ክፍል 27 ትንቢታዊ አንቀጽ/ ካልዓይ
ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች ማለትም በክፍል
25 ስለ አበይት አናቅጽ፤ማለትም ስለ ሐላፊ ወይም ቀዳማይ፤ ትንቢት ወይም ካልአይ፤ እንዲሁም ዘንድ እና ትእዛዝ ወይም ሳልሳይ፤
ስለሚሉት ግሦች ጠቅለል ባለመልኩ ተምረናል። በክፍል 26 ደግሞ ከነዚሁ 4 አናቅጽ መካከል አንዱ ስለሆነው ስለ ሐላፊ ግሥ ተምረናል።
ዛሬ ደግሞ ስለ ትንቢት ወይም ካልአይ አንቀጽ እንማራለን።
ትንቢት ወይም ካልአይ ተብሎም ይጠራል። ካልአይ ሁለተኛ ማለት ነው
በግእዝ ቋንቋ የመጀመሪያው ግሥ ሐላፊ ነው፤ ማለትም
ማነኛውም የግእዝ ግሥ ተጽፎ የሚገኘው በሐላፊ ጊዜ ነው። ቀጥሉ ሁለተኛው ትንቢት ወይም ካልአይ ይባላል። (ስናረባው ማለት ነው)
ስለዚህ ዛሬ ከግሥ ርባታ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስለሚገኘው ስለ ትንቢት አንቀጽ እንማራለን ማለት ነው። ለምሳሌ
ግሡ “ወሀበ”
ቢሆን ይህ ግሥ “ሐላፊ” ይባላል። ምክንያቱም ትርጉሙ ሰጠ ማለት ነው። ሰጠ ማለት ደግሞ ያለፈ ድርጊትን
ነው የሚነግረን። የዚህ ግሥ ሁለተኛው ወይም ትንቲታዊው “ይሁብ” ይሆናል። ይሁብ
ማለት ደግሞ ይሰጣል ማለት ነው። ይሰጣል ስንል ያለፈ ድርጊት ሳይሆን ወደፊት
የሚደረግ ነው። ስለዚህ ትንቢት አንቀጽ የሚባለው ለዚህ ነው።
የትንቢት አንቀጽ አበይት መለያወች እና አገልግሎቶች
1.
ወደ ፊት ለሚደረግ ድርጊት
የሚያገለግል ነው (Futur tense )
2.
ተዘውትሮ ለሚደረግ () ድርጊትም
ይሆናል(present tense)
3.
አገባቦችን በመጠቀም በመደረግ
ላይ ለሚገኝ ድርጊትም ይሆናል።(present continuous) ስለዚህ በብዙ ዓይነት መልኩ
እንጠቀምበታለን ማለት ነው።
4.
ከግሡ መጀመሪያ ላይ ባእድ
ሆሄን ይጨምራል (እነዚህ ባዕድ ሆሄያት ስማቸው አሥራው ሲባሉ ቁጥራቸው 4 ነው። በአማርኛ “ሥሮች” ማለት ነው። ይ፤ት፤ን፤እ፤ ናቸው።
በ ሀ እና በ አ ግሦች ግዕዛቸውና
ራብአቸውም ይገኛል። (በትንቢት ፤ በዘንድ፤ በትእዛዝ፤ አናቅጽ ብቻ የሚገቡ ናቸው) ለወደፊቱ ስለነዚህ ፊደላት ሙሉ ትምህርት እንማራለን፤
ለአሁኑ ግን ጠቅለል አድርገን ነው የምናያቸው።
ከዚህ ቀጥሉ ካልአይ ግሥ ለትንቢታዊ ፤ ተዘውትሮ ለሚደረግ፤
እና በመደረግ ላይ ላለ ድርጊት እንዴት እንደሚገባ እናያለን። በመጨረሻም ስለሚጨምራቸው ባዕድ ፊደላት በሦስት ግሦች እንደ ምሳሌ
እናያለን።
መሳሌ፡1 ለትንቢታዊ ድርጊት
·
አነ አሀውር
ኀበ ብሔረ ግብፅ ድኅረ ሰለስቱ ዓመታት
ምሳሌ፡2 ዘወትር ለሚደረግ ድርጊት
·
“ይብል ዓብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር”
(ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል)
·
አንትሙ ተአምሩ
ልሳነ ግእዝ
·
ሕጻን ይበኪ እንዘ ይበልእ
ምሳሌ 3፡ በመደረግ ላይ ላለ ድርጊት
ምንተ ትገብሩ አኀውየ? እንዘ ንትሜሀር ልሳነ ግእዝ
ምሳሌ
4፡ ከግሡ መጀመሪያ ላይ ባእድ ሆሄን ሲጨምር
ሰአለ
=ይስእል (ለመን)
ባረከ=ይባርክ
ገብረ=ይገብር