Saturday, November 28, 2015

ግእዝ ፈተና 2 ክፍል 31

Ge'ez part 31 exam 2



የግእዝ ትምህርት ክፍል ሁለት ጠቅላላ የመመዘኛ ፈተና   



ዛሬ በዚህ በክፍል 31 ትምህርታችን ክፍል ሁለት አጠቃላይ የመመዘኛ ፈተናን እንሠራለን። ይህ ፈተና ከክፍል 13 ጀምሮ እስከ ክፍል 30 ያሉትን ሁሉ ያጠቃለለ ነው። በዚህ የመመዘኛ ፈተና ውስጥ 31 ጥያቄዎች ሲኖሩ ክነዚህ ውስጥ 21ዱ አንድ አንድ ጥያቄዎችን የያዙ ሲሆን ቀሪዎቹ 10 ጥያቄዎች ደግሞ ከአንድ በላይ የሚሆኑ ጥያቄዎችን ይዘዋል። ለማስታዎስ ያህል 1ኛው 4 ጥያቄዎች፤ 3ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 4ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 6ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 12ኛው 5 ጥያቄዎች፤ 19ኛው 3 ጥያቄዎች 25ኛው 5 ጥያቄዎች፤ 26ኛው 2 ጥያቄዎች፤ 27ኛው 2 ጥያቄዎች፤ እና 29ኛው 2 ጥያቄዎች አሏቸው። በጠቅላላ 50 ይሆናሉ ስለዚህ እያንዳንዱ ጥያቄ ሁለት ነጥብ ይኖረዋል ማለት ነው። 20 ጥያቄዎችን ለማቅረብ ነበር የተነጋገርነው የበለጠ ለማጥናት ይጠቅማችኋል ብየ ስላሰብኩ 50 አደረግሁላችሁ። ስለዚህ ሰፊ ጌዜ እሰጣችኋለሁ በርትታችሁ አጥኑ። መልካም ፈተና።

ለሚከተሉት 15 ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ይስጡ።

1.  “ዛቲ ጦማረ መልእክት ትብጻህ ኀበ አርድእተ ልሣነ ግእዝ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ
·       የዐ/ነገሩን ባለቤት-----
·       የዐ/ነገሩን ማሠሪያ አንቀጽ------------
·       የ”ጦማርን” ቅጽል ይናገሩ------------------(4)

2. አበይት አናቅጽ የሚባሉትን አራት ግሦች “ሰብሐ” በሚለው ግሥ ምሳሌ ያሳዩ

3. አእማድ” የሚባሉት  ስንት ናቸው? ስማቸውንም ይጥቀሱ(2)እርማት ተደርጎበታል (በቪድዮው ላይ ሳነብ ሆሄያት ብያለሁ "አዕማድ" ግን ሆሄያት ሳይሆኑ በሆሄያት አማካኝነት ትርጉማቸውን የሚቀይሩ ግሦች ናቸው። ስለዚህ "ሆሄያት" የሚለው ቃል ይቀራል)

4. “አሥራው” የሚባሉት ሆሄያት ስንት ናቸው? ስማቸውንም ይጥቀሱ(2)

5. “ኢታንሥእ ዘኢያንበርከ” ማለት ምን ማለት ነው?

6. በ5ኛ ተራ ቁጥር ላለው ዐ/ነገር ትእዛዝ ሰጭውንና ትእዛዝ ተቀባዩን በተውላጠ ስሞች ይናገሩ፤(2)

7. “አስማት” ማለት ምን ማለት ነው?

የሚከተሉትን ወደ ግእዝ ቋንቋ ይቀይሩ

8. እንደ ምን አደርክ ወንድሜ?

9. ልጂሽ የት ነው እኅቴ?

10. እንደ ምን አደሩ እናቴ?

11. ለምን መጣችሁ ወንድሞቼ?

12. ቅድመ ሠለስቱ ዓመታት ፈለስኩ እምነ ብሔርየ ከመ እሁር ኀበ ሐገረ ባእድ፤ ወድኅረ ክልኤቱ አውራኅ እትመየጥ መንገለ አዝማድየ። ባሕቱ አቡየ ይቤለኒ ኢትትመየጥ ኀበ ዝንቱ ሐገር።

ከዚህ በላይ ባለው ምንባብ ውስጥ ተጠቅሰው የሚገኙትን 5 ግሦች ወይም አናቅጽ ለይተው በማውጣት የያንዳንዱን ግሥ ዓይነት ይናገሩ (የሚገልጸውን ጊዜ) ።(5)

13. ከ4ቱ አበይት አናቅጽ ውስጥ በቀጥታ ራሱን ችሉ የዐረፍተ ነገር ማሠሪያ መሆን የማይችለው ግሥ የትኛው ነው? ስሙን ይጥቀሱ።

14. ወለተ ማርያም ለብሰት ጸሊመ ልብሰ። በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ “ጸሊም” የሚለው ቃል የሚቀጸለው ለማነው? ወይም የሚገልጠው ማንን ነው?

15. “ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን” የዚህ ዐ/ነገር ማሠሪያ አንቀጽ “ቀዳማይ፤ ካልአይ፤ ሳልሳይ፤ ወይስ ራብአይ አንቀጽ የትኛው ነው?

16. “እግዚአብሔር ይባርኪ ወያብርህ ገጾ ላእሌኪ” ምን ማለት ነው?

17. “ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ “ድንግል” የሚለው ቃል ስንተኛ መደብ ነው?

18. እፎ ሐደርከ (ኪ፤ክሙ፤ክን) ለዚህ ቃል መልሳችን ሊሆን የሚችለውን በግእዝ ይጻፉ

19. “አርዌ ምድር አስፈጠተኒ ወበላእኩ”(3)
·       በዚህ ዐ/ነገር(በ19ኛው ጥያቄ) “አስፈጠተኒ” የሚለው ቃል መሠረታዊ ግሡ ማነው?
·       ትርጉሙስ ምን ማለት ነው?
·       “አስፈጠተኒ” የሚለው ቃል ራሱን ችሎ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ምን ማለት ነው?

20. “ገንጰለ” ማለት ምን ማለት ነው?
21. መርድአ ግእዝ አእመረ ልሳነ ግእዝ ወ ቅኔ ተምሂሮ እምነ አውደ ጥናት ዘግእዝ። ምን ማለት ነው?

22. “ንግሩኒ ስማ ለብእሲት” ምን ማለት ነው?

23. ማነኛውም ርባ ግሥ መነሻው ምን ዓይነት የግዜ ትርጉም ነው?

24. “ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ማለት ምን ማለት ነው?

25. በአውደ ጥናት የትምህርት ማእከል ተገኝተው ስለ ግእዝና ቅኔ ሰፊ ማብራርያ የሰጡት የቤተ ክርስቲያናችን ምሁር ማን ይባላሉ? ከቻሉ ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ የሰጡትን መልስ ጠቅለል አድርገው በ5 ወይም ከዚያ በታች በሆኑ ዐ/ነገሮች ይግለጹት። (5)

ለሚከተሉት 5 ጥያቄዎች እውነት ሐሰት በማለት ይመልሱ

26. “ዛቲ ጦማረ መልእክት ትብጻህ ኀበ አርድእተ ልሣነ ግእዝ” በዚህ ዐ/ነገር ውስጥ የያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ እንደ ሚከተለው ነው።(2)
·       ዛቲ = የጦማር ቅጽል
·       ጦማር = የዐ/ነገሩ ባለቤት
·       መልእክት = የጦማር ዘርፍ
·       ትብጻህ = ማሠሪያ አንቀጽ
·       ኀበ = ንዑስ አገባብ
·       አርድእት(ተ) =  አገባብ የወደቀበት
·       ልሳን =  የአርድእት ዘርፍ
·       ግእዝ = የልሳን ዘርፍ

27. “አምጣነ አቅረብኩ ለከ እሳተ ወ ማየ ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ” የዚህ ዐ/ነገር የአማርኛ ትርጉምና የያንዳንዱ ቃል የሥራ ድርሻ የሚከተለውን ይመስላል።(2)

= እሳትና ውሀን አቅርቤልሃለሁና እጅህን ወደ ወደድከው(ወደ መረጥከው) አስገባ (ጨምር)
·       አቅረብኩ = የአገባብ ባለቤት
·       ለከ = ለአንተ ማለት ሲሆን ዝርዝር ይባላል (አንተ ለሚለው ይዘረዘራል)
·       እሳት =  የአቅረብኩ ተሳቢ
·       ወ =   አጫፋሪ(እሳትንና ውሀን)
·       ውሀ =  በ ወ ተጫፍሮ የአቅረብኩ ተሳቢ
·       ደይ = ማሠሪያ አንቀጸ
·       እዴከ =  የ “ደይ” ተሳቢ
·       ኀበ =  ንዑስ አገባብ
·       ዘ =  አቢይ አገባብ ሲሆን ፈቀድከ የሚለው ግሥ እንዳያሥር ይጠብቀዋል
·       ፈቀደ =  አገባብ(ዘ) የወደቀበት (ባለቤት)

28. 99 ሴቶችና 1 ወንድ በድምሩ 100 ሰዎች በአንድ አዳራሽ ተሰብስበዋል፤ እርሰዎ በዚህ ጉባኤ ላይ ከጥዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ (በአገራችን አቆጣጠር) በግእዝ ቋንቋ ንግግር እንዲያደርጉ ስለተጋበዙ በታዳሚዎቹ ፊት ለፊት ቆመው “ እፎ ሐደርክን አኃትየ ወእኁየ”? በማለት መጀመር ይጠበቅበዎታል።

29. “ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ይእቲ” በሚለው ዐ/ነገር ውስጥ የሚከተሉት ትክክል ናቸው።(2)
·       ቤት(ቤተ) = የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት
·       ክርስቲያን = የቤት ዘርፍ
·       ቅድስት = የ ቤት ቅጽል
·       ይእቲ = ማሠሪያ አንቀጽ

30. “እለ ትነብሩ ተንሥኡ” በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ
ትእዛዝ የሚሰጠው በተውላጠ ስም ሲቀመጥ “አነ” ወይም “ንሕነ” ትእዛዝ የሚቀበሉት ደግሞ “አንትሙ” የሚባሉት ናቸው፡፡(ማለትም 1ኛ መደብ እና 2ኛ መደብ)

31. ከአውደ ጥናት ለእናንተ (ለግእዝ ተማሪዎች) ደብዳቤ መላክ ቢያስፈልግ ከፖስታው ጀርባ ላይ የሚከተሉት ይጻፋሉ።

እምነ/ ከ/ From
አውደ ጥናት Awde Tinat
1111 Gojam Ave.
Damot, GM 666
            
ለ/ ለ /To
አርድእተ ግእዝ/Ardete Ge’ez
2222 Piasa St. 444

 


                                                

Friday, October 30, 2015

የግእዝ ቋንቋ አሥራው ሆሄያት



Ge'ez Lesson for Beginers part 30/አሥራው






አሥራው ማለት ሥሮች ማለት ሲሆን ለነጠላ “ሥርው” ይሆናል ሥር ማለት ነው። ሥር ማለት ደግሞ መነሻ መጀመሪያ ማለት ነው።
አሥራው የሚባሉት የእርባ ግሥ ወይም የዘር ግሥ ሁሉ መነሻዎች ናቸው። ቁጥራቸው 4 ሲሆኑ
1.     
2.    
3.    
4.    
የሚባሉት ናቸው። እነዚህ ሆሄያት የግሥ ባዕድ መነሻዎች ይባላሉ።

ከትንቢት አንቀጽ በላይ አይወጡም ከትዕዛዝ አንቀጽ በታችም አይወርዱም። ስለዚህ በትንቢት፤በዘንድ፤ እና በትዕዛዝ አናቅጽ በሦስቱ ብቻ ይገኛሉ። ባዕድ በመባል የሚጠሩበት ምክንያትም

ምሳሌ፦ “አእመረ” ይህ መሠረታዊ ግሥ ነው፤ 4 ሆሄያትን ይዟል፤ (አ፤እ፤መ፤ረ) እነዚህ አራት ሆሄያት ሦስት ሊባሉም ይችላሉ ምክንያቱም “አ” እና “እ” የአንድ ሆሄ ዘር ስለሆኑ በ”አ” ዘር ይጠቃለላሉ።

 ስለዚህ “አእመረ” የሚባለው ግሥ ወይም አንቀጽ 3 የተለያዩ ሆሄያትን ይዟል 4ኛው ግን ከሦስቱ ውስጥ የአንዱ ዘር ነው። ልብ አድርጉ አሁን አእመረ የሚለውን ግሥ በምንገሥ ወይም በምናረባው ጊዜ ከጠቀስናቸው ሦስት የተለያዩ ሆሄያት ውስጥ ያልነበረ ወይም የሦስቱ ዘር ያልሆነ ሆሄ ወይም ፊደል ካየን ያ ሆሄ ወይም ፊደል “ባዕድ” ይባላል። ባዕድ ማለት ዘመድ ያልሆነ ማለት ነው። በሌላ አባባል ከመሠረታዊው ግሥ ውስጥ ከሚገኙት ሆሄያት ጋር የማይዛመድ ማለት ነው።

 አሁን ግሡ ሲረባ እንመልከት የሚከተሉት 4 ግሦች ወይም አንቀጾች በተደጋጋሚ እንደተነጋገርነው አበይ አናቅጽ ይባላሉ። ታላላቅ ግሦች ማለት ነው። 1ኛው “ሐላፊ አንቀጽ” ወይም “ቀዳማይ አንቀጽ”፤ 2ኛው፤ “ትንቢት አንቀጽ” ወይም “ካልአይ አንቀጽ”፤ 3ኛው “ዝንድ አንቀጽ” ወይም “ሣልሳይ አንቀጽ”፤ 4ኛው “ትእዛዝ አንቀጽ” ወይም “ሣልሳይ አንቀጽ”[1]  ይባላሉ።
1.      እመረ
2.   የአምር
3.   ያእምር
4.   ያእምር
 ወይም አምር ) የመጀመሪያዎቹ ሆሄያት ማለትም  “የ”  እና “ያ” ባዕድ ሆሄያት ናቸው
ከዚህ በላይ ያሉትን 4 አበይት አናቅጽ ስንመለከት መሠረታዊው ግሥ 4 ሆሄያት ወይም 2 የተለያዩ፤ 2 ተመሳሳይ ሆሄያት በድምሩ 4 ሆሄያት አሉት እነዚህም = አ፤ እ፤ መ፤ ረ፤ የተባሉት ሲሆኑ “አ” እና “እ” የአንድ አይነት ፊደል ዘሮች ስለሆኑ እንደ አንድ እንደሚቆጠሩ ተነጋግረናል። ስለዚህ ከመሠረታዊ ግሥ የተለየ እንግዳ ሆሄ በግሡ ላይ ከተጨመረ “ባዕድ” ይባላል ብለናል። “ባዕድ ሆሄ”ን መጨመር ደግሞ የትንቢት፤የዘንድ፤ እና የትእዛዝ አናቅጽ” መለያ ባሕርይ ነው።

 ስለዚህ “የአምር” ሲል “የ” የተባለ ከመሠረታዊው ግሥ ከ”አእመረ” ውስጥ ያልነበረ ሆሄን እናያለን ስለዚህ ይህንን ሆሄ “ባዕድ”[2] እንለዋለን ማለት ነው።
“ይ” በሦስት አናቅጽ
·         በአንድ ወንድ፤
·         በብዙ ወንዶች፤
·         በብዙ ሴቶች በኀላፊ አናቅጽ ውስጥ ይገኛል።
ምሳሌ፦ ግሡ “ሖረ” ቢሆን ለአንድ ሩቅ ወንድ
ሐውር፤ ሑር፤ይሑር

“ሖሩ” ለብዙ ወንዶች ለሩቆች
 ሐውሩ፤ ሑሩ፤ይሑሩ

“ሖራ” ለብዙ ሴቶች ለሩቆች
 ሐውራ፤ ሑራ፤ሑራ

“ት” በ5 አናቅጽ
1.      በቅርብ ወንድ፤
2.     ወንዶች፤
3.     ሴት፤
4.     ሴቶች፤ እና
5.     በአንዲቷ ሩቅ ሴት ይገኛል

ግሡ “ጸለየ” ቢሆን የቅርቡ ወንድ “ጸለይከ” ይሆናል ስለዚህ
ለቅርብ ወንድ
·         ጼሊ
·         ጸሊ
·         ጸሊ

ለብዙ ወንዶች ለቅርቦቹ በቅርቦቹ አናቅጽ በትእዛዝ አንቀጽ ላይ አሥራው አይገኙም
·         ጼልዩ
·         ጸልዩ
·         ጸልዩ
ለአንዲት ሴት ለቅርቢቱ
·         ጼልዪ
·         ጸልዪ
·         ጸልዪ

ለቅርቦቹ ብዙ ሴቶች
·         ጼልያ
·         ጸልያ
·         ጸልያ
ለሩቅ ሴት ለአንዷ
·         ጼሊ
·         ጸሊ
·         ጸሊ

“እ” እና “ን” በአንደኛ መደብ አናቅጽ ይገባል በሁለት ማለትም
በአነ እና በንሕነ አነ ለሚለው አንድ ነጠላ ለወንድም ለሴትም
·         ጸለይኩ
·         ጼሊ
·         ጸሊ
·         ጸሊ
ንሕነ ለሚለው ለብዙ ወንዶችም ሴቶችም
·         ጸለይነ
·         ጼሊ
·         ጸሊ
·         ጸሊ

ራብአቸውና ግእዛቸው የሚገኘው
በአድራጊ እና በአደራራጊ ግሦች፤ እንዲሁም “ሀ” እና “አ” በግሡ “መጀመሪያ”፤ “መካከል” ፤ እና “መጨረሻ ላይ ሲሆኑ ነው።

ምሳሌ፦ ግሡ “ቀተለ” ቢሆን አድራጊና አደራራጊ ግሦቹ “አቅተለ” እና “አስተቃተለ” የሚሉት ናቸው ስለዚህ

አንድ ሩቅ ወንድ አስደራጊ
·         ቅትል (“ት” ይጠብቃል)
·         ቅትል
·         ቅትል
አንድ ሩቅ አደራራጊ
·         ስተቃትል(“ት” ይጠብቃል)
·         ስተቃትል
·         ስተቃትል
በ”ሀ” እና በ”አ” ግሦች “አእመረ” በሚለው ግሥ ለአንድ ሩቅ ወንድ
·         አምር
·         እምር
·         እምር
ስለዚህ ሌሎችንም ግሦች በዚህ ዓይነት መልኩ ይሞክሩ።




Sunday, October 25, 2015

የመዝሙር ግጥሞች

የመዝሙር ግጥሞችን የሚፈልጉ ከሆነ አውደ ጥናትን በሚከተሉት መንገዶች ያነጋግሩ

Saturday, October 10, 2015

ግእዝ ክፍል 29

ትእዛዝ አንቀጽ


ትእዛዝ አንቀጽ ማለት ማዘዣ ወይም የማዘዣ ግሥ ፤ ትዕዛዝ የሚተላለፍበት ቃል ማለት ነው።
ትእዛዝ በቅጥራ የሚተላለፈው ከ1ኛ መደብ ወደ 2ኛ መደብ ሲሆን ቀጣ ባልሆነ መልኩ ግን በመልእክትና በመሳሰሉት ከ1ኛ መደብ በ2ኛ መደ በኩል ሌ3ኛ መደብ ይተላለፋል።

በልዋ ለእምየ ንኢ ኀቤየ

እኔ እናንተን “እናቴን እንድታዝዟት አዘዝኳችሁ
እንዲሁም ከ3ኛ መደብ በ1ኛ መደብ በኩል ለ2ኛ መደብ ይደርሳል።
“ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ  ለእለ ይትለአኩ”  ምልዕዎንኬ ለእላ መሳብክት ማየ”
ምሳሌ፡ለቀጥታ ትዕዛዝ ከ1ኛ መደብ ለ2ኛ መደብ
እኔ አንደኛ መደብ ነኝ፤
እናንተ ደግሞ 2ኛ መደብ ናችሁ፡

አጽምኡ ዘእቤለክሙ (አኃውየ ወአኃትየ!)

ምሳሌ 2፡ ቀጥታ ያልሆነ እና በታሪክ መልክ ከ1ኛ መደብ ለ2ኛ መደብ የሚነገር  ትእዛዝ፡
ቀጥታ ላልሆነ ትእዛዝ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን  በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ያለው  ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ  ለሠርግ አሳላፊዎች የተሰጠው ትእዛዝ ነው።
1.      ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእለ ይትለአኩ

2.   “ምልዕዎንኬ  ለእላ መሳብክት ማየ”

አንደኛውን ዐረፍተ ነገር የተናገረው ወንጌላዊው ነው
ሁለተኛውን ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ይህ ትእዛዝ በወቅቱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥዕሉ ላይ እንደምታዩት  በቀጥታ ያስተላለፈው ወይም የሰጠው ትእዛዝ ነው።

በኋላ ግን ወንጌላዊው በታሪክ መልክ “አላቸው” በማለት  በሓላፊ ግሥ  ነገረን።
ስለ ትእዛዝ አንቀጽ በሰፊው ማወቅ ከፈለጋችሁ  ወደ ቤተ ክርስቲያን የምትሄዱ ሰዎች የቅዳሴውን ጸሎት በትኩረት ተከታተሉ።፡በተለይ ዲያቆናቱ የሚያስተላልፉ ወይም የሚናገሩት የጸሎት ክፍል የሚተላለፈው ቢያንስ 98 ከመቶው በትእዛዝ መልክ ነው።
ትእዛዝ አንቀጽ በሆሄያትና በድምጽ ወይም በአነጋገር በንባብ ከዘንድ አንቀጽ ጋር ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ ነው። መለየት የምንችለው  ከግሥ እርባታ ውስጥ ከሆነ “ትእዛዝ አንቀጽ” የሚገነው መጨረሻ ላይ ንው፤

በሥነ ጽሁፍ ውስጥ ከሆነ ግን መለየት የምንችለው በትርጉሙ ብቻ ነው።

ከግሡ መነሻ ላይ “ባዕድ ፊደላትን” ይጨምራል።
watch video about this topic

Tuesday, August 11, 2015

ግእዝ ክፍል 17

Part 17 inside The paradise


እግዚአብሔር፣ አዳም፤ ሔዋን፤ እና እባብ
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
“.. አይቴ ሀሎከ አዳም.. ?
ይቤሎ አዳም ለእግዚአብሔር
“.. ሰማዕኩ ቃለከ እንዘ ታንሶሱ ውስተ ገነት ወፈራህኩ እስመ ዕራቅየ አነ ወተኀባእኩ.. ”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
 “.. መኑ አይድዐከ ከመ ዕራቅከ አንተ እም ዕፅኑ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ እምኔሁ በላእከ?.. ”
ይቤሎ አዳም ለእግዚአብሔር
 “.. ብዕሲት እንተ ወሀብከኒ ምስሌየ ትንበር ይእቲ ወሀበተኒ ወበላእኩ-”
ይቤላ እግዚአብሔር ለብእሲት(ሔዋን)
“.. ለምንት ገበርኪ ዘንተ?.. ”
ትቤሎ ብእሲት፡ ለእግዚአብሔር
“.. አርዌ ምድር አስፈጠተኒ ወበላእኩ.. ”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአርዌ ምድር
 “.. እስመ ገበርኮ ለዝንቱ ግብር ርጉመ ኩን እምኵሉ እንስሳ ወእምኵሉ አራዊተ ምድር ወበ እንግድዓከ ሑር ወመሬተ ብላዕ..”
ይቤላ እግዚአብሔር ለብእሲት(ሔዋን)
 “.. (ብዙኃ) አብዝኆ አበዝኆ ለኀዘንኪ ወለሥቃይኪ ወበጻዕር ለዲ..”
ይቤሎ እግዚአብሔር ለአዳም፡
 “.. እስመ ሰማዕከ ቃለ ብእሲትከ ወበላዕከ እም ውእቱ ዕፅ ባሕቲቱ ዘአዘዝኩከ ከመ ኢትብላዕ ርግምተ ትኩን ምድር…”


Friday, July 24, 2015

ግእዝ ጽሁፍ ክፍል 28 ዘንድ አንቀጽ

Ge'ez Lessons for Beginners part 28 text (ዘንድ አንቀጽ = in order to)


መሀረ = አስተማረ (ያለፈ ድርጊት) past
ህር= ያስተምራል (ወደፊት የሚደረግ ትንቢት) futur
ይምሀር= ያስተምር ዘንድ (ምክንያታዊ ) in order to


እርማት፡ መሀረ = አስተማረህር 
ይምሀር
ይምሀር
መሐረ = ይቅር አለ የሚለው ግስ ሲሆን ነው ህር በማለት የሚረባው። መሀረ = አስተማረ የሚለው ግን መሀረ (ሐላፊ) ይህር (ትንቢት) ማለትም በትንቢት (በሁለተኛው ግስ) የሚገኘው ሆሄ "ም" ሳይሆኝ "" (ይህር) ይሆናል።



ተንሥአ ይምሀር መምህረ ግእዝ =የግእዝ መምህር ያስተምር ዘንድ ተነሣ
ዘንድ አንቀጽ = In order to
ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች በክፍል 25 ስለ አራቱ አበይት አናቅጽ ስለ
1.      ሃላፊ፤
2.     ትንቢት፤
3.     ዘንድ  እና
4.     ትዕዛዝ (ዘንድ እና ትዕዛዝ ሳልሳይ ወይም 3ኛ ይባላሉ) ጠቅለል ባለ መልኩ ተምረን ነበር።
በድጋሚ ለማስታዎስ ያህል ግሦቹ የሚከተሉት ናቸው።
ሖረ=  ሄደ  ሃላፊ አንቀጽ
ይሐውር= ይሄዳል  ትንቢት አንቀጽ
ይሑር= ይሄድ ዘንድ  ዘንድ አንቀጽ
ይሑር= ይሂድ  ትእዛዝ አንቀጽ
በመሆኑም እነዚህን ግሦች መሠረት አድርገን እንደ መግቢያ ከተማርን በኋላ በመቀጠልም አንድ በአንድ  በክፍል 26 ስለ ሃላፊ ግሥ ወይ አንቀጽ፤ በክፍል 27 ስለ ትንቢት ግሥ ወይም አናቅጽ ተምረናል።
በዛሬው በክፍል 28 ትምህርታችን ደግሞ
ስለ ዘንድ አንቀጽ እንማራለን። ዘንድ አንቀጽ ሳልሳይ ተብሎም ይጠራል ።ሦስተኛ ማለት ነው። ምክንያቱም በሦስተኛ ተራቁጥር ስለሚገኝ ነው። ዘንድ አንቀጽ የሚባለውም ዘንድ ተብሎ ስለሚተረጎም ነው። (ይሄድ ዘንድ)
ዘንድ አንቀጽ ከአበይት ግሦች ሦስተኛው አንቀጽ ሲሆን በቀጥታ ማሠሪያ አንቀጽ አይሆንም ማለትም አያሥርም። (ውእቱን መርምሮ ካልሆነ በስተቀር)፤
 ስለዚህ ሌላ ተጨማሪ አንቀጽን ይፈልጋል። ውእቱ (ገብረ ሥላሴ) ተንሥአ ይሁር = እሱ ይሄድ ዘንድ ተነሣ፤ ብንል የዚህ ዐረፍተ ነገር ማሠርያ የሆነው “ተንሥአ” የሚለው ግሥ ሲሆን ይሁር የሚለው ምክንያቱን ይገልጻል እንጂ አያሥርም። ስለዚህ በዚህ ዐረፍተ ነገር ሁለት አበይት ግሦች ሲኖሩ አንዱ ብቻ ማሠሪያ ሆነ። ለዚህም ነው ዘንድ አንቀጽ በቀጥታ ስለማያሥር ሌላ ሁለተኛ አንቀጽን ይሻል ያልነው።
ዘንድ አንቀጽ አገባባዊ ባሕርይ አለው፤ (ከመ ከሚለው አገባብ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም እና ሥራ አለው። ሁለቱ ማለትም ከመ እና ዘንድ አንቀጽ በአንድ ላይ ይነገራሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ዘንድ አንቀጹ የተለመደውን ትርጉሙን ሲይዝ “ከመ” የሚለው አገባብ የዘንድ አንቀጹ ሞገሥ ወይም አጃቢ ይባላል።
ለምሳሌ
መርድእ ሖረ ከመ ይትመሀር ልሣነ ግእዝ = ተማሪ የግእዝን ቋንቋ ይማር ዘንድ ሄደ። በዚህ ዐ/ነገር ላይ ከመ የይትመሀር አዳማቂ ሆነ እንጂ ሌላ አገልግሎት አልሰጠም። ምክንያቱም “ይትምሀር” የሚለው ግሥ ራሱ ትርጉሙ “ይማር ዘንድ” የሚል ነው። ልዩነታቸው ዘንድ አንቀጽ  አንቀጽም ነው እንደ አገባብም ይተረጎማል፤ “ከመ” ግን “እንደ” የሚል ትርጉም ነው ያለው። ስሙም አገባብ ይባላል። ለሁለቱም ማለትም ለዘንድ አንቀጽና “ከመ” ለሚለው አገባብ ምሳሌዎቹን ተመልከቱ
መነኮስ ቆመ ከመ ይጼሊ= መነኩሴ ይጸልይ ዘንድ ቆመ።
መነኮስ ቆመ ይጸሊ = መነኩሴ ይጸልይ ዘንድ ቆመ።
 በነዚህ በሁለቱ ዐረፍተ ነገራት መሠረት ዘንድ አንቀጽና “ከመ” የሚለው አገባብ ተመሳሳይ አገልግሎት አላቸው። ነገር ግን “ከመ” ከአንቀጽ ጋር በመሆን አንቀጹ እንዳያሥር ለመከላከል ነው የሚያገለግለው፤ ዘንድ አንቀጽ ግን   ብቻውን በመሆን ነው የሚነገረው የራሱ የሆነ አገባባዊ ባሕርይ አለው ማለት ነው።
ዘንድ አንቀጽ ከሁሉም ግሦች (ከሐላፊ፤ከትንቢት፤ እና ከትእዛዝ አናቅጽ ) ጋር አብሮ ይሠራል።
ምሳሌ፡
·         ይብላእ ሆረ = ይበላ ዘንድ ሄደ (ሃላፊ)
·         የሐውር ይብላእ= ይበላ ዘንድ ይሄዳል (ትንቢት)
·         ይሁር ይብላእ= ይበላ ዘንድ ይህድ(ትእዛዝ)
ዘንድ አንቀጽ በዓረፍተ ነገር ሲገባ ለሌላ ድርጊት ወይም አንቀጽ እንደ ምክንያት በመሆን ይገባል።
ለምሳሌ “ መርድእ ሖረ ይትምሀር” ቢል የዓረፍተ ነገሩን ባለቤት የጎዞ ምክንያት ይገልጽለታል። ማለትም ተማሪው የሄደበት ምክንያት “ይማር ዘንድ” ወይም ለመማር ነው። በማለት ምክንያቱን ገለጸለት ማለት ነው።
ከግሡ መጀመሪያ ላይ ባእድ ሆሄን ይጨምራል ሆሄያቱም አሥራውይባላሉ
ምሳሌ
መሀረ መሠረታዊ ግሥ ሲሆን
ይትመሀር እና ባእድ ሆሄ ይባላሉ ። ምክንያቱም ከመሠረታዊው ግሥ ያልነበሩ የመሠረታዊው ግሥ ወገን ስላልሆኑ ነው። ከግሡ መጀመሪያ ላይ ስለሚገኙ ደግሞ “አሥራው” ይባላሉ በአማርኛ ሥሮች ማለት ነው፤፡
ስለዚህ ለማጠቃለል ያህል የዘንድ አንቀጽ መሠረታዊ ወይም አበይት መለያዎችን  ባጭሩ እንደሚከተለው ይመልከቱ።
·         ዘንድ አንቀጽ ከአበይ አናቅጽ መካከል ሦስተኛው አንቀጽ ነው በዚህም ሳልሳይሦስተኛይባላል
·         ዘንድ ተብሎ ስለሚተረጎምዘንድ አንቀጽእየተባለ ይጠራል። ስለዚህ ስሙ ከትርጉም ጋር የተያያዘ ነው።
·         ብቻውን ስለማያሥር ሌላ ግሥ (ሃላፊ፤ ትንቢት፤ ወይም ትእዛዝአናቅጽ) ያስፈልገዋል።
·         ከሁሉም አበይ አናቅጽ ማለትም ከሃላፊ፤ከትንቢት፤ እና ከትእዛዝ አናቅጽ ጋር እየተቀናጀ ያገለግላል
·         አገባባዊ ትርጉምና ሥራ አለው። ለምሳሌከመከሚለው አገባብና ከመሰሎቹ ጋር በትርጉምና በአገልግሎት ይመሳሰላል
·         ሁለት ነገሮችን በአንድ ላይ ይዟል፡ ዘንድ የሚል አገባብ() እና አንቀጽያእምር”= ያውቅ ዘንድ= ያውቅ(አንቀጽ) ዘንድ=አገብባብ() ስለዚህ አገባብና አንቀጽ በአንድ ላይ ይበኙበታል።
·         የዐረፍተ ነገርን ምክንያታዊ ተግባር ይገልጻል
·         ከግሡ መጀመሪያ ላይአሥራው የሚባሉትን ሆሄያት ይጨምራል።