Saturday, June 6, 2015

ግእዝ ክፍል 26 ሐላፊ አንቀጽ

ክፍል 26


ሐላፊ ግሥ/past tense

በሃላፊ ጊዜ በግእዝ ሆሄ የሚጨርሱ ግሶች (መራሕያን)

ሐላፊ ግሥ ወይም አንቀጽ ቀዳማይ በመባልም ይጠራል መጀመሪያ ማለት ነው፤ ስለዚህ የመጀመሪያ ስለሆነ ቀዳማይ ወይም የመጀመሪያ ተባለ። በዛሬው በክፍል 26 ትምህርታችን ይህንኑ ሐላፊ ግሥን ብቻ የሚከተሉትን 5 ግሦች መሠረት አድርገን እንማራለን።

በግእዝ ቋንቋ ሐላፊ ግሥ የሚሆነው የመጀመሪያው መሠረታዊ ግሥ ነው። ማለትም ማነኛውም ግሥ ተጽፎ የሚገኘው በሐላፊ ጊዜ ነው። ማነኛውም ግሥ የሚጀምረው በሦስተኛ መደብ በወንድ ጾታ፤ በአንድ ቍጥር ነው። ስለዚህ የግእዝን መዝበበ ቃላት መጽሐፍ ገልጠን ብንመለከት ዘር ግሥ ሁሉ ተጽፎ የሚገኘው በሦስተኛ መደብ ነጠላ በወድ ፆታ ሲሆን ጊዜውም በሃላፊ ጊዜ ነው።

በሚከተለው ዓይነት ማለት ነው። የሚከተሉት የአምስቱ ግሦች ባለቤት ሦስተኛ መደብ ነጠላ ለውንድ ሲህን ይህም “ውእቱ” የሚለው ተውላጠ ስም ነው።
·         ቀደሰ
·         ሆረ
·         አእመረ
·         ኀሠሠ
·         ባረከ
ሐላፊ ማለት ያለፈ ጊዜን የሚያመለክት የተደረገ፤ የተሠራ፤ ያለቀለት፤ ሥራ ወይም ድርጊት ነው። ሐላፊ ጊዜን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ እንደ ቅድመቅድምትማልም፤ ወዘተ የመሳሰሉትን አገባቦች መጠቀም እንችላለን።
·         ቀደሰ፡= አመሰገነ
ውእቱ ቀደሰ ምስለ ካህናት =እሱ ከካህናት ጋር አመሰገነ። ይህ ዐረፍተ ነገር ወይም ግሥ የሚነግረን ነገ የሚደረግ፤ ወይም በመደረግ ላይ ያለ ድርጊትን ሳይሆን ያለፈ፤ የተደረገ፤ ያለቀለትን ታሪክ ነው። ሓላፊ ግሥ በአሥሩ መራኅያን ሁሉ እንደ ሚከተለው ይረባል።
3ኛ መደብ
1.      ቀደ-
2.     ቀደ-
3.     ቀደ-ሰት
4.     ቀደ-
2ኛ መደብ
5.     ቀደ-ስከ
6.     ቀደ-ስክሙ
7.     ቀደ-ስኪ
8.     ቀደ-ስክን
1ኛ መደብ
9.     ቀደ-ስኩ
10.    ቀደ-ስነ




ሐላፊ ግሣቸውን ወደ ግእዝ ሆሄ የሚቀይሩ ወይም ሃላፊ ግሳቸው ግእዝ የሚሆን ግሦች ወይም መራሕያን ሦስት ናቸው።

በሐላፊ ጊዜ የመጨረሻውን የግሡን ሆሄ ወደ ግእዝ ሆሄ የሚቀይር ግሥ ወይም መራሂ

ውእቱ ሆ(ይህ ግሥ ምንጊዜም ግእዝ ሆሄን ቢጠቀምም እንደ ግሱ ሁኔታ ይቀያየራል፤ ግእዝነቱን ግን አይቀይርም።

አንተ ሆር (ይህ ግሥ በማነኛውም ዓይነት ግሥ ይሁን ለሐላፊ ጊዜ“ከ” የሚለውን ሆሄ ብቻ ይጠቀማል።

ንሕነ ሆር(ይህ ግሥ በማነኛውም ዓይነት ግሥ ይሁን ለሐላፊ ጊዜ“ነ” የሚለውን ሆሄ ብቻ ይጠቀማል።

በነዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሱት በሦስቱ መራሕያን በ3ኛ መደብ ነጠላ ለወንድበሁለተኛ መደብ ነጠላ ለወንድ፤ እና በአንደኛ መደብ ብዙ ለወንድም ለሴትም ግሡ ለሃላፊ ጊዜ ሲሆን በግእዝ ሆሄ ይጨርሳል። ወይም የመጨረሻው ሆሄ ግእዝ ይሆናል።

በተጨማሪም አንተ በሚለው የግሱ የመጨረሻ ሆሄ ከግእዝ ወደ ሳድስ ይቀየርና “ከ” የሚለውን ሆሄ ይጨምራል። ለምሳሌ. “ከ”
ንሕነ በሚለው ደግሞ የግሱን የመጨረሻ ሆሄ ወደ ሳድስ ይቀይርና “ነ” የሚለውን ሆሄ ይጨምራል። ለምሳሌ.“ነ”

ውእቱ በሚለው ግን ግሱ አይቀየርም “ሆረ”

No comments:

Post a Comment