Friday, January 15, 2016

ግእዝ የፈተና 2 መልሶች

የግእዝ ትምህርት ክፍል 32 ጠቅላላ የመመዘኛ ፈተና ሙሉ መልስ      






ዛሬ በዚህ በክፍል 32 ትምህርታችን ለክፍል ሁለት አጠቃላይ የመመዘኛ ፈተና ሙሉ መልስ እሰጣችኋለሁ። በሚቀጥለው በክፍል 33 ደግም በጥያቄዎቹና በመልሶቻቸው ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራርያ እሰጣለሁ በሰላም ያቆየን።
ለሚከተሉት 15 ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ።
1.  “ዛቲ ጦማረ መልእክት ትብጻህ ኀበ አርድእተ ልሣነ ግእዝ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ
·       የዐ/ነገሩን ባለቤት---ጦማር
·       የዐ/ነገሩን ማሠሪያ አንቀጽ----ትብጻህ
·       የ”ጦማርን” ቅጽል ይናገሩ--ዛቲ (4)
2.  አበይት አናቅጽ የሚባሉትን አራት ግሦች “ሰብሐ” በሚለው ግሥ ምሳሌ ያሳዩ
·       ሰብሐ-ሐላፊ
·       ይሴብሕ- ትንቢት
·       ይሰብሕ-ዘንድ
·       ይሰብሕ- ትእዛዝ
3.  “አዕማድ” የሚባሉት ስንት ናቸው? ስማቸውንም ይጥቀሱ(2)
አምስት ናቸው
·       አድራጊ
·       አስደራጊ
·       አስደራራጊ
·       ተደራጊ
·       ተደራራጊ
4.  “አሥራው” የሚባሉት ሆሄያት ስንት ናቸው? ስማቸውንም ይጥቀሱ(2)
·       ዐራት ናቸው እነዚህም
·       ይ፤ት፤ን፤እ፤ የሚባሉት ናቸው
5.  “ኢታንሥእ ዘኢያንበርከ” ማለት ምን ማለት ነው?
·       ያላስቀመጥከውን(ያላኖርከውን) አታንሣ(አትውሰድ)
6.  በ5ኛ ተራ ቁጥር ላለው ዐ/ነገር ትእዛዝ ሰጭውንና ትእዛዝ ተቀባዩን በተውላጠ ስሞች ይናገሩ፤(2)
·        አነ ወይም ንሕነ (ትእዛዝ ሰጭ)
·        አንተ(ትእዛዝ ተቀባይ)
7.  “አስማት” ማለት ምን ማለት ነው?
·       ስሞች (ስም የሚለው ሲበዛ)


የሚከተሉትን ወደ ግእዝ ቋንቋ ይቀይሩ
8.  እንደ ምን አደርክ ወንድሜ?
·       እፎ ኀደርከ እኁየ?
9.  ልጂሽ የት ነው እኅቴ?
·       አይቴ ውእቱ ወልድኪ እኅትየ?
10.         እንደ ምን አደሩ እናቴ?
·       እፎ ኀደርኪ እምየ?
11.         ለምን መጣችሁ ወንድሞቼ?
·       ለምንት መጻእክሙ አኃውየ?
12. ቅድመ ሠለስቱ ዓመታት ፈለስኩ እምነ ብሔርየ ከመ እሁር ኀበ ሐገረ ባእድ፤ ወድኅረ ክልኤቱ አውራኅ እትመየጥ መንገለ አዝማድየ። ባሕቱ አቡየ ይቤለኒ ኢትትመየጥ ኀበ ዝንቱ ሐገር።
ከዚህ በላይ ባለው ምንባብ ውስጥ ተጠቅሰው የሚገኙትን 5 ግሦች ወይም አናቅጽ ለይተው በማውጣት የያንዳንዱን ግሥ ዓይነት ይናገሩ (የሚገልጸውን ጊዜ) ።(5)
·       ፈለስኩ-ሐላፊ
·       እሁር- ዘንድ
·       እትመየጥ- ትንቢት
·       ይቤለኒ- ሐላፊ
·       ኢትትመየጥ- ትእዛዝ
12.          ከ4ቱ አበይት አናቅጽ ውስጥ በቀጥታ ራሱን ችሉ የዐረፍተ ነገር ማሠሪያ መሆን የማይችለው ግሥ የትኛው ነው? ስሙን ይጥቀሱ።
·       ዘንድ አንቀጽ
13.          ወለተ ማርያም ለብሰት ጸሊመ ልብሰ። በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ “ጸሊም” የሚለው ቃል የሚቀጸለው ለማነው? ወይም የሚገልጠው ማንን ነው?
·       ለ ልብስ(ልብሰ)
14.          “ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን” የዚህ ዐ/ነገር ማሠሪያ አንቀጽ “ቀዳማይ፤ ካልአይ፤ ሳልሳይ፤ ወይስ ራብአይ አንቀጽ የትኛው ነው?
·       ራብዐይ (ትእዛዝ)
15.          “እግዚአብሔር ይባርኪ ወያብርህ ገጾ ላእሌኪ” ምን ማለት ነው?
·       እግዚአብሔር ይባርክሽ፤ ፊቱንም ያብራልሽ(ፊቱንም በአንቺ ላይ ያብራ)
16.  “ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ “ድንግል” የሚለው ቃል ስንተኛ መደብ ነው?
·        ሁለተኛ(አንቲ)
17.          እፎ ሐደርከ (ኪ፤ክሙ፤ክን) ለዚህ ቃል መልሳችን ሊሆን የሚችለውን በግእዝ ይጻፉ
·       እግዚአብሔር ይሰባሕ
19. “አርዌ ምድር አስፈጠተኒ ወበላእኩ”(3)
·       በዚህ ዐ/ነገር(በ19ኛው ጥያቄ) “አስፈጠተኒ” የሚለው ቃል መሠረታዊ ግሡ ማነው?
·       ትርጉሙስ ምን ማለት ነው?
·       “አስፈጠተኒ” የሚለው ቃል ራሱን ችሎ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ምን ማለት ነው?
o   አስፈጠ
o   አሳሳተ
o   አሳሳተችኝ
20. “ገንጰለ” ማለት ምን ማለት ነው?
·       ገለበጠ
21. መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ ወ ቅኔ ተምሂሮ እምነ አውደ ጥናት ዘግእዝ። ምን ማለት ነው?
·       የግእዝ ተማሪ የግእዝን ቋንቋና ቅኔን ከአውደ ጥናት ተምሮ አወቀ
22. “ንግሩኒ ስማ ለብእሲት” ምን ማለት ነው?
·       የሴትዮዋን ስም (ስሟን) ንገሩኝ
23. ማነኛውም ርባ ግሥ መነሻው ምን ዓይነት የግዜ ትርጉም ነው?
·       ሐላፊ
24. “ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ማለት ምን ማለት ነው?
·       ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል
25. በአውደ ጥናት የትምህርት ማእከል ተገኝተው ስለ ግእዝና ቅኔ ሰፊ ማብራርያ የሰጡት የቤተ ክርስቲያናችን ምሁር ማን ይባላሉ? ከቻሉ ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ የሰጡትን መልስ ጠቅለል አድርገው በ5 ወይም ከዚያ በታች በሆኑ ዐ/ነገሮች ይግለጹት። (5)
·       መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ (ማጠቃለያውን ለግእዝ ተማሪዎች ጊዜ ወስዳችሁ እንድትመልሱት እፈልጋለሁ)
ለሚከተሉት 5 ጥያቄዎች እውነት ሐሰት በማለት ይመልሱ

26. “ዛቲ ጦማረ መልእክት ትብጻህ ኀበ አርድእተ ልሣነ ግእዝ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ እንደ ሚከተለው ነው።(2)
·       ዛቲ = የጦማር ቅጽል
·       ጦማር = የዐ/ነገሩ ባለቤት
·       መልእክት = የጦማር ዘርፍ
·       ትብጻህ = ማሠሪያ አንቀጽ
·       ኀበ = ንዑስ አገባብ
·       አርድእት(ተ) =  አገባብ የወደቀበት
·       ልሳን =  የአርድእት ዘርፍ
·       ግእዝ = የልሳን ዘርፍ
o   እውነት
27. “አምጣነ አቅረብኩ ለከ እሳተ ወ ማየ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ” የዚህ ዐ/ነገር የአማርኛ ትርጉምና የያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ የሚከተለውን ይመስላል።(2)
= እሳትና ውሀን አቅርቤልሃለሁና እጅህን ወደ ወደድከው(ወደ መረጥከው) አስገባ (ጨምር)
·       አቅረብኩ = የአገባብ ባለቤት(አገባብ የወደቀበት)
·       ለከ = ለአንተ ማለት ሲሆን ዝርዝር ይባላል (አንተ ለሚለው ይዘረዘራል)
·       እሳት =  የአቅረብኩ ተሳቢ
·       ወ =   አጫፋሪ(እሳትንና ውሀን)
·       ውሀ =  በ ወ ተጫፍሮ የአቅረብኩ ተሳቢ
·       ደይ = ማሠሪያ አንቀጸ
·       እዴከ =  የ “ደይ” ተሳቢ
·       ኀበ =  ንዑስ አገባብ
·       ዘ =  አቢይ አገባብ ሲሆን ፈቀድከ የሚለው ግሥ እንዳያሥር ይጠብቀዋል
·       ፈቀደ =  አገባብ(ዘ) የወደቀበት (ባለቤት)
o   እውነት
28. 99 ሴቶችና 1 ወንድ በድምሩ 100 ሰዎች በአንድ አዳራሽ ተሰብስበዋል፤ እርሰዎ በዚህ ጉባኤ ላይ ከጥዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ (በአገራችን አቆጣጠር) በግእዝ ቋንቋ ንግግር እንዲያደርጉ ስለተጋበዙ በታዳሚዎቹ ፊት ለፊት ቆመው “ እፎ ሐደርክን አኃትየ ወእኁየ”? በማለት መጀመር ይጠበቅበዎታል።
·       ሐሰት (ምክንያቱም በግእዝ ቋንቋ ብዙ ሴቶች ቢኖሩም አንድ ወንድ በመካከል ካለ በወንድ አንቀጽ ነው የሚነገረው ስለዚህ ትክክለኛው “እፎ ኀደርክሙ” ነው)
29. “ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ይእቲ” በሚለው ዐ/ነገር ውስጥ የሚከተሉት ትክክል ናቸው።(2)
·       ቤት(ቤተ) = የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት
·       ክርስቲያን = የቤት ዘርፍ
·       ቅድስት = የ ቤት ቅጽል
·       ይእቲ = ማሠሪያ አንቀጽ
o   እውነት
30. “እለ ትነብሩ ተንሥኡ” በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ
ትእዛዝ የሚሰጠው በተውላጠ ስም ሲቀመጥ “አነ” ወይም “ንሕነ” ትእዛዝ የሚቀበሉት ደግሞ “አንትሙ” የሚባሉት ናቸው፡፡(ማለትም 1ኛ መደብ እና 2ኛ መደብ)
·       እውነት

31. ከአውደ ጥናት ለእናንተ (ለግእዝ ተማሪዎች) ደብዳቤ መላክ ቢያስፈልግ ከፖስታው ጀርባ ላይ የሚከተሉት ይጻፋሉ።

እምነ/ ከ/ From
አውደ ጥናት Awde Tinat
1111 Gojam Ave.
Damot, GM 444
            
ለ/ ለ /To
አርድእተ ግእዝ/Ardete Ge’ez
2222 Piasa St. 444


·       እውነት

No comments:

Post a Comment