለን በጀመርነው ትምህርት ስለ ግእዝ አጠር አድርገን ተመልክተናል። አሁን ደግሞ መግቢያ ክፍል ሁለትን እንጨርስና በሚቀጥለው የግእዝ ትምህርት ክፍል አንድ በማለት ዋናውን ትምህርት እንጀምራለን ማለት ነው። እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።
ግእዝ ባለፈው እንደ ጠቀስኩት መጀመሪያ ማለት ሲሆን የግእዝ ፊደል የመጀመሪያው ሆሄም ግእዝ ይባላል፡ ይህም አንደኛ ለማለት ነው። ለዚህም ነው::




ከአማዞን ልዩ ልዩ ነገሮችን መጻሕፍት ተክኖሎጂ መሣሪያዎችንም ለመግዛት የሚከተለውን “ግእዝ” የሚለውን ቃል ይጫኑ፡
geez

 ( ግእዝ  ካዕብ  ሳልስ  ራብእ  ሀምስ  ሳድስ ሆ ራብዕ) የምንለው  (ግእዝ ማለት 1ኛ፤ ካዕብ ማለት 2ኛ፤ ሳልስ ማለት 3ኛ፤ ራብዕ ማለት 4ኛ፤ ሓምስ ማለት 5ኛ፤ ሳድስ ማለት 6ኛ፤ ሳብዕ ማለት ደግሞ 7ኛ ነው)፡ ከሁለተኛ እስከ 7 ያሉት ሆሄያት የተጨመሩት በአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ጊዜ ነው።

ግእዝ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቋንቋ ከመሆኑም አልፎ በትውፊት እንደ ሚተረከው የአዳምና የእግዚአብሔር ቋንቋም ነበረ ይባላል። በባቢሎን የሰው ልጅ ቋንቋ በእግዚአብሔር ፈቃድ እስከ ተለያየበት ድረስ በአለም ላይ አንድ ቋንቋ እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ሆኖም ግን  ቋንቋ የትኛው መሆኑን አይነግረንም።

ግእዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች ተብለው ከሚጠሩት ከእብራይጥ፤ አራማይክና ግሪክ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ይህንን የዓለም ምሁራንም በትክክል ይቀበሉታል።

መጽሐፈ ኩላሌና መጽሐፈ ሄኖክ የተባሉት መጻሕፍት በባቢሎን ምርኮ ከጠፉ በኋላ በ1956 ዓ/ም ኩምራን በተባሉት ዋሻዎች በሥነ ምድር ተመራማሪዎች በተደረገው ቁፋሮ በግእዝ ቋንቋ ተገኝተው ነው ለዓለም መዳረስ የቻሉት ዓለም ስለ እነዚህ መጻሕፍት ያወቀው ግእዙን በማስተርጎም ነበር። ይህንን ታሪክ ዓለም አቀፍ ምሁራን በሕብረት ተቀብለውታል። ለዚህም መጽሐፈ ሄኖክን “ኢትዮፒ ሄኖክ” በማለት መዝግበውት ይገኛሉ።

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋነቱ ስለታመነበት በውጪው ዓለማት ለምሳሌ በጀርመን በአሜሪካ በቲኦሎጂ ተቋማት ያስተምሩታል። በአገራችን ብዙ ጥንታውያን ታሪኮች በግእዝ ብቻ ተጽፈው ስለሚገኙ እነዚህን መጻህፍት ለመረዳ የግእዝን ቋንቋ ማወቅ አማራጭ የለውም።
ግእዝ ቋንቋ እንደ መሆኑ መጠን እሱን ለመማር የሃይማኖት የፆታና የሌላም ልዩ ልዩ ተጽዕኖ ሳይኖር እንደ አንድ ተፈላጊ ቋንቋነቱ ፍላጎት ያለው ሁሉ ሊማረው ይገባል።

ግእዝ የእንግሊዘኛን ቋንቋ ትክክለኛ ትርጉም ለመረዳት እጅግ ይጠቅማል ምክንያቱም ለምሳሌ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ዲክሽነሪ  ወይም መዝገበ ቃላት የተቀመጡት አንዳንድ ቃላት ንዑስ አንቀጽ፤ መስተጻምር በመባል ተጠቅሰዋል። በመሆኑም መስተጻምር ወይም ንዑስ አንቀጽ ምን ማለት መሆኑን ካላወቅን የእንግሊዘኛውን አገባብ መጠቀም ብንቺል እንኳን በአማርኛ ፍችውን መናገር አንቺልም። 
ለዚህም ነው አንዳንዶቻችን እንግሊዘኛውን ከሌላ ቋንቋ ጋር እየቀላቀልን የምንናገረው። ግእዝ ለሥነ ጽሁፍ ወይም ለድርሰት እጅግ ጠቃሚ ነው።
ግእዝን ማወቅ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አይነተኛ ቋንቋ ነው ምክንያቱም በአማርኛ ወይም በሌሎች የአገራችን ቋንቋዎች ተተርጉሞ ከሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ የመጀመሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች ለሆኑት ለእብራይስጥና ለግሪክኛው መጽሐፍ ቅዱስ በጣም የሚቀርበው በግእዝ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ከሁሉም በላይ ግእዝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ ታላቅ ቦታ አላው የዜማ የቅኔ የመጻሕፍት ትርጓሜ በአጠቃላይ የአብነት ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ቋንቋቸው ግእዝ ነው። እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን የአምልኮት ሥርዓት ይከናወንበታል። እስካሁንም ቢሆን የግእዝን ቋንቋ በሕያውነቱ ጠብቃ ለትውልድ ያቆየቺ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስለሆነች ትውልድ ሊዘነጋው የማይችል ውለታ ነው።

መግቢያውን ባጭሩ ከዚህ ላይ ጨርሰናል በሚቀጥለው ዋናውን ትምህርት እንጀምራለን አስተያየትና ማሳሰቢያ ካላችሁ ላኩልኝ፤ ከወደዳችሁትም ላይክ የሚለውን ክሊክ አድርጉ እንዲሁም ሰብስክራብ አድርጉ ምክንያቱም ልቀጥል የምችለው የሚፈልግ ሰው ሲኖር ሲሆን ፈላጊ መኖሩን የማውቅበት መንገድ ደግሞ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ብቻ ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።

watch video

6 comments:

  1. በጣም እናመሰግናለን እግዚኣብሔር ይስጥልን

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር ያክብርልን

    ReplyDelete
  3. በጣም እናመሰግናለን እግዚኣብሔር ያክብርልን

    ReplyDelete
  4. እግዚአብሔር ያክብርልን

    ReplyDelete
  5. እናመስግናለን እግዚኣብሔር ያክብርልን

    ReplyDelete
  6. ጥሩ ነው ብርታቱን ሰጥቶ ያስፈጽምዎት።

    ReplyDelete