Friday, July 18, 2014

Geez part 11 Exam one Answers

የግእዝ ትምህርት ክፍል 11 የመመዘኛ ፈተና አንድ ሙሉ መልስ

ይህ የመጀመሪያ የመመዘኛ ፈተና ባጣም መሠረታዊና ጠቃሚ በመሆኑ በትክክል ለመመለስ ሞክሩ። ፈተናውን ሠርታችሁ መልሱን ለመላክ 7 ቀናት እሰጣችኋለሁ የሚቀጥለው ቅዳሜ July 12, 2014 መላክ አለበት።

መልሱን July 19, 2014 እነግራችኋለሁ። ከjuly 12, 2014 በኋላ የላከ ሰው አይታረምለትም። በርግጥ የፍላጎት ትምህርት ስለሆነ እኔም የማስተምረው በራሴ ፍላጎት ነው እናንንተም የምትማሩት በራሳችሁ ፍላጎት ነው።

 ስለዚህ በመካከል የሚያስገድደን የለም ። ሆኖም ግን ከልብ መማር የሚፈልግ ራሱን በማስገደድ መሥራት ይኖርበታል። ምክንያቱም ፈተና ካልሠራን በሥርዓተ ትምህርት መሠረት ራሳችን ካልመራን ማወቅ የምንፈልገውን ማወቅ አንችልም።

በመሆኑም ራሳችንን አዘን በወቅቱ ሠርተን በተመደበልን ጊዜ መመለስ ይሆርብናል ማለት ነው። በክፍል 10 የሰጠኋችሁን ሁለት የግእዝ ጽሁፎች ከፈተናው መልስ በኋላ ትርጉሙን እየተረጎምን አገባቡንም ጭምር እናያለን እስከዚያው ግን ራሳችሁ ለመተርጎም መሞከር እንዳለባችሁ ተነጋግረናል አሁንም ማሳሰቢያየ ያው ተመሳሳይ ነው፡ለመተርጎም ያልሞከራችሁ ካላችሁ አሁንም ጊዜ አላችሁ ሞክሩ።

የግእዝ ትምህርት ክፍል 11 (አሥራ አንድ) የመመዘኛ ፈተና አንድ

ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ የጥያቄውን ቍጥር እና የመልሱን ፊደል በኮሜንት ቦታ እንደሚከተለው ያስቀምጡ

ምሳሌ አንድ::

1.      “ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኃበ እግዚአብሔር”.። ለዚህ ዐረፍተ ነገር የሚስማማው መራሒ ወይም የስም ተለዋጭ የትኛው ነው?

A.    ውእቱ
B.     ይእቲ
C.    አነ

ምሳሌ ሁለት፡

2.     “አነ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም”። የዚህ ዐረፍተ ነገር ባለቤት ወይም የሥም ተለዋጭ ----ይባላል።
A.    1ኛ መደብ ነጠላ
B.     2ኛ መደብ ብዙ ለሴቶች
C.    3ኛ መደብ ነጠላ ቁጥር

This is comment area under youtube video

Q.1. A. B.

Q.2. A. A.

ከዚህ በላይ ለምሳሌነት የተሰጡት መልሶች ሲተነተኑ

ለጥያቄ አንድ መልሱ B.;


ለጥያቄ ሁለት ደግሞ መልሱ A. ነው ማለት ይሆናል።

ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ የጥያቄውን ቍጥር እና የመልሱን ፊደል በኮሜንት ቦታ ያስቀምጡ

1.      ጳውሎስ ሆረ ኀበ አቴና። የዚህ ዐረፍተ ነገር ተውላጠ ስም የትኛው ነው?

A.    ውእቱ
B.     ውእቶሙ
C.    አንተ

2.     አቤል ----በእደ ቃኤል። ለዚህ ዐረፍተ ነገር የሚስማማው አንቀጽ

A.    ቀተለ
B.     ተቀትለ
C.    አቅተለ

3.     አርድእተ ግእዝ አእመሩ ሰዋስወ ግእዝ። የዚህ ዐረፍተ ነገር ባለቤት

A.    1ኛ መደብ ብዙ ተባእታይ
B.     2ኛ መደብ ነጠላ
C.    3ኛ መደብ ብዙ ተባእታይ

4.     አእማድ ማለት ምን ማለት ነው? አእማድ የሚባሉትስ ስንት ናቸው?

A.    መሪዎች፤ 5
B.     ምሰሶዎች፤ 10
C.    ምሰሶዎች፤ 5

5.     አንቲ---ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እም ገነት። በተማርነው መሠረት ለዚህ ዐረፍተ ነገር የሚስማማው ነባር ግሥ የቱ ነው?

A.    ውእቶሙ
B.     ውእቱ
C.    ውእቶን

6.     አበይት አናቅጽ ወይም ታላላቅ ግሦች ወይም አናቅጽ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?

A.    ሃላፊ፤ ትንቢት፤ ዘንድ፤ እና ትእዛዝ
B.     ቅጽል፤ነባር፤ እና ግሥ
C.    አእማድና መራሕያን

7.     አነ ውእቱ ። ማለት ---ማለት ነው ወይም ይሆናል ።

A.    እኔ ነኝ
B.     እሷ ናት
C.    እኛ ነን

8.     አበበ ወገብረ ማርያም ሐተቱ መጻሕፍተ። ለሚለው ዐረፍተ ነገር የሚስማማው ተውላጠ ስም ወይም የስም ተለዋጭ የትኛው ነው?

A.    ንሕነ
B.     ውእቶን
C.    ውእቶሙ

9.     መርድአ ግእዝ ጸሐፈ መጽሐፈ። የዚህን ዐረፍተ ነገር ባለቤት፤ ማሠሪያ አንቀጽ፤ እና ቀጥተኛ ተሳቢ የያዘውን የመልስ ሆሄ በመምረጥ መልስ ይስጡ።

A.    መርድእ፤ ጸሐፈ፤ መጽሐፍ(መርድአ፤ጸሐፈ፤ መጽሐፈ)
B.     ግእዝ፤ ጸሐፈ፤ ሰዋስው፤
C.    መርድእ፤ መጽሐፍ፤ ግእዝ፤

10.   ገብረ ማርያም ቀደሰ ቅዳሴ ሐዋርያት። በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ በአገባብ ትንታኔ ትምህርታችን መሠረት “ሐዋርያት” የሚለው ቃል ወይም ስም ሙያው ምን ይባላል?

A.    የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት
B.     ማሠሪያ አንቀጽ
C.    የቅዳሴ ዘርፍ

እግዚአብሔር ይክስት ለክሙ ምሥጢረ ወየሐብክሙ ዘትትናገሩ

ወስብሐት ለ እግዚአብሔር

አሜን
አዘጋጅና አቅራቢ “አውደ ጥናት” 

No comments:

Post a Comment